.ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መሪነቱን አጠናክሮ ቀጥሏል… ለዚህ ውጤት መገኘት ደግሞ የተከላካይ ክፍሉ የራሱን ሚና መወጣቱ ይታመንበታል…ከተከላካይ መስመሩ ደጀን መሃል አንዱ ደግሞ ፈቱዲን ጀማል ነው…”ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ዋንጫ ብቻ ነው የምፈልገው” የሚለው ፈቱዲን ከሊጉ ዮሴፍ ከፈለኝ ጋር በነበረው ቆይታ “በህይወቴ እንደ ታሪክ የማወራው የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ እፈልጋለሁ” ብሏል…ጾም ለማሸነፍ ስላለው ጥቅም ሲናገርም “ለማሸነፍ የሚያስፈልገው ጾም ብቻ ከሆነ ሜዳ መግባት አያስፈልግም” ሲል ጾም በጠንካራ ስራ መታጀብ እንዳለበት ገልጿል…..ቃለ ምልልሱን ይዘናል……
…ቅዱስ ጊዮርጊሶች ነገ በመዝናኛ ማዕከላቸው አንድ ቀጠሮ ይዘዋል…ከአዲስ አበባ ቢራ እስከ ቅዱስ ጊዮርጊስ በሚል መሪ ቃል መስዋትነት ከፍለው ስኬታማ የሆኑበትን የ40 አመት ታሪክ ያለውን ክስተት ይዘክራሉ….መረጃዎችን ይዘናል….
*……በውጪ ዘገባ ደግሞ ………
* ….. መድፈኞቹ በሻምፒየንስ ሊግ ተፈትነዋል… የአርሰናል ጉዞስ ምን ይመስላል…. ? መረጃዎችን ይዘናል…. ስለ ካይ ሃቨርትዝም የምንለው አለ…
*…… እስቲ ስለ ሞ ሳላህ እንነጋገር…ወቅታዊ ብቃቱና የአንፊልድ ቆይታው ምን ይመስላል……? አርኖልድም ተመልሷል…የቀዮቹ ወሳኝ ተጨዋቾች እየተመለሱ ነው በዚህ ዙሪያ መረጃዎችን ይዘናል….
*……ወጣቱና የማን.ሲቲ የነገ ተስፋ ስለሆየው ከ9 አመቱ ጀምሮ በሲቲ ቤት ስለሚገኘው ሚካህ ሃሚልተን የምንላችሁ አለ…
*…..አንድ የስፔን የቴሌቭዥን ጣቢያ የባርሴሎናውን ላሚን ያማል ላይ ያላገጠውን ተንታኙን አባሯል…በክስተቱ ዙሪያ መረጃዎችን አካተናል….
*….. ክርስቲያኖ ሮናልዶ የመጨረሻዬን አሳምረው ማለት ሳይኖርበት አይቀርም…ስለ ፖርቱጋላዊው ውዝግብ ዙሪያ መረጃዎችን ይዘናል….
….. እናም ሌሎች ያልተሰሙ መረጃዎችን ይዘናል …
ነገ ጠዋት ቡናዎን ሲፈልጉ ማኪያቶዎን ወይም ያሻዎት ሌላ ከሆነ ልብዎ የፈለገውን እየተጎነጩ ሊግን በእጅዎ ያስገቡ…
….ቅዳሜና እሁድዎ የሚደሰቱበት ቀኖችዎ ይሁኑ…