በነገው ዕትም በሀገር ውስጥ ዘገባችን የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን በ12 ግብ በኮከብ ግብ አግቢነት እየመራ ያለው አሊ ሱሌይማን እንግዳችን ነው …የሴካፋ ኮከብ ግብ አግቢ ሆኖ ያጠናቀቀው ኤርትራዊው አሊ ሱሌይማን ከሊጉ ዮሴፍ ከፈለኝ ጋር ባደረገው ቃለምልልስ ” የሴካፋ ኮከብ ግብ አስቆጢሪነትን በፕሪሚየር ሊጉ ለመድገም እጥራለሁ”… ሲል ተናግሯል። ለሀዋሳ ከተማ ደጋፊዎች ያለውን ፍቅርና አክብሮት የገለጸው አሊ ” በጥሎማለፉ ኢትዮጵያ ቡናን በማሸነፍ ደጋፊያችንን እንደምናስደስት ርግጠኛ ነኝ” ብሏል… ቃለምልልሱን ይዘናል….
*… የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በኮሚሽነር ሸረፋ ደሌቾ የሚመራውን የብሄራዊ ዳኞች ኮሚቴን በማሰናበት አዲስ ኮሚቴ ተክቷል….ሸዋንግዛው ተባባልና ሊዲያ ታፈሰ ስለሚመሩት አዲሱ ኮሚቴ መረጃዎችን ይዘናል።
*……በውጪ ዘገባ ደግሞ ………
*…… መላው ዓለም በጉጉት የሚጠብቀው የስፔኑ ኤልክላሲኮ ትንቅንቅ እሁድ ምሽት ይካሄዳል.. ባርሴሎናስ ድል ቀንቶት ልዩነቱን ያጠብ ይሆን ..? መረጃዎችን ይዘናል….
* ….. በእንግሊዝ ኤፍ ኤ ካፕ የግማሽ ፍጻሜ ሁለት ጨዋታዎች ቅዳሜና እሁድ ሲካሄዱ ማን.ሲቲ ከቸልሲ ማን.ዩናይትድ ከኮቨንተሪ ይጫወታሉ… የጋርዲዮላ ቡድን ፈተና ስለሆነው የግማሽ ፍጻሜ ትንቅንቅ የምንላችሁ አለ…
*….. አርሰናል ለሁለት ዋንጫ ሲጠበቅ በቀናቶች ልዩነት ውስጥ ከሻምፒየንስ ሊግ ሲሰናበት ፕሪሚየር ሊጉም አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል…. የመድፈኞቹ ባቡር ሃዲዱን ስቶ ይሆን ..? በሚካኤል አርቴታ ቡድን ዙሪያ የሚያጠነጥን መረጃዎችን ይዘናል…
*……በፕሪሚየር ሊጉ ስለደመቁ ፈረንሳዊያን መረጃ ይዘናል…
*….. በፍትህ አደባባይ አሮጊቷ ጁቬንቱስ በጎልማሳው ክርስቲያኖ ሮናልዶ ተሸንፋለች … መረጃዎችን ይዘናል….
*……አንድ ጥያቄ እንጠይቅዎ….እርስዎ በቆመ ኳስ አጠቃቀም የማን አድናቂ ኖት ..? ለዛሬ የቆመ ኳስ ስፔሻሊስት ስለሆኑ ተጨዋቾች መረጃዎችን ይዘናል……
….. እናም ሌሎች ያልተሰሙ መረጃዎችን ይዘናል …
ነገ ጠዋት ቡናዎን ሲፈልጉ ማኪያቶዎን ወይም ያሻዎት ሌላ ከሆነ ልብዎ የፈለገውን እየተጎነጩ ሊግን በእጅዎ ያስገቡ…
….ቅዳሜና እሁድዎ የሚደሰቱበት ቀኖችዎ ይሁኑ…