Google search engine

የባንክ አብዮቱን ያቀጣጠለው አማራ ባንክና የጣና ዋንጫ ተጣምረዋል

 

በአለም ሰገድ ሰይፉ

“ከባንክ ባሻገር” በሚል መርህ የተቋቋመውና በአጭር ጊዜ የምስረታ ዕድሜ የሀገሪቱን የባንክ አብዮት ማቀጣጠል የቻለው ግዙፉ አማራ ባንክ እንደስያሜው ሁሉ በማህበራዊ ዘርፍ የሚያደርገውን የእንቅስቃሴ አድማስ አሁንም እያሰፋ ይገኛል፡፡ ከ6 ቢሊዮን በሚበልጥ የተፈረመ ካፒታል በመጀመር አግራሞትን መጫር የቻለው አማራ ባንክ “ከባንክ ባሻገር” በሚለው መርህ የአርት ናይት በማዘጋጀት፣ የደም ልገሳ በማዘጋጀትና በምስረታው ዕለት 600 የአንበሳ አውቶብሶች ለማህበረሰቡ የነፃ ግልጋሎት እንዲሰጡ በማድረግ ማህበራዊ ኃላፊነቱን መወጣት የጀመረ ሲሆን አሁን ደግሞ የስፖርቱን ዘርፍ በመደገፍ የትውልድ ጤናን በመጠበቅ ወዳጅነትን በማጠናከርና የቱሪዝም ዘርፉን ማነቃቃት ይቻል ዘንድ የአማራ ባንክ የጣና ዋንጫ ውድድርን ስፖንሰር አድርጓል፡፡

ከመስከረም ስድስት ጀምሮ በውቢቷና በቱሪዝም መስዕቧ ተለይታ በምትታወቀው በባህርዳር ከተማ በሚጀመረው የአማራ ባንክ ጣና ዋንጫን በታይትል ስፖንሰርነት በመደገፍ ሁለገብ የሆነ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት መሰናዳቱን በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተነግሯል፡፡ ባንኩ ነግዶ ከማትረፍ በዘለለ መልኩ ይሄንን ውድድር በታይትል ስፖንሰርነት ለስፖርት አፍቃሪያኑ ሲያቀርብ ለማህበረሰቡ ያለው ፋይዳና የሚያስገኘውን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ከግምት በማስገባት መሆኑን የባንኩ ማርኬቲንግና ብራንዲንግ ማናጀር አቶ አስቻለው ታምሩ ተናግረዋል፡፡

የአማራ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ፣ ጎፈሬ ኤቨንትና አማራ ባንክ በጋራ በሰጡት መግለጫ እንደተገለፀው ከ መስከረም 6 እስከ14 ድረስ በ6 የሊጉ ክለቦችና ሁለት በተጋባዥነት ከዮጋንዳ በሚመጡ ክለቦች መካከል ውድድሩ የሚካሄድ ሲሆን ይኸው ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያለው የአማራ ባንክ ጣና ዋንጫ ውድድር አንድም ክለቦች ከፕሪምየር ሊጉ በፊት አቋማቸውን መፈተሽ የሚያስችላቸው ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ የማህበረሰቡን ተሳትፎ በማንቃትና የከተማዋን የቱሪዝም ገቢ ከፍ በማድረግ ረገድ የላቀ ሚና እንደሚጫወት ይጠበቃል፡፡ በዚህ ውድድር ላይ የተለያዩ ሰፕራይዞች እንደሚኖሩና ለአሸናፊው ቡድንም ለየት ያለ ሽልማት መሰናዳቱ ተነግሯል፡፡

አማራ ባንክ ለዚህ የውድድር ስኬት 5 ሚሊዮን ብር ስፖንሰር ያደረገ ሲሆን በቀጣይነትም “ከባንክ ባሻገር” የሚለውን መርህ አጠንክሮ በመቀጠል ስፖርቱን በከፍተኛ ደረጃ የማገዝ ፍላጎት እንዳለው የባንኩ ማርኬቲንግ ማናጀር አቶ አስቻለው ታምሩ በአፅንኦት ተናግረዋል፡፡

ህብረተሰባችን ለስፖርቱ ያለውን ከፍተኛ ፍቅር ከግምት በማስገባት የዚህን ውድድር ታይታል ስፖንሰርነት የወሰደው አማራ ባንክና የአማራ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የስምምነት ሰነዱን ተፈራርመዋል፡፡ ውድድሩም እጅግ ስኬታማ በሆነ መልኩ እንዲጠናቀቅ ለማስቻል የክልሉ መንግስት አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታ ማጠናቀቁን የክልሉ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አብርሃም ተናግረዋል፡፡ ይህ መነሻ እንደሆነ አክለው የገለፁት የባንኩ ማርኬቲንግ ማናጀር በቀጣይነትም ስፖርቱን በከፍተኛ ደረጃ መደገፍ የአማራ ባንክ ተቀዳሚ መርህ ነው ብለዋል፡፡ ለዚህ ውድድር ስኬታማነትም የጎፈሬ ስፖርት ትጥቅ አምራች ኩባንያና የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ሳሙኤል ከፍተኛ ሚና መጫወታቸው ተገልጿል፡፡

አማራ ባንክ በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ባለአክሲዮኖች ብዛት ቀዳሚ በመሆን አዲስ ታሪክ ያስመዘገበ ሲሆን በምስረታው ዕለት ብቻ በአንድ ጀምበር ከ72 በላይ ቅርንጫፎችን በመክፈትም በባንክ ኢንዲስትሪው ዘርፍ አስደማሚ ታሪክ መፃፍ የቻለ ባንክ ነው፡፡ በእዚህ ወቅትም የባንኩ ቅርንጫፎች ብዛት 110 መድረስ ችሏል፡፡ “ከባንክም ባሻገር” የሚል መርህ ያነገበው አማራ ባንክ፤

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

%d bloggers like this:
P