በነገው ዕትም በሀገር ውስጥ ዘገባችን ቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ አተኩረናል…. ክለቡ ከዚህ በፊት ያልገጠመው ውጤት ማጣት የገጠመው ይመስላል ባለፉት 6 ጨዋታዎች አኔድም ጨዋታ ማሸነፍ አልቻለም …. ደጋፊውና ቦርዱ መሃል ደግሞ ንፋስ ገብቷል… በዚህ ዙሪያ የሊግ ማኔጂንግ ኤዲተር አለምሰገድ ሰይፉ የፈረሰኞቹ የቦርድ አባልና የማርኬቲንግ ሃላፊ ከሆነው አቶ ዳዊት ውብሸት ጋር ቆይታ አድርጓል… አቶ ዳዊት ሲናገር ” ቅዱስ ጊዮርጊስን በከፍተኛ ደረጃ እየጎጎዳ ያለው የውስጥ ጠላቱ ነው” ሲል ተናግሯል….ቃለምልልሰን ይዘናል…..
*……ከውጪ ዘገባ ደግሞ ………
*…… በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ልብ አንጠልጣዩ ሳምንት ከተባለ ይህ ሳምንት ነው ….ማን.ሲቲና አርሰናል ለዋንጫው ተፋጠዋል…አርሰናል ዋንጫውን ካጣ የሚያጣበትን ምክንያትና ጨዋታዎችን የሚዘረዝር ዘገባ አካተናል……
*….. በጉዳት ከማን.ዩናይትድ የመሃል ክፍል የታጣው ብሩኖ ፈርናንዴዝ ዕጣ ፈንታ ምን ይሆን …? በዚህ ዙሪያ የምንለው አለ….
*……የማን.ሲቲ የሰሞኑ ምርጡ ተጨዋች ግቫርዲዮል ዙሪያ የሚያጠነጥን መረጃ አካተናል….
*…..ብራዚላዊው ካሴሚሮ ተደጋጋሚ ስህተቶቹ እያስተቹት ነው …ተጨዋቹ በማን.ዩናይትድ አብቅቶለት ይሆን..? በዚህ ዙሪያ የሚያጠነጥን መረጃ አካተናል…
*……የጀርመናዊው አሰልጣኝ የርገን ኖልበርት ክሎፕ የመጨረሻ ጨዋታና ስንብት ዙሪያ መረጃ አካተናል…..
*….. ቸልሲ ቀጣም ተነቃቅቷል… የፖቸቲኖ ቡድን መነቃቃት ከረፈደ በኋላ ይሆን …? መረጃዎችን ይዘናል…
….. እናም ሌሎች ያልተሰሙ መረጃዎችን ይዘናል …
ነገ ጠዋት ቡናዎን ሲፈልጉ ማኪያቶዎን ወይም ያሻዎት ሌላ ከሆነ ልብዎ የፈለገውን እየተጎነጩ ሊግን በእጅዎ ያስገቡ…
….ቅዳሜና እሁድዎ የሚደሰቱበት ቀኖችዎ ይሁኑ…