Google search engine

“የአሸናፊነትን መንፈስ ስለተላበስን ለሻምፒዮናነት ነው የምንጫወተው” ዮናስ ገረመው /መቀሌ 70 እንደርታ/

የመቀሌ 70 እንደርታው የአማካይ ስፍራ ተጨዋች ዮናስ ገረመው /አላባ/ ወላይታ ድቻን ወደ ቡዲቲ በማምራት
በሚገጥሙበት የነገው የሜዳቸው ውጪ ጨዋታ ሶስት ነጥብን ይዘው እንደሚወጡና የፕሪምየር ሊጉንም መሪነት
አጠናክረው እንደሚያስቀጥሉ አስተያየቱን ለሊግ ስፖርት ጋዜጣ ሰጥቷል፡፡
የመቀሌ 70 እንደርታ ክለብ በሊጉ የሁለት ሳምንታት ጨዋታዎች ተጋጣሚዎቹን በማሸነፍ 6 ነጥብን ይዞና ኢትዮጵያ
ቡናን በጎል ክፍያ በልጦ በመሪነት ላይ የተቀመጠ ሲሆን ክለቡ በቀጣይ ጊዜ በሚኖራቸው ጨዋታዎችም የአሸናፊነትን
መንፈስ በመላበስ ዘንድሮ ለሻምፒዮናነት እንደሚጫወቱም አስተያየቱን ለጋዜጣው አክሎ ሰጥቷል፡፡
የመቀሌ 70 እንደርታው የአማካይ ስፍራ ተጨዋች ዮናስ ገረመው በቡድናቸው ወቅታዊ አቋም፣ ወላይታ ድቻን
ስለሚፋለሙበት ጨዋታ፣ በሊጉ ተሳትፎአቸው ዘንድሮ ስለሚያስመዘግቡት ውጤት እና ተጨማሪ ጥያቄን ጠይቀነው
ምላሹን እንደሚከተለው ሰጥቷል፡፡
የመቀሌ 70 እንደርታን ወቅታዊ አቋም አስመልክቶ ለዮናስ ገረመው በቅድሚያ ለቀረበለት ጥያቄ ምላሹን ሲሰጥ
“የቡድናችን ወቅታዊ አቋም በአሁን ሰዓት ካለን ጥሩ የተጨዋቾች ስብሰባ፣ ከተላበስነው የአሸናፊነት መንፈስ
አንፃር እና ከአሰልጣኛችንም ገብረመድህን ኃይሌ ጥሩ ልምምድ የማሰራት ብቃቱ በመነሳት በመልካም ሁኔታ ላይ ነው
የምንገኘው፤ በጥሩ ብቃት ላይ ለመሆናችንም በተለይ ደግሞ የሚሰጠን አዳዲስና የተለያየ ስልጠና እኛን በጣም
የሚረዳን ሆኖ አግኝተነዋልና ሁላችንም የቡድኑ ተጨዋቾች ልምምዱን ተቋቁመንም በመስራት ላይ ነው የምንገኘው፡፡
የወላይታ ድቻን በሊጉ የአራተኛ ሳምንት ጨዋታ ከሜዳቸው በመውጣት ስለሚፋለሙበት ጨዋታም ለቀረበለት ጥያቄ
ሲመልስ “የመቀሌ 70 እንደርታ ክለብ የሊጉን እያንዳንዳቸውን ጨዋታዎች በሜዳውም ከሜዳውም ውጪ ሲያከናውን
ለግጥሚያዎቹ ከፍተኛ ትኩረትን ሰጥቶ ነው ወደ ሜዳ የሚገባው፤ ከወላይታ ድቻም ጋር የነገውን ጨዋታ ስናከናውን
ከግጥሚያው 3 ነጥብን ይዘን ለመውጣት ተዘጋጅተናል፤ ይህም ውጤት ይሳካልናል” ብለን ተስፋ አድርገናል፡፡
የመቀሌ 70 እንደርታ ክለብ በሊጉ ጅማሬ በአሸናፊነት መንፈሱ ቀጥሏል የእዚህ ዋንኛው ሚስጥር ምንድን ነው፤ ድሉስ
ይቀጥላል.. “በሊጉ የውድድር ጅማሬያችን ላይ ክለባችን ግጥሚያዎችን እያሸነፈ ያለበት ዋንኛው ሚስጥር
የአሰልጣኛችን የስልጠና ታክቲክ ለብዙዎቻችን ተጨዋቾች በሚመች መልኩ በመቅረቡና እያንዳንዱን
እንቅስቃሴያችንንም በጋራ አድርገን ስለምንጫወት ነው፤ ሌላው የአሸናፊነት መንፈሳችንም ከፍ ያለ ስለሆነ ይህ
ውጤትን አምጥቶልናል፤ ድሉም ቀጣይነት ይኖረዋል”፡፡ በማለት ምላሹን ሰጥቷል፡፡
የመቀሌ 70 እንደርታን የተጨዋቾች ስብስብ አስመልክቶና በክለቡ የአጭር ጊዜ ቆይታው ውስጥ ራሱም ስላለው የሊጉ
ጅማሬም ለቀረበለት ጥያቄ ምላሽን ሲሰጥ “የክለባችን የዘንድሮ የተጨዋቾች ስብስብ ወጣቶችንና በሊጉ ከፍተኛ
ልምድ ያላቸውን ልጆች አቀላቅለን የያዝንበት ነው፤ ተጨዋቾቹም አሰልጣኙ ለሚፈልገው አጨዋወት ተመርጠው
የመጡ ስለሆኑ ይሄ በሊጉ ለምናደርገው ጉዞ ይጠቅመናል፤ በመቀሌ 70 እንደርታ ቡድን ውስጥ እኔ ስላለኝ ቆይታ

መናገር የምፈልገው ወደ መቀሌ የመጣሁት ያለኝን እንቅስቃሴ በሚረዳኝ አሰልጣኝ ገብረመድህን ለመሰልጠን
በመሆኑ እስካሁን ድረስ ተመችቶኝ ነው እየተጫወትኩ ያለሁት በእዚህ ዓመትም የተሳካ የውድድር ጊዜን እንደ ዓምናው
ከአሰልጣኜ ጋር አሳልፋለው”ሲልም ሀሳቡን ሰጥቷል፡፡
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ ዘንድሮ መቀሌ 70 እንደርታ ምን ውጤት ያመጣል “የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ ዓምና
ክለቡ ጠንካራ ተፎካካሪ ነበር፤ ያመጣው ውጤትም ከታችኛው ሊግ እንደመምጣቱ በጥሩነቱ የሚጠቀስለት ነው፤
ዘንድሮ ደግሞ ከአምናው ክፍተቶቻችን የተማርንበት ነገር ስላለ በተጨዋቾች ስብስቡም የተጠናከረና የዓምናውን
ስኬታማውን አሰልጣኝም ገብረመድን ኃይሌን ወደ ቡድኑ በማስመጣቱና አሰልጣኙም በማጥቃት ላይ ያተኮረን
አጨዋወትም የሚጠቀም ስለሆነ በሊጉ የምንጫወተው ዋንጫውን ለማንሳት ነው፤ ይህንን የምናሳካበትም ሙሉ
አቅም አለን”፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

%d bloggers like this:
P