Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ የምናነሳበት ጊዜ ሩቅ አይደለም”አቡበከር ናስር /ኢትዮጵያ ቡና/

የኢትዮጵያ ቡናና የዋልያዎቹ የአጥቂ ስፍራ ተጨዋች አቡበከር ናስር በዘንድሮ የውድድር ዘመን ከመቼውም ጊዜ በተሻለ አቋሙ በመቅረብ ክለቡንም ሆነ ብሔራዊ ቡድናችንን ለመጥቀም
መዘጋጀቱን እየተናገረ ይገኛል፡፡
ኢትዮጵያ ቡናዎች በቅርቡ ውሉን በማራዘም ለአምስት ዓመታት በክለቡ እንዲቆይ ያደረጉት ይኸው ወጣት ተጨዋች በሜዳ ላይ በሚያሳየው ማራኪ የሆነ የጨዋታ እንቅስቃሴው የብዙዎቹን
የስፖርት አፍቃሪዎችና የቡድኑን ደጋፊዎች ቀልብ በመሳብ ከፍተኛ አድናቆትን ያገኘ ሲሆን ይኸው ተጨዋች ከእዚህ በኋላ በሚኖረው የኳስ ህይወቱም ከክለቡ ጋር የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ
የሚያነሱበት ጊዜ ሩቅ እንደማይሆንና ሀገራችንም ለአፍሪካ ዋንጫ የምታልፍበት ትክክለኛው ወቅት አሁን ነው ሲልም ከሊግ ስፖርት ጋዜጣ ለቀረበለት ጥያቄ ምላሹን ሰጥቷል፤ ሊግ ስፖርት
ለአቡበከር ከእሱ ጋር ተያያዥነት ባላቸው ሌሎች ጥያቄዎች ዙሪያም ቆይታን ያደረገች ሲሆን አጠቃላይ ምልልሱም በሚከተለው መልኩ ቀርቧል፡፡
ኢትዮጵያ ቡና ለቀጣዮቹ አምስት ዓመታት አንተን የቡድኑ ንብረት አደርጎሃል፤ ቡድኑና አንተ እንዴት ከእዚህ ውሳኔ ላይ ልደርሱ እንደቻላችሁ፡- “ክለባችን ለእዚህን ያህል ዓመታት እኔን
ሊያስፈርም የቻለው ከራሱ እና ከአሰልጣኙ ካሳዬ አራጌ እቅድ ተነስቶ ነው፤ በክለቡ ውስጥ ለረጅም ጊዜ ለመጫወት እንድችልም ይህን ጥያቄ ቡድኑ ሲያቀርብልኝም በደስታ ነው ልቀበለው
የቻልኩት፤ ኢትዮጵያ ቡና በጣም የምወደው ክለቤ ነው፤ በእዚሁ ክለብ ውስጥ የኳስ ጨዋታ ጊዜዬንም ማጠናቀቅ እፈልጋለው፤ በተለይ ደግሞ በቅርቡ እንደተዘከረው የክለቡ የቀድሞ
ተጨዋች አሸናፊ በጋሻውም ለረጅም ዓመታትም በመጫወት የእሱን ታሪክ መጋራትና እንደዚሁም ደግሞ ብዙ የስኬታማነትንም ውጤቶች በእዚህ ክለብ ውስጥ ማስፃፍንም ስለምፈልግ ነው
ለቡድኑ ፊርማዬን ያኖርኩት”፡፡


ለኢትዮጵያ ቡና በዘንድሮው የውድድር ዘመን ተሳትፎ ምን ሊሰራለት እንደተዘጋጀ፡- “ኢትዮጵያ ቡና የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ የሚያነሳበት ጊዜ ጊዜ ሩቅ አይደለም፤ ከእዚህ መነሻነትም ነው
ከዘንድሮ የውድድር ዘመን አንስቶ ይሄንን እልማችንን ልናሳካለት የተዘጋጀነው፤ በእዚህ ቡድን ቆይታዬም ከእዚህ በፊት ብዙ ጨዋታዎች በጉዳት የተነሳ አልፈውኝ ነበር፤ ሙሉ ጨዋታዎችንም
እየተጫወትኩ በክለቡ ውስጥ አልቆየውም፤ አሁን ላይ ግን ራሴን በብቁ ሁኔታ እያዘጋጀው የምገኝበት ወቅት ላይ ስለሆንኩ ቡናን ለዋንጫ ባለቤትነት እስከማብቃት ነው ጥቅምን የምሰጠው፤
ለዛም የውድድሩን መጀመር ብቻም እየተጠባበቅኩኝ ነው የምገኘው”፡፡
ኢትዮጵያ ቡና ከአንተ ውጪ የሚኪያስ መኮንንን፣ የአማኑኤል ዩሃንስን እና የወንድሜነህ ደረጄን ውል በማደስ ለመጪዎቹ 5 ዓመታት የክለቡ ንብረት አድርጓቸዋል፤ በእዚህ ዙሪያ ስለምትለው
ነገር፡- “ኢትዮጵያ ቡና ውል የነበረባቸውንና እንደዚሁም ደግሞ በክረምቱ ወራት ክለቡን ለቅቆ የነበረውን ተጨዋች ዳግም በመመለስ በቀጣይ ለሚገነባው ቡድን እነዚህን ተጨዋቾች ለአራት
እና ለአምስት ዓመታት እንዲቆዩ በማድረግ ያስፈረመበት ሁኔታ ከእነዚህ አንድአንድ ተጨዋቾች ጋር ተላምደን ከመጫወት ባሻገር በሚገባም ልንግባባ የቻልንበት ሁኔታ ስላለ በጣም ደስ ይላል፤
አንድ ቡድን ሊገነባ የሚገባው እንደ ቤተሰብ ነው፤ ወደ ውጪዎቹ ስናመራ ተጨዋቾቻቸው ለአምስት ዓመታት እና ከዛ በላይም ለሆነ ዓመታት ቡድኑ ውስጥ ይቆያሉ፤ እኛም ጋር ውጤት
ለማምጣት ከዚህ በኋላ መሆን ያለበት ለቡድኑ ሊጠቅሙ የሚችሉ ተጨዋቾችን ለእዚያን ያህል ጊዜ ማቆየት መቻል ነውና ቡና የሰራው ስራ ሊደነቅ እና ሊበረታታ የሚገባው ነው”፡፡
ኢትዮጵያ ቡናን ዘንድሮ ያለ ደጋፊው ሲጫወት ማየትና በእዚህ ዓመት ያለ እነሱ ድጋፍ ሊያመጡት ስላሰቡት ውጤት፡- “ኢትዮጵያ ቡናን ብቻ ሳይሆን ሌሎችንም በርካታ ደጋፊዎች ያላቸውን
ክለቦች በእዚህ ዓመት ላይ ያለ ደጋፊዎቻቸው ሲጫወቱ ማየት መቻል በእግር ኳሱ ላይ የሚፈጥረው ጉዳት ከፍ ያለ እንደሆነ ሁላችንም እናውቃለን፤ ያም ሆኖ ግን ኮቪድ አስከፊ ወረርሽኝ
ለመሆን በመቻሉ ያለ ደጋፊ መጫወት ግዴታ ሆኗል፤ ስለዚህም ሁላችንም ያለ ደጋፊ መጫወት መቻልን ከወዲሁ መላመድ ይገባናል፤ የእኛ ክለብን በተመለከተ አሁን ላይ ያለ ደጋፊ መጫወት
መቻልን ሊላመድ ይገባዋል፤ በእዚህ መልኩ ተጉዘንም ነው የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ ለማንሳት መጣር እና መንደርደርም የሚኖርብን፤ ቡና ደግሞ የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ የሚያነሳበት ጊዜ
ብዙ ሩቅ አይሆንምና ይሄን ድል ማሳካታችን የማይቀር ነው”፡፡
ያለ ደጋፊዎቻችሁ በምትጫወቱበት የዘንድሮ የውድድር ዘመን ጎል ስታስቆጥር ደስታህን በምን መልኩ እንደምትገልፅ፡- “እሱን ጊዜው ደርሶ አብረን ብናየው ይሻላል”፡፡
ለኢትዮጵያ ቡና ስትጫወት በቀይ ካርድ ከሜዳ የወጣህበት ጊዜ አለ፤ ያን ጊዜ ምን ብለህ እንደሆነ፡- “ከባህር ዳር ከተማ ክለብ ጋር ስንጫወት ነበር አለአግባብ በሆነ ሁኔታ በቀይ ካርድ
ከሜዳ የወጣሁት፤ በዛ ጨዋታ መጀመሪያ ፋውል የተሰራብኝ እኔ ላይ ነበር፤ ተንበርክኬ በነበርኩበት እና ግጥሚያው እንዲቀጥልም በተደረገበት ሰዓት ላይም ምንም አይነት አክሽን በእሱ ላይ
ሳልወስድ ብድግ እንደማለት ስል መልሼ ስመታም ነው ሁለታችንም ከሜዳ እንድንወጣ የተደረግነው፤ ዳኛው በእዛን ሰዓት ከአጠገባችን አልነበረም፤ ተሰዳድበን ቢሆን እንኳን ሩቅ ከመሆኑ
አንፃር ሊሰማንም አይችልም ነበር፤ ያን ጨዋታ በጊዜው ከሜዳ በቀይ ካርድ መውጣት አልነበረብኝም ነው የምለው”፡፡
ለኢትዮጵያ ቡና ስትጫወት ስሜታዊ የመሆን ነገር ይታይብሃል፤ ይሄ ጎድቶህ ወይንም ደግሞ ጠቅሞህ እንደሆነ፡- “የእግር ኳስን ሜዳ ገብተህ ስትጫወት ስሜታዊ መሆን መቻል የሚያጋጥምና
ያለም ነገር ነው፤ ስሜታዊ ለመሆን መቻልም የሚጎዳህም የሚጠቅምህም ወቅት አለና ይሄን በሁለት መልኩ ነው የምመለከተው፤ የመጀመሪያው አንዱ በጣም ስሜታዊ በምትሆንበት ሰዓት
በትንሽ ነገር ተበሳጭተህ ከዳኛ ጋር ወይንም ደግሞ ከተቃራኒ ቡድን ተጨዋች ጋር ሳትግባባ በመቅረት አላስፈላጊ ጥፋትን በመፈፀም ከሜዳ በቀይ ካርድ ልትወጣ የምትችልበት አጋጣሚ
ይኖራልና ያ መሆን መቻሉ አንተንም ቡድንህንም ሊጎዳ ይችላልና ለእዚህ ደግሞ ረጋ እና ሰከን ማለት ያስፈልግሃል፤ በጥቅም ደረጃ የምጠቅሰው ሌላው የስሜታዊነት ባህሪይ ደግሞ አንድአንዴ
ግጥሚያዎችን ለማሸነፍ ስትል የምታሳየው ከፍተኛ የመነሳሳት ባህሪይም አለና እሱንም ልጠቅስ እፈልጋለሁ፤ ያለበለዚያ በእዛ መልኩ ካልተጫወትኩ ሜዳ ላይ ኃላፊነቴን የተወጣውም
አይመስለኝም”፡፡
በኢትዮጵያ ቡና ክለብ ውስጥ አሁን ላይ የምታጠልቀው የማሊያ ቁጥር አንተ ፈልገኸው እና ጠይቀህ የተሰጠ ነው ወይንስ እነሱ ልበስ ብለው የሰጡህ፡- “የ10 ቁጥር ማሊያውን ለመልበስ
የመጀመሪያው ጠያቂ እኔ ነበርኩ፤ ይሄን ቁጥር ለብሼም የመጫወት ፍላጎቴም ከፍተኛ ስለነበር መጀመሪያ ላይ እምቢ ተብዬም ነበር፤ በኋላ ላይ ግን ክለቡ ውስጥ ባሉት ተጨዋቾች እና
አንድአንድ ሰዎች አማካኝነት ይሄ ቁጥር እንዲሰጠኝ ግፊት ስለተደረገ ይኸው እስካሁን ማሊያውን እየተጫወትኩበት እገኛለው”፡፡
ከኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች ውስጥ ከአጠገብህ በመሆን የተለየ ምክርና መበረታታት የሚሰጥህ፡- “ብዙዎቹ የክለቡ ደጋፊዎች ከጎኔ ናቸው፤ በተለይ ደግሞ አብዱራህማን መሐመድ /አቡሸት/
ከደጋፊነቱ እና ከብዙ ተጨዋቾችም ጋር ከመግባባቱ ባሻገር በኳሱ ውስጥም ተጫውቶ አሳልፏልና ሁሌም ከአጠገቤ በመሆንና እያንዳንዱንም የጨዋታ እንቅስቃሴዎቼንም በመከታተል
ማድረግ ያለብኝን ነገር ሁሉ ይነግረኛልና ለእሱም ሆነ ለሌሎቹ ደጋፊዎች ታላቅ ምስጋናን አቀርባለውኝ”፡፡
ከኢትዮጵያ ቡና የደጋፊዎች መዝሙር ውስጥ ለአንተ ምርጡ፡- “ብዙ መዝሙሮች ያሉ ቢሆንም ለእኔ ግን በተለየ መልኩ ስሜት የሚሰጠኝ እና ወደሜዳም ገብቼ ስጫወት በጣም
የሚያነቃቃኝ “ሳዜም ነው ያደግኩት” የሚለውና “ታሸንፋላችሁ” የሚለውን መዝሙር ሲዘምሩት ነው”፡፡
ለኢትዮጵያ ቡና ስትጫወት ጎል ካስቆጠርክ በኋላ ለመጨፈር ያልሄድክበት የመመልከቻ ቦታ፡- “እስካሁን ድረስ ወደ ካታንጋ እና ከማን አንሼ ሄጄ አልጨፈርኩም፤ ወደ ጥላፎቅም ቢሆን
ለአንዴ ማልያ ለማሳየት ካልሆነ በስተቀር በተደጋጋሚ ጊዜ ወደዛ ሄጄ አልጨፈርኩም፤ ብዙ ጊዜም ጎል ሳገባ ሄጄ የምጨፍረው ወደ ዳፍ ትራክ እና ሚስማር ተራም ነው”፡፡
ለኢትዮጵያ ቡና ጎል ካስቆጠርክ በኋላ ለመጨፈር ሄደህ በድባቡ ሁኔታ የተገረምክበት የመመልከቻ ቦታ፡- “ብዙ ጊዜ በዳፍ ትራክ ያለው የድባብ ሁኔታ በጣም የሚያስገርመኝ እና በጣምም
ደስ የሚለኝ ነው፤ ከዛ ውጪም ጎል አስቆጥሬ ወደዛ ሳመራም የደጋፊዎቻችን የአጨፋፈር ሁኔታም ስሜታቸውን መቆጣጠር እስኪያቅታቸው ድረስ በመሆኑም አንድአንዴ የሚያስፈራ ነገርንም
ትመለከታለህ”፡፡
የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች አንተን በማድነቅ እስከዛሬ ከሰጡህ ስጦታዎች ውስጥ ምርጡና የተለየ የምትለው፡- “የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች ለእኔ ችሎታ አድናቆትን በመስጠት ሁሌም ቢሆን
ከጎኔ እንደሆኑ በሚገባ አውቃለው፤ ጎል ሳስቆጥር ብቻ ሳይሆን ስስትም ለቀጣይ ጊዜ ራሴን አሻሽዬ እንድመጣ የሚያበረታቱኝም ናቸውና በክለቡ የተጨዋችነት ታሪክ እስካሁን ለእኔ ከሰጡኝ
የአድናቆት ሽልማቶች መካከል ምርጡ የምለው በማህበራዊ ድረ-ገፅ ከቡና ሰማይ ስር ብለው የሚፅፉት የቡድናችን ደጋፊዎች በ2010 ላይ ለእኔ፣ ሚኪ እና እያሱ ታምሩ እንደዚሁም ደግሞ
በ2011 ላይ ደግሞ የክለቡ ምርጥ ተጨዋች ብለው የሰጡኝን ነውና ያ ለቀጣይ ጊዜ የኳስ ህይወቴ ጠንክሬ እንድሰራ ያደረገኝ ነው”፡፡
የኢትዮጵያ ቡና ተጨዋች ሆነህ በሜዳ ላይ ከተፋለሙህ /ከገጠሙህ/ የተቃራኒ ቡድን ተጨዋቾች ውስጥ በጣም የምታደንቀው ተጨዋች እና አንተን ማርክ በማድረግ ደግሞ ሙጫ የሆነብህ
ተጨዋች፡- “ለኢትዮጵያ ቡና ስጫወት ከአንድ ጨዋታ ውጪ ብዙ ጊዜ ማርክ ተደርጌ አላውቅም፤ አንዴም ቢሆን ማርክ የተደረግኩት ከእነሱ ጋር ስንጫወት ሳለአምላክ እየተከታተለ
አላጫወት ያለኝ ጊዜ ነውና ያን ነው ልጠቅስ የምችለው፤ ከዛ ውጪ ግን በኳስ ህይወቴ እስካሁን ከገጠሙኝ የተቃራኒ ቡድን ተጨዋቾች ውስጥ ለእኔ ምርጡ የምለው እና የማደንቀው
ተጨዋች የቅ/ጊዮርጊሱንና የብሔራዊ ቡድናችንን የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች አስቻለው ታመነን ነው፤ የእሱ አጨዋወት በጣምም ደስ ይለኛል”፡፡
በእግር ኳስ ተጨዋችነቱ የምንጊዜም ምርጡ ጨዋታው፡- “በብሔራዊ ቡድን ደረጃ ከሆነ ምርጡ ጨዋታዬ የምለው በአፍሪካ ዋንጫ የታዳጊዎች ማጣሪያ ጨዋታ ላይ ለኢትዮጵያ ታዳጊ
ብሔራዊ ቡድን /u-17/ ከግብፅ አቻችን ጋር ድሬዳዋ ላይ ስንጫወት 2-1 ያሸነፍናቸውን ነው፤ ይሄ ጨዋታ ለእኔ የመጀመሪያዬ ኢንተርናሽናል ግጥሚያና በበርካታ ደጋፊዎች ፊት ታጅቤ
የተጫወትኩበትም ነበር፤ በግጥሚያው ሁለት ጎሎችንም ላስቆጥርበት ችያለው፤ በክለብ ደረጃ ከሆነ ደግሞ የእኔ ምርጡ ጨዋታ ባህር ዳር ከተማን 5-0 ባሸነፍንበት ጨዋታ ላይ ሁለት
ጎሎችን አስቆጥሬ ነበርና ያ ግጥሚያ ፈፅሞ የማይረሳኝ ነው”፡፡
በእግር ኳስ ተጨዋችነት ዘመኑ የምንጊዜም ምርጡ ጎሌ ስለሚላት፡- “ምርጧ ጎሌ ከደቡብ ፖሊስ ጋር ስንጫወትና 2-1 ስንሸነፍ በፎርቢች ያስቆጠርኳት ናት”፡፡
በጨዋታ ዘመንህ ጎል እንድታስቆጥር ምርጥ አቀባበል /አሲስት/ ያደረገልህ ተጨዋች፡- “በእዚህ ደረጃ በጣም ከማስታውሰው ውስጥ የምጠቅሰው የመጀመሪያው ተጨዋች የእኔ የቡድን
አጋሬ የሆነውን ሚኪያስ መኮንን /ሚኪን/ ነው፤ እሱ ከወላይታ ድቻ ጋር በነበረን ጨዋታ ላይ በጉዳት የተነሳ ከሜዳ ርቄ ነበርና ገና ወደ ጨዋታ በተመለስኩበት ግጥሚያ ላይ ጎል እንዳስቆጥር
ጥሩ አቀባበልን አድርጎልኝ ነበርና ያን አልረሳም፤ ከሚኪ ውጪ ለእኔ ሌላ ጥሩ ኳስ በማቀበል የምጠቅሰው ተጨዋች ደግሞ የቡድናችን ተጨዋች የነበረውን ጋቶች ፓኖምን ነው፤ ጋቶች
ከአዳማ ከተማ ጋር 2009 ላይ ስንጫወት በጭንቅላቴ ገጭቼ ጥሩ ጎል እንዳገባ አድርጎኝ ነበርና እሱንም ልጠቅሰው እፈልጋለሁ”፡፡
በእግር ኳስ ጨዋታ ዘመንህ ምርጡ ጥምረቴ የምትለው ከእነማን ጋር የተጫወትክበትን ነው?፡- “ወደ ኢትዮጵያ ቡና ከመጣሁበት ጊዜ አንስቶ ከአጠገቤ በመጫወት ለእኔ ምርጥ ጥምረቴ
የነበሩት ተጨዋቾች መስዑድ መሐመድ፣ ኤልያስ ማሞ፣ አማኑኤል ዩሃንስ፣ አብዱልከሪም ሀሰን /ምርምር/ እና ጋቶች ፓኖም ናቸው፤ እነዚህን ተጨዋቾች በቅድሚያ ልጠቅሳቸውም
የቻልኩት በጊዜው እንደ መሀል ሜዳ ተጨዋችም የተጫወትኩበት ጊዜም ስለነበር ነው”፡፡
ምርጡ ጓደኛህ፡- “ሚኪያስ መኮንን ነው፤ ከእሱ ጋር አብረን ነው ያደግነው፤ በክለብም ሆነ በብሔራዊ ቡድን ደረጃም በጣም የምንዋደድ የቅርብ ጓደኛማማቾችም ነን”፡፡
ለመዋያ የምትመርጠው ምርጡ ሰፈር፡- “ፒያሳ ነዋ! እዛ መዋል ብዙ ጊዜ ይመቸኛል”፡፡
በዲ.ኤስ.ቲቪ ከተመለከትካቸው ጨዋታዎች የአንተ ምርጡ ጨዋታ፡- “ለእኔ ምርጡ ጨዋታ የምለው በቻምፒዮንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ ላይ የምደግፈው አርሰናል ከባርሴሎና ጋር ተጫውቶ
የተሸነፈበትን ነው፤ በዛ ጨዋታ ቫንፐርሲ በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥቶ ነበርና በአርሰናል ሽንፈት አዝኜም ነበር”፡፡
የኢትዮጵያ ምርጡ ተጨዋች ለእሱ ማን እንደሆነ፡- “ብዙ ቢኖሩም ከፊት እና በአንደኛ ደረጃ የማስቀምጠው ተጨዋች ግን መስዑድ መሐመድን ነው፤ መስዑድ የተለየ ችሎታ እና አቅም ያለው
ተጨዋች ነው፤ በጣምም ነው የሚመቸኝ”፡፡
ከባህር ማዶ ተጨዋቾችስ ለአንተ ምርጡ ተጨዋች፡- “ሊዮኔል ሜሲ ነዋ! እሱን ሲጫወት ማየትም ሁሌም ያስደስተኛል”፡፡
የኢትዮጵያ እግር ኳስ እንደሌሎች ሀገራት ሁሉ ወደ ውድድር ሊመለስ ነው፤ በእዚህ ስለተፈጠረብህ ስሜት፡- “ይሄን ዜና ለመስማት መቻላችን ለእኛ ተጨዋቾች ብቻ ሳይሆን ለስፖርቱ ቤተሰቡ
ጭምር ትልቅ የምስራች ነው፤ በተለይ እንደ እኛ ላሉና እግር ኳስን በጣም በፍቅር ለሚወዱ ሀገራት የእዚህ ውድድር መጀመር መቻል የሚፈጥረው ብዙ አስደሳች ነገርም ስለሚኖር የሊጉን
የውድድር መጀመሪያ ቀናትን በጉጉት እየተጠባበቅኩኝም ነው የምገኘው”፡፡
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከኮቪድ 19 ጋር በተያያዘ የሚጀመረው ያለተመልካች ነው፤ ፉክክሩ ምን አይነት ስሜት እንደሚኖረው፡- “እግር ኳስን ያለ ተመልካች ማየት በጣም ያማል፤ እነሱ
ሲኖሩም ነው ፉክክሩ ሊያምር የሚችለው፤ ስለዚህም ሊጉ ብዙ ጣህም ይኖረዋል ብዬ አላስብም”፡፡
የአውሮፓ ሊጎች ስለመጀመራቸው እና ስለውድድሩ ይዘት፡- “ውድድሮቹ መጀመራቸው በጣም ደስ ይላል፤ ያም ሆኖ ግን ኳሱ ያለ ተመልካች ስለሚካሄድ እና ድባብና የደጋፊዎች ጩኸትም
ስለማይታይበት ግጥሚያዎቹን እንደምጠብቃቸው አላገኘኋቸውም”፡፡

በእግር ኳስ ባለው ችሎታ ተመልክተኸው እና አድንቀኸው ትልቅ ቦታ ባለመድረሱ የሚቆጭህ ተጨዋች፡- “እኛ ሀገር ላይ ብዙ አሉ፤ በተለይ ደግሞ በየሰፈሩ እየተጫወቱ ሳይታዩና ወደ ክለብ
ሳይገቡም እዛው ባክነው የሚቀሩ፤ ከዛ ውጪ ደግሞ ክለብ ገብተውም በሚፈልጉበት ትልቅ ደረጃ ላይ ሳይደርሱም የሚያስቆጩ ተጨዋቾችም አሉ፤ ለምሳሌ ከእኔ ጋር አብሮ የተጫወተውና
ከእኛም የተሻለ አቅም የነበረውን እሱባለውን መጥቀስ ይቻላልና በእሱባለው ትልቅ ደረጃ ላይ አለመድረስ ይቆጨኛል”፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋች በመሆኑ ስለተፈጠረበት ስሜት እና በቡድኑ ቆይታው ምን ነገርን እያለመ እንደሆነ፡- “የብሔራዊ ቡድን ተጨዋች ለመሆን መቻል የደስታ ስሜቱ
ከምነግርህ በላይ ነው፤ ሀገርን ወክሎ መጫወት ሁሌም ያስደስታል፤ መታደልም ነው፡፡ ይሄንን ካልኩ በእዚህ የብሔራዊ ቡድን የተጨዋችነት ቆይታዬ ከዋልያዎቹ ስብስብ ጋር በአሁን ሰዓት
እያለምኩ ያለሁት ብሔራዊ ቡድናችንን ለአፍሪካ ዋንጫ ማሳለፍ ነው፤ በማጣሪያው ጨዋታ የእግር ኳሱ ትልቅ ሀገር የሆነችውን ኮትዲቭዋርን ካሸነፍን በኋላ በህዝቡም ሆነ በእኛ ተጨዋቾች
ዘንድ ከፍተኛ መነቃቃት እየታየ ነው፤ እነሱን ካሸነፍን ሌላው አያቅተንም በሚል ስሜት ውስጥም ነው የምንገኘው፤ ይህን የምናሳካው ግን የልምምድ ስራችንን ጠንክረንና በስነ-ስርዓት
ከሰራን እንደዚሁም ደግሞ ራሳችንን ሳናሳንስ፣ ሳናወርድ እና በተጋጣሚዎቻችን ትልቅ ስም ብቻ ግምት ሰጥተን ወደ ሜዳ ካልገባን ነው፤ ከእዚህ በኋላ በማጣሪያው ጨዋታ ከኒጀር ጋር
ተከታታይ ሁለት ጨዋታ አለን፤ ከዛ ማዳጋስካርን እንፋለምና በመጨረሻም በድጋሚ ከኮትዲቭዋር ጋር እንጫወታለንና በእነዚህ ውስጥ የምናስመዘግባቸው ጥሩ ውጤቶች ስለሚኖሩ የእኔ
የአሁን ሰዓት እልም ያለምንም ጥርጥር ለአፍሪካ ዋንጫ የምናልፍ ይሆናል የሚል ነው”፡፡
ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እንደ አጥቂነትህ በስም የሚመዘገብ ጎል ያስፈልግሃል፤ ይሄን መቼ ያሳካ እንደሆነ፡- “ለብሔራዊ ቡድን እስካሁን ሁለት ጨዋታዎችን ለማድረግ ችያለሁ፤ በእዚህ
ቡድን ቆይታዬም አሁን ላይ እኔን የሚያስጨንቀኝ ጎል ማግባት ሳይሆን ቡድኑ ባለድል ሆኖ ለአፍሪካ ዋንጫ የሚያልፍበት ሁኔታ ነው፤ ለዛ ስልም በሜዳ ላይ የጨዋታ እንቅስቃሴዬ የእኔ
የመጀመሪያ ግብ ለሀገሬም ሆነ ለቡድኔ ስጫወት መጀመሪያ መሳተፍ የምፈልገው የቡድን ስራ ላይ ነው፤ እኔ ሳላገባ ሌሎች እንዲያገቡ አስተዋፅኦ ማድረግ የቅድሚያ ግቤ ነው፤ ይህን ማድረግ
ከቻልኩ በእኔ ስም የሚመዘገብ ግብ ደግሞ ወደፊት እንደሚኖሩኝ ባለሙሉ ተስፋ ነኝ”፡፡
በመጨረሻ፡- “በእግር ኳስ አሁን ላይ ለደረስኩበት እና አንድ ምዕራፍ ለተሸጋገርኩበት ደረጃ በመጀመሪያ አምላኬን አመሰግናለሁ፤ ከዛ በኋላ ደግሞ ቤተሰቦቼን፣ ከእነሱ በመቀጠልም በሐረር
ሲቲ የታዳጊ ቡድን ውስጥ ያሰለጠነኝን እስማኤል አቡበከርን፤ እስማሄልን በተመለከተ እኔን በማሰልጠንና በችሎታዬም ላይ መሰረትን በመጣል ለኢትዮጵያ ታዳጊ ብሔራዊ ቡድን ጥሪ
ባልተደረገልኝ ሰዓት እሱ ይሄን ልጅ ተመልከቱት፤ ጥሩ ችሎታ አለው፤ ለሀገርም ይጠቅማል በሚል ጥቆማ በመስጠት ለቡድኑ እንድመረጥ ምክንያት የሆነኝ ነበርና በጣም ነው ላመሰግነው
የምፈልገው፤ ሌላ የማመሰግናቸው ደግሞ በአሰልጣኝነት እኔን በኃላፊነት የመሩኝን ባለሙያዎች፤ እንዲሁም የአሁኑን አሰልጣኜን ካሳዬ አራጌን፤ ከዛ ውጪም የሰፈሬ ቀበሌ 21 ልጆችንና
ታዳጊ በነበርኩበት ሰዓትም እኔን እየመከሩና እያበረታቱ ከጎኔ የነበሩትን ደረጄ ተፈራንና ዳዊት ተፈራን ለማመስገን እወዳለውኝ”፡፡
የኮቪድ 19 ወደ አገራችን ከገባ በኋላ ያለፉትን በርካታ ወራቶች ከስር ከተጠቀሱት ሁኔታዎች መካከል በምን መልኩ እንዳሳለፈ
ስለተመለከታቸው ፊልሞች፡- “ከተከታታይ የቱርክ ፊልሞች መካከል “ኤር ቱ ጉል” የሚለውን ለመመልከት ችያለሁ”
ስላነበባቸው መፅሐፎች፡- “ብዙ ጊዜ መፅሐፍ የማንበብ ልምዱ የለኝም”፡፡
ለብዙ ጊዜ ስልክ የተደዋወለው፡- “ከመስዑድ መሐመድ፣ ከሚኪያስ መኮንን፣ ከእያሱ ታምሩ፣ ከኤልያስ ማሞ፣ ከአህመድ ረሺድ /ሺሪላ/ እና ከአስናቀ ሞገስ ጋር፤ ከእነዚህ ጓደኞቼ
ውስጥ ከአንድአንዶቹ ጋር ኳስ አብረን የምንጫወትበት አጋጣሚም ስላለ ነው በተደጋጋሚ ጊዜ የምንደዋወለው”፡፡
በኮቪድ 19 ጊዜ ስለጨረሳቸው የሳኒታይዘር ብዛቶች፡- “በቁጥር ደረጃ አላውቀውም ግን ብዙ ጨርሻለው”፡፡
ለብዙ ጊዜያት እንቅልፍ ስለሚተኛበት ሰዓታት፡- “እንቅልፍ የምተኛበትን የሰዓታት መጠን አላውቀውም፤ ግን ብዙ ስለማላመሽ እና ፊልም ተመልክቼም ስለሚደክመኝ ወዲያው ነው ስተኛ
የሚስተዋለው”፡፡
ከሚኖርበት መኖሪያው በተደጋጋሚ ጊዜ ስለሄደበት ቦታ፡- “ብዙ ጊዜ የምሄደው ወደ መድኃኒዓለም አካባቢ ወደ ሚገኘው ጓደኛዬ የሆነው አህመድ ረሺድ /ሺሪላ/ ቤት ነው”፡፡
በተደጋጋሚ ጊዜ ስለተመገበው ምግብ፡- “ከኮቪድ በኋላ አሁን ላይ ደጋግሜ የተመገብኩት ምግብ ቢኖር ማክሰኞ፣ ሐሙስ እና ቅዳሜ ኳስን ከእነ ኤልያስ ማሞ እና ሌሎች የቅርብ ጓደኞቼ ጋር
በመሆን በ35 ሜዳ ላይ ስለምንሰራ ከጨዋታ በኋላ ተገናኝተን የተለያየ የተደበላለቀ ምግብ ነው የምንበለው፤ በጋራ ሆነህ ምግብ ስትበላም እንዴት ደስ እንደሚል”፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P