የሊጉ አዲስ አዳጊው የውበቱ አባተ ሰበታ ከተማ በክረምቱ ከፈረሰኞቹ ጋር የተለያየውን ታደለ መንገሻን አስፈርመዋል።
ባሳለፍነው ረቡዕ በተዘጋው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የተጨዋቾች ዝውውር መስኮት ንቁ የሆነ ተሳትፎ እያደረጉ ሚገኙት ሰበታዎች ኢትዮጵያ ውስጥ በፈጠራ ክህሎታቸው ከሚታወቁ ተጨዋቾች አንዱ የሆነውን ታደለ መንገሻን በመጨረሻ ሰዓት አስፈርመዋል ሲል ሀትሪክ ዘግቧል ።
ከዚህ ቀደም ለቅዱስ ጊዮርጊስ፣ደደቢት፣አርባምንጭ መጫወት የቻለው ታደለ መንገሻ ማጥቃት ላይ መሰረት ያደረገውን የውበቱ አባተን አጨዋወት ለመተግበር ከፍተኛ ሀላፊነት ከሚሰጣቸው ተጨዋቾች አንዱ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል ።