Google search engine

“የኢትዮጵያ ቡናን አጨዋወት ለመተግበርም ሆነ ውጤት ለማምጣት እኛ ተጨዋቾች አሰልጣኙን ልንረዳው ይገባል” አስራት ቶንጆ /ኢትዮጵያ ቡና/


በመሸሻ ወልዴ /G.BOYS/

ኢትዮጵያ ቡና መቀመጫውን ዝዋይ /ባቱ/ከተማ ላይ አድርጎ የፕሪ ሲዝን ዝግጅቱን በቀድሞ ተጨዋቹና አሰልጣኙ ካሳዬ አራጌ አማካኝነት ከ15 ዓመታት በኋላ ዳግም በመገናኘት መስራትን ጀምረዋል፤ ቡናዎች ይሄን ልምምድ መስራት በጀመሩበት የአሁን ሰዓት ላይም ተጨዋቾቹ የአሰልጣኙን የጨዋታፍልስፍናና ታክቲክ በሜዳ ላይ ለመተግበር ሙከራን እያደረጉ መሆናቸውን እየተናገሩሲሆን ይህን አጨዋወት በሚላመዱበት ሰዓትም ጥሩ ውጤትን ለማምጣት እንደሚችሉ አስተያየትንም እየሰጡበት ይገኛል፡፡
ኢትዮጵያ ቡናዎች የፕሪ ሲዝን ዝግጅታቸውን በተጠናከረ መልኩ እየሰሩ ባለበት የአሁን ሰአት ላይ ከክለቡ ተጨዋቾች መካከል አንዱ የሆነውንና በሊጉ ቆይታውም ለቡድኑ ጥሩ መንቀሳቀስ የቻለውን አስራት ቶንጆን በተለያዩ ጥያቄዎች ዙሪያ ያናገርነው ሲሆን ተጨዋቹም ምላሹን በሚከተለው መልኩ ሰጥቷል፡፡
ኢትዮጵያ ቡና በዝዋይ /ባቱ/ እያከናወነ ስላለው የፕሪ ሲዝን ዝግጅት
“የኢትዮጵያ ቡና የእስካሁኑ የፕሪ ሲዝን ዝግጅት በጣም ጥሩ እና የእኛንምችሎታ የሚያሳድግልን ነው፤ አዲሱ አሰልጣኛችን ካሳዬ አራጌ በአሁን ሰዓት እየሰጠን ያለው ስልጠና ከኳስ ጋር የተያያዘና አድካሚም የሆነ ልምምድ ነው፤ እኛም የእሱን የአጨዋወት ፍልስፍናና ልምምድ በሜዳ ላይ ለመተግበር ጊዜ ሊወስድብን ቢችልም ሙከራን በማድረግ ላይ ነን፤ለእሱምቢሆን ስራውን በተግባር ላይ ለማዋል በቂ ጊዜም ያስፈልገዋልና በእዚህ ሁኔታ ውስጥ ሆነን ነው እየተለማመድን የምንገኘው”፡፡
በኢትዮጵያ ቡና ውስጥ አሁን ላይ እየሰራችሁት ያለው የፕሪ ሲዝን ልምምድ በአንተ የኳስ ህይወት ውስጥከከዚህ ቀደሙ የሚለይ ነው
“አዎን! ይኸኛው በጣም ይለያል፤ አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌአብዛኛው ስልጠናው ከኳስ ጋር የተያያዘ ሆኖ የአዕምሮ ስራን ነው እያሰራን የሚገኘው፤ ብዙ ኮቾች ከዚህ ቀደም የፕሪ ሲዝን ልምምድን ሲያሰሩ የነበሩት ሩጫ የሚበዛበትና አቅምንም የሚጨርስ ነበር፤ የካሳዬ ግን ኳስን መሰረት ባደረገ እና አሰራሩም ድካም ያለው በመሆኑ ይሄ ለእኔ ለየት ብሎብኛል”፡፡
በፕሪ ሲዝን ዝግጅቱ አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ እስካሁን እንደ ግል ያለህ ነገር አለ?
”የለም፤ምክንያቱም የግሸን ማርያምን በዓል ለማክበር ወደ ስፍራው ሄጄ ስለነበርናየቡድኑንምየፕሪ ሲዝን ዝግጅት የተቀላቀልኩት ዘግይቼም ስለነበር እስከአሁን ተቀራርበን ያወራነው አንዳችም ነገር የለም”፡፡
በኢትዮጵያ ቡና የአዲሱ አሰልጣኝ አጨዋወት ውስጥ ዘንድሮ የተሳካ ጊዜያትን የምታሳልፍ ይመስልሃል?
“አሁን ላይ ሆኜ እንዲህ ማለት አልችልም፤ ምክንያቱም የኢትዮጵያ ቡናው አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ በሚፈልገው አጨዋወት ውስጥ እኔን የእርስ በርሱ ግጥሚያ ላይ እየተጠቀመብኝ ያለው ከዚህ ቀደም ብዙም ተጫውቼ በማላውቅበት የስቶፐር አጨዋወት ውስጥ ነውና በእዚያቦታ ላይ ያለኝን አቅም በቀጣይነት ሳውቅ ነው የእዚህ ዓመት ላይ የተሳካ ጊዜያትን አሳልፋለሁ ልልህ የምፈልገው”፡፡
ኢትዮጵያ ቡና በእዚህ ዓመት ይዞት በሚቀርበው አዲሱ አጨዋወቱ ሻምፒዮና ይሆናል?
“እሱን ጊዜ ነው የሚፈታው፤ ክለባችን ዘንድሮ ለየት ባለ አጨዋወትና የእግር ኳስ አስተሳሰብ ለውድድር ይቀርባል፤ የአሰልጣኙን የአጨዋወት ፍልስፍና እኛ ተጨዋቾች ተግባራዊ ለማድረግ ከቻልን ሻምፒዮና እንሆናለን፤ ያን ካላደረግን ደግሞ ሻምፒዮና አንሆንም፤ከእነዚህ ነገሮች ውስጥ ግን ቡድናችን ቅድሚያ የሚሰጠው አዲሱን የቡድኑን አጨዋወት በሜዳ ላይ ተግባራዊ ማድረግ ነው፤ ከዛ በመቀጠልም አጨዋወቱን ጠብቆ የሻምፒዮናነቱን ዋንጫ ማንሳት መቻል ነው”፡፡
በኢትዮጵያ ቡና የውል ጊዜህን እንደጨረስክ ወደ ሌሎች ክለቦች ልታመራ ነበር ተብሏል፤ በኋላ ላይ ግን ወደ ቡድኑ ተመለስክ፤ ይሄ የሆነበት ምክንያት ምን ነበር?
“የኢትዮጵያ ቡናዎች ጋር የነበረኝን የውል ጊዜ እንዳጠናቀቅኩ መጀመሪያ ላይ ወደየትም ክለብ ለመግባት አላመራሁም ነበር፤ ምክንያቱም ቡናዎች እኔን በቡድኑ ለማስቀጠል ይፈልጉ ነበርና በድርድር ላይ ነው የቆየሁት፤ ያኔ ታዲያ ከእነሱ ጋር በገንዘብ ክፍያው ልንስማማ ባልቻልንበት ሰዓት የውል ጊዜዬ መጠናቀቁን ያውቁ ወደነበሩና እኔን ወደሚፈልጉኝበርካታ ክለቦች ላመራ እየተዘጋጀው ባለበት ሰዓት ከቡና ጋር በድጋሚ በክፍያው ዙሪያ ተነጋግረን ከስምምነት ላይ ለመድረስ በመቻላችን በስተመጨረሻ ለሌሎቹ ቡድኖች ሳልፈርም የቡናንየመጨረሻ ውሳኔ ልጠብቅ ስለቻልኩ የጥቅም ማስተካከያ ተደርጎልኝበክለቡ ውሌን ላራዝም ቻልኩ”፡፡
ለኢትዮጵያ ቡና ጥሩ ብትጫወትም ለብሄራዊ ቡድን ግን መመረጥ አልቻልክም፤ ለምን?
“ይሄ እኔን ግራ ያጋባኝ ጉዳይ ቢሆንም ለምን አልተመረጥኩም ብዬ ግን አሰልጣኞችንም ሆነ ሌሎች ማንኛውንም ሰዎች አልወቅስም፤ ምክንያቱም ከአጨዋወት ዘይቤ ጋር በተያያዘ አሰልጣኞች የየራሳቸው የሆነ የጨዋታ ፍልስፍና እንዳላቸው ስለማውቅ ነው፤ ያም ሆኖ ግን ለብሄራዊ ቡድን ተመርጬ መጫወትን እፈልጋለሁና ወደፊትም ቢሆን ጠንክሬ ሰርቼ በመምጣት እድሉን ማግኘት እፈልጋለሁ”፡፡
በእግር ኳስ አሁን ያለህበትን ደረጃ የት ቦታ ላይ ታስቀምጠዋለህ?
“የእግር ኳስን ስትጫወት ብዙ ጊዜ ስለራስህ መግለፅና ማውራት በጣም አስቸጋሪ ነገር ነው፤ ሌላ ሰው ስለአንተ ሲያወራልህ መስማት ነው በጣም ደስ የሚለው”፡፡
በመጨረሻ…..?
“የኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ክለብ የዘንድሮው የውድድር ዘመን ተሳትፎው ላይ ለሃገር ጭምር ይጠቅማል ተብሎ የሚታሰበውን የጨዋታ ፍልስፍና በሜዳ ላይ ተግባራዊ ለማድረግና ብሎም ደግሞ ሻምፒዮና ለመሆንም ነው የሚጫወተው፤ ይህን ካሰብን አዲሱ አሰልጣኝን እኛ የቡድኑ ተጨዋቾች በጣም ልንረዳው ይገባናል”፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

%d bloggers like this:
P