የሊግ ጋዜጣ ባለቤትና መስራች የሆነው ጋዜጠኛ
አለምሰገድ ሰይፉ በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያዊያን ስፖርትና ባህል ፌዴሬሽን የህዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊ ሆኖ መሾሙ ተነገረ።
ጋዜጠኛ አለምሰገድ በቅርቡ ወደ ደቡብ አፍሪካ ተጉዞ በፕሪቶሪያ፣ጆበርግና ረስተንበርግ ከተሞች ጉብኝት ከማድረጉም በተጨማሪ የአሰልጣኝ አስራት ኃይሌ የገቢ ማሰባሰቢያ የፍጻሜ ጨዋታንም ተከታትሎ ተመልሷል።
በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያዊያን ስፖርትና ባህል ፌዴሬሽን ከ2017 ጀምር አመታዊ ውድድር የሚጀምር ሲሆን ጋዜጠኛ አለምሰገድ የፌዴሬሽኑ የመጽሄት የጋዜጣና በአጠቃላይ የሚዲያ ስራዎችን በበላይነት እንደሚሰራ ታውቋል።
የበርካታ አመታት የጋዜጠኝነት ልምድ ያለው አለምሰገድ ሰይፉ የሰሜን አሜሪካ የእግርኳስ ፌዴሬሽን የህዝብ ግንኙነት ክፍል ባልደረባም መሆኑ ይታወቃል።