Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“ጥሩ እየተጫወትን የምንፈልገውን ውጤት አለማስመዝገባችን አስቆጭቶናል”  አማኑኤል ጎበና /አዳማ ከተማ/

 

በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ለአዳማ ከተማ እግር ኳስ ክለብ በአማካይ ስፍራው ላይ በመጫወት የሚታወቀውና ጥሩም እንቅስቃሴ እያሳየ የሚገኘው አማኑኤል ጎበና ቡድናቸው ከወዲሁ በሜዳ ላይ እያሳየ ከሚገኘው እንቅስቃሴ አንፃር እያስመዘገበ ያለው ውጤት የሚመጥነው እንዳልሆነ ገልፆ፤ በእዚህም ያለፉት ሶስት ጨዋታዎቹ ዘጠኝ ነጥቦችን ለማግኘት አቅደው አራት ነጥብን ብቻ ማግኘታቸው እንዳስቆጫቸውም ለሊግ ስፖርት ጋዜጣ አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡

የአዳማ ከተማው የአማካይ ስፍራው ተጨዋች አማኑኤል ጎበና ከሊግ ስፖርት ጋዜጠኛው መሸሻ ወልዴ ጋር በእዚህና በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ያደረጉት ቆይታም በሚከተለው መልኩ ቀርቧል፡፡

ስላለፉት ሶስት የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎቻቸው

“በስኳዷችን ከያዝነው ምርጥ የተጨዋቾች ስብስብና አስቀድመን ከአቀድነው አንፃር የምንፈልገውን ዘጠኝ ነጥቦችን ለማግኘት ባንችልም በሜዳ ላይ የነበረንን እንቅስቃሴ ግን እንደተመለከትኩት ከሞላ ጎደል በጣም ጥሩ የነበረ ነው፤ ያም ሆኖ ግን የምንፈልገው ነጥብ አልተገኘምና ያ አስቆጭቶናል”፡፡

ዘጠኝ ነጥቦችን ለማግኘት ስላልቻሉበት ሁኔታ

“ወደ ሐዋሳ ከተማ በመጣንበት ወቅት በተከታታይ ሶስት ጨዋታዎች ላይ ዘጠኝ ነጥቦችን እንደምናገኝ በጣም እርግጠኞች ነበርን፤ ያም ሆኖ ግን በእግር ኳስ አንድአንዴ ያሰብከው ሳይሳካ ይቀርና እኛን ተቃራኒ የሆነ ውጤት ገጥሞናል፤ በውድድሩ ቆይታችን እኛ በምንፈልገው ሁኔታ ነጥብ ያላገኘነው ጥሩ ሳንሆን ቀርተን አይደለም፤ በኳሱ በሚያጋጥም ጊዜያዊ ሁኔታም ነው ዘጠኝ ነጥብን ሳናገኝ ቀርተን አራቱን ብቻ ልናሳካ የቻልነው”፡፡

ከዘንድሮ ስብስባችሁ በመነሳት አዳማ ከተማን ስትገልፀው 

“ዘንድሮ ቡድኑ ከአምና ብዙ ነገሮችን በመማር በጣም ጠቃሚ ተጨዋቾችን አስፈርሞ ይገኛል፤ የተሻለ ውጤትን ለማምጣት ስለፈለገም ጥሩ አሰልጣኝን አምጥቶም ልምምዱን በተሳካ ሁኔታ እየሰራም ይገኛል፤ እንደ ቡድን የሚጫወት ክለብም ነው በመሰራት ላይ የሚገኘው፤ ይሄም ደግሞ ባለፉት ሶስት ጨዋታዎች ላይ ጥሩ ፍንጭን አሳይቶም ተገኝቷልና የዘንድሮ ቡድን ወደፊት ብዙ የሚጓዝም ይመስለኛል”፡፡

ከሶስቱ ጨዋታዎቻቸው በጣም የተቆጨበት

“የመጀመሪያው የመክፈቻ ግጥሚያችን ስለነበር ከወልቂጤ ከተማ ጋር አድርገን አቻ የተለያየንበትን ፍልሚያ ነው እኔ የተቆጨሁበት፤ በዛ ጨዋታ ላይ እኛ ጥሩ ነበርን፤ የፍፁም ቅጣት ምትም አግኝተን ልንጠቀምበት ሳንችል ቀርተናል፤ ያን ግጥሚያ ማሸነፍ ብንችል ለቀጣዮቹም ግጥሚያዎች ከሞራል አንፃርም የበለጠ ሙሉ አቅማችንን አውጥተንም እንድንጫወት ያደርገን ነበርና የወልቂጤው ጨዋታ የሚያስቆጭ ነው”፡፡

ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ከተቋረጠበት ወደ ውድድሩ ሲመለስ አዳማን በምን ውጤት እንደሚጠብቁት

“አዳማ ከተማ በዘንድሮ የውድድር ተሳትፎው ጥሩ ውጤትን ለማስመዝገብ ነው እየተወዳደረ የሚገኘው፤ ካለፉት ሶስት ጨዋታዎቹም የሚማራቸው ብዙ ነገሮች አሉ፤ እነዛንም ከአሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ከሚሰጠው ስልጠናና በቪዲዮ ከምንመለከታቸው እንቅስቃሴዎችም በመነሳት ክፍተቶቹን ይደፍናቸዋል፤ ካለፉት ጨዋታዎች ውስጥ በሁለቱ ስኬትን ያጣነው ጊዜያዊ በገጠመን የውጤት ማጣት ችግር ነው፤ ቡድናችን በቀጣይነት ወደ ውድድሩ ሲመለስ ተሻሽሎም ይመጣል፤ ከእኛ የክለቡ ሀላፊዎች፣ አሰልጣኞቻችንና ደጋፊዎቻችን ብዙ ነገሮችን የሚጠብቁም ናቸውና ያኔ ራሳችንን በብቃት አዘጋጅተን ለክለቡ ጣፋጭ የሆነ ውጤትን የምናስመዘግብለት ይሆናል”፡፡ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ ማን እንደሚያነሳ

“አሁን ላይ ሆኜ ይሄ ቡድን ዋንጫውን ያነሳል አልልህም፤ የውድድሩ ሻምፒዮናነት ለሁሉም ቡድኖች ክፍት ነው፤ ጠንክረው ከሰሩ ሁሉም ቡድኖች ይህን ስኬት የመጎናፀፍ እድሉ አላቸው፤ እኛም የምንጫወተው ዋንጫውን ለማንሳት ነው፤ ያን ብናጣ እንኳን የውድድሩ ጠንካራ ተፎካካሪ እንሆናለንና ዘንድሮ ዋንጫውን የሚያነሳው እስከ መጨረሻው የሚለፋው ቡድን ነው”፡፡

በአዳማ ከተማ መለያ ለቡድኑ ጥሩ እንቅስቃሴን ማድረግ ስለመጀመሩ

“አሁን ላይ ጥሩ መንቀሳቀስ ልጀምር እንጂ ከዚህ በላይ ለቡድኔ የተሳካ ግልጋሎት መስጠት እንዳለብኝ አምናለው፤ ለዛም ደግሞ ከአሰልጣኜ የሚሰጠኝን ልምምድ በአግባቡ መስራትም አለብኝና ለዛም ሁሌም ራሴን እያዘጋጀሁት ነው”፡፡

በመጨረሻ….?

“ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ኳሳችንን በዲ.ኤስ.ቲ.ቪ እያስተላለፈልን በመሆኑ ለሀገራችን ጥሩ ነገርን ይዞልን መጥቷል፤ ከእነዛም መካከል ለተጨዋቾቻችን እየፈጠረላቸው ያለው የፕሮፌሽናል ተጨዋችነት የመታየት እድል ቅድሚያውን ይወስዳል፤ ከዛ ውጪም ለተጨዋቹ፤ ለክለቦቻችንና ለሀገራችንም ትልቅ ጥቅምን እያስገኘልንም ነውና ብዙ ነገሮችን ቀይሮልን ይገኛልና ይህ ጉዞ ይበል የሚያሰኝ ነው፤ ከዚህ ሌላ አንድ ማስተላለፍ የምፈልገው ነገር በአሁን ሰዓት ሀገራችን ላይ በጦርነቱ ሳቢያ ሰላምን ስላጣን ያለው ነገር ደስ አይልም፤ ብዙ ሰዎችን በሞትና በስደት እያጣን ነው፤ ይሄ በመሆኑም ፈጣሪ ነፃ እንዲያወጣን ሁላችንም እንደየእምነታችን ፀሎት ከማድረግ ጀምሮ ለተጎዱ አካላቶች የአቅማችንን የምናደርግበት ሁኔታን ብናመቻች ጥሩ ነው፤ በተለይም ደግሞ በስፖርቱ አካባቢ ያለን ሰዎች ኳሱ የሚኖረው ሰላም ሲኖርም ነው፤ ስለዚህም በጦርነቱ የተጎዱ ብዙ ወገኖች አሉንና እነሱን ለመርዳት እያሰብን የበኩላችንን እናድርግ፤ አጋዣቸውም እንሁን፤ ፈጣሪ ሀገራችንንም ሰላም ያድርግልን፡፡

 

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P