Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine


“የፋሲል ከነማ በነጥብ መራቅ አያስፈራም አይባልም፤ ጠንክረን ሰርተን እነሱ ላይ ለመድረስ ነው መጣር ያለብን”አብዱልከሪም ወርቁ /ወልቂጤ ከተማ/


በቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊጉ በሜዳ ላይ ባሳየው የጨዋታ እንቅስቃሴ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለመመረጥ የቻለው የወልቂጤ ከተማው የአማካይ ስፍራ ተጨዋች አብዱልከሪም ወርቁ ቡድናቸው ዘንድሮ እያከናወነ ባለው የውድድር ተሳትፎው ሊጉን ከ1-4ኛ ባለው ደረጃ ውስጥ ሆኖ እንደሚያጠናቅቅ የሊግ ስፖርት ጋዜጣ አዘጋጅ ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ ላቀረበለት ጥያቄ ምላሽን ሰጥቷል፡፡
ለወልቂጤ ከተማ በመሀል ሜዳው እንቅስቃሴ የተዋጣለትን ብቃት እያሳየ ያለውና ብዙዎችም አድናቆታቸውን እየቸሩት ያሉት ይኸውን ወጣት ተጨዋች በሌሎች ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮችም ጭምር አናግረነው የሰጠንን ምላሽ በሚከተለው መልኩ አቅርበነዋል፡፡


ሊግ፡- በቤት ኪንግ የፕሪምየር ሊጉ ተሳትፎአችሁ ለእናንተ ምርጡ የነበረው አዲስ አበባ? ወይንስ ጅማ?


አብዱልከሪም፡- በአዲስ አበባ የጨዋታ ቆይታችን ከሞላ ጎደል በውጤት ደረጃ ምንም እንኳን ለቡድናችን ማድረግ በምንፈልገው መልኩ ብዙ ነገርን ልናደርግ ባንችልም፤ ምርጥ የሚባልንም ውጤት ለማስመዝገብ ባንችልም በእንቅስቃሴ ደረጃ ግን እኛ ጥሩ ነበርን፤ ወደ ጅማ ስናመራ ደግሞ በጨዋታችን ላይ አዲስ አበባ ከነበረን አንፃር በመጠኑም ቢሆን ተቀዛቅዘናል፤ በውጤት ደረጃም ነጥባችንን ወደ መሪዎቹ ከፍ ሳናደርግ ቀርተናል፡፡


ሊግ፡- በቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ምርጥ ቡድን ነው ያላችሁ?
አብዱልከሪም፡- አዎን፤ እያስመዘገብን ያለነው ውጤት ግን እኛን አይገልፀንም፤ ያም ሆነ ይህ ግን ጥሩ ቡድን አለን ብዬ ነው የማምነው፤ በቀጣይ ጊዜ ጨዋታዎቻችን ላይ ደግሞ ባሉብን ክፍተቶች ላይ የበለጠ በመስራት እና በደንብም በመዋሀድ በሂደት አቋማችንን እናስተካክላለን፤ ከአሁን የበለጠ ቡድንም እንሰራለን ብዬ አስባለው፡፡


ሊግ፡- እንደ ቡድን ያላችሁ ጥንካሬና ክፍተት ጎን ምንድን ነው?
አብዱልከሪም፡- የእኛ ጠንካራ ጎን ኳስን በግል ሳይሆን እንደ ቡድን ለመጫወት መቻላችን ሲሆን በክፍተት ደረጃ ላነሳ የምፈልገው ደግሞ በዋናነት ወደ ተቃራኒ ቡድን ይግብ ክልል እንደርስና ጎሎችን የማስቆጠር ችግር አለብን፡፡


ሊግ፡- በቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊግ የሻምፒዮናው ውድድር ወልቂጤ ከተማ በዓመቱ መጨረሻ በየቱ ስፍራ ላይ ይገኛል?
አብዱልከሪም፡- ከ1-4ኛ ባለው ደረጃ ላይ ሆነን ሊጉን እናጠናቅቃለን እያልን ነው፤ ይሄን ለማሳካትም እስከ መጨረሻው ሰዓት ድረስ ጠንክረን እንፋለማለን፡፡


ሊግ፡- የቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊጉ መሪ ፋሲል ከነማ ተከታዮቹን ቡድኖች በ5 ነጥብ እና ከዛ በላይ ርቋቸው ሄዷል፤ ይሄ አያስፈራችሁም?
ፍፁም፡- እንዴት አያስፈራንም? ያስፈራል እንጂ፤ አንድ ቡድን በነጥብ እየራቀህ ሲሄድ ለራስህ የምትሰጠው ግምት እያነሰ ነው የሚሄደው፤ ከአንተ የሚጠበቀው ግን እነሱ ላይ ለመድረስ መጣር እና ጠንካራ ከሆንክ ደግሞ አይደለም እነሱ ላይ መድረስ ምንም ነገርን ማድረግም እንደምትችል ነው በዋናነት ልታውቅ የሚገባው፡፡


ሊግ፡- ወልቂጤ ከተማ ካደረጋቸው የቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ምርጡ ጨዋታ ለአንተ የቱ ነው?
አብዱልከሪም፡- ምርጡ ጨዋታችን ባህርዳር ከተማን ያሸነፍንበት ነው፤ ይሄን ያልኩት ሁለታችንም ጥሩ ጨዋታ ስላደረግንና በተለይም ደግሞ እኛ ጠንካራነታችንን ስላሳየንበትም ስለሆነ ነውና በጨዋታው ልደሰትበትም ጭምር ችያለው፡፡


ሊግ፡- የተከፋህበት ጨዋታስ አለ?
አብዱልከሪም፡- በጣም እንጂ በሲዳማ ቡና የተሸነፍንበት ያ ጨዋታ ያስቆጨኛል፡፡


ሊግ፡- ወልቂጤ ከተማ ባህርዳር ላይ የተለየ ሆኖ ይቀርባል?
አብዱልከሪም፡- አትጠራጠር በአጨዋወትም፤ በውጤትም ከአዲስ አበባም ሆነ ከጅማ ከተማ በተሻለ መልኩ ምርጥ የሆነን ቡድን ነው ይዘን የምንቀርበው፤ እዛ በምናደርገው ጨዋታ ውጤታችንንም በጣም ከፍ እናደርገዋለን፡፡
ሊግ፡- በቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ወልቂጤ ከተማ በሚያደርጋቸው ጨዋታዎች ጥሩ በመጫወት ጎልተህ እየወጣህ ነው፤ በያዝከው አጨዋወትህም እስከ ብሔራዊ ቡድን ደረጃም ልትመረጥ ችለሃል፤ በእዚህ ዙሪያ ምን ትላለህ?
አብዱልከሪም፡- የእውነት ነው፤ ግን አንድ እንድታውቁልኝ የምፈልገው ነገር ቢኖር ለእዚህ ለምወደው ክለቤ ጥሩ ልጫወት እና እስከ ብሔራዊ ቡድን ደረጃም ለመመረጥ የቻልኩበት ዋናው ምክንያት በራሴ ጥረት ብቻ እንዳልሆነ ነው፤ እኔ ጥሩ የሆንኩት የወልቂጤ ከተማ ሁሉም ተጨዋቾች ጥሩ ስለሆኑ ነውና ለእገዛቸው በጣም ላመሰግናቸው እፈልጋለው፡፡
ሊግ፡- ቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊጉን ጨዋታዎችን ከተከታተልክ ለአንተ የትኛው ተጨዋች ምርጡ ነው?
አብዱልከሪም፡- ጨዋታዎቹን ስለምከታተል ብዙ ምርጥ ተጨዋቾችን አይቻለው፤ ማንን ጠርተህ ማንን ትተዋለህ፡፡
ሊግ፡- ለብሔራዊ ቡድን መመረጥ ስሜቱ የቱን ያህል ነው?
አብዱልከሪም፡- ከዚህ በፊት እድሜያቸው ከ23 ዓመት በታች በሆነው ቡድን ውስጥ ተመርጬ ነበር ደስታውን ያየሁት ያኔ ነው፤ አሁን ደግሞ ከፍ ወዳለው ቡድን ስትመረጥ እንደ ሀገር የሚሆን ምንም ነገር የለም እና በአንተ ላይ ደስታው የበለጠ ነው የሚጨምረው፡፡
ሊግ፡- አሰልጣኛችሁን በተመለከተ ምን ትላለህ?
አብዱልከሪም፡- ወጣት ነው፤ ሁሌም አዲስ ነገርን ለማወቅ እና ለመማር በጣም ይጥራል፤ በእኛ ባለን ችሎታ ላይም ተጨማሪ ብቃት እንዲኖረንም የተለየ ልምምድንም ይሰጠናልና ጥሩ አሰልጣኝ እንዳለን ነው የማምነው፡፡
ሊግ፡- ቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊጋችንን እንዴት ተመለከትከው?
አብዱልከሪም፡- የሀገራችን ተጨዋቾች በችሎታቸው እንዳላቸው አቅም ሊጉ ጥራት አለው ብዬ አላስብም፤ ገና ይቀረናል፤ በደምብ ከሰራንበት ግን በጣም መጓዝ እና የተሻለ ደረጃ ላይ መድረስ ይቻላል፡፡
ሊግ፡- ሊጋችን በዲ.ኤስ.ቲቪ በመታየቱ ዙሪያስ ምን አልክ?
አብዱልከሪም፡- መተላለፉ ጥሩ ነው፤ ለውጥም ልናመጣበት እንችላለን፤ በተለይ ደግሞ ተጨዋቾቻችን ያላቸውን ችሎታ አውጥተው ለመጫወት በመጣር በኩል የተሻሻሉ ነገሮችን አይቼበታለው፡፡
ሊግ፡- በሜዳ ላይ ያለህ የግል ክህሎት ከተፈጥሮ ወይንስ ከስራ እና ከስልጠና የመጣ ነው?
አብዱልከሪም፡- አብዛኛው በተፈጥሮ ይዤው የመጣሁት ነው፤ ከዛ በሚሰጠኝ ስልጠና ጠንክሬ ሰርቼ ላዳብረው ቻልኩ፤ ስለዚህ የሁለቱም እጅ አለበት፡፡


ሊግ፡- በምርጥ አቋምህ ላይ ነው የምትገኘው?
አብዱልከሪም፡- እኔ አላልኩም፤ ገና የኳስ ጀማሪ ነኝ፤ ብዙም ነገር ይቀረኛል፡፡


ሊግ፡- በኳሱ የደረስክበት ደረጃስ ፈጥኗል?
አብዱልከሪም፡- አዎን፤ ምክንያቱም በአጭር ጊዜ ውስጥ ነው፤ ለልደታው ኒያላ ታዳጊ ቡድን፤ ከዛ ቀጥዬ ደግሞ ለመድን ወጣት እና በቢጫ ቲሴራ ደግሞ ለዋናው እና ባለፉት ጥቂት ዓመታት ደግሞ ገና ለወልቂጤ ከተማ እየተጫወትኩ ባለሁበት ሰዓት ላይ ነው እዚህ ደረጃ ላይ ማለትም እስከ ብሔራዊ ቡድን ደረጃ መመረጥ የደረስኩትና በኳሱ ከቆየሁበት አጭር ጊዜ አኳያ እድገቴ ፈጣን ነው፡፡


ሊግ፡- በቤት ውስጥ ስንት ወንድም እና እህት አለ? ባህሪይስ እንዴት ይገለፃል?
አብዱልከሪም፡- በባህሪዬ ብዙ ማውራት አልችልም፤ ዐይናፋር ነኝ፤ ሁለት ወንድም እና ሁለት እህቶችም አሉኝ፡፡
ሊግ፡- ከኳሱ ውጪ ጊዜህን የምታሳልፈው?
አብዱልከሪም፡ የቲቪ ጌም በመጫወት፡፡


ሊግ፡- በቤተሰብህ እግር ኳስን አትጫወት ተብለህ ነው ያደግከው?
አብዱልከሪም፡- አይደለም፤ ምንም አይነት ተፅህኖ አልነበረብኝም፤ ከዛ ይልቅ ቤተሰቦቼ በብዙ ነገሮች እያገዙኝ ስለመጡ ነው ኳስን በመጫወት ያደግኩት፤ በጣምም አበረታቱኝ ለዚህ ደረጃም ደረስኩኝ፡፡


ሊግ፡- ከባህር ማዶ የየቱ ክለብ እና ተጨዋች አድናቂ ነኝ አልክሳ?
አብዱልከሪም፡- ከተጨዋች ሊዮኔል ሜሲን ነው የማደንቀው፤ የማንቸስተር ዩናይትድ ደግሞ ደጋፊ ነኝ፡፡


ሊግ፡- እናጠቃል?
አብዱልከሪም፡- በእግር ኳስ ተጨዋችነት ህይወቴ እስከ አውሮፓ ድረስ ሄዶ ስለመጫወት ነው የማስበው፤ ለዛ ትልቅ እልም አለኝ፤ ይሄን ካልኩ ወደ ምስጋና ልሂድ በመጀመሪያ የፈጠረኝን አምላክ አላምዱሊላሂ ብዬ አመሰግናለው፤ ከዛ ቤተሰቦቼን፤ በመቀጠል ደግሞ ከፕሮጀክት ጀምሮ በተለያየ ወቅት አሁንም ድረስ እያሰለጠኑኝ ያሉትን አለምዬ መኩሪያን፣ ደረጄ በላይን፣ ደግአረገ ይግዛውን፣ ሌሎች ስማችሁን ያልጠቀስኩትንና የወልቂጤ ከተማ ክለብ ዋና ቁልፍ ሰው የሆኑትን አቶ አበባውን እና የሰፈሬ የ5ኛ ፖሊስ ጣቢያ አካባቢ ጓደኞቼን ከልብ ማመስገን እፈልጋለው፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P