በነገው ዕትም በሀገር ውስጥ ዘገባችን አርባምንጭ ከተማ በወረደበት አመት ወደፕሪሚየር ሊጉ እንዲመለስ ያደረገው አሰልጣኝ በረከት ደሙ እንግዳችን ነው…. የደጋፊዎቹን እንባ ያበሰ በበሚል የተሞገሰው አሰልጣኙ ” 9 አመት በስልጠና ቆይቼ ልምድ የለህም ብባል አልቀበልም” ሲል ከሊጉ ዮሴፍ ከፈለኝ ጋር በነበረው ቆይታ ተናግሯል። ቃለምልልሱን ይዘናል…
*….. የትግራይ ክለቦችን እንታደግ ታላቅ ዘመቻ አካል የሆነው ቴሌቶን የፊታችን ሰኔ18/2016 በሸራተን አዲስ ይካሄዳል….በዚህ ዙሪያ ተሰጠውን ጋዜጣዊ መግለጫ የተከታተለው የሊጉ ዮሴፍ ከፈለኝ ያዘጋጀው መረጃም ተካቶበታል …
*……ከውጪ ዘገባ ደግሞ ………
*…… ብዙ ሲያወያይ ሲያነጋግር የነበረው የክሊያን ምባፔ ዝውውር ዜና ፍጻሜውን አግኝቷል… ተጨዋቹ በይፋ የሪያል ማድሪድን ማሊያ ለቀጣዮቹ አምስት አመታት ለመልበስ በመስማማት የሳንቲያጎ በርናባው አድማቂ መሆኑ ተረጋግጧል… በአዲሱ የነጩ ቤት ኮከብ ዙሪያ የሚያጠነጥን መረጃዎችን ይዘናል…
*……የዝውውር መስኮቱ ከቀናቶች በኋላ በይፋ ይከፈታል… በዚህ መስኮት መድፈኞቹ ማንን ያስፈርማሉ..? በዚህ ዙሪያ መረጃዎችን ይዘናል….
*….ሆላንዳዊው አዲሱ የሊቨርፑል አሰልጣኝ አርን ስሎት ቀዮቹን እንዴት ባለ መንገድ ይመራ ይሆን ..? የሚለው የብዙዎች ጥያቄ ነው…በዚህ ዙሪያ መረጃዎቾን ይዘናል…
*….. ማን.ሲቲ ከ110 በላይ ክሶች ተከሷል …ብዙ እያከራከረ ባለው የሲቲ የፍርድ ቤት ውሎ የሚያጠነጥን መረጃዎችን አካተናል…..
….. እናም ሌሎች ያልተሰሙ መረጃዎችን ይዘናል …
ነገ ጠዋት ቡናዎን ሲፈልጉ ማኪያቶዎን ወይም ያሻዎት ሌላ ከሆነ ልብዎ የፈለገውን እየተጎነጩ ሊግን በእጅዎ ያስገቡ…
….ቅዳሜና እሁድዎ የሚደሰቱበት ቀኖችዎ ይሁኑ…