Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“በሊጉ መሪ ኢትዮጵያ መድን ላይ የተቀዳጀነው ድል በጣም ጣፋጭ ነው” “የድሬዳዋ ደጋፊ ጥሩ ከተጫወትክ አይደለም ለራሱ ለተቃራኒ ቡድንም የአድናቆት ድጋፉን ይሰጣል” ዮሴፍ ዩሃንስ /ድሬዳዋ ከተማ/

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ድሬዳዋ ከተማ በሜዳው እና በደጋፊው ፊት ተጫውቶ የሊጉ መሪውን ኢትዮጵያ መድንን 3-1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

ባለፈው የውድድር ዘመን ከሊጉ ላለመውረድ ይጫወት የነበረው ድሬዳዋ ከተማ ዘንድሮ በእዛ ዞን ውስጥ ከመገኘት ይልቅ የሊጉ ጠንካራ ተፎካካሪ እንደሚሆን የክለቡ የአማካይ ስፍራ ተጨዋች ዮሴፍ ዩሃንስ ከሊግ ስፖርት ጋዜጠኛው መሸሻ ወልዴ /G.BOYS/ ጋር በነበረው ቆይታ ገልጿል።

የድሬዳዋ ከተማው አማካይ በቡድናቸው ዙሪያ ከጋዜጣችን ጋር አድርጎት የነበረው አጠቃላይ ቆይታም ይህን ይመስላል። መልካም ንባብ።

ሊግ፦ በመጀመሪያ ለቃለ-ምልልሱ ፈቃደኛ ስለሆንክ ከልብ እናመሰግንሃለን?

ዮሴፍ፦ እኔም በጣም አድርጌ አመሰግናችኋለሁ።

ሊግ፦ የሊጉን መሪ በሜዳችሁ እና በደጋፊዎቻችሁ ፊት ለማሸነፍ ችላችኋል፤ ስለ ጨዋታው ምን ትላለህ?

ዮሴፍ፦ እንደ ቡድን ጥሩ ነበርን፤  የድሉ ውጤትም የሚገባን ነው። እንደ ፈጣሪ ፈቃድም ይሄን ስኬት ስለተጎናፀፍን በጣም ደስ ብሎናል።

ሊግ፦ የእናንተን ተጋጣሚ ኢትዮጵያ መድንን በጨዋታው እንዴት ተመለከትካቸው?

ዮሴፍ፦ በጣም ጠንካራ የሆነ ቡድን ነው ያላቸው። ኳስንም መስርተው የሚጫወቱ ናቸው። እንዲህ ያለ ጥሩ ቡድንን ስታሸንፍ ደግሞ  የደስታህ መጠን በጣምም ይጨምራል።

ሊግ፦ በሊጉ ባህርዳር ላይ አሁን ደግሞ ድሬዳዋ ከተማ ላይ እየተሳተፋችሁ ይገኛል? ስለ ሁለቱ ከተማዎች አጠቃላይ ተሳትፎአችሁ የምትለን ነገር ካለ……?

ዮሴፍ፦ ባህርዳር ላይ በነበረን ቆይታ ክለባችን እስከ አስራ አንድ የሚደርሱ ተጨዋቾችን ከውጪ በማምጣት ነው ቡድኑ እንደ አዲስ የተሰራው። ያኔ ክለቡ የመዋሀድ ችግር  ነበረበት። አሁን ላይ ግን ወደ ድሬዳዋ ስንመጣ ክለቡ ላይ ያለው ክፍተትና ችግር በአሰልጣኛችን ዮርዳኖስ አባይ ሊነገረንና በስራም ላይ እንድንመለከት ስላደረገን  የነበረብንን ችግር በመፍታትና እንደ ቡድንም በሚገባ ልንዋሀድ ስለቻልን ጥሩ ነገርን እየሰራን ነው የሚገኘው።

ሊግ፦ በሊጉ የእስካሁን የጨዋታ ተሳትፎዎቻችሁ አስቆጪ የምትለው ውጤት አለ?

ዮሴፍ፦ አዎን፤ በባህርዳር ከተማ ሳለን ከሐዋሳ ከተማ ጋር በነበረን ጨዋታ ግጥሚያውን 2-1 እየመራንና ጥሩም ቡድን ይዘን ቀርበን  አንድ ደቂቃ ሲቀር ነበር ግብ የገባብን። ያ የሚያስቆጨን ውጤት ነው።

ሊግ፦ በእዚህ ዓመት የሊጉ  ተሳትፎአችሁ ምን ውጤትን ማምጣት ነው ያለማችሁት?

ዮሴፍ፦ እንደ ቡድን መጀመሪያ ያቀድነው ከፊት ለፊት ያሉብንን እያንዳንዱን ግጥሚያዎች ማሸነፍ ነው። እያሸነፍ በሄድክ ቁጥር ደግሞ የምትደርስበት ከፍታ ላይ ትደርሳለህ። ያ በመሆኑም ዘንድሮ ከአምናው የተማርናቸው ቡዙ ነገሮች ስላሉ የሊጉ ጠንካራ ተፎካካሪ ሆነን እንቀርባለን።

ሊግ፦ ስለ ክለባችሁ ወጣት አሰልጣኝ ዮርዳኖስ አባይ ምን የምትለው ነገር አለ? ስለ እሱስ የምታውቀው ነገር ምንድን ነው?

ዮሴፍ፦ ዮርዳኖስን ሲጫወት በስም ነው የማውቀው። ዘንድሮ ቡድኑን ስቀላቀልም እሱ ነው ወደ ክለቡ እንድመጣ ያደረገኝ። ወደ ቡድኑ ከመጣው በኋላም ነፃ ሰው እንደሆነም አይቻለሁ። በመነጋገርም የሚያምን ነው። ኳስ ተጫውቶ ያሳለፈ ስለሆነም ተጨዋቾችን ይረዳል። በአጠቃላይ እሱን ከወዲሁ ስመለከተው ጥሩ አሰልጣኝ ነው። ተጨዋቾቻችንም ለእሱ ጥሩ ነገር ነው ያላቸው። አሁን ለምንገኝበት ውጤትም ይህ ሁኔታ እኛን የረዳን ይመስለኛል።

ሊግ፦ ፕሪምየር ሊጉን እንደ አጠቃላይ እንዴት ተመለከትከው?

ዮሴፍ፦ የዘንድሮ ውድድር ቡድኖች ትንሽ ጠንካራ ሆነው የመጡበት ነው። የትኛው ቡድን ድክመት እንዳለበትም አታውቅም። ሁሉም የተሻለ ሆኖም ነው የመጣው። ለእዚህ ማሳያ መድንን መመልከት ይቻላል። ሊጉን እየመራ ነው። ከእዚህ አንፃር ነገሮችን ስመለከት የሊጉ ውድድር ሁሉንም ቡድን የሚፈትን ይመስለኛል።

ሊግ፦ ከአዳማ ከተማ ወደ ድሬዳዋ ከተማ ያደረግከው ዝውውር ምን ይመስላል?

ዮሴፍ፦ ብዙ ክለቦች ፈልገውኝ የነበረ ቢሆንም አንድ ስፖርተኛ የሚፈልገው ነገር አለ። ያንን በማሰብም ነው ለእኔ የተሻለ ነገር ስለቀረበልኝ ወደ ድሬዳዋ ከተማ ክለብ ያመራሁት። ወደ ቡድኑ ስገባም ነዋሪዎቹ ለኳስ ያላቸው ፍቅር ከፍ ያለና የሚደግፉትም ኳስንና ኳስንም በመሆኑ ከእዛም ባሻገር አሰልጣኙም ወጣት በመሆኑም ከእሱ ጋር መስራት አለብኝ በሚልም ዝውውሩን አድርጌያለሁ።

ሊግ፦ ስላሳለፍከው የኳስ ህይወት ምን ትላለህ?

ዮሴፍ፦ የኳስ ህይወቴን በተመለከተ እንዲህ ነው ብዬ የምገልፅበት ቃላት የለኝም።  እንደ አንድ ተጨዋች ማስተካከል ያሉብኝ ነገሮች ቢኖሩም ጥሩ ጊዜን  ነው ለማሳለፍ የቻልኩት። በሲዳማ ቡና፣ በአዳማ ከተማም ሆነ አሁን ላይ በድሬዳዋ ሳለሁኝ እኔ በምፈልገው መልኩ ኳሱን እየተጫወትኩም ስለሆነ በእዛ ደስተኛ ነኝ።

ሊግ፦ የአንደኛው ዙር ሊጠናቀቅ ተቃርቧል፤ በእዚህ ዙሪያ ማለት የምትፈልገው ነገር ካለ?

ዮሴፍ፦ የሁለት ሳምንት መርሀ ግብር ሊጨመር እንደሚችል የሰማሁበት ሁኔታ ቢኖርም እኛ አሁን እያሰብን የምንገኘው ከወልቂጤ ከተማ ጋር ስላለብን ጨዋታ ነው። ይህን ግጥሚያም በተሳካ ሁኔታ ድል አድርገንና ሶስት ነጥብንም ከሜዳ ይዘን ወጥተን የሊጉን የመጀመሪያ ዙር በጥሩ ደረጃ ማጠናቀቅ ነው የምንፈልገው።

ሊግ፦ ድሬዳዋ ከተማን እንዴት ተመለከትከው? ስለ ደጋፊዎቻቸውስ ምን ትላለህ?

ዮሴፍ፦ የድሬዳዋ ከተማ ቡድንን እስካሁን  ደስ በሚል ሁኔታ ነው እየተመለከትኩት የሚገኘው። ደጋፊዎቻቸውም ኳስና ኳስን ብቻም ነው የሚያስቡት። ኳስ የምትጫወት ከሆነና ጥሩ  እንቅስቃሴን የምታደርግ ከሆነ ይወዱሃል። ያበረታቱካልም። ጥሩ ካልሆንክ የተቃራኒ ቡድንንም ነው የሚደግፉትና እነሱ በእዚህ በኩል ለየት ይላሉ። እንደ ቡድን እኛን ስመለከት ደግሞ ክቡር ከንቲባው እየመጣ ያበረታታናል። እያንዳንዱን እንቅስቃሴያችንንም በቅርብ ርቀት ሆኖም ይከታተላል። ይሄ ሁኔታም ለስፖርተኛው አሪፍ ተነሳሽነትን የሚፈጥርለት ስለሆነ ቡድናችን አሁን ላይ ጥሩ ነው።

ሊግ፦ አምና ከሊጉ ላለመውረድ ነው ስትጫወቱ የነበረው?

ዮሴፍ፦ ዘንድሮ ይሄ አይደገምም፤  ከአሰልጣኛችን ጋር ጥሩ ስራን እየሰራን ነው። አሁን ላይ  ያለን ነገር ጥሩ ስለሆነም ከፈጣሪ እርዳታ ጋር ጥሩ ተፎካካሪ ሆነን ነው ሊጉን የምንጨርሰው።

ሊግ፦ እንደ ቡድን ያላችሁ ጠንካራና  ክፍተት ጎን ምን ይመስላል?

ዮሴፍ፦ በአብዛኛው ጥሩ ጎን ነው ያለን።  የጎላ ክፍተት አለብን ብዬም አላስብም። በእርግጥ ኳስ ላይ የሚኖሩ ስህተቶች ቢኖሩም እነዛን አሰልጣኛችን ስለሚያርምልን በቡድናችን ላይ  ጥሩ ነገርን  እየተመለከትን ነው።

ሊግ፦ የዓለም ዋንጫን እየተከታተልክ ነው?

ዮሴፍ፦ አዎን።

ሊግ፦ የማን ደጋፊ ነህ? ዋንጫውንስ ማን ያነሳል?

ዮሴፍ፦ ይህን ዋንጫ ስለሚያነሳው ሀገር አሁን ላይ መገመት ይከብዳል። ምክንያቱም ትላልቅ ሀገራት ብዙም በእግር ኳሱ ባልተጓዙ ቡድኖች ለምሳሌ ጀርመን በጃፓን እንደዚሁም ደግሞ አርጀንቲና በሳውዲ አረቢያ የተሸነፉበትን ሁኔታም እየተመለከትንም በመሆኑ ነው። ከምደግፈው ሀገር ጋር በተያያዘ እኔ የቤልጂየምና የፖርቹጋል ደጋፊ ነኝ። አንዳቸው ዋንጫውን ቢያነሱት ደስ ይለኛል።

ሊግ፦ በመጨረሻ…..?

ዮሴፍ፦ የሊጉ ውድድር ሁላችንንም ተጨዋቾች ለዓለም እያስመለከተን ያለበት ሁኔታ ስላለና ያለንን የጨዋታ ብቃትም እንድናውቅ ስላደረገን  ጨዋታዎቹ በዲ ኤስ ቲቪ መተላለፉም ራሳችንን ለገበያ እንድናቀርብም ስላደረገን ለእኛ ብቻ ሳይሆን ወደፊት ለሚመጡት ተጨዋቾች ጥሩ ተምሳሌት የሆነን ነገር እያሳየንም ነው።  ከእዛም በመነሳት

እኛም ወደፊት ለሚመጡት ተጨዋቾች ጥሩ ጥሩ ነገርን ልናስተምራቸውም ነው የሚገባው። በእዚህ አጋጣሚ ይሄ የሊግ ውድድር እኛን ዕድለኛ አድርጎን በእዚህ መልኩ እንዲደረግ ላስቻሉት ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አመራሮችና ለሊግ ካምፓኒውን ከፍተኛ ምስጋናዬን ለማቅረብ እፈልጋለሁ።

ከእዛ ውጪ ሌላ ማለት የምፈልገው ነገር ለቡድን ጓደኞቼ አሁን እያደረግን የምንገኘው ነገር ጥሩ ስለሆነ በእዚሁ ቀጥለን ጥሩ ውጤት እንድናመጣ ነው።

 

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P