ሞገስ ባጋጠመው የጤና እክል ሳቢያ በየካቲት 12 ሆስፒታል በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ትናነት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።
ሞገስ ታደሰ በአዳማ ከተማ፣ በቅዱስ ጊዮርጊስ፣ በሲዳማ ቡና፣ በወልዲያ፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫውቷል።
ተጫዋቹ ዛሬ በ9 ሰዓት በቀጨኔ ደብረ ሰላም መድሐኒአለም ቤተክርስቲያን ወዳጅ ዘመዶቹ እና የእግርኳስ ቤተሰቦች በተገኙበት ሰርዓት ቀብሩ ተፈፅሟል።
ሊግ ስፖርት ጋዜጣና ድህረ-ገፅ በተጫዋቾቹ ህልፈት የተሰማትን ጥልቅ ሀዘን ትገልፃለች።
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ! ?