Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“ጎል ሳላስቆጥር ከሜዳ ስወጣ እበሳጫለሁ” “አጀማመራችን የአማረ ቢሆንም  ዋንጫውን እናነሳለን ብዬ አልዋሽህም” ጌታነህ ከበደ /ወልቂጤ ከተማ/

 

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ተሳትፎው ላይ ለወልቂጤ ከተማ ቡድን በመጫወት ከጅማሬው ጎል ማስቆጠር ጀምሯል፤ የጎል ዕድልንም ሊፈጥር ችሏል።

ቡድኑ በሊጉ ባደረጋቸው ሁለት ጨዋታዎች ላይ ስድስት ነጥብን እንዲይዝም የበኩሉን ድርሻ የተወጣው ካፒቴኑ ጌታነህ ከበደ ስለ ቡድናቸው የሊጉ ጅማሬ፣ ስለ ራሱ እና ሌሎችንም ጥያቄዎች የሊግ ስፖርቱ ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ /G.BOYS/ አቅርቦለት ተከታዩን ምላሽ ሊሰጥ ችሏል።

ሊግ፦ በቅድሚያ ለቃለ-ምልልሱ ፈቃደኛ ስለሆንክ ከልብ አናመሰግናለን?

ጌታነህ፦ እኔም አክብራችሁ እንግዳችሁ ስላደረጋችሁኝ ከልብ አመሰግናችኋለሁ።

 

ሊግ፦  ሁለት ተከታታይ ጨዋታዎችን በማሸነፍ ፕሪምየር ሊጉን በመቶ ፐርሰንት ሪከርድ ጀምራችኋል፤ ስለ ጨዋታዎቹ ምን የምትለው ነገር ይኖራል?

ጌታነህ፦ ከክለባችን ሁኔታ ስነሳ መጀመሪያ ቡድናችንን እንደምታውቀው በዝውውር መስኮቱ ላይ ከአቅም ማነስ የተነሳ ብዙም አልተሳተፈም፤ በእዛም ትላልቅ የሚባሉ ወጪዎችንም አላወጣም። ከሱፐር ሊግና ከፕሪምየር ሊግ ላይ በመካከለኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ አሉ የሚባሉ ተጨዋቾችን ነው ለማምጣት የቻለው። ብዙ ተጨዋቾችም ወደ ሌላ ቡድኖች ሊሄዱብንም ችለዋል።

እንደዛም ሆኖ ግን በአዳማ ከተማ ላይ በነበረን የቅድመ ሲዝን ዝግጅት ላይ በቂ የአቋም መለኪያ ጨዋታ ስላደረግንና  በባህርዳር ላይ ያደረግነው የሲቲ ካፕ ውድድርም ቡድናችንን በበላይነት እንዲያጠናቅቅ ስላስቻለሁ እና ውድድሩም በጣሙን ስለጠቀመን የሊጉ አጀማመራችንን የአማረ እንዲሆንልን አድርጓል።

ሊግ፦ ከአርባምንጭ ከተማ ጋር በነበራችሁ የመጀመሪያው ሳምንት ጨዋታ የአንተ ምርጥ የቅጣት ምት ጎል ለቡድናችሁ ድል ወሳኝነት ነበራት፤ ጎሏን በማስቆጠርህ ምን ስሜት ተፈጠረብህ?

ጌታነህ፦ በሁሉም ዓለም ላይ የመጀመሪያ ጨዋታዎች ሁሌም በጣም ነው የሚከብዱት፤ ክለቦችም በእዚህ የመጀመሪያ ጨዋታዎቻቸው ላይ ሶስት ነጥብን መያዝ አጥብቀው ነው የሚፈልጉት ከእዛም የተነሳ በዘንድሮ ውድድር ላይ ጥሩ ጥሩ ተጨዋቾችን ከሰበሰበው እና ዓምናም ጥሩ ተሳትፎ  አድርጎ ከነበረው ጠንካራው የአርባምንጭ ከተማ ቡድን ላይ  የመጀመሪያ ሶስት ነጥብን መውሰድ መቻላችንና  የድሏንም ግብ ለማስቆጠር በመቻሌ በጣም ደስ ብሎኛል።

ሊግ፦ በጨዋታው ላይ የህመም ስሜት አጋጥሞህ ወደ ሆስፒታል የሄድክበት አጋጣሚም ነበር?

ጌታነህ፦ አዎን፤ ከምግብ ጋር በተያያዘ የፉድ ፖይዝን ህመም ነበር ያጋጠመኝ፤ ኪኒን ወስጄም ነው የተጫወትኩት። በኋላ ላይ ትንሽ ራሴን ሲያዞረኝ ከሜዳ ተቀይሬ ልወጣና ወደ ሆስፒታልም ላመራ ችያለሁ። አሁን ላይ ደግሞ በመልካም ጤንነት ላይ በመሆን የረቡዕ ዕለትን ጨዋታ ለማድረግ ችያለሁ።

ሊግ፦ የወልቂጤ ከተማ እግር ኳስ ክለብን በካፒቴንነት ኃላፊነት እንደመምራትህ ዘንድሮ ምን ውጤትን ማምጣት አልማችኋል?

ጌታነህ፦ በመጀመሪያ ደረጃ ዘንድሮ  ወልቂጤ ከተማን ለዋንጫ ይፎካከራል ለማለት እንደሌሎቹ ቡድኖች መሆን ይገባሃል። ምክንያቱም ይሄ ቡድን  ከደመወዝ ክፍያ ጋር በተያያዘ እና ጨዋታዎችን ከማሸነፍ ጋር በኢንሴንቲቭ በኩል  መዘግየቶች ስላሉ ብዙ ጥያቄዎች የሚነሳበት ቡድን ስለሆነና በዝውውር ገበያው ላይም እንደ ሌሎች በደንብ ያልተሳተፈም ስለሆነ ለዋንጫ እንጫወታለን ማለት ለአፍ ለማውራት ካልሆነ በስተቀር የውሸት እና ዘበት ነው። አይደለም እንደዛ ሆነህ ጥሩ ጥሩ ተጨዋቾች ኖሮህም እኮ ከዋንጫው ፉክክር ትወጣለህ። ስለዚህም በውድድር ዘመኑ ላይ እኛ ልናመጣ ያሳብነው ውጤት ሊጉን በጥሩ ደረጃ ላይ ሆነን ማጠናቀቅ ነው።

ሊግ፦ ጎል ከማስቆጠር ጋር በተያያዘ አሁንም ከጅማሬው አለህበት በእዚህ ዙሪያ የምትለው ነገር ካለ? ወደፊትስ አንተነትህን የሚገልፅ ነገር እንመለከታለን?

ጌታነህ፦ የእኛን ቡድን ዘንድሮ እንደተመለከትከው ከሲቲ ካፑ  ጨዋታ ጀምሮ ጎል ማስቆጠር ጀምሯል። በሲቲ ካፑ የመጨረሻ ጨዋታም ላይ እኔ ጎል አግብቼ ነበር። አሰልጣኙም ጎል እንዲቆጠር የሚፈልገው ከእኔ ብቻ ሳይሆን ከተለያዩ ተጨዋቾችም ነውና ዘንድሮም እንደ ቀድሞ ሁሉ ሌሎች ጎሎችን ለማስቆጠር ራሴን በሚገባ እያዘጋጀው ነው።

ሊግ፦ ጎሎችን ሳታስቆጥር  ከሜዳ በምትወጣባቸው ጨዋታዎች ላይ ትናደዳለህ?

ጌታነህ፦ እንደ አንድ አጥቂ ዓለም ላይም ያለ ነውና ጎል ሳታስቆጥር ከሜዳ ስትወጣ ትናደዳለህ፤ እኔም እናደዳለሁ። አሲስት ሳታደርግና የጎል ሙከራ እንኳን ባላደረግክበት ጨዋታም ላይ ንዴቱ ይኖራል። ሙከራ አድርጌ ስስት ግን ያን ያህል ንዴቱ አብሮኝ አይኖርም።

ሊግ፦ እስከ ብሄራዊ ቡድን ደረጃና በትላልቅ ክለቦች ውስጥ  ለመጫወት ችለሃል፤ ዛሬም ላይ ሊጉን ከተቀላቀለ አጭር ዓመታት ለሆነው ለወልቂጤ ከተማ ክለብ እየተጫወትክ ይገኛል? በእዚህ ዙሪያ ምን አልክ?

ጌታነህ፦ በመጀመሪያ ደረጃ ወደ ወልቂጤ ከተማ ክለብ ውስጥ ከመምጣቴ በፊት ትላልቅ የሚባሉ ክለቦች እኔን ወደ እነሱ ለማዘዋወር እና  ለመውሰድ ጥያቄዎችን አቅርበውልኛል። ያም ሆኖ ግን አንተ መሄድ ያለብህ ይሄ ክለብ ለእኔ ይስማማኛል ብለህ እና እነሱ የሚሰጥህን  ነገር ተከትለህ ነው። ዘንድሮ እኔ ውል እያለብኝ ወደ ሌላ ክለብ ለማምራት ከጫፍ ደርሼ ነበር። ግን ውሌን በማክበር እና ክብርንም ለእኔ ስለሰጡኝ ከእነሱ ጋር ልቀጥል ችያለሁ።

ሊግ፦ ወልቂጤ ከተማን አጠር ባለ መልኩ ግለፀው ብትባልና ልምድህን ለሌሎች የቡድኑ ተጨዋቾች ስለምታካፍልበት መንገድ አንድ ነገር ብትል?

ጌታነህ፦ ስለ ቡድናችን ማለት የምፈልገው አምና የእኛ ቡድን ተቸግሮ የነበረውና ውጤትን አጥቶ የነበረው ልምድ ያላቸው ተጨዋቾች በቡድኑ ውስጥ ብዙ ስላልነበሩ ነው።  በዘንድሮ ተሳትፎአችን  ላይ ግን ነጥብን ይዘን እየወጣን ያለነው ልምድ ያላቸው ተጨዋቾችን አምጥተን ከወጣቶች ጋር በማጣመር እየተጫወትንም ስለሆነ ነጥቦችን ይዘን በመውጣት ላይ ነው የምንገኘው። ይሄን ነገር ለወደፊትም ለማስቀጠል  እየተዘጋጀው  ነው። ስለ ራሴ ማለት የምፈልገው ደግሞ በሊጉ ላይ 13 ዓመት እየተጫወትኩ ነው ያለውት ያን ልምዴን ለወጣት ተጨዋቾች እያካፈልኳቸው ነው። ከ2001 ጀምሮ በሊጉ ላይ በጥሩ አቋም ላይ ሆኜ እየተጫወትኩ ስለሆነና ያንንም ብቃት ስላመጣሁበት ሁኔታ ስለምነግራቸው ለቀጣዩ የኳስ ህይወታቸው ይጠቅማቸዋል ብዬ አስባለው።

ሊግ፦ ወደ ሜዳ ገብተህ ስትጫወት ሁሌም እለኸኛነትህ እና አልሸነፍ ባይነትህ ይገርማል? አሁንም ይህ ሁኔታ አብሮህ አለ….

ጌታነህ፦ ወደ ኳስ ተጨዋችነቱ የሚመጡት  አሁን ያሉት ታዳጊዎች ላይ ይህ ነገር በውስጣቸው ብዙም የለም ነበር፤ የበፊት  ታዳጊ ተጨዋቾች ደግሞ መሸነፍን አይወዱም። አሁን ላይ ይህ ሁኔታ ሊፈጠር የቻለው ክለቦች ለተጨዋቾቻቸው አጠር ያለ ኮንትራትን ስለሚያስፈርሟቸው ነው። ነገር ግን ተጨዋቾች ሁሌም ቢሆን ለሚጫወቱበት ክለብ ታማኝ በመሆን በአልሸነፍ ባይነት ስሜት ቢጫወቱ ለራሳቸው ሲሉ ጥሩ ነው።

ሊግ፦ በቅጣት ምት አጠቃቀምህ ላይ ሁሌም ጥሩ ነህ፤ ይህ ከምን መጣ?

ጌታነህ፦ የቅጣት ምት አጠቃቀሜን በተመለከተ የልምምድ ውጤት ነው። እዛ የምሰራውንም ነው በሜዳ ላይ የማሳየው።

ሊግ፦ በመጨረሻ ስለ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ አንድ ነገርን በልና እናጠቃል?

ጌታነህ፦ ውድድሩ ገና ነው፤ ይሄ ቡድን ሻምፒዮና ይሆናል የምትልበትም ጊዜ አይደለም። ያም ሆኖ ግን ዓምና ተጨዋቾቻቸውን ይዘው የቆዩት ቡድኖች የሊጉን ዋንጫ ሊያነሱ የሚችሉበት ዕድላቸው የተሻለ ይመስለኛል።

 

 

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P