Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“ድሬዳዋን ካሸነፍን በኋላ ስላለፉት ሁለት ውጤት ያጣንባቸው ጨዋታዎች መቆጨት ጀምረናል” አስቻለው ታመነ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)

በመሸሻ ወልዴ /G.BOYS/


የቅ/ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብን መለያ ማጥለቅ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በአቋሙ ብዙ ሳይዋዥቅ ለቡድኑ ውጤታማነት ጥሩ ብቃቱን በተደጋጋሚ ጨዋታዎች ላይ ማሳየት ችሏል፤ የሊጉ ኮከብ ተጨዋች ተብሎም በፌዴሬሽኑ ከዚህ ቀደም ተሸልሟል፤ ይሄ ጠንካራው የቅ/ጊዮርጊስ ክለብ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች አስቻለው ታመነ ክለባቸው ዘንድሮ ተሳትፎ ባደረገበት የፕሪምየር ሊጉ ውድድር ዙሪያ የተለያዩ ጥያቄዎችን ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ አቅርቦለት የሚከተለውን ምላሽ ሰጥቷል፡፡

ሊግ፡- ቅዱስ ጊዮርጊስ ድሬዳዋ ከተማን ማሸነፉ አስቆጭቶታል እየተባለ ነው፤ አሸንፎ መቆጨት አለ እንዴ?
አስቻለው፡- እንዴት አይኖርም፤ የተቆጨነው እኮ ድሬዳዋን ስላሸነፍን አይደለም፤ ምናለ ከድሬዳዋ ከተማ ጨዋታ በፊት ባደረግናቸው እና ነጥብ ከጣልንባቸው ግጥሚያዎች መካከል ሁለቱን ጨዋታ አሸንፈን ቢሆን ኖሮ በሚል ነው የድሬዳዋ ከተማን ካሸነፍን በኋላ የሂሳብ ስሌቱን ስንሰራ የነጥብ ልዩነቱ የሚያስቀምጠንን ቦታ ስናውቅ ጊዜ ልንቆጭ የቻልነው፡፡ ከመከላከያ እና ከደ/ፖሊስ ጋር ባደረግነው ጨዋታ ግጥሚያዎቹን አሸንፈን ቢሆን ኖሮ ወደ ዋንጫው ፉክክር በጣም እንጠጋ ነበር፡፡ ግን ምን ያደርጋል እነዚያን ግጥሚያዎች በተስፋ መቁረጥ ስሜት ላይ ሆነን መጫወታችን ነው አሁን ላይ ከድሬዳዋው ውጤት በኋላ በጣሙን ልንቆጭ የቻልነው፡፡
ሊግ፡- የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሊጠናቀቅ የ4 ሳምንታት ጨዋታዎች በቀሩበት የአሁን ሰአት እናንተ በ6 ነጥብ አንሳችሁ ተከታዩን ስፍራ ይዛችኋል፤ በሊጉ ከዚህ በኋላ የሚኖራችሁ ተሳትፎ ምን ውጤትን ለማምጣት ነው?
አስቻለው፡- ቅዱስ ጊዮርጊስ በቀሪዎቹ የ4 ሳምንታት ጨዋታዎች አሁንም ከዋንጫው ፉክክር ባይወጣም 4ቱን የሊጉን ጨዋታዎች የሚያደርገው የሚያስቀምጠው ቦታ ላይ ሆኖ ውድድሩን ለመጨረስ ነው፤ የእግር ኳስ ጨዋታ ላይ አንዳንዴ የሚፈጠሩ ነገሮች አይታወቁም፤ ለእኛ ዋንጫ ባንበላ እንኳን አሁን ካለንበት አቋም አንፃር ውድድሩን ሁለተኛ ሆነን መጨረስ ብንችል በራሱ ጥሩ ነው፡፡
ሊግ፡- ቅዱስ ጊዮርጊስ አንድ ዓመት ዋንጫ ቢያጣ በቀጣዩ ዓመት ዋንጫ አያጣም ነበር፤ አሁን ላይ ሁለተኛ ብንወጣ ጥሩ ነው እንዳልከው ቢሳካላችሁ ተቀባይነትን የምታገኙ ይመስልሃል?
አስቻለው፡- አይመስለኝም፤ ቅዱስ ጊዮርጊስ የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ በተደጋጋሚ ጊዜ በማንሳት የሚታወቅ ከመሆኑ አንፃር ከዋንጫ ውጪ ሌላ ውጤት በቡድናችን ውስጥ ተቀባይነት የለውም፤ ሌሎች ውጤቶች ክለቡን ባይመጥነውም ዓምናም ሁለተኛ ሆነን ጨርሰናል፤ የዘንድሮ ውጤት ማጠናቀቂያችንን አሁን ላይ ባናቀውም በቀጣይ ጨዋታዎቻችን ላይ በምናስመዘግበው ውጤቶች ክለባችንን የሚያስቀምጠው ቦታ ላይ ሆነን ውድድሩን ልናጠናቀቅ ዝግጁ ነን፡፡
ሊግ፡- ድሬዳዋ ከተማን በአንተ ሁለት የፍፁም ቅጣት ምት ጎሎች ማሸነፍ ችላችኋል፤ ጨዋታውን እንዴት አገኘኸው?
አስቻለው፡- ቅዱስ ጊዮርጊስ ድሬዳዋ ከተማን ያሸነፈበት ጨዋታ በሁለታችንም መካከል ጥሩ ፉክክር ያልተደረገበት ነበር፤ ብዙም የግብ ሙከራ ጨዋታም ላይ አልነበረም፤ ያም ሆኖ ግን የእኛ ቡድን ባገኘው ሁለት የፍፁም ቅጣት ምት ጎሎች ጨዋታውን ልናሸንፍ ችለናል፡፡
ሊግ፡- ለቅዱስ ጊዮርጊስ ሁለት ጎሎችን በፍፁም ቅጣት ምት አስቆጥረሃል፤ በጨዋታስ ግብ አታገባም?
አስቻለው፡- አገባለሁ እንጂ፤ ግብ የማስቆጥርበት ጊዜም ሩቅ አይሆንም፤ በጨዋታ ግብ ስለማስቆጠር በወደፊቶቹ የቡድናችን ጨዋታዎች ላይ እያሰብኩበት ነው፤ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ከዚህ ቀደም በኢንተርናሽናል ጨዋታ ላይ እና በአንድ ከሐዋሳ ከተማ ጋር በተደረገ የሊግ ጨዋታ ላይ አስቆጥሬያለሁ፤ ያንን ወደፊትም መድገም እፈልጋለውና ሌሎች በርካታ ግቦች ከፍፁም ቅጣት ምት ውጪም እንዲኖሩኝ እፈልጋለሁ፡፡
ሊግ፡- የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች በሁሉም ግጥሚያዎች ላይ በተለይ ደግሞ ለአንተ የተለየ አድናቆት እየሰጡህ ያሞግሱሃል፤ እናቱ የወለደችው፤ ጀግና እና ሌሎችም ሙገሳዎችን ነው የሚሰጡህ ይሄን ስትሰማ ምን ትላለህ?
አስቻለው፡- የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች በቡድኑ ውስጥ እስካለህ ድረስ አንዳችን ነገር ሳትሳሳት ሁሌም ቢሆን ለክለቡ ጥሩ ግልጋሎትን የምትሰጥ ከሆነ በየጨዋታው ላይ ለአንተ ምስክርነታቸውን የሚሰጡልህ ስለሆነ ለእኔም የሙገሳ ቃላቶችን እያወጡ አድናቆታቸውን የሚሰጡኝ እንደዚሁም ደግሞ ለቡድኑም ሌላ አደራ እንዲኖሩብኝ የሚያደርጉት የተለየ ነገር ኖሯቸው ሳይሆን በሜዳ ላይ ምንም ነገር መጣ አቋሜ ብዙ ሳይዋዥቅ ጥሩ እንቅስቃሴን ስለማደርግ ነውና ለዚሁ አድናቆታቸው ምስጋናዬን አቀርባለሁ፡፡
ሊግ፡- ደደቢትን ለመግጠም ወደ መቐለ ተጉዛችኋል፤ ስለጨዋታው ምን ትላለህ? ማንስ የግጥሚያው አሸናፊ ይሆናል?
አስቻለው፡- ቅዱስ ጊዮርጊስ ከደደቢት ጋር ለሚያደርገው ጨዋታ ወደስፍራው ያመራው ለግጥሚያው ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ ነው፤ ደደቢት ከሊጉ መውረዱን ብናውቅም ሁሉም ቡድኖች ከእኛ ጋር ሲጫወቱ 200 ፐርሰንት ራሳቸውን ለማሳየት የሚጫወቱበት ሁኔታ አለና ይሄ ግጥሚያ እኛን አያዘናጋንም፡፡ ክለቡን ወደታችኛው ዲቪዝዮን ወርዷል ብለንም አናቀልምና ደደቢትን በጨዋታው አሸንፈን ለመምጣት ተዘጋጅተናል፡፡
ሊግ፡- በመጨረሻ….
አስቻለው፡- ቅዱስ ጊዮርጊስ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ዋንጫ አይቶ የማይመለስ ቡድን ነበር፡፡ አሁን ግን በተለያዩ ምክንያቶችና ዋና ዋና ችግሮቻችን ከዋንጫው መራቅ ጀምረናል፡፡ ስለዚህም የቀጣይ ጊዜ የውድድር ተሳትፎአችን ላይ በቡድኑ ዙሪያ ጥልቅ ውይይትን ከክለቡ አመራሮች ጋር በማድረግ እና የሊጉ ውድድር ሲጀመርም ከመጀመሪያው ዙር አንስቶ እንዴት ውጤታማ መሆን እንዳለብን ተዘጋጅተን የቅዱስ ጊዮርጊስን የቀድሞ ስምና ዝና ልንመልስለት ይገባል፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P