Google search engine

የሊግ ጉዞ ቀጥሏል……

 

በየሳምንቱ ቅዳሜ ለንባብ የምትበቃው ሊግ ጋዜጣ በነገው ዕለት ምርጥ ምርጥ ዘገባዎችን አካትታ እጅዎ ትገባለች….
በነገው ዕትም ከሀገር ውስጥ የዳኞችና ታዛቢዎች የሙያ ማህበር ም/ል ፕሬዝዳንት ፌዴራል አርቢትር ሚካኤል አርአያ እንግዳችን ነው… 7 አመት በረዳት ዳኝነት 17 አመት ደግሞ በዋና ዳኝነት አገልግሏል…. ለዳኞች ባለው ተቀርቋሪነት ይታወቃል….በዚህም ኢንተርናሽናል አርቢትር መሆንን ጨምሮ በርካታ ጥቅሞቹን አጥቷል…. ከሰሞኑ የማህበሩ አመራሮች መሃል በተነሳው አለመግባባት በአፍሪካ ህብረት በተካሄደውም የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ሳይወከሉ ቀርተዋል….
ከሊጉ ዮሴፍ ከፈለኝ ጋር ቆይታ ያደረገው ፌዴራል አርቢትር ሚካኤል አርአያ በተፈጠረው ችግር ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥቷል። “ለባለሙያተኞች በመታገሌ በአምላክ ተሰማ 5ኛ ወጥቶ እኔ 4ኛ ወጥቼም ኢንተርናሽናል አርቢትር የመሆን እድሌን አጥቻለሁ” የሚለው ፌዴራል አርቢትር ሚካኤል አርአያ
“በዚህ ማህበር የመጣው ለውጥ ሁሉ ከ90 በመቶ በላይ የኔ ትግል ውጤት ነው” ሲል በል ሙሉነት ተናግሯል ….ቃለምልልሱን ይዘናል…

 

……በውጪ ዘገባ ደግሞ:…..

* በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የማን.ዩናይትድ የቁልቁለት ጉዞ አነጋጋሪ ሆኗል….. ደካማው ውጤት የአሰልጣኝ ቴን ሃግና የማንቸስተር ዩናይትድን እህል ውሃ እንዲያበቃ ያደርግ ይሆን…? መረጃውን ይዘናል……

* ክሮሺያዊው ሉካ ሞድሪች በሪያል ማድሪድ ማሊያ በሚያሳየው ብቃት አድናቆት ጎርፎለታል…በዚህ ላይ የምንላችሁ ነገር አለ….

* የማን.ሲቲው አለቃ ፔፕ ጓርዲዮላ ልክፍትን ያውቁ ይሆን ….? መረጃዎችን ይዘናል……

* እንደ አህጉር ከላቲን እንደ ሀገር ከተቀናቃኞቹ ብራዚልና አርጀንቲና ማዕጸን የተገኙ ናቸው …..
የሁለቱ ኮከቦች ልብ ግን ይፈላለጋል…. የሮናልዲንሆ ጎቾ ዲ አሲስ ሞሪየራና የሊዮኔል አንድሬስ ሜሲ ወዳጅነት ዙሪያ የምንለው አለ…

* ሊዮኔል ሜሲ ባሎንዶርን ለ8ኛ ጊዜ አሸንፎ ኮከብነቱን አውጇል …. ስለዚህ የባሎን ዶር አሸናፊ እግር ኳሳዊ ዕድገት ያዘጋጀነው መረጃ አለን…..

….. እናም ሌሎች ያልተሰሙ መረጃዎችን አካተናል …

ነገ ጠዋት ቡናዎን ሲፈልጉ ማኪያቶዎን ወይም ያሻዎት ሌላ ከሆነ ልብዎ የፈለገውን እየተጎነጩ ሊግን በእጅዎ ያስገቡ…

….ቅዳሜና እሁድዎ የሚደሰቱበት ቀኖችዎ ይሁኑ….

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

ትኩስ ዜናዎች

%d bloggers like this: