Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“የኢትዮጵያ ኳስ የማያድገው ኳሱ በአሰልጣኞችና በደላሎች እጅና ስር ስለሆነ ነው” በባህሬን ሊግ የሚጫወተው ሚካኤል እሸቱ

 

በኢትዮጵያ ውስጥ በነበረው የተጨዋችነት ቆይታው የባንኮች ተስፋ ቡድንን ጨምሮ ለሞጆ ከነማ፣ ለወራቤ ከነማ፣ ለቡታጀራ ከነማ እና ለደብረማርቆስ ከነማ በመጫወት አሳልፏል፤ በሀገር ውስጥ በዚህ ደረጃ መጫወት ከቻለም በኋላ ወደ ሌሎች ክለቦች ገብቶ ለመጫወት ዕድሌ በእኛ ሀገር ደረጃ በአብዛኛው አስቸጋሪና ፈተና ሆነብኝ በሚል ተጨዋቹ ወደ ባህሬን በመጓዝ የአሁን ሰዓት ላይ በባህሬን አንደኛው ሊግ ውስጥ ኢስትረፋ ለሚባል ክለብ እተጫወተ ይገኛል፤ ይሄ ተጨዋች በሀገር ውስጥ በነበረበት ጊዜ ስለነበረው ቆይታ እና ወደ ባህሬን ከተጓዘ በኋላም ስላጋጠሙት ነገሮች በጥቂቱም ይህን ብሏል፡፡
“በኢትዮጵያ ውስጥ በወጣትነት ዕድሜ ላይ ሆኜ ኳስን እስካለፈው ዓመት ድረስ በታችኛው ሊግ ደረጃ ለመጫወት ችያለው፤ ከዛ በኋላም ክለብ ገብቶ ለመጫወት ብዙ ነገሮች አስቸጋሪ እና ፈታኝ ነው የሆኑብኝና አማራጬን ፈልጌ ነው ወደ ውጪ በመውጣት የባህሬን ሊግ ላይ እየተጫወትኩ የምገኘው፤ በኳስ ህይወትህ እና በሌላ ጉዳዮች ብዙ ፈተናዎች ይኖራሉ፤ በህይወት አጋጣሚም አንድ ሰው ባህር ውስጥ ይወረውረሃል፤ እዛ ባህር ውስጥ አንድ እንጨት አለ፤ ያንን እንጨት ይዘህ ዋኝተህ ካልወጣ እዛው ሰምጠህ ትቀራለህና የኢትዮጵያም እግር ኳስም እንደዛው ነው፤ “የኢትዮጵያ ኳስ የማያድገው ኳሱ በአሰልጣኞችና በደላሎች እጅና ስር ስለሆነ ነው” ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ አቅም ያላቸው እና ያልታዩ ልጆችም አሉ በማለትም አስተያቱን ሰጥቶ በባህሬንም ስላለው ቆይታ ሲናገር “ወደባህሬን በኤጀንት ስላልመጣው ብዙ ውጣ ውረድ አሳልፌያለው፤ ያም ሆኖ ግን ቤተሰቦቼ እዛ ስለነበሩና ብዙ ስላገዙኝ እንደዚሁም ደግሞ የእኔና የፈጣሪ ጥረትም ተጨምሮበት ልጫወት ችያለው በዚህ አጋጣሚም ፈጣሪዬን አመሰግናለውም በማለት አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡ ተጨዋቹን በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ጠይቀነው የሰጠን ምላሽ ይህን ይመስላል፡፡
ሊግ፡- በቅድሚያ ራስህን አስተዋውቅ?
ሚካኤል፡- ሚካኤል እሸቱ እባላለሁ፤ ተወልጄ ያደግኩት በሞጆ ከተማ ነው፡፡
ሊግ፡- እድሜ?
ሚካኤል፡- 24፡፡
ሊግ፡- ቁመትና ክብደት?
ሚካኤል፡- 74 ኪሎ ስመዝን 1ሜትር ከ77 ሜትር ቁመት አለኝ፡፡
ሊግ፡- የምትጫወትበት ቦታ?
ሚካኤል፡- የቀኝ አማካኝ እና ቀኝ ተደራቢ አጥቂ፡፡
ሊግ፡- በቅድሚያ ራስህን አስተዋውቅ?
ሊግ፡- የእግር ኳስን ለመጀመሪያ ጊዜ የት መጫወት ጀመርክ?
ሚካኤል፡- የእግር ኳስን በታዳጊነት ዕድሜዬ መጫወት የጀመርኩት ተወልጄ ባደግኩበት የሞጆ ከተማ ውስጥ ነው፤ እዛም ብርሃን ሞጆ ለሚባል የሰፈር ቡድን ሰልጥኜና ተጫውቼ ካለፍኩ በኋላ ትንሽ ከፍ ስል በአሰልጣኝ ሲሳይ ከፍያለው አማካይነት ለሞጆ ከተማ እንድጫወት ጥሪ ቀርበልኝና በዚሁ መልኩ ነው ክለብ ውስጥ ገብቼ መጫወት የጀመርኩት፡፡
ሊግ፡- ለሞጆ ከተማ በጊዜው የተጫወትክበት ሂደት እንዴት እና ምን ይመስል ነበር?
ሚካኤል፡- ጊዜው 2003 አካባቢ ነው፤ የሞጆ ከተማ ክለብ ያኔ ይጫወት የነበረውም በኦሮሚያ ሊግ ደረጃም ጭምር ነበርና ጥሩ እና አበረታች እንቅስቃሴ በማሳየቴ ነው በመቀጠል በአሰልጣኝ አለባቸው በሚሰለጥነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተስፋ ቡድን እንድሞክር ተላኩኝና ይሄ ተሳክቶልኝ ለክለቡ ልፈርም የቻልኩት፤ በጊዜው በአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለም ሃላፊነት ወደሚመራው የዋናው ቡድንም ለማደግ ከጫፍ ደርሼ በኋላ ላይ ሳይሳካልኝ ቀረ፡፡
ሊግ፡- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተስፋ ክለብን ከለቀቅክ በኋላስ ወደየት አመራህ?
ሚካኤል፡- ከባንኮች ጋር ከተለያየሁ በኋላ በቀጥታ ያመራሁት ወደ ወራቤ ከነማ ነው፤ እዛም ለአንድ ዓመት ተጫወትኩ፤ በመቀጠል ደግሞ ወደ ቡታጀራ ከነማ እና የደብረማርቆስ ከነማ ክለቦች ውስጥ ገባሁና የሀገር ውስጥ የጨዋታ ጊዜዬን በዚሁ አጠናቅቄ ወደ ባህሬን አመራሁ እዛም አሁን እየተጫወትኩ ነው፡፡
ሊግ፡- ወደ ባህሬን ከማምራትህ በፊት ኢትዮጵያ ውስጥ በነበረህ ቆይታ ወደ ሌሎች ክለቦች ለማምራት አልቻልክም፤ ለምን?
ሚካኤል፡- አዎን፤ ኢትዮጵያ ውስጥ በአሁን ሰዓት ኳስ ተጨዋች ለመሆን ብዙ መስዋዕትነትን ትከፍላለህ፤ የፈለገ ችሎታው ቢኖርህ ወደ ክለብ በቀላሉ ለመግባት ሁኔታዎች በጣም አስቸጋሪ የሆነበት ጊዜ ስላለም ነው ለምን አንድ ነገር ከወዲሁ አልወስንም ከሀገር ወጥቼስ ለምን አልጫወትም በሚለው ጉዳይ ላይ ከራሴ ጋር ከተነጋገርኩ በኋላ በባህሬን ቤተሰቦች ስላሉኝ ለእነሱም ሁኔታውን አሳወቅኳቸውና በመጀመሪያ ወደ እነርሱ ጋር አመራሁ፤ እዛም ከደረስኩ በኋላ ክለብ ገብቶ ለመጫወት በኤጀንት ስላልመጣው እና የእነሱ ሁሉም ነገር አሰራር ደግሞ ፕሮፌሽናል ስለሆነ ብዙ ነገሮች ለእኔ ከባድ ከሆኑብኝ በኋላ ነው በግሌ ከፍተኛ ጥረትን ካደረግኩኝ በኋላ ክለብ ውስጥ ገብቼ ልጫወት የቻልኩት፡፡
ሊግ፡- በባህሬን በየትኛው የሊግ ደረጃ ላይ ነው የምትጫወተው? የክለባችሁ ስም ምን ይባላል? ክለባችሁስ በምን ደረጃ ላይ ይገኛል? ስንት ክለቦችስ ናቸው የሚሳተፉት?
ሚካኤል፡- በአሁን ሰዓት በባህሬን የምጫወትበት የሊግ ደረጃ የላይኛው እና የመጀመሪያው ነው፤ የክለባችን ስምም ኢስትረፋ ይባላል፤ 10 ክለቦችም ናቸው በሊጉ ላይ ተሳታፊ የሆኑት፤ የእኛ ቡድንም የአሁን ሰአት ላይ አንደኛው ዙር ተጠናቆ በ5ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡
ሊግ፡- በባህሬን ሊግ ከመሪው ክለብ ጋር ያላችሁ የነጥብ ልዩነት ስንት ነው?
ሚካኤል፡- በባህሬን ሊግ ባለን የውድድር ተሳትፎአችን የአንደኛው ዙር ተጠናቆ ክለባችን ከመሪው ጋር ያለው የነጥብ ልዩነት የ3 ነው፤ መሪው ክለብ 28 አለው እኛ 25 አለን፤ ሌሎቹም በተቀራረበ ነጥብ ላይ ነው የሚገኙትና ጥሩ ፉክክር እየተደረገ ነው፡፡
ሊግ፡- በባህሬን የምትጫወተው ኢትዮጵያዊ ተጨዋች አንተ ብቻ ነህ?
ሚካኤል፡- ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያለው ተጨዋች በእኛ ክለብ ውስጥ ከሆነ አዎን እኔ ብቻ ነኝ፤ ነገር ግን በሌላ ዌስትረፋ በሚባል ቡድን ውስጥ እናትና አባቱ ኢትዮጵያዊ ሆነው በሳውዲ አረብያ ስለተወለደ ብቻ የእዛ ሃገር ዜግነት ያለው ዋሊድ የሚባል ተጨዋች አለ፡፡
ሊግ፡- የውጪ ሃገር ዜግነት ያላቸው ሌሎች ተጨዋቾችስ በክለባችሁ ውስጥ አሉ? በባህሬን ሊግ የውጪ ሀገር ዜግነት ያለው ተጨዋች ስንት ይፈቀዳል?
ሚካኤል፡- የባህሬን ሊግ ላይ አንድ ክለብ ሊያስፈርማቸው የሚችላቸው የውጪ ሀገር ስደተኛ ተጨዋቾች ቁጥር ብዛት ሶስት ብቻ ነው፤ በዚህ በኩል አሰራራቸው እንደ ኢትዮጵያ አይደለም፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሶስት በላይ ነው ተጨዋቾች የሚፈርሙት፤ ያ ስለሆነም በእኛ ክለብ ውስጥ የአሁን ሰዓት ላይ የሚገኙት የዉጪ ተጨዋቾች እኔ አንድ ሴኒጋላዊ ተጨዋች እና ሌላ ሶሪያዊ ተጨዋች ናቸው፡፡
ሊግ፡- በባህሬን የኢስትረፋ ክለብ ውስጥ ያለህ ተሳትፎ ምን ይመስላል? በቋሚ ተሰላፊነትስ ነው የምትጫወተው?
ሚካኤል፡- በባህሬን የፈረምኩበትን ክለብ ስቀላቀል መጀመሪያ ላይ ከቡድናችን ስፔናዊ አሰልጣኝ ጋር ከአጨዋወት ታክቲኩና የጨዋታ ፍልስፍናው ጋር በተያያዘ በፍጥነት ታክቲኩን ከመቀበል ጋር ያልተስማማንበት ሁኔታ ስለነበር መጀመሪያ አካባቢ የመጫወት እድሉ አልነበረኝም ነበር፤ እሱ አጫጭር ኳስን ይወዳል እኔም ደግሞ እወዳለሁ፤ ግን የእሱ የአጨዋወት ፍልስፍና ከበድ ይል ስለነበር ለመጫወት ቸግሮኝ ነበር የመጨረሻ ጨዋታዎች ላይ ግን ታክቲኩን እየተላመድኩና እየተቀበልኩት ስመጣ እያሳለፈኝና እያጫወተኝ ነው፡፡
ሊግ፡- ወደ ባህሬን ስትጓዝ ከሜዳ ውጪስ ለመጫወት የከበዱህ ነገሮች ነበሩ?
ሚካኤል፡- አዎን፤ መጀመሪያ አካባቢ ከባድ ሁኔታዎች ገጥሞኝ የነበረ ቢሆንም በፈጣሪ እርዳታ እና በራሴም ከፍተኛ ጥረት ነው ወደ ክለብ ገብቼ የመጫወት እድሉን ያሳካሁት፤ እዛ ክለብ ገብቶ ለመጫወት ስትመጣ መጀመሪያ ፓስፖርት ሊኖርህ ይገባል? ማንስ ነው ያመጣህ? እንዴትስ መጣህ ትባላለህ? እኔ በቀጥታ እንደሄድኩም ያለ ኤጀንት ስለሄድኩ ይሄ ሁኔታ አጋጥሞኝ የነበረ ቢሆንም በራሴ ጥረትና ድፍረት ነው ወደ ኢስትረፋ ክለብ በቀጥታ አምርቼ እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ፤ እዛም ክለብ እጫወት ነበር፤ ስለዚህም የሙከራ እድል ስጡኝ ብዬ በመናገሬ ነው እነሱ እድሉን ሰጥተውኝ ሙከራ ያደረግኩትና በሙከራውም የተሳካልኝ፤ በባህሬን ሊግ ሙከራ አድርገህ ክለብ ለመግባት አንተ በሀገሩ ከሚገኙ ተጨዋቾች የተሻለ እና የሚበልጥ ብቃትህን ማሳየት አለብህ፤ ያለበለዚያ ከእነሱ ተጨዋቾች እኩል የምትጫወት ከሆነ ለአገራቸው ዜጋ ነው ቅድሚያን የሚሰጡትና እኔም የተሻለ ነገርን ስላሳየውም ነው የተቀበሉኝ፤ ወደፊት ደግሞ ይሄንን ጥንካሬዬን በማስቀጠልም ወደ ሌሎች ሀገሮች የራሴ ወኪል እንዲኖረኝ በማድረግም ለመጫወት እፈልጋለው፡፡
ሊግ፡- የቤተሰቦችህ ናፍቆት አለብህ?
ሚካኤል፡- ቤተሰቦቼ ግማሽ የሚሆኑት እዛ ናቸው ያሉት፤ ከእነሱም ጋር የምገናኝበት እድሉ ስላለኝ ያን ያህል የብቸኝነት ስሜቱ አይሰማኝም፡፡
ሊግ፡- በባህሬን ሊግ ስትጫወት በካምፕ ነው የምትኖረው ወይንስ በቤት?
ሚካኤል፡- በካምፕ ነው የምንኖረው፡፡
ሊግ፡- የባህሬኑ ክለብ ለአንተ የሚከፍለው ወርሃዊ ደመወዝ ስንት ነው? ጥቅማ ጥቅሙስ?
ሚካኤል፡- ወደ ባህሬን መጀመሪያ ህጉን ጠብቄ ስላልመጣሁ ከወርሃዊ ደመወዝ ክፍያ ውጭ የማገኛቸው ሌሎች ጥቅሞች የሉም፡፡ ደመወዝ የሚሰጡኝ በራሳቸው ፍላጎት ነው ለወደፊት ግን ይጨመርልካል ብለውኛል፤ አሁን የማገኘውነው 300 ዲናር ወይንም /1ሺህ ዶላር/ ነው፡፡
ሊግ፡- በሀገር ውስጥ ማንን ተጨዋች ነበር የምታደንቀው?
ሚካኤል፡- ያሬድ ዝናቡን፤ እሱ የተለየ ተጨዋች ነበር፤ ለእኔ ተምሳሌቴም ነበር፡፡
ሊግ፡- በመጨረሻ..
ሚካኤል፡- የኳስ ህይወቴ ላይ እስካሁን በተጓዝኩበት መንገድ የረዱኝን ሁሉ ማመስገን እፈልጋለው፤ የመጀመሪያው ምስጋና ለፈጣሪ ይሁን ከዛ ለቤተሰቦቼ በተለይ ደግሞ ለእናቴ፤ ከእነሱ ውጪም ለአሰልጣኝ ጉልላት ፍርዴ እና ወርቁ ደልገባም ምስጋናን ማቅረብ እፈልጋለውኝ፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P