በየሳምንቱ ቅዳሜ ለንባብ የምትበቃው ሊግ ጋዜጣ በነገው ዕለት ምርጥ ምርጥ ዘገባዎችን አካትታ እጅዎ ትገባለች…. በነገው ዕትም በሀገር ውስጥ ዘገባዋ የኢትዮጵያ ቡናው ግብ ጠባቂ በረከት አማረ እንግዳችን ነው……በአዲሱ የሰርቪያ አሰልጣኝ ኮቫዞቪች ኒኮላ የሚሰለጥነው ኢትዮጵያ ቡና እየተመራ ለ2016 ጠንካራ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን የክለቡ አምበልና ሲኒየር ተጨዋች በረከት አማረ ከሊጉ ዮሴፍ ከፈለኝ ጋር ባደረገው ቃለምልልስ ተናግሯል… ግብ ጠባቂው ሲናገር “2016 የኢትዮጵያ ቡና ጊዜ ነው”” ሲል የሚመኘውን ተናግሯል….
** የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባኤ የፊታችን ጥቅምት 18/2016 አዲስ አበባ ላይ ይካሄዳል .. የአፋር፣ የትግራይና የደቡብ ምዕራብ ክልሎች ተወካዮችን ለመምረጥ በሚደረገው ምርጫ ዙሪያ የሚያጠነጥነውን መረጃ አካተናል….
በውጪ ዘገባ ደግሞ:-
**** በመላው ዓለም በጉጉት የሚጠበቀው የሰሜን ለንደን ደርቢ በጠንካራ አቋም ላይ በሚገኙት አርሰናልና ቶተንሃም መሃል ከነገ በስቲያ እሁድ ይካሄዳል… በዚህ አጓጊ ጨዋታ ዙሪያ የምንላችሁ አለ…
**** የአምናው የስፔን ላሊጋ ሻምፒዮን የካታላኑ ኩራት ባርሴሎና ወደለመደው አዝናኝ አቋም ተመልሷል….. በዚህ ዙሪያ መረጃ አለን….
*በሊቨርፑል አዲሱ መልክ ዙሪያ የምንላችሁ አለ…
እና ሌሎች ያልተሰሙ መረጃዎችን አካተናል …
ነገ ጠዋት ቡናዎን ሲፈልጉ ማኪያቶዎን ወይም ያሻዎት ሌላ ከሆነ ልብዎ የፈለገውን እየተጎነጩ ሊግን በእጅዎ ያስገቡ…
….ቅዳሜና እሁድዎ የሚደሰቱበት ቀኖችዎ ይሁኑ…