Google search engine

የሊግ ጉዞ ቀጥሏል……

 

በየሳምንቱ ቅዳሜ ለንባብ የምትበቃው ሊግ ጋዜጣ በነገው ዕለት ምርጥ ምርጥ ዘገባዎችን አካትታ እጅዎ ትገባለች….
በነገው ዕትም ከሀገር ውስጥን የአዳማ ከተማው ዮሴፍ ታረቀኝ እንግዳችን ነው… የ2015 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተስፋ የተጣለበት ወጣት ኮከብ ተብሎ ተመርጧል…አዳማ ከተማዎች አሉኝ ከሚሏቸው ኮከቦች አንዱ ሆኖ ይጠቀሳል… ድፍረቱ በዝቶ በራስ መተማመኑ በጣም ጨምሮ እብሪተኛ አድርጎታል የሚሉ ወገኖች ቢኖሩም ወጣቱ ተስፈኛ ዮሴፍ ታረቀኝ ግን አባባሉ እኔን አይገልጽም ሲልም ይናገራል .. ለግብጹ አረብ ኮንትራክተር ሊፈርም ከጫፍ ደርሶ ሳይሳካለት ቀርቷል…ለምን ..? ምክንያቱስ ..? ዮሴፍ ሲናገር
“የክለቤ አመራሮች ለግብጹ ዓረብ ኮንትራክተር ክለብ 40 ሚሊዮን ብር ጠይቀው ዝውውሩ ባለመሳካቱ ከፍቶኛል” ሲልም ተናግሯል…ከሊጉ ዮሴፍ ከፈለኝ ጋር ቃለምልልስ ያደረገው ተስፈኛው ዮሴፍ ታረቀኝ ስለ አጠቃላይ እግርኳሳዊ ጉዳይ ዙሪያ ለቀረበለት ጥያቄዎች ምላሹን ሰጥቷል… ቃለምልልሱን ይዘናል….

**** የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ስታዲየም ዙሪያ ያለው ነዳጅ ማደያ ጨረታ ጉዳይ ብዙ አነጋግሯል…. ዘጠኝ ተወዳዳሪዎች ተፋልመው 46 ሺህ ብር የነበረው ኪራይ 905 ሺህ ባቀረበ ተወዳዳሪ አሸናፊነት ሁለቱ ወገኖችም ውል ተፈራርመዋል …ሂደቱ ምን ይመስላል ..? በርካቶችን ሲያነጋግር የነበረው የፌዴሬሽኑ ህንጻ ስም ከዞረ አመት ሞልቶታል እየተባለ ነው.. እውነት ነው ..? ፊፋ ለኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን 127 ሺህ ኳስ ሰጥቷል…ለምን …? የፌዴሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ባህሩ ጥላሁን ከሊጉ ዮሴፍ ከፈለኝ ጋር በነበራቸው ቆይታ ምላሹን ሰጥተዋል…አቶ ባህሩ “46 ሺህ ብር የነበረውን የነዳጅ ማደያ ኪራይ 905 ሺህ ብር በማድረሳችን መሸለም እንጂ መተቸት አይገባንም” ሲሉ አስተያየት የሰጡበትን ቃለምልልስ ይዘናል…..

…….በውጪ ዘገባ ደግሞ:…..

**** መላው ዓለም በጉጉት የሚጠብቀውና የስፖርት ቤተሰቡን ልብ ሰቅዞ የያዘው የስፔኑ ኤል ክላሲኮ
ነገ በኑካምፕ ይካሄዳል…. በጉዳት የተፈተነው ባርሴሎና በቤሊንግሃም የሚመራውን ሪያል ማድሪድን ያስተናግዳል…ስለ ጨዋታው የሚገልጽ ዘገባ ይዘናል …

**** በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊጉ ሁለቱን ጸጉረ አልባ መላጣ ባለሙያዎችን ፔፕ ጓርዲዮላና ኤሪክ ቴንሃግን ያፋጠጠው
የማንቹሪያን ደርቢ እሁድ ምሽት ኦልድትራፎርድ ላይ ይከሰታል …. ሆላንዳዊው ባለሙያ ኤሪክ ቴንሃግ ለስፔናዊው ፔፕ ጓርዲዮላ ቡድን ምላሽ አላቸው?… በጨዋታው ዙሪያ መረጃዎችን ይዘናል….

**** መድፈኞቹ በሻምፒየንስ ሊጉ ምሽት ጥቂት ቡድኖች ብቻ ማድረግ የሚችሉትን ሲቪያን በሜዳው ማሸነፍን አድርገውት ተመልሰዋል … ነገር ግን የድሉ ደስታ ላይ ውሃ የቸለሰውን ጉዳት በወሳኙ አጥቂ ጋብርኤል የሱስ ላይ ተከስቷል …የብራዚላዊው ጉዳት የማይክል አርቴታ ቡድንን ጉዞ ያስተጓጉላል? በዚህ ላይ የሚያጠነጥን ዘገባ አካተናል…..

**** የቀድሞ የሊቨርፑል አምበል ጆርዳን ሄንደርሰን በ12 ሚሊዮን ፓውንድ ለሳዑዲ አረቢያው አል ኢቲፋቅ ከፈረመ ሰነባብቷል … ነገር ግን ሰብአዊ መብት ትጥሳለች ወደሚሏት ሳዑዲ በማቅናቱ የሀገሩን ማሊያ አድርጎ በተጫወተ ቁጥር የብሄራዊ ቡድን ደጋፊዎች ተቃውሞ እያሰሙበት ነው…እሱም የተሰማውን ቅሬታ በዝምታው እየገለጸ ይገኛል …በዚህ ዙሪያ ዘገባ ይዘናል…

….. እናም ሌሎች ያልተሰሙ መረጃዎችን አካተናል …

ነገ ጠዋት ቡናዎን ሲፈልጉ ማኪያቶዎን ወይም ያሻዎት ሌላ ከሆነ ልብዎ የፈለገውን እየተጎነጩ ሊግን በእጅዎ ያስገቡ…

….ቅዳሜና እሁድዎ የሚደሰቱበት ቀኖችዎ ይሁኑ….

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

ትኩስ ዜናዎች

%d bloggers like this:
P