Google search engine

…… የሸገር ደርቢ ስደቱ ቀጥሏል…

 

*…የወላይታ ድቻና የሲዳማ ቡና ጨዋታም  ተጠባቂ ሆኗል…..

 

በቻን ምክንያት የተቋረጠውን የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ   የጸጥታ ዋስትና ባለማግኘቱ ከአዳማ ወደ ድሬዳዋ በመመለስ ዛሬ  በሚደረገው  የሸገር ደርቢ  ይቀጥላል።

ከ41 ቀናቶች በኋላ  በአዳማ  ሊካሄድ በርካታ የእግርኳስ አፍቃሪዎች በጉጉት የጠበቁት ስደተኛው ደርቢ አሁንም ወደ መዲናዋ አዲስ አበባ የሚመልሰው ታዳጊ ሳያገኝ ስደቱ ቀጥሏል። በአቡበከር ናስር ሀትሪክ  የታገዘውና ኢትዮጵያ ቡና ቅዱስ ጊዮርጊስን 3ለ2 ከረታበት የአዲስ አበባ ስታዲየም ጨዋታ በኋላ ያለፉት አራት የሸገር ደርቢዎች በሸገር ሳይካሄዱ ቀርቷል። ድሬዳዋ ከተማ የዛሬውን ጨምሮ ሁለት ጊዜ ሀዋሳና አዳማ አንድ አንድ ጊዜ  የደርቢውን ጨዋታ ማስተናገዳቸው ታውቋል።

ሁለቱ እግርኳሳዊ ተቀናቃኞች ከ1991 ጀምሮ 44 ጊዜ ተገናኝተው  ቅዱስ ጊዮርጊስ 22 ጊዜ በማሸነፍ የበላይነቱን የወሰደ ሲሆን ኢትዮጵያ ቡና 8 ጊዜ ረትቶ 14 ጊዜ ደግሞ አቻ ተለያይተው ዛሬ ደግሞ ለ45ኛ ጊዜ የሚያደርጉት ፍልሚያ ሆኗል። ቅዱስ ጊዮርጊስ 25  ጊዜ በፕሪሚየር ሊጉ ተሳትፎ 15 ዋንጫ ሲያነሳ 26ቱ ላይ የተሳተፈው ኢትዮጵያ ቡና በበኩሉ ዋንጫውን ያነሳው አንድ ጊዜ ብቻ ነው

ሁለቱ ቡድኖች በዘንድሮ የውድድር አመት ባደረጓቸው 12 ጨዋታዎች  ፈረሰኞቹ 7 ጊዜ  አሸንፈው .4 ጊዜ አቻ ወጥተው አንድ ጊዜ ብቻ ተሸንፈው በ25 ነጥብና  በ21 ግብ 2ኛ ደረጃ ላይ ሲገኙ  እንደ ፈረሰኞቹ ሁሉ ተመሳሳይ ጨዋታ ያደረገው ኢትዮጵያ ቡና  በ5 ድል በ5 ሽንፈትና በ2 አቻ ውጤት በ17 ነጥብና 2 ግብ  9ኛ  ደረጃ ላይ ይዞ የሚያደርጉት ጨዋታ ይሆናል።

“የሸገር አርማዎች” በሚል ቅጽል በደጋፊዎቻቸው የሚጠሩት ሁለቱ ቡድኖች ዛሬ ከቀኑ 11 ሰአት ላይ በድሬዳዋ ስታዲየም ሲፋለሙ ጨዋታውን ኢንተርናሽናል  አርቢትር  ዶክተር ሃ/የሱስ ባዘዘው ይመራዋል ተብሎ ይጠበቃል።  አራተኛ ዳኛነቱን ኢንተርናሽናል አርቢትር አሸብር ሰቦቃ  ሲሆን ለረዳትነቱ አዲሱ ኢንተርናሽናል ረዳት ዳኛ አበራ አብርደውና ፌዴራል ረዳት ዳኛ ሻረው ጌታቸው መመደባቸው ታውቋል።

የተስተካካይ ጨዋታ መርሃግብሩ እሁድም ሲቀጥል  የወላይታ ድቻና የሲዳማ ቡና ጨዋታ  ከቀኑ 11ሰአት ይካሄዳል። ሁለቱ ቡድኖች በዘንድሮ የውድድር አመት ባደረጓቸው  ጨዋታዎች  የተለያየ አቋም ያሳዩ ሲሆን ወላይታ ድቻዎች 12  ጊዜ  ተጫውተው 5 ጊዜ ረትተው  4 ጊዜ አቻ ወጥተው 3 ጊዜ ተሸንፈው በ19 ነጥብና ያለምንም ግብ  5ኛ  ደረጃ ላይ ሲገኙ እንደ ወላይታ ድቻዎች ሁሉ ተመሳሳይ ጨዋታ ያደረገው ሲዳማ ቡና   በ3 ድል  በ3 አቻና በ6 ሽንፈት  በ12 ነጥብና  በ10 የግብ ዕዳ 14ኛ ደረጃ ላይ ይዞ የሚያደርጉት ጨዋታ ይሆናል።

ሁለቱም ቡድኖች የሚያደርጉትን ጨዋታ ፌዴራል አርቢትር   ቢኒያም ወ/ አገኘሁ ይመራዋል ተብሎ ይጠበቃል። ረዳቶቹ  ኢንተርናሽናል ረዳት ዳኛ  ይበቃል ደሳለኝ  ፌዴራል ረዳት ዳኛ አብዱ ይጥና ሲሆኑ አራተኛው ዳኛ ፌዴራል አርቢትር ኤፍሬም ደበሌ መሆኑ ታውቋል።

ፕሪሚየር ሊጉ የፊታችን ሃሙስ፣ ዓርብ፣ ቅዳሜና እሁድ  ከቀኑ 10 ሰዓትና ከምሽቱ 1 ሰዓት  በሚደረጉ  የ14ኛ ሳምንት መርሃግብር የሚቀጥል ሲሆን እስከ 17ኛ ሳምንት የሚደረጉት 32 ጨዋታዎች በድሬዳዋ ስታዲየም የሚቀጥሉ መሆኑ ታውቋል። ሊጉ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከጊኒ አቻው ጋር ላለበት የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የደርሶ መልስ ጨዋታ ሲባል መጋቢት 3/2015 ለ20 ቀናት እንደሚቋረጥ ሊግ  ስፖርት ያገኘችው መረጃ ያስረዳል።

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

%d bloggers like this: