የአዲስ አበባ ከተማ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በከተማ ደረጃ ከሚገኙ የብሔራዊ ሊግ፣ የከፍተኛ ሊግና የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ጋር በጋራ መስራትና ድጋፍ መስጠት ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ በኢንተርኮንትኔንታል ሆቴል አካሂዷል።
በውይይቱም ላይ ፌዴሬሽኑ እስካሁን ድረስ ለአዲስ አበባ ክለቦች ምንም አይነት ድጋፍ ያላደረገ መሆኑን ፕሬዝዳንቱ ገልፀው፤ በቀጣይ የአዲስ አበባ ክለቦች የማዘውተሪያ እና የውድድር ሜዳ ችግር፣ የስፖርታዊ ጨዋነት ችግር፣ የውድድሮች ችግር እና አዳዲስና የማፍረስ አደጋ ያለባቸውን ክለቦች የመደገፍ ጠንካራ ስራ ለመስራት እንደተዘጋጀ ተገልጿል።
ውይይቱ ቀጣይነት ያለው መሆኑ አፅዕኖት ተሰጥቶበታል።