በየሳምንቱ ቅዳሜ ለንባብ የምትበቃው ሊግ ጋዜጣ በነገው ዕለት ምርጥ ምርጥ ዘገባዎችን አካትታ እጅዎ ትገባለች…. በነገው ዕትም በሀገር ውስጥ ዘገባዋ :-
የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የብሄራዊ ዳኞች ኮሚቴ ሰብሳቢ ኮሚሽነር ሸረፋ ደሌቾ እንግዳችን ናቸው…… በቅርቡ በርካታ ዳኞች ስለወደቁበት የዳኞች የአካል ብቃት ፈተና፣ ተቃውሞ ስለ ገጠመው የኢንተርናሽናል ዳኞች ምደባ፣ ልምድና ኢንተርቪውን ከመመዘኛ ውጪ ስላደረጉበት ምክንያት፣ ዳኞች የሚመዘኑበት ቋሚ መመዘኛ ለምን እንደሌለ እና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ምላሽ ሰጥተዋል። ኮሚሽነር ሸረፋ
“አንድ ቀን ፊሽካና ፍላጉን ይዞ የማያውቅ ሰው ፌዴራል ዳኛ ተብሎ አግኝተናል” ሲሉ ከልምድ ጋር ተያይዞ ያለውን ክፍተት ከሊጉ ዮሴፍ ከፈለኝ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ተናግረዋል…
በውጪ ዘገባ ደግሞ:-
**** በታላቅ ጉጉት የሚጠበቀው የአርሰናልና የማን.ሲቲ ፍጥጫ የፊታችን እሁድ ኢምሬትስ ላይ ይካሄዳል ….
በርካቶች የመምህሩና የደቀመዝሙሩ ፍጥጫን ማን በበላይነት ያጠናቅቅ ይሆን ሲሉ ይጠይቃሉ ….? ይህን የፔፕ ጋርዲዮላና የሚካኤል አርቴታ ታክቲካዊ ፍጥጫን በተመለከተ መረጃዎችን ይዘናል….
**** የማን.ዩናይትድ የውጤት ቀውስ የበርካቶችን ቀልብ ስቧል ….. አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሃግን ጫና ውስጥ የዠ
ስለከተቱት ሳምንታት ያዘጋጀነው ዘገባ አለ….
**** ጀርመናዊው ኤልካይ ጉንዶጋን በኑካምፕ ደምቋል …. ስለዚህ እውነተኛ የዣቪ ኧርናንዴዝ አምሳያ የምንለው አለ…..
**** በ60 ሚሊዮን ፓውንድ ሊቨርፑልን የተቀላቀለው ሃንጋራዊው ዶሚኒክ ሶቦዝላይ “አዲሱ ስቴቨን ጄራርድ” እየተባለ ነው….ስለተጨዋቹ የሚገልጽ መረጃንም አካተናል ….
**** ጋምቢያዊው ኒኮላ ጃክሰን በአሰልጣኝ ማውሪሲዮ ፖሺቲኖ ለሚሰለጥነው ቸልሲ “ቀጣዩ ዲዲየር ድሮግባ” ነው ተብሎ እየተሞካሸ ነው….ቸልሲ የረጅም ጊዜ ዕቅዱ ስላደረገው ጋምቢያዊ የምንላችሁ አለ..
እና ሌሎች ያልተሰሙ መረጃዎችን አካተናል …
ነገ ጠዋት ቡናዎን ሲፈልጉ ማኪያቶዎን ወይም ያሻዎት ሌላ ከሆነ ልብዎ የፈለገውን እየተጎነጩ ሊግን በእጅዎ ያስገቡ…
….ቅዳሜና እሁድዎ የሚደሰቱበት ቀኖችዎ ይሁኑ…