Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“የደርቢው አሸናፊ እኛ ነን፤ በዲ.ኤስ.ቲቪ ጨዋታው መተላለፉም ጥሩ ነገርን እንድናሳይ የሚያደርገን ነው”
ሀብታሙ ታደሰ /ኢትዮጵያ ቡና/

በመሸሻ_ወልዴ

ሊግ፦ ከፀጉር ቁርጥህ ልነሳ፤ የተቆረጥክበት ምክንያት አለ?

ሀብታሙ፦ አዎን፤ ፀጉሬን በፊት እንደምታውቀው በዚህ መልኩ አልነበረም። ያም ሆኖ ግን ለእኔ ብዙ ነገርን ያደረገልኝ የኢትዮጵያ ቡናው ደጋፊ ቴዲ ቡናማው ህይወቱ በማለፉ እሱ ትዝ እያለኝ ነው ፀጉሬን ለእሱ ማስታወሻነት እንዲውል በማድረግ ልቆረጥ የቻልኩት።

ሊግ፦ ቅ/ጊዮርጊስን በተጠባቂው የሸገር ደርቢ ጨዋታ ነገ ምሽት ትፋለማላችሁ፤ በዚህ ጨዋታ ዙሪያ ምን ትላለህ? ማንስ የጨዋታው አሸናፊ ይሆናል?

ሀብታሙ፦ የእሁዱ የሸገር ደርቢው ጨዋታ ለሀገሪቱ ትልቁ ግጥሚያ ቢሆንም እኔ ግን ከሌሎቹ ፍልሚያዎቻችን አንፃር እሱን ለይቼ በተለየ መልኩ አላየሁም። ይህን ጨዋታ ምንአልባት ለየት ሊያደርገው የሚችለው ሁለታችንም ያለ ደጋፊዎቻችን የምንጫወት መሆናችንና ደጋፊው በዲ.ኤስ.ቲቪ የሚያየው መሆኑ ነው። በዚህ ሁኔታ መጫወቱ ተፅህኖ ቢኖረውም ይህን ጨዋታ ለማሸነፍ ወደ ሜዳ እንገባለን።

ሊግ፦ ሸገር ደርቢውን ለማሸነፍ እንገባለን ነው ወይንስ በእርግጠኝነት እናሸንፋለን ነው?

ሀብታሙ፦ እርግጠኛ ሆነን እናሸንፋለን ነው እንጂ። ምክንያቱም በአሁን ሰዓት ላይ ቡድናችን በተነቃቃ መንፈስ ላይ ነው የሚገኘው። ከዛ ውጪም በቅርብ ርቀት የሚከተለንን ይኸውን ቡድን ከወዲሁ በነጥብ መራቅ ስለሚያስፈልገን እናሸንፈዋለን።

ሊግ፦ ሸገር ደርቢን ለስንት ጊዜ ተጫውተሃል? ስሜቱስ ምን ይመስላል? በነገ ግጥሚያስ ከአንተ ምን ይጠበቅ?

ሀብታሙ፦ እስካሁን ለሁለት ጊዜ ነው ይህን ጨዋታ ያደረግኩት። የመጀመሪያውን ዓምና ያደረግኩት ሲሆን ዘንድሮ ደግሞ ድል በቀናን የአንደኛ ዙር ጨዋታ ላይ ላከናውን ችያለሁ። የደርቢ ጨዋታ ላይ መጫወትን በተመለከተ ስሜቱ ደስ እንደሚል ተመልክቻለሁ፤ በተለይ ደግሞ ግጥሚያውን ካሸነፍክ ብዙ ሰውም በአንተ ይደሰታል። ለልጆችህም የምትነግራቸው ታሪክም ይኖርሃል። እኔም ነገ በሚኖረኝ ጨዋታ ከቡድን ጓደኞቼ ጋር ሆኜ ጥሩ በመንቀሳቀስ ክለቤን የጨዋታው አሸናፊ ለማድረግ በምችለው አቅም ጥሩ እንቀሳቀሳለሁ።

ሊግ፦ የኢትዮጵያ ቡናን ቤትኪንግ ተሳትፎን በምን መልኩ ትገልፀዋለህ?

ሀብታሙ፦ የውጤት ጉዞአችንን በሚመለከት በምንፈልገው ደረጃ ባይሄድልንም መጥፎ የሚባል አይደለም። እስካሁን ባደረግናቸው ጨዋታዎችም እኛን ነጥብ ያስጣሉን ቡድኖች በፉክክሩ ውስጥ ያሉትና በደረጃው ወገብ ያሉት እንደዚሁም ደግሞ ከዛም ዝቅ ያሉ አንዳንድ ቡድኖች ነበሩና ይሄ ከመሪው ክለብ ፋሲል ከነማ በነጥብ እንድንርቅ አድርጎናል።

ሊግ፦ ከፋሲል ከነማ በነጥብ የራቃችሁት እና እየተከተላችሁት ያላችሁት በ9 ነጥብ በማነስ ነው፤ ዋንጫ የማግኘት ተስፋ አላችሁ?

ሀብታሙ፦ ካሉት ቀሪ ጨዋታዎች አንፃር በእግር ኳስ ምን እንደሚፈጠር ማንም ስለማያውቅ አሁንም ለእኛ ጊዜው አልረፈደብንም። ሀገራችን ለአፍሪካ ዋንጫ ዘንድሮ ያለፈችበትን አስገራሚ ዕድልንም ስለምናስብ በቀሪዎቹ ግጥሚያዎቻችን ላይ ያሉትን ሁሉ በማሸነፍ እና የራሳችንን የቤት ስራ በመጨረስ የሚመጣውን ውጤት ልንቀበል ዝግጁ ነን።

ሊግ፦ ኢትዮጵያ ቡና ዋንጫ ካልተገኘ የሁለተኛነትን ደረጃ ይዞ ማጠናቀቅ የግድ ብሏል፤ የእውነት ነው?

ሀብታሙ፦ አዎን፤ ግን የእኛ ዋና ዓላማ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ዋንጫውን ማንሳት ነው። ለዛም ገና ውድድሩ ስላልተጠናቀቀ የምንችለውን ሁሉ እንሞክራለን። ያ የማይሳካልን ከሆነ ደግሞ ሌላው ትኩረት ያደረግንበትን እና ለአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ካፕ የሚያሳልፈንን ሁለተኛ ደረጃን ይዘን ማጠናቀቅም እንፈልጋለንና ለዛም ከዚህ ሰዓት ጀምሮ ከተከታዮቻችን በነጥብ መራቅ እንዳለብን ልንረዳ ችለናል።

ሊግ፦ ከሜዳ ከጉዳት ርቀህ ነው ወደ ጨዋታ የተመለስከው፤ አሁን በምን ሁኔታ ላይ ነው የምትገኘው?

ሀብታሙ፦ ባህርዳር ላይ በነበረው የጨዋታ ተሳትፎአችን በጉዳት ከሜዳ ርቄ ስለነበር ቡድኔን መጥቀም እየፈለግኩ አልተጫወትኩለትም። የደረሰብኝ ጉዳትም ከድካም አንፃርና ከምጫወትበት ቦታም አኳያ በፊትነስ እና በሳይኮሎጂ ስለጎዳኝ ቶሎ ወደ ሜዳ እንዳልመለስ ቢያደርገኝም ካለፈው ድል ካደረግንበትና እኔ ተቀይሬ ከገባሁበት ጨዋታ ጀምሮ ግን አርፌ እንደመምጣቴ አሁን ላይ በግል ሌሎቹ ተጨዋቾች በሚገኙበት የፊትነስ እና የኢንዱራንስ ደረጃ ለመስተካከል እየሰራሁ በመሆኑ ቡድኔን በምፈልገው መልኩ ማገልገሌ አይቀርም።

ሊግ፦ በጉዳት ከሜዳ መራቅን አስመልክቶ ስሜቱ ምን ይመስላል?

ሀብታሙ፦ ስሜቱ በጣም ደባሪ ነው። ጉዳት አህምሮን ይነካልና ያን ጊዜ የስፖርተኛውን ስሜት ልትጠብቅለት ይገባል። ለቡድንህ በዛን ወቅት ሳትጫወትለት ስትቀር እንኳን ደጋፊው ይህን በአግባቡ ተረድቶ ከጎንህ ሊቆምና ሊረዳህም ይገባል። አንድ ስፖርተኛን ጉዳት ሊያበሳጨው የሚችለው ነገር ለክለቡ ሊሰጥ ያሰበውን ስኬታማ ግልጋሎት ሳይጫወት በሚቀርበት ሰዓት ሲያሳጣው ሲቀር ነው። ያኔም ይቆጨዋል። በኳስ መድረስ ባለበት ደረጃ ላይም ሳይገኝ ሲቀር ይከፋዋል። ተጎድቶ ወደ ሜዳ በሚመለስ ሰዓትም ስራውን ከዜሮ የሚጀምርበት ሁኔታም ስላለና ልፋት ውስጥም ስለሚገባ ተጨዋቹም የራሱን አህምሮ በደንብ አድርጎ ሊጠብቅና ራሱንሞ በደንብ ሊያዘጋጅም ነው የሚገባው።

ሊግ፦ ዋልያዎቹ ለአፍሪካ ዋንጫ አለፉ፤ የተሰማህ ስሜት ምን ይመስላል?

ሀብታሙ፦ እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ እና እንደ እግር ኳስ ተጨዋችነቴ በውስጤ የተሰማኝ ስሜት በጣም ከፍ ያለ ነው። ዋልያዎቹ ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፋቸው ሁሉንም ህዝብ እና እኛ ተጨዋቾችን አነሳስቷል። ከስር የሚመጡ ታዳጊ ተጨዋቾችንም ሞራል ከመገንባት ባሻገር ኳስ የመጫወት ፍላጎታቸውን ይጨምራል። ለእነዚህ ተጨዋቾችም ወደ ውጪ ወጥተው እንዲጫወቱም ብዙ እድልን ይፈጥራል። ከዛ ውጪም ከኳሱ ርቀው የነበሩ ሰዎችም ወደ ፉትቦሉ እንዲመለሱም ያደርጋል። ይህ ሁሉ እንዳለ ሆኖ እኛ ተጨዋቾችም ለአፍሪካ ዋንጫው ላለፈው ቡድን አባል ለመሆንና አንድ ታሪክንም ለሀገር ለመስራት ከፍተኛ ጥረትንም የምናደርግበትም ስለሆነ የዋልያዎቹ ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፍ እንደ ግልም እንደ ቡድንም በጣም ነው ደስ ያለኝ።

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P