Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኘሪሚየር ሊግ ክለቦች የሊግ ካምፓኒ ምሥረታ ዝግጅት እንዲያደርጉ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባው በገለጸው መሠረት ጥር 7 ቀን 2011 ዓ.ም በኢንተርኮንትኔታል ሆቴል ከኘሪሚየር ሊግ ክለቦች አመራሮች ጋር የጋራ ውይይቱን አካሂዷል፡፡

 

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኘሪሚየር ሊግ ክለቦች የሊግ ካምፓኒ ምሥረታ ዝግጅት እንዲያደርጉ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባው በገለጸው መሠረት ጥር 7 ቀን 2011 ዓ.ም በኢንተርኮንትኔታል ሆቴል ከኘሪሚየር ሊግ ክለቦች አመራሮች ጋር የጋራ ውይይቱን አካሂዷል፡፡

በእለቱም የፌዴሬሽኑ ኘሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጂራ በቀጣይ እንዲካሄድ አጀንዳ የተያዘለት የኢትዮጵያ ኘሪሚየር ሊግ የሊግ አደረጃጀት ቢሆንም በአሁኑ ሠዓት እየተካሄዱ የሚገኙት የኘሪሚየር ሊግ ውድድሮች በተለያዩ የመንግሥት አካላት፣ የእግር ኳስ ፌዴሬሽኖች፣ የክለብ አመራሮች፣ የደጋፊ ማህበራት እና ደጋፊዎች እንዲሁም የእግር ኳስ አፍቃሪው ማህበረሰብ በአደረጉት ጠንካራ የሰላም ድጋፍ ውድድሮቹ በየክልሉ በሰላማዊ መንገድ እንዲካሄዱ ለአበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን በፌዴሬሽኑ እና በኘሪሚየር ሊግ ክለቦች ስም አቅርበዋል፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በአዘጋጀው የአደረጃጀትና የሪፎርም ጥናት ሰነድ ከዘጠኙ ችግር መፍቻ ርዕሰ ጉዳዮች አንዱ የሊግ አደረጃጀት በመሆኑ ለተሰብሳቢው ግልጽ በሆነ መልኩ ለማስረዳት፣ የፌዴሬሽኑ ሥራ ውድድሮችን ለመምራት ብቻ ባለመሆኑና ይህንን ለመቅረፍ እንዲቻል፣ ትራንስፎርም ለማድረግ እና እግር ኳሳችንን ለማዘመን በማለት የአዘጋጀውን ሰነድ ለሊግ ካምፖኒ ምስረታው መነሻነት እንዲያገለግልና ከአገራችን እግር ኳስ አንፃር ለትግበራ እንዳያዳግት ጥናቱን ከአካሄዱት ባለሙያዎች አንዱ በሆኑት በአቶ ገዛህኝ ወልዴ ቀርቧል፡፡ በቀረበውም ሰነድ ዙሪያ የተለያዩ ሃሳቦች ከተሰብሳቢ ክለቦች አመራሮች ቀርበው ሰፊ ውይይት ተደርጒባቸዋል፡፡

የክለብ አመራሮችም አዲሱ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ለጠቅላላ ጉባኤው ቃል በገባው መሠረት የጥናት ሰነዱ እንዲዘጋጅ በማድረግ ለሊግ አደረጃጀቱ መነሻ በግብሃትነት በማቅረቡ እንዲሁም ጥናቱን የአካሄዱትን ባለሙያዎች አመስግነዋል፡፡ በማከልም ፌዴሬሽኑ ክለቦችን የሚወክል የሊግ ኮሚቴ መስራች ተወካይ እንዲልክ በመጠየቀው መሠረት ግማሹ የአሳወቀ በመሆኑና የቀሩት ባለማሳወቃቸው ምክንያት ሚዛናዊ አሠራር ለመስራት እንዲቻል በቀጣይ የ16ቱ ክለቦች ተወካዮች ታውቀው የአተገባበር ሂደቱን በማጥናትና መሠረት ማሲያዝ የሚቻልበት አሰራር መኖር እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

በዚህም ፌዴሬሽኑ ተወካዮቻቸውን የላኩ ክለቦች ለጉዳዩ ያላቸውን ቁርጠኝነት የሚገልጽ መሆኑንና ያላሳወቁ ክለቦች እንዲያሳውቁ ያሳሰበ ሲሆን ክለቦቹ የሚወክሏቸውን ባለሙያዎች ሲመርጡ የእግር ኳስ ኢንዱስትሪውን የሚያውቁ፣ ሥራውን በብቃት መወጣት የሚችሉ፣ የጥናትና የሊግ አደረጃጀት ሥራ ለመስራት አቅም ያላቸውን መሠረት ማድረግ እንደሚገባቸው አጽንዎ በመስጠትና የተመረጠውንም አንድ ተወካይ እስከ ጥር 14 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ ለፌዴሬሽኑ ጽ/ቤት በደብዳቤ እንዲያሳውቁና በቀጣይ የሊግ ካምፖኒ መስራች ኮሚቴ ቡድኑ ወደ ሥራ እንደሚገባ ገልጿል፡፡ በፌዴሬሽኑ በኩል ቡድኑ በአፋጣኝ ወደ ዝግጅቱ ለመግባት እንዲያስችለው የመሰብሰቢያ ቢሮ እንደሚመቻችና አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ እንዲሁም የሊግ መስራች ኮሚቴ ቡድኑ የስራ እቅዱን በማውጣት ተጨማሪ የባለሙያ ድጋፍ የሚያስፈልገው ከሆነ ለጽ/ቤት በማሳወቅ በጥናት ሰነድ ዝግጅት በአገኘው ጥሩ ተሞክሮ መሠረት ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የከፍተኛ ባለሙያዎችን ድጋፍ በመጠየቅ እንደሚያሟላላቸው አረጋግጧል፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P