የቅዳሜ ጋዜጣዎ ሊግ ስፖርት በገበያ ላይ
ሊግ ስፖርት በሳምንት አንድ ቀን ለንባብ የምትበቃ የቅዳሜ የእርስዎ ጋዜጣ ናት፤ ይህቺ ጋዜጣ ነገ ለንባብ ስትበቃ በሀገር ውስጥና በባህር ማዶ ዘገባዋ ምን ታስነብቦት ይሆን?
በሀገር ውስጥ ለቅ/ጊዮርጊስ ክለብ ዳግም ለሁለት ዓመት ለመጫወት ፊርማውን ያኖረው ሙሉዓለም መስፍን /ዴኮ/ በክለቡ ውሉን ስላራዘመበት ሁኔታና ሌሎችን ጉዳዮች አስመልክቶ ለተነሱለት ጥያቄዎች የሚለው አለው፤
ከእነዚህ ውስጥም “ለቅ/ጊዮርጊስ ተጫውቼ አሳልፌያለሁ ማለት ብቻ ዋጋ የለውም፤ ለክለቡ የግድ ዋንጫ ልታመጣለት ይገባል” ሲል ሌላው “የኢትዮጵያ ቡናን አጨዋወት ለመተግበርም ሆነ ውጤት ለማምጣት እኛ ተጨዋቾች አሰልጣኙን ልንረዳው ይገባል” ያለው ደግሞ ለኢትዮጵያ ቡና ውሉን ያራዘመው አስራት ቶንጆ ነው፤ ከሁለቱ ተጨዋቾች ጋር በሌሎች ጥያቄዎች ዙሪያም ቆይታን አድርገናል፤ ምላሻቸውንም ሰጥተውናል፡፡
ሊግ ስፖርት በባህር ማዶ ዘገባዋም ነገ ለንባብ ስትበቃ ስለ ምዕረት የለሹ ሊቨርፑል፣ ስለ ጀርመናዊው ወጣት እና ድንቅ ተጨዋች ሰርጌ ናብሪ እንደዚሁም ደግሞ ኦዚል በአርሰናል
ቤት መቆየት ይችል ይሆን በሚሉና በሌሎች ዘገባዎች ዙሪያ ነገ ሊግን የምታገኟት ይሆናል፤ ሊግ አታምልጦት
የቅዳሜ ጋዜጣዎ ሊግ ስፖርት በገበያ ላይ ሊግ ስፖርት በሳምንት አንድ ቀን ለንባብ የምትበቃ የቅዳሜ የእርስዎ ጋዜጣ ናት፤ ይህቺ ጋዜጣ ነገ ለንባብ ስትበቃ በሀገር ውስጥና በባህር ማዶ ዘገባዋ ምን ታስነብቦት ይሆን?
ተመሳሳይ ጽሁፎች