Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“የሴካፋን ዋንጫ እዚሁ ማስቀረት የቅድሚያ ዓላማችን ነው”“አንድ ቀን የግብ ጠባቂው የወንድሜ ፍቅሩ ወዴሳ የኋላ ከለላ ሆኜ መጫወትን እፈልጋለውገወ ሰለሞን ወዴሳ /ባህርዳር ከተማ/

 

ለባህርዳር ከተማ በዘንድሮው የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ዘመን ተሳትፎው በተከላካይ ክፍሉ ላይ ጥሩ እንቅስቃሴን በማሳየቱ ከእግር ኳስ ቤተሰቡ ከፍተኛ አድናቆትን አትርፏል፤ በእግር ኳስ ጨዋታ ዘመኑም ገና ወጣት ተጨዋች ሆኖ ለሐዋሳ ከተማ ተተኪ ቡድን ከተጫወተ በኋላ ለወራቤና ለኢትዮጵያ መድን እግር ኳስ ክለቦች በከፍተኛው ሊግ ተጫውቶ አሁን ወደሚገኝበት የባህርዳር ከተማ በማምራት ካለፈው የውድድር ዘመን አንስቶ ለክለቡ በበርካታ ግጥሚያዎች ላይ በመሰለፍ በስኬታማ ብቃቱ ሊጫወት ችሏል፤ ይሄ አበረታች የሆነ የሜዳ ላይ ብቃቱም በሀገራችን አስተናጋጅነት ለሚካሄደው ዕድሜያቸው ከ23 ዓመት በታች ለሆናቸው ብሔራዊ ቡድን አስመርጦት ሀገሩን በጥሩ ሁኔታ ለማገልገልም በመዘጋጀት ላይ ነው የሚገኘው፡፡

የባህርዳር ከተማ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋቹን ሰለሞን ወዴሳን የሊግ ስፖርቱ ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ በዘንድሮ የውድድር ዘመን ተጨዋቹ ያሳለፈውን ጥሩ ጊዜ ተንተርሶና በሌሎችም የኳስ ህይወቱ ዙሪያ  ተጨዋቹ ካለበት የብሔራዊ ቡድናችን ስብስብ ውስጥ ስልክ ደውሎለት በኳስ ህይወቱ ዙሪያ የሰጠውን  ምላሽ በሚከተለው መልኩ አቅርቦታል፤ ተከታተሉት፡፡

ሊግ፡- እድገትህና ውልደትህ የት ነው?

ሰለሞን፡- በሐዋሳ ከተማ ወረዳ 7 በተለምዶ አጠራር ኬሮ ሰፈር ላይ ነው ተወልጄ ያደግኩት፡፡

ሊግ፡- ይሄ ሰፈር ከአንተ ውጪ ያፈራቸው ሌሎች ኳስ ተጨዋቾች አሉበት?

ሰለሞን፡- አዎን፤ ለታላቅ ደረጃ የበቁ ባይሆኑም እንደ ዳዊት ታደሰና ቸርነትን የመሳሰሉት ተጨዋቾች የእዚሁ አካባቢ ተወላጆች ናቸው፤ ከእነሱም ጋር በክፍለ ከተማ ደረጃም እንጫወት ነበር፡፡

ሊግ፡- የእግር ኳስን በክለብ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ የት ተጫወትክ?

ሰለሞን፡- ለሐዋሳ ከተማ ወጣትና የተስፋ ቡድን ውስጥ ነው ለሶስት ዓመታት ያህል ልጫወት የቻልኩት፤ ከዛም ወደዋናው ቡድን የሙከራ እድሉን አግኝቼ ላመራ ብችልም በጊዜው ለዋናው ቡድን ሊያጫውተኝ በሚችል አቅሜ ላይ ስላልደረስኩና በምጫወትበት ቦታ ላይም ዜጎችን ጨምሮ ልምድ ያላቸው ተጨዋቾች ስለነበሩ ገብቶ የመጫወት ዕድሉና ሳላገኝ ቀረውኝ፤ በጊዜው አሰልጣኝ ውበቱ አባተም እኔ በችሎታዬ ጥሩ ነገር እንዳለኝና ወደፊትም ለቡድኑ መጫወት እንደምችል ነግሮኝ ካበረታታኝ በኋላ ክለባችን በውሰት እኔን ጨምሮ ገብረመስቀል ዱባለን /አቤን/ ለወራቤ ከተማ ሊሰጠን ቻለ፡፡

ሊግ፡- ወደ ዋናው ቡድን ለሙከራ ተልከህ የነበርከው አንተ ብቻ ነህ?

ሰለሞን፡- አይደለሁም፤ በአጠቃላይ 9 የምንደርስ ልጆች ነው የተላክነው፤ ከዛ ውስጥ 5ቱ ብቻ ተያዙ በወቅቱ ወደዋናው ቡድን ለሙከራ ያልተላኩ ሌሎችም ምርጥ ተጨዋቾችም ነበሩና የእዚያን ጊዜ የቡድናችን ስብስብ በምርጥ ተጨዋቾች ጭምር የተገነባም ነበር፡፡

ሊግ፡- በውሰት ከሄዳችሁበት ሐዋሳ ከተማ ዳግም መምጣት ችላችሁ ነበር፤ አንተ ግን አሁንም ለቡድኑ ልትያዝ አልቻልክም?

ሰለሞን፡- አዎን፤ በወራቤ ለአንድ ዓመት ከቆየን በኋላ ለ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ተጠርተን ነበር፤ ከሐዋሳ ከተማ ቢሮ ተደውሎልንም በውሰት የተሰጣችሁ ስለሆነ ወደ ክለባችሁ ትመለሳላችሁ ተባልንና መጣን፤ ይሄን ጊዜ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ቡድኑን የለቀቀበት ወቅት ላይ ነበርና አዲሴ ካሳ የቡድኑን ሀላፊነት ሲረከብ አሁን ቡድኑ ውስጥ ያለው ክፍት ቦታ የአጥቂ ብቻ ነው፤ የተከላካይ ስፍራው ሙሉና ዝግ ነው ሲለኝ በአጥቂ ቦታ ላይ የሚጫወተው ደግሞ ገብረመስቀል ስለሆነ እሱ ለቡድኑ ተያዘ፤ እኔ ደግሞ በአሰልጣኝ በፀሎት ወደሚሰለጥነው የመድን ክለብ ለመጫወት ወደዛ አመራሁኝ፡፡

ሊግ፡- የኢትዮጵያ መድን ቆይታህ በምን መልኩ የሚገለፅ ነወ?

ሰለሞን፡- የተወዳደርነው በሱፐር ሊግ ደረጃ ቢሆንም ጥሩ ጊዜን ነው ያሳለፍኩት፤ በተለይ አሰልጣኝ በፀሎት እኔን የተሻለ ደረጃ ላይ እንድደርስ ያደርግልኝ የነበረው ጥረት የማይረሳኝም ነው፡፡

ሊግ፡- በባህርዳር ከተማ ክለብ ቆይታህ ነው በብዙዎች የስፖርት አፍቃሪዎች ልብ ውስጥ ልትገባ የቻልከው ቆይታህ ጣፋጭ ነበር ማለት ነው?

ሰለሞን፡- በጣም እንጂ፤ ወደዚህ ቡድን ከመጣሁበት ጊዜ ጀምሮ አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ለእኔ ብዙ ነገሮችን ነበር ሲያደርግልኝ የነበረው፤ ገና ከከፍተኛው ሊግ /ሱፐር ሊግ/ የመጣው ተጨዋች ሆኜና የፕሪምየር ሊጉ ልምድ ሳይኖረኝ እሱ ግን በእኔ ችሎታ ላይ እምነትን ጥሎ ብዙ አሰልጣኞች በማይደፍሩበት መልኩ በበርካታ ጨዋታዎች ላይ ከዓምና አንስቶ ስላጫወተኝ በዚህ አጋጣሚ በጣሙን ላደንቀውም ላመሰግነውም እፈልጋለው፡፡

ሊግ፡- የባህርዳርን የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ የዘንድሮ ተሳትፎ በምን መልኩ የምትገልፀው ነው?

ሰለሞን፡- ካለን ጥሩ የተጨዋቾች ስብስብና ጥንካሬያችን አንፃር ዘንድሮ ያስመዘገብነው ውጤት ደስ አይልም፤ ለሻምፒዮናነት ነበርም መጫወት የነበረብን፤ ያም ሆኖ ግን ወደ መጨረሻ ጨዋታዎቻችን አካባቢ የጣልናቸው ነጥቦች ክፍተቶችን ፈጥሮብን ዋጋ ሊያስከፍለን ስለቻለ ዘንድሮ ያልጠበቅነውን ውጤት ነው ልናስመዘግብ የቻልነው፡፡

ሊግ፡- በቤቲኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ራስህን እንዴት አገኘከው?

ሰለሞን፡- ከአምናው በተሻለ ዘንድሮ ራሴን በጥሩ ብቃት ላይ አግኝቼዋለው፤ ባለፈው ዓመት ኮቪድ ውድድሩን እስኪያቋርጠው ድረስ ከ17 ጨዋታዎች በ13ቱ ስጫወት ዘንድሮ ደግሞ ከ24ቱ ውስጥ በሁሉም ላይ ተጫውቼ ጥሩ በመንቀሳቀስ እስከብሔራዊ ቡድን ድረስ ልመረጥበትም በቅቻለው፡፡

ሊግ፡- ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለመመረጥ ችለሃል፤ ዝግጅታችሁ ምን ይመስላል? ምን ውጤትንስ ታስመዘግባላችሁ…

ሰለሞን፡- በጣም ጥሩ በሆነ መልኩ እየተዘጋጀን ነው፤ ስብስባችንም አሪፍ ነው፤ በዚህ የሴካፋ ውድድርም አዘጋጅ እንደመሆናችን ይህን ዋንጫ እዚሁ እንደምናስቀረው እርግጠኛ ነኝ፡፡

ሊግ፡- ፋሲል ከነማ ቤትኪንጉና አሸንፏል፤ አቡኪም ኮከብ ተብሏል፤ ምን አልክ?

ሰለሞን፡- ሁለቱም ይገባቸዋል፤ ከፍተኛ ልዩነቶችን ፈጥረውም ነው የውድድሩ ተሸላሚም የሆኑት፤ አቡኪ በተለይ የሚገርም ተጨዋች ሆኖ ነው ያገኘሁት፤ ከእሱ ጋር በፊት በተተኪው ብሔራዊ ቡድን አብረን ጥቂት ቆይታ አድርገን ነበር፤ ራሱን አሻሽሎና አሳድጎ የመጣ ተጨዋች ነው፤ ወደፊት ለሀገሩ ብዙ የሚሰራም ነው፡፡

ሊግ፡- በጣም የምትመኘው ነገር?

ሰለሞን፡- በእግር ኳሱ ለታላቅ ደረጃ ከመድረስ ባሻገር ከወንድሜ ፍቅሩ ወዴሳም ጋር አብሮ መጫወትን አልማለው፤ ከእሱ ጋር በብሄራዊ ቡድን ተመርጠን አብረን ነበርን በፓስፖርት ችግር አሁን ቡድኑ ጋር የለም እንጂ አብረን የመጫወት እድሉ ይኖረን ነበር፤ ወደፊት ይሄን ማሳካት እፈልጋለው፤ እሱ ግብ ጠባቂ እንደመሆኑ እኔ ተከላካይ ስለሆንኩ ከለላው መሆን እፈልጋለው፡፡

ሊግ፡- በመጨረሻ?

ሰለሞን፡- በእግር ኳስ እዚህ ደረጃ ላይ እንድደርስ የብዙ ሰዎች እገዛ አለበት፤ በሐዋሳ ቆይታዬ እንደ እንደ ተመስገን ዳና አይነት አሰልጣኞች እኔ ላይ ለፍተው እዚህ አድርሰውኛል፤ አዲሴን አሰልጣኝ በፀሎትና ፋሲል ተካልኝን የባህርዳር ከተማ ደጋፊዎችንና አመራሮችን እንዲሁም ቤተሰቦቼንና በቅድሚያ ደግሞ ፈጣሪዬን ለማመስገን እፈልጋለው፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P