Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“በቅ/ጊዮርጊስ ቆይታዬ ዋንጫ ሳላነሳ ከክለቡ ብለያይ ኖሮ ከባድ ሀዘን ውስጥ እገባ ነበር” “ቅ/ጊዮርጊስን ብለያይም በቆይታዬ ከስኬት በተጨማሪ ክብርንና ፍቅርን አግኝቻለሁ” የአብስራ ተስፋዬ /ባህርዳር ከተማ/

“በቅ/ጊዮርጊስ ቆይታዬ ዋንጫ ሳላነሳ ከክለቡ ብለያይ ኖሮ ከባድ ሀዘን ውስጥ እገባ ነበር”

“ቅ/ጊዮርጊስን ብለያይም በቆይታዬ ከስኬት በተጨማሪ ክብርንና ፍቅርን አግኝቻለሁ”

የአብስራ ተስፋዬ /ባህርዳር ከተማ/

በኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮና ከቅ/ጊዮርጊስ ጋር በታሪኩ የመጀመሪያውን የሊግ ዋንጫ ካነሳ በኋላ በክረምቱ የተጨዋቾች ዝውውር መስኮት ባህርዳር ከተማን ተቀላቅሏል፤ ወደ ቡድኑ ካመራ በኋላም ከአዲሱ ክለቡ ጋር እንደ ቅ/ጊዮርጊስ ቆይታው ሁሉ ዳግም ይህን ዋንጫ ማንሳት ዋንኛ እልሙ እንደሆነም ወጣቱ ተጨዋች የአብስራ ተስፋዬ ይናገራል፡፡

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የተጨዋችነት ዘመን ቆይታው ከአሳዳጊ ክለቡ ደደበት እና በኋላም ላይ ዝውውር ካደረገበት የቅ/ጊዮርጊስ ክለብ ጋር ጥሩ የጨዋታ ጊዜን ያሳለፈው የአብስራ ተስፋዬ ከሊግ ስፖርት ጋዜጠኛው መሸሻ ወልዴ /G.BOYS/ ጋር በተለያዩ ጥያቄዎች ዙሪያ ቆይታን አድርጎ ለጋዜጣው ምላሹን ሰጥቷል፤

ሊግ፦ በቅድሚያ ለቃለ-ምልልሱ ፈቃደኛ ስለሆንክ ከልብ እናመሰግናለን?

የአብስራ፦ እኔም ወደ አዲሱ ቡድኔ በተቀላቀልኩበት ሰሞን እንግዳችሁ አድርጋችሁ ስላቀረባችሁኝ በተራዬ ከልብ ላመሰግናችሁ እወዳለሁ።

ሊግ፦ በክረምቱ የተጨዋቾች ዝውውር መስኮት በቅ/ጊዮርጊስ የነበረህን የውል ጊዜ አጠናቀህ ባህርዳር  ከተማን ተቀላቅለሃል፤ አዲሱ ቡድንህን  እንዴት የቅድሚያ ምርጫህ አደረግህ? በሌሎች ክለቦችስ ጥያቄ አልቀረበልህም?

የአብስራ፦ ቀርቦልኛል፤ እኔን የቡድናቸው ተጨዋች ለማድረግም ደጋግመው ጠይቀውኛል፤ ያም ሆኖ ግን ከእነዚህ ቡድኖች መካከል አንዱ የነበረውን ባህርዳርን ለምፈልገው አጨዋወቴ በመምረጤ፤ ክለቡም ትልቅ ስለሆነና አሰልጣኙም ለሚፈልገው አጨዋወትም እኔ ተገቢው ሰው ስለሆንኩና ከዚህ ቀደም ደግሞ ዕድሜያቸው ከ23 ዓመት በታች ለሆናቸው የብሔራዊ ቡድን ውስጥ መርጦኝና ጠርቶኝ ያጫወተኝ ስለሆነም ቡድኑን የቅድሚያ ምርጫዬ በማድረግ ወደ እነሱ ለማምራት እና ፊርማዬንም ለማኖር ችያለሁ።

ሊግ፦የፕሪ-ሲዝን ዝግጅትን ጀምራችኋል፤ ልምምዳችሁ ምን ይመስላል?

የአብስራ፦ እስካሁን በጥሩ ሁኔታ ነው በሜዳ ላይም በጂም ደረጃም ልምምዳችንን እየሰራን  ያለነው፤ ተጨዋቾቻችንም በመልካም ሁኔታም ላይ ነው የሚገኙት፤ ጥሩና ጠንካራ ቡድን ለመስራትም ነው እየተዘጋጀን የምንገኘው።

ሊግ፦ የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ውድድር ሲጀመር ከቡድናችሁ ምን ውጤት ይጠበቅ?

የአብስራ፦ አሁን ላይ እኛ የፕሪ-ሲዝን ዝግጅታችንን በምን መልኩ ሰርተን ማጠናቀቅ እንዳለብን ነው ትኩረት አድርገን የምንገኘው፤ ወደ ውድድሩ ስንገባ ደግሞ የራሳችንን ግብ እናስቀምጣለን፤ ያኔም በእያንዳንዱ ጨዋታዎች ላይ የምናስመዘግባቸው ውጤቶች ሁሉንም ነገሮች ይዞልን የሚመጣም ነው።

ሊግ፦ ወደ ባህርዳር ከተማ ለመፈረም ስታመራ በክለቡ በኩል የተደረገልህ አቀባበል ምን ይመስላል?

የአብስራ፦ እነሱ ገናቡድኑን ሳልቀላቀል ጀምሮ ነው በጥሩ ሁኔታ ትሪት እያደረጉኝ ሲጠብቁኝ የነበሩት፤ ወደዛ ካመራው በኋላም ከጠበቅኩት በላይ ነው ደስ የሚል እና ደማቅ የሆነ አቀባበልም ያደረጉልኝና በእዛ በጣም ደስተኛ ነኝ።

ሊግ፦ ወደ ክለቡ ካምፕ ስታመራስ አንተን በማላመዱ እና ክለቡንም በደምብ አድርገህ እንድታውቅ በማድረግ በኩል እነማን አገዙ?

የአብስራ፦ አንድ ቡድን ላይ ቆይተህ ወደ ሌላ ስታመራ ብዙ ጊዜ ነገሮች ለአንተ ከባድ ይሆንብኛል ብለህ ማሰብህ ባይቀርም እኔ ወደ ክለቡ ካመራሁበት ጊዜ አንስቶ ግን እስካሁን ብዙም  የከበደኝ ነገር ምንም የለም፤ ባህርዳርን ስቀላቀል ከብዙዎቹ ተጨዋቾች ጋር እንተዋወቅ ስለነበር  ቡድኑን በማላመዱ በኩል አግዘውኛል፤ እነዚህ ተጨዋቾች በጣም አሪፍ ልጆችም ናቸው፤ እነሱንና ቡድኑን በመቀላቀሌም በጣም ደስተኛ ነኝ።

ሊግ፦ በደደቢት የኳስ ጅማሬህን ካደረግክ በኋላ ወደ ቅ/ጊዮርጊስ አምርተህም ተጫውተሃል፤ ስለ ሁለቱ ቡድኖች የተጨዋችነት ዘመን ቆይታዎችህ ምን የምትለው ነገር አለ?

የአብስራ፦ በደደቢት ቆይታዬ ምንም እንኳን ክለቡ በመጨረሻ ሰዓት ላይ ቢወርድም፣ በእዛም ባዝንም ቡድኑን ከታችኛው ከተተኪው አንስቶ ኳሱን በጥሩ ሁኔታ ተጫውቼ ያሳለፍኩበት ወቅት ስለሆነ ያ ደስተኛ እንድሆን አድርጎኛል፤ ይሄ ክለብ በወቅቱ የሀገሪቱ ትልቅ ቡድን ነበር፤ ለእኔ ደግሞ ብዙም ነገሮችንም አድርጎልኛል፤ የኳስ መነሻዬም የሆነ ቡድን ነበር፤ ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ሳመራ ደግሞ ወደ እነሱ የተጓዝኩበት ዋናው ምክንያት ትልቅ ቡድን እንደመሆኑና በተደጋጋሚም ስኬታማ ክለብ በመሆኑ የሊጉን ዋንጫ ለማምጣት ነው እቅዳችን የነበረው፤ ያም ሆኖ ግን ብዙ ችግሮችንና መከራዎችን አሳልፈን ላለፉት አራት ዓመታት ውጤት በማጣታችን ልናዝን ብንችልም በስተመጨረሻ ላይ ግን ከዓመታት ቆይታችን በኋላ ይኸውን ያሰብነውን ዋንጫ ወደለመደው ቡድን ለማምጣት ስለቻልንና የእዛም ታሪክ ተሳታፊና የድሉ ባለቤትም ስለሆንኩኝበጣም ደስተኛ ከመሆኔ ባሻገር ራሴን  እድለኛ አድርጌም ነው እየቆጠርኩኝ ያለሁት፤ አሁን ደግሞ ወደ ባህርዳር ከተማ ክለብም አምርቻለውና ከእነሱም ጋር ጥሩ የስኬት ጊዜን ለማሳለፍ እየተዘጋጀው ነው የምገኘው።

ሊግ፦ አንድ እግር ኳስ ተጨዋች ከሚጫወትበት ክለብ ጋር ዋንጫ ሊያነሳ እንደሚችለው ሁሉ ከሊጉ የመውረድ እጣም ሊያጋጥመው ይችላል፤ አንተ በእዛ ውስጥ አልፈሃልና ስሜቱን እንዴት አድርገህ ነው የምትገልፀው?

የአብስራ፦ ከእዚህ በፊትም ተናግሬዋለሁ የደደቢት መውረድ በጣም ነበር ያሳዘነኝ፤ ምክንያቱም ክለቡ የብዙ ተጨዋቾች መፍለቂያ ስለነበርና በወጣት ተጨዋቾች ላይም እምነት የነበረው ክለብም ስለነበር ነው፤ በቅ/ጊዮርጊስ ደግሞ ሻምፒዮና መሆን ዝም ብሎ ነው የሚመስለኝ፤ አሁን ስኬታማ ከሆን በኋላ ያለውን የደስታ ስሜት ስገልጸው ባለ ዋንጫ መሆን ለካ እንዲህ  ነው የደስታ ስሜቱ የሚል ነገርንስለተመለከትኩኝ እና በእግር ኳሱ ዘመኔም ወደፊት ልናገረው የምችለው አንድ ታሪክን ላስፅፍም ስለቻልኩኝ በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡

ሊግ፦ በቅ/ጊዮርጊስ የዘንድሮ የተጨዋችነት ዘመን ቆይታህ ከክለቡ ጋር ዋንጫን ባታነሳ ኖሮ በውስጥህ ምን አይነት ስሜት ይፈጠርብህ ነበር?

የአብስራ፦ ቅ/ጊዮርጊስ የሊጉን ዋንጫ ማምጣት እየፈለገ በቅርብ ዓመታቶች ይህን ስኬት አጥቶ ስለነበር ከባድ እና ጥሩ ያልሆነ ስሜት ነበር በውስጤ የሚፈጠርብኝ፡፡

ሊግ፦ በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ዋንጫውን ለማንሳታችሁ በተለየ ሁኔታ የምትገልፀው ነገር አለ?

የአብስራ፦ አዎን፤ ዋናው ነገር የሊጉ ጅማሬያችን ጥሩ መሆኑና ምርጥ የሆነ ቡድንም ስለነበረን ነው፤ ይሄን የመሰለ ቡድን ይዘን ዋንጫ ባናመጣ ደግሞ በኳስ አፍቃሪውም ሆነ በደጋፊዎቻችን ዘንድ ከባድ ሀዘን ውስጥ እንድንገባም ያደርገን ስለነበር በስተመጨረሻ ግን በፈጣሪ እገዛ ጭምር ድሉን አሳክተነዋልና በእዛ ደስተኛ ነኝ፡፡

ሊግ፦ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ዘንድሮ ምን አይነት ገፅታ ነበረው?

የአብስራ፦ የዘንድሮ ውድድር ሻምፒዮናውም ሆነ አንዱ ወራጅ ቡድኑ በመጨረሻው ቀን ጨዋታ የታወቀ ስለነበር በጣም አጓጊ ነበር፤ ለእኛ ቡድን ደግሞ ከአራት ዓመታት ቆይታ በኋላ ዋንጫውን ያገኘንበት ስለነበር ደስታችን በጣም ልዩ ነበር፡፡

ሊግ፦ ብዙዎቹ ደጋፊዎቻችሁ አንተን ከቅ/ጊዮርጊስ ትለቃለህ ብለው አልጠበቁም ነበር፤ መልቀቅህ ግን እውን ሆነ? እንዴት እና በምን መልኩ ልትለያይ ቻልክ?

የአብስራ፦ ምክንያቱን ይሄ ይሄ ነው ማለት ባልፈልግም እኔም ቡድኑን እለቃለሁ ብዬ ፈፅሞ አልጠበቅኩም ነበር፤ ምክንያቱም ቡድናችን ከፊቱ የአፍሪካ ክለቦች ቻምፒዮንስ ሊግ የውድድር ተሳትፎ ስለነበረበትም ጭምር ነው፤ ከእዛ ውጪ በክለቡ ቆይታዬ በቋሚ ተሰላፊነትነም እየተጫወትኩ ነበር፤ ሌላው ቅ/ጊዮርጊስ የሀገሪቱ ትልቁም ቡድን ነው፤ ይህን አይተህ ዋንጫ ካነሳ ቡድን ጋር መለያየት በጣም ከባድም ነውና ፈጣሪ ባለው ሁኔታ ነው ከክለቡ ጋር ልለያይ የቻልኩት፡፡

ሊግ፦ በቅ/ጊዮርጊስ ቆይታህ ደጋፊዎቻችሁን ግለፃቸው ብትባል…?

የአብስራ፦ እነሱን በቀላል ቋንቋ የምትገልፃቸው አይደሉም፤ ከሀገር ሀገር የማይቀሩ እና እኛን በጥሩ ሁኔታ የሚደግፉን ናቸው፤ በተለይም ደግሞ ይሄን ዓመት ላይ የዋንጫው ጉጉታቸው ከፍ ያለ ስለነበር በተለየ መልኩ ሲደግፉንና ከጎናችንም የነበሩ ናቸው እና ላመጣነው ውጤት የእነሱ እገዛ ከፍ ያለ ነበር፤ እነሱ ለሰጡን ድጋፍም ሊመሰገኑ ይገባል፡፡

ሊግ፦ በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ የመጨረሻው ቀን ጨዋታ ላይ ዋንጫውን ስታነሱ የአንተ የደስታ ስሜት ምን ይመስል ነበር? ማሊያህን ወይንም ደግሞ ሜዳሊያህንለደጋፊ ሰጥተሃል?

የአብስራ፦ ዋንጫውን ስናነሳ የነበረው የእዛን ዕለቱ ደስታዬ ልዩ እና በጣምም ጣህም የነበረው ነው፤ ማሊያን በተመለከተ የሊጉ ውድድር ሳይጠናቀቅ ጀምሮ ደጋፊዎች ስጠን ብለው ይጠይቁኝ ነበር፤ በእዚህ አጋጣሚ ስላልሰጠዋቸው ይቅርታን መጠየቅ እፈልጋለሁ፤ ሜዳሊያን በተመለከተ ደግሞ ለእኔ ታሪኬ ስለሆነ ለእነሱ ሳልሰጥ በቤቴ አስቀምጬዋለሁ፡፡

ሊግ፦ በአዲሱ የውድድር ዘመን ምን አይነት የሊጉ ፉክክር ሊኖር ይችላል፤ ዲ. ኤስ. ቲቪ ወደ ሀገራችን ከመጣ በኋላስ እግር ኳሱ ላይ ያለው ገፅታ ምን ይመስላል?

የአብስራ፦ የዲ. ኤስ. ቲቪ መምጣትና የጨዋታዎቹ የቀጥታ ስርጭት ማግኘት መቻል በእግር ኳሱ ላይ ብዙ ለውጦችን በተጨዋቾች ላይም ሆነ በቡድኖች ላይ እንድንመለከት አድርጎናል፤ ክለቦች ከዓመት ዓመት እየተጠናከሩ መጥተዋል፤ ተጨዋቾችም ብቃታቸውን በማሻሻል ራሳቸውን ገበያ ላይ ለማውጣት እየታገሉም ናቸው፤ ይሄን ካልኩ ዘንድሮ ስለሚኖረው ውድድር ደግሞ በሊጉ ላይ ጠንካራ ፉክክር እንደሚኖር አምናለሁ፡፡

ሊግ፦ ቤትኪንጉ አቡበከር ናስርን ወደ ደቡብ አፍሪካው ማሜሎዲ ሰንዳውንስ አምርቶ እንዲጫወት እድሉን ፈጥሮለታል፤ ስለ አቡበከር ምን የምትለው ነገር አለ?

የአብስራ፦ ስለ አቡኪ እኔ ብቻ ሳልሆን ህዝቡ ሁሉ ጭምር ነው ምስክርነቱን የሚሰጠው፤ ወደ ውጪ ወጥቶ በመጫወቱም በጣም ደስተኛ ነኝ፤ እሱ ዲ. ኤስ. ቲቪ ከመጣ ጀምሮ የተሻለ እንቅስቃሴን ነው እያደረገ ያለው፤ ከዓመት ዓመት ችሎታውን እያሻሻለም ነው የመጣው፤ ጠንክሮ መስራት ይጠበቅበታል እንጂ ከእዚህ በላይም በችሎታው መጓዝ ይችላል፡፡ በሜዳ ላይ አሁን እያሳየ ከሚገኘው የጨዋታ እንቅስቃሴው አንፃርም የኳስ ማቆሚያው ሰንዳውንስ ብቻም አይደለም፤ ከአቡኪ ጋር ከታች ጀምሮ ስንጫወት የማውቀውም ልጅ ነበርና ሌሎች የተሻሉ በሚባሉ ሀገራትም መጫወት የሚችል ልጅ ነው፡፡

ሊግ፦ በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ የቱ ተጨዋች ነው ዘንድሮ ጎልቶ የወጣብህ?

የአብስራ፦ ስም መጥቀስ ባልፈልግም በአብዛኛው የእኛ ቡድን ተጨዋቾች ናቸው ወጥ የሆነ አቋም ስለነበረን ከሌሎች ይልቅ ጎልተው ሊወጡ የቻሉት፡፡

ሊግ፦ የአብስራን በመጪው ዓመት እንዴት እንጠብቀው?

የአብስራ፦ ባህርዳር ከተማን እንደመቀላቀሌ በቡድኑ በሚኖረኝ ቆይታዬ ከዘንድሮ በተሻለ አቋም ላይ ሆኜ የውድድሩን ዘመን ለማሳለፍ ዝግጁ ነኝ፡፡

ሊግ፡- ለብሔራዊ ቡድን መመረጥ አልናፈቅህም?

የአብስራ፦ ናፍቆኛል እንጂ፤ ይሄ የሁሉም ተጨዋቾች ምኞትም ነው፤ በቀጣዩ ዓመት እንደምጠራ ደግሞ እርግጠኛ ነኝ፡፡

ሊግ፦ የክረምቱ የእረፍት ጊዜ በአንተ በኩል እንዴት አለፈ?

የአብስራ፦ወደ እረፍት ጊዜው የሄድኩት ሻምፒዮና ሆነን ስለነበርና ጊዜውንም በአግባቡ ተጠቅሜው ስለነበር ደስ በሚል ሁኔታ ነው ከቤተሰቦቼ እና ከጓደኞቼ ጋር  ክረምቱን ያሳለፍኩት፡፡

ሊግ፦ በመጨረሻ…?

የአብስራ፦ በቅ/ጊዮርጊስ የተጨዋችነት ዘመን ቆይታዬ ዘንድሮ ደጋፊዎቻችን የተመኙትንና ያለሙትን ዋንጫ ሊያገኙ በመቻላቸው በጣም ደስተኛ ነበርኩ፤ ከእዛ ውጪ ልናገር የምፈልገው ደግሞ በኳስ ዘመኔ ከእኔ ጎን ሆኖ ለረዳኝ ፈጣሪዬ፣ ቤተሰቦቼ፣ የክለብ አጋር ጓደኞቼ፣ ደጋፋቻችን፣ ጓደኞቼ እንደዚሁም ደግሞ የእኔ ጓደኛም ብዙ ያደረጉልኝ ነገር ስላለ እነዚህን አካላቶች አመሰግናለሁ፡፡

 

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P