Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“በአቡበከር ናስር መንፈሳዊ ቅናት አድሮብኛል” “ለኢትዮጵያ ቡና ለመጫወት  ማምራቴ የህይወቴ መጨረሻ ነው ብዬ አላስብም” ጫላ ተሺታ /ኢትዮጵያ ቡና/

 

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ውስጥ እነ ያሬድ አበጀን፣ መስፍን አህመድን /ጢቃሶ፣ ኤፍሬም አለምነህንና ሌሎች ተጨዋቾችን ካፈራችው የሻሸመኔ ከተማ ውስጥ በመፍራት ነው ወደ እግር ኳሱ መንደር  ብቅ ሊል የቻለው።

ይህ ተጨዋች ጫላ ተሺታ ይባላል፤  የእግር ኳሱን ከልጅነቱ ዕድሜ ጀምሮ በእዚሁ ክልል ውስጥ በመጫወት ለተለያዩ ክለቦችና  ለኢትዮጵያ ታዳጊ ብሄራዊ ቡድን ሊጫወት ችሏል።  ለታዳጊ ብሄራዊ ቡድን ግብፅ ላይ ሲጫወት ባሳየው እንቅስቃሴም የቱኒዚያው ክለብ ኢቶሀል ዲ ሳህል አይን ውስጥ ገብቶም የክለቡን ሙከራ ከሌላው የታዳጊ ብሄራዊ ቡድን አጋሩ ተጨዋች ሚኪያስ መኮንን ጋር  ሊያደርግም በቅቷል።

በኢትዮጵያ የቤትኪንግ ፕሪምየር  ሊግ ሻምፒዮና ለሲዳማ ቡናና ለወልቂጤ ከተማ ተጫውቶ ያሳለፈው እና  ከአንድ ወር በፊት በተከፈተው  የክረምቱ የተጨዋቾች ዝውውር መስኮት ለኢትዮጵያ ቡና ለመጫወት ፊርማውን ያኖረው ፈጣኑ አጥቂ ጫላ ተሺታ ከሊግ ስፖርቱ ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ /G.BOYS/  ጋር  ወደ አዲሱ ቡድኑ ስላደረገው ዝውውር፣ በክለቡ ስለሚጠብቀው የውድድር ጉዞ፣ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ምን ነገሮችን እንዳቀደ እና ስላሳለፋቸው የእግር ኳስ ህይወቱ  ውይይትን አድርጎ ተከታዮቹን ምላሾቹን ለጋዜጣችን ሰጥቷል። ቃለ-ምልልሱም በሚከተለው መልኩ ቀርቧል። ተከታተሉት።

ሊግ፦ በቅድሚያ ለቃለ-ምልልሱ ፈቃደኛ ስለሆንክ እናመሰግንሃለን?

ጫላ፦ እኔም የጋዜጣችሁ እንግዳ አድርጋችሁ ስለጋበዛችሁኝ ከልብ አመሰግናችኋለሁ።

ሊግ፦ በክረምቱ የተጨዋቾች ዝውውር መስኮት ወደ አዲሱ ክለብህ ኢትዮጵያ ቡና ለማምራት ችለሃል፤ ለቡድኑ ፊርማህን በማኖርህ የተፈጠረብህ ስሜት ምን ይመስላል?

ጫላ፦ ኢትዮጵያ ቡና ትልቅ ቡድን ነው፤ በርካታም ደጋፊዎች ያሉት ነው። ይሄ በመሆኑም ለእዚህ ቡድን ለመጫወት ሳስብ ብዙ ራዕዮችን ሰንቄ የመጣውና ከክለቡ  ጋርም  የተለያዩ ስኬቶችን  መቀዳጀት ስለምፈልግም  ቡድኑን  ስለተቀላቀልኩ  በጣም ነው ደስ ያለኝ። በእዚህ ቡድን በሚኖረኝ ቆይታዬም ከፈጣሪ እርዳታ ጋር ጥሩ እና አሪፍ ጊዜን ለማሳለፍም ተዘጋጅቻለሁ።

ሊግ፦ ወደ ኢትዮጵያ ቡና ስታመራ የተደረገልህ አቀባበል ምን ይመስላል?

ጫላ፦ ለክለቡ ፊርማዬን ካኖርኩበት ጊዜ ጀምሮ ነው ጥሩ አቀባበል የተደረገልኝ። በተለይም ደግሞ በአዲስ መልክ ለክለቡ  የፈረምነውን ተጨዋቾች ጨምሮ ነባሮቹንም በማካተት ኢትዮጵያ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በሆነ ልዩ አቀባበልም ነውጰ ከደጋፊው ጋር በአበበ ቢቂላ ስታዲየም የክለቡ የተለያዩ ህብረ-ዜማዎችን በጋራ እንድናዜምም ተደርጎም ሊቀበሉን የቻሉት እና ቀኑ በጣም ደስ ይልም ነበር።

ሊግ፦ በእዛን ዕለት የተደረገላችሁን አቀባበል ስትመለከት ስለ ቡድናችሁ ምን ነገሮችን አሰብክ?

ጫላ፦ በምርጦቹ ደጋፊዎች የተደረገልን  የአቀባበሉ ሁኔታ የአማረ  እና ታይቶም የማይታወቅ  መሆኑ ለእኛ ቡድን ተጨዋቾች ትልቅ ተነሳሽነትን ነው የሚፈጥርላቸው። ደጋፊው ደግሞ በእዚሁ  መልኩ እንዲሁ ብሎ  ከተቀበለን እኛ ደግሞ ለእነሱ የሚገባቸውን ነገር ለማድረግም  የፕሪ-ሲዝን ዝግጅታችንን ጀምረናል። ከፈጣሪ እርዳታ ጋርም  በአዲሱ ዓመት ለቡና የሚመጥነውን ውጤት ልናስመዘግብለት ተዘጋጅተናል።

ሊግ፦ ወደ እግር ኳስ ተጨዋችነትህ  ከመምጣትህ በፊት ስለ አዲሱ ቡድንህ ኢትዮጵያ ቡና ምን ምን ነገሮችን ታውቅ ነበር?

ጫላ፦ ያኔ ልጅ የነበርኩበት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያ ቡና ትልቅ ቡድን እንደሆነና ብዙም ደጋፊ እንዳለው አውቅ ነበር። ደጋፊው ደግሞ የቡድኑ የጀርባ አጥንት እንደሆነም እሰማም ነበርና ወደ ክለቡ በመጣሁበት የአሁኑ ወቅትም የተረዳሁት ነገር ያን ነው። ቡናን ስለተቀላቀልኩም በጣም ደስተኛ ነኝ።

ሊግ፦ ስለ ኢትዮጵያ ቡና  ያኔ  ስለ የትኞቹ ተጨዋቾችስ ነበር  በደምብ አድርገህ የምታውቀው እና  ትሰማ የነበረው?

ጫላ፦ በእነ ታፈሰ ተስፋዬ፣ መስዑድ መሐመድ እና ዳዊት እስጢፋኖስ ጊዜ የነበሩትን ነው የማውቀው፤ ስለ እነሱ በተደጋጋሚ ጊዜም እሰማ ነበር። ጥሩ ተጨዋቾችም ነበሩና ለክለቡም የመጫወት ፍላጎቱ ያደረብኝ ከእዛን ጊዜ ጀምሮ ነው፤  መጫወቱን ደግሞ አሁን ላይ ላሳካውም ዝግጁ ነኝ።

ሊግ፦ ኢትዮጵያ ቡና አዳዲስ ተጨዋቾችን እያስፈረመ እና አዲስም ቡድን  እየገነባ ከመሆኑ አኳያ ስለ ክለቡ  ምን ማለት ይቻላል?

ጫላ፦ ቡድኑን እንዳየሁት ከሆነ በወጣቶች ላይ ተመስርቶ የተሰራ  ነው። ጥሩ ስብስብም አለውና ከፈጣሪ እርዳታ ጋር ስኬታማ የውድድር ጊዜያትን እናሳልፋለን ብዬ አስባለሁ።

ሊግ፦ ለኢትዮጵያ ቡና በቋሚ ተሰላፊነት ለመጫወት የሚኖር ፉክክር አለ፤ ያን እንዴት እና በምን መልኩ ልታስተናግደው ዝግጁ ሆነሃል?

ጫላ፦ በቦታው ብዙ የተሻሉ የተሻሉ  ተጨዋቾች እና ልጆች  አሉ። የእነሱ መኖርም ለመሰለፍ  ፉክክሩን እንዲበዛ  ከማድረጉ ባሻገር በውስጥህ የያዝከውንም እምቅ ችሎታም አውጥተህ እንድትጫወትም ያደርግሃልና  በቦታው ተፎካክሬ ለቡና በቋሚነት ለመጫወት ጥረትን አደርጋለሁ።

ሊግ፦ ለኢትዮጵያ ቡና መጫወት ቡድኑ ካለው ዘርፈ ብዙ ደጋፊ  እና ውጤትንም ከመፈለጉ  አኳያ ጫና አለው፤  ከባድ ነውም የሚሉ አሉና በእዚህ ዙሪያ የአንተ ምላሽ ምንድን ነው የሚሆነው? በቡና ቆይታህ ትቸገራለህ? ወይንስ የተሳካ ጊዜያትን ታሳልፋለህ?

ጫላ፦ ወደ ቡና ሳመራ የተሳካ ጊዜያትን አሳልፋለሁ ብዬ እንጂ እቸገራለሁ ብዬ አይደለም።  በእርግጥ ኳሱ ውስጥ ስትገባ ብዙ ነገሮች ሊያጋጥሙህ ይችላሉ፤ ጥሩ ስትሆን ትወደሳለህ፤ ደጋፊው የሚፈልገውን ነገር ካላደረግክለት ደግሞ ትወቀሳለህ። ያን ወቀሳ  ደግሞ እንደ ሽንፈት  መቀበልና  መቁጠር ሳይሆን እንደ መነሻ ነው ልትመለከት የሚገባው እና  በቡና ቆይታዬ እንዲህ ያሉ ሁኔታዎች ይረብሹኛል፤ ይቸግሩኛል ብዬ ከማሰብ ይልቅ ጥሩ ጊዜያትን እንደማሳልፍ ነው የማስበው።

ሊግ፦ ከእዚህ ቀደም አዲሱ ክለብህን  ኢትዮጵያ ቡናን በተቃራኒነት ለመግጠም ችለሃል፤ በእዛ መልኩ መጫወት ያለው ስሜት ምን ይመስላል?

ጫላ፦ ኢትዮጵያ ቡናን በተቃራኒነት የገጠምኩት የሲዳማ ቡናና የወልቂጤ  ከተማ  ክለብ ተጨዋች እያለሁኝ ነው፤ ያኔ ከእነሱ ጋር ስንጫወትም ከፍልሚያው በላይ በጣም ትዝ የሚለኝ የደጋፊዎቹ  የድባብ ስሜትና የአደጋገፍ ሁኔታቸውም በጣም ደስ የሚል መሆኑን የተመለከትኩበትም ነው። በእነዚህ ደጋፊዎች ፊት መጫወትም ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ተጨዋች የሚፈልገው ጭምር ስለሆነም መታደል ብዬም ነው የማስበው።

ሊግ፦ የፕሪ-ሲዝን ዝግጅታችሁን ጀምራችኋል፤  የልምምዱ ሁኔታ ምን ይመስላል?

ጫላ፦ ዝግጅታችንን የጀመርነው  ሰሞኑን ቢሆንም እስካሁን በቀን ሁለት ጊዜ ነው በመለማመድ ላይ የምንገኘው፤ በእዚሁ የዝግጅት ወቅት ልምምድ ላይም ተጨዋቾች የአሰልጣኙን  ስልጠና ለመቀበል ያላቸው ፍላጎት እና ተነሳሽነታቸው  ደስ የሚል  ሆኖ ስላገኘሁትም  ልምምዱን በጥሩ ሁኔታ እያስቀጠልነው ነው።

ሊግ፦ ወደ ኢትዮጵያ ቡና ለመጫወት አምርተሃልና ከወዲሁ  ምን ምን ነገሮችን አቀድክ?

ጫላ፦ የመጀመሪያው ዓላማዬ እና ግቤ ከፈጣሪ እርዳታ ጋር   በመሆን ክለቡን ከጓደኞቼ ጋር  ሻምፒዮና ማድረግ ነው፤ ከእዛ ባለፈ ደግሞ በግሌ የእዚህ ቡድን ተጨዋች ሆኜም ለብሄራዊ ቡድናችን ለመጠራት ያለኝን አቅም ሁሉ ከቡና ጋር ሆኜ ማሳየትን እፈልጋለሁ።

ሊግ፦  ወደ እግር ኳስ  ተጨዋችነቱ የመጣህበት መ

 

ንገድ ምን ይመስላል?

ጫላ፦  ወደ ኳስ ተጨዋችነቱ ሙያ  የመጣሁት ተወልጄ ባደግኩበት የሻሸመኔ ከተማ ውስጥ ነው። በእዛም የክልል ቆይታዬም  ነው ከልጅነቴ ዕድሜ አንስቶም  ኳሱን ቦርቄ የተጫወትኩበት። በኋላም ላይ ወደ ሻሸመኔ ከተማ ቡድን ውስጥ ገብቼ በቢጫ ትሴራም ልጫወት ቻልኩ።

ሊግ፦ ወደ ኳስ ተጨዋችነቱ ስታመራ ቤተሰብስ ዝም አለ?

ጫላ፦  ያኔ ከኳስ መጫወቴ ውጪ በትምህርቱ በኩልም ጥሩ ነበርኩ፤ በውስጤ ግን ኳስ የመጫወቱ ፍላጎቴ ከፍ ያለ ስለነበር ትምህርቱን ወደ ጎን በመተው  የኳሱን ዓለም ተቀላቀልኩ። ያኔ ወደ ኳሱ ዓለምም ስገባ የቤተሰብ ጫናም ነበረብኝ። አባቴ በተለይ ኳስ እንድጫወት አይፈልግም ነበር። እናቴ ብቻም ናት ትደግፈኝ የነበረችውና በመጨረሻ ግን ያሉትን ጫናዎች ሁሉ ተቋቁሜ ኳስ ተጨዋች ሆንኩ።

ሊግ፦ በቤተሰባችሁ ውስጥ ስንት ወንድም እና እህት አለ?

ጫላ፦ አራት ወንድሞች እና አንድ እህት ነው ያለኝ፤ እኔም የመጨረሻው ልጅ ነኝ።

ሊግ፦ ለመጨረሻ ልጅ የተለየ እንክብካቤ ይደረጋል ይባላል፤ ይሄን አንተ አጋጥሞሃል?

ጫላ፦ የመጨረሻ ልጅ ስትሆን አንድ አንዴ የተለየ እንክብካቤው ይኖራል። ያም ሆኖ ግን የእኛ ቤተሰብ ጋር ስትሄድ በአብዛኛው ሁሉንም በአንድ አይን የማየት ነገር ነው ያለው።

ሊግ፦ ከቤተሰቡ ውስጥ ስፖርተኛው አንተ ብቻ ነህ?

ጫላ፦ አዎን፤ በፊት የሚጫወቱ ልጆች ነበሩ፤ ያም ሆኖ ግን በኳሱ ብዙ ሳይገፉበት ቀሩ።

ሊግ፦ በእግር ኳሱ ወደ ክለብ ተጨዋችነት የመጣህበት መንገድ ምን ይመስላል? ለማን ለማን ቡድኖችስ እስካሁን ተጫወትክ?

ጫላ፦ የእግር ኳስን መጀመሪያ ላይ መጫወት የጀመርኩት በሻሸመኔ ከተማ ውስጥ የክልል ውድድሮች ነበሩና በተስፋ ቡድን ደረጃ ነው። ወዲያውም ለሻሸመኔ ከተማ ቡድን በቢጫ ትሴራ ለመጫወት ወደ ክለቡ አመራሁኝ። ይሄን ጊዜም የኢትዮጵያ ታዳጊ ብሄራዊ ቡድን የተጨዋቾች ምርጫን ያደርግ ስለነበር ለሙከራ ሄድኩና በአሰልጣኝ አጥናፉ ዓለሙ በመመረጥ የታዳጊ ቡድኑን ልቀላቀል ቻልኩኝ። ከእዚህን ጊዜ በኋላ ነው እንግዲህ ችሎታዬን እያሳደግኩኝ በመምጣት የሲዳማ ቡናን እና በመቀጠል ደግሞ  የወልቂጤ ከተማ ክለቦችን በመቀላቀል ለቡድኖቹ ተጫውቼ ያሳለፍኩት።

ሊግ፦ ከእዚህ ቀደም ለኢትዮጵያ የታዳጊ ብሄራዊ ቡድን በመመረጥ ከግብፅ አቻ ጋር በነበረው እና ድል ባደረጋችሁበት ድንቅ ጨዋታ ላይ ለመጫወት ችለህ ነበር፤ ግብ ማስቆጠርም ችለሃል፤ ያኔ ለቡድኑ ስትመረጥ እና ጎል ስታስቆጥርስ የነበረህ ስሜት ምን ይመስላል?

ጫላ፦ ያ ጨዋታ ነው የእኔ የእግር ኳሱ መነሻዬ፤ በወቅቱ እነ አቡበከር ናስር እና ሚኪያስ መኮንንም የነበሩበት ምርጡ ቡድንም ነበር። በእዛም ጨዋታ ላይ ጥሩ ከመንቀሳቀሴ በተጨማሪ የድል ግብንም ላስቆጥር ችያለሁ እና ደስታዬ ከፍተኛም  ነበር።

ሊግ፦ ግብፅን ማሸነፋችሁ እና ወደ ቀጣዩ  ዙር ማለፋችሁ ያልተጠበቀ ነበር?

ጫላ፦ አዎን፤ ምክንያቱም ግብፅ በእግር ኳሱ ትልቅ ሀገር ስለሆነች ነው። እኛ ግን በጊዜው በያዝነው ስኳድ ጥሩ ጥሩ ተጨዋቾችን ስለያዝንና የቡድን መንፈሳችንም /ቲም ስፕሪቱ/ ጥሩ ስለነበር፤ ከእዛ ውጪም በሁሉም ነገር  አይዞህ አይዞህ በመባባልና የአልሸነፍ ባይነትም ስሜት ስለነበር ለውጤታችን እነዚህ ነገሮች ናቸው የረዱን።

ሊግ፦ ግብፅን አሸንፈን ብናልፍም በቀጣዩ ጨዋታ ደግሞ ማሊዎች እኛን አሸንፈው  ከውድድሩ አስወጡን፤ የእዚህ ሽንፈት ምክንያቱ ምንድን ነበር?

ጫላ፦ ከማሊዎች ጋር ስንጫወት በዋናነት ጎድቶን እንድንሸነፍ ያደረገን የአየሩ ሁኔታ ነው። አየሩ በጣም ሞቃት ነበር። ከእዛ ውጪ ከዳኛ ጋር ተያይዞም ፌር ውሳኔዎች ለእኛ አይወሰኑም ነበርና በመጨረሻ ደቂቃዎች ላይ የገቡብን ጎሎች ከውድድሩ አስወጥተውናል።

ሊግ፦ የአየሩ ሞቃታማነት፤ የዳኛ የውሳኔ አሰጣጥ ፌር አለመሆን የሚሉ ነገሮች ኢትዮጵያ ውስጥ ለሽንፈታችን በተደጋጋሚ የሚነገሩ ምክንያቶች ናቸው፤ በእነዚህ ብቻ ነው የተሸነፍነው ማለት ነው?

ጫላ፦ አንዱ ምክንያት ነው አልኩ እንጂ  ሙሉ ለሙሉ የተሸነፍነው በእዛ የአየር ሁኔታ ነው ብቻ አላልኩም። የአየር ሞቃታማነት አንዳንዴ አንተን ቻሌንጅ ያደርግሃል። የእውነት አየሩ ያኔ ይከብድ ነበር። ማሊም የማይካደው የተሻለ እና  ከባድ  ቡድንም  ስለነበርም ነው ያሸነፈን።

ሊግ፦ በግብፅ የታዳጊ  ብሄራዊ ቡድን ላይ ስላስቆጠርከው የመጀመሪያ ኢንተርናሽናል ጎልህ ምን አልክ? ጎሏን ካስቆጠርክ በኋላስ ምን ስሜት ተፈጠረብህ?

ጫላ፦  በሰዓቱ ጨዋታው የኢንተርናሽናል ግጥሚያ እንደመሆኑና ጎሏን ያስቆጠርኩት ደግሞ ለሀገርም ጭምር  ስለሆነ እስከዛሬ ካደረግኳቸው ሌሎች  ግጥሚያዎች ሁሉ  በተለየ  ሁኔታ ነው ቦታ ሰጥቼያት ያገኘዋት ስለሆነ ጎሏ ከፍተኛ ደስታን ትሰጠኛለች። በእዚህ ጨዋታ ላይ እንደ ቡድኑ ሁሉ እኔም ጥሩ የተጫወትኩበት ነው። የቡድን አጋሬ አቡበከር ናስርም የግብፅ ተከላካዮችንና ግብ ጠባቂውን አሰቃይቶ ግብ ያስቆጠረበትም ጨዋታ ነበርና ያኔ ያገኘነው ድል በጣም ጣፋጭም ነበር።

ሊግ፦ የሀገርን ብሄራዊ ቡድን መለያ አድርጎ መጫወት ምን ስሜት ይሰጣል?

ጫላ፦ ትልቁ ነገር እሱ ነው።  አንድ ሀገርን ወክለህ ስትጫወት ባንዲራን አውለብልበህ ስለሆነ ስሜቱ ከባድ ነው። በሰዓቱ ቦታው ላይ ስትገኝ ሁኔታዎቹ ትልቅ ተነሳሽነትንም ነው የሚፈጥርብህና የእዛ አንዱ አካል መሆን መታደልም ነው።

ሊግ፦ በቀጣይነት የዋልያዎቹ ተመራጭ እና ቋሚ ተሰላፊ  ተጨዋች መሆንስ  አልናፈቀህም?

ጫላ፦ ይናፍቃል እንጂ ከፈጣሪ እርዳታ ጋር በአዲሱ ዓመት ላይ ብዙ ነገሮችን ነው  በኢትዮጵያ ቡና ተጨዋችነቴ የምጠብቀው፤  ቡናን ሻምፒዮና ማድረግና በብሄራዊ ቡድን ውስጥ ተመርጬ ደግሞ ስሜን ማስጠራትን በጣም ነው የምፈልገው።

ሊግ፦ ከግብፅ የታዳጊ ብሄራዊ ቡድን  ጋር ስንጫወት የነበረህ ብቃት ታይቶ ወደ ቱኒዚያው ክለብ በፕሮፌሽናል ተጨዋችነት ለመጫወት ለሙከራ  ከሚኪያስ መኮንን ጋር ወደ ስፍራው አምርተህ ነበር፤ እዛ ስለሆነው እና ስላጋጠማችሁ ሁኔታ አንድ ነገር ብቴለን?

ጫላ፦ ለሙከራ የሄድንበት ክለብ ኢቶሆል ደ ሳህል ይባላል። በቱኒዚያ ውስጥ ከሚገኙት ትላልቅ ቡድኖች ውስጥ አንዱ ቡድንም ነበር፤ ለአንድ ወር ሙከራም ነው ወደ ስፍራው ያመራነው። እዛ ከተጓዝንም በኋላ ላመሰግነው እፈልጋለሁ ጋዜጠኛ ሰይድ ኪያር እያንዳንዱ የምንገኝበትን ሁኔታ እንዴት ናችሁ? በምን ሁኔታ ላይ ትገኛላችሁ? አይዘዞአችሁ፤ በርቱ እያለ ስልክ በመደወል ይጠይቀን ነበር። ያም ሆኖ ግን ወደዛ የተጓዝንበት ሁኔታ በአንዳንድ ነገሮች ሳይሳካ ቀርቶ ወደ ሀገር ቤት ልንመለስ ችለናል።

ሊግ፦ ያኔ ወደ ሀገር ቤት ስትመለሱ ምክንያት ሆኖ ከቀረበው ውስጥ እዛ የሚከፈለው ክፍያ ከእኛ ሀገር አንፃር አነስተኛ መሆኑና ኮንትራት የምትፈርሙትም ለረጅም ጊዜ እንደሆነም ተደርጎ ነበር?

ጫላ፦ አይደለም፤ በጊዜው  ወደ እዛ  ከተጓዝን በኋላ እኛን በዋናነት እንዳንጫወት ያደረገን ከአጠገባችን ሆኖ ኮንታክት የሚያደርጉን ሌሎች ሰዎች ስላልነበሩ ነው። ያኔ ከሰይድ ኪያር ውጪ  እኛን በስልክ የሚያገኘን ሌላ ሰው አልነበረም። በእዛ የቱኒዚያው ቆይታችንም ከእሱ ጋርም ቢሆን በእጃችን ላይ ሲም ካርድ  ስላልነበረን ብዙ የመገናኘቱ አጋጣሚም አልነበረንምና ለእዛ ነው ነገሮች ከብደውብን ልንመለስ የቻልነው። ያኔ ኮንታክት የሚያደርገን ብዙ ሰው ቢኖር ኖሮ ጉዞአችን ፌል አያደርግምም ነበር።

ሊግ፦ ለሙከራው ወደ ቱኒዚያ በተጓዛችሁበት ወቅት ከእዛ ቆይታችሁ የተማራችሁት ነገር አለ?

ጫላ፦ አዎን፤ ያኔ ወደዛ ባመራንበት ወቅት ስለ ውጪ ሀገር ወጥቶ መጫ

 

ወት እውቀቱ አልነበረንም። ስላለው ሁኔታም  በሰዓቱ አስቀድሞ  የሚነግረንም ሰው አልነበረንም። ብዙ ነገሮችን በጊዜው የጨረስነውም ራሳችን ተጨዋቾቹ ከቡድኑ ማናጀሮች ጋር እያወራንም ነበር። ለሙከራው የጉዞ ትኬቶቹን ሲልኩልንም ራሳችን አውርተናቸውም ነው የላኩልን። በእዛን ሰዓት ልጅነቱም አለና ብዙ ነገሮችን አናውቅምም ነበር። ያኔ በእዚህ ጉዳይ ዙሪያ ስልጠናዎች ተሰጥቶን ቢሆን ኖሮ የፕሮፌሽናል ተጨዋችነት እልማችንን እናሳካው ነበር።

ሊግ፦ የቱኒዚያውን ክለብ ኢቶሀል ደ ሳህልን ያኔ ሄደህ ስትመለከት የቡድኑን  ፋሲሊቲ እንዴት ተመለከትከው?

ጫላ፦ ትልቅ ቡድን ነው። ብዙ ነገሮች የተሟሉለትም ነው። ከአንድ አልፎ ሰባት እና ስምንት ሜዳም ነው ያላቸው። በሰዓቱ ለእኛ ትንሽ ድጋፍ ቢደረግልን ኖሮ እዛ ለመጫወት የተሻለ ነገሮችን አስብም ነበር።

ሊግ፦ ወደ እዛ ካመራህ በኋላ በብቃት ደረጃ የእነሱን ተጨዋቾች ከእኛዎቹ ጋር ስታነፃፅራቸው እንዴት አገኘካቸው?

ጫላ፦ እነሱ ከታች ይዘውት የሚመጡት ነገር አለ፤ ብዙ ጊዜ ስራዎችን የሚጀምሩት  እዛም ነው። እኛ ሀገር ላይ ደግሞ በእዛ ደረጃ ላይ ሆኖ መስራት  የተለመደ አይደለም። እነሱ ብዙ ድጋፍ አላቸው። ምን ጎደለ? ምን አነሰ? ብሎ የሚጠይቃቸው ብዙ አካል አለ። እነዚህ ነገሮችም ናቸው እነሱን በኳሱ ከፍ ያደረጋቸው እንጂ እኛ ኢትዮጵያኖች ብዙ ስኪል ያላቸው ተጨዋቾች አሉን። እነሱ ያላቸው ይሄ ነገር እኛ ሀገር ላይ ቢሰራ እግር ኳሳችን ከአሁን በተሻለ ጎዳና ላይ መራመድም የሚቻል ይመስለኛል። አሁን ለእዚህ ማሳያ አቡበከር ናስርን ማንሳትም ይቻላል።

ሊግ፦ ከአቡበከር ናስር ጋር አብረህ የመጫወቱን ዕድል አግኝተሃልና ስለ እሱስ አሁን ላይ ወደ ደቡብ አፍሪካው ማሜሎዲ ሰንዳውንስ ሄዶ ስለመጫወቱስ ምን አልክ?

ጫላ፦ ሁለታችን አንድ ላይ የተጫወትነው ለኢትዮጵያ ታዳጊ ብሄራዊ ቡድን በተመረጥንበት ጊዜ በልጅነት ዕድሜያችን ላይ ነበር። ለቡድኑ ስንመረጥና ስንጫወት አብሮ አደጌም እንደመሆኑ  የእሱ ወደ ደቡብ አፍሪካ ተጉዞ ጥሩ መጫወቱ  መንፈሳዊ ቅናት እንዲያድርብኝም አድርጎኛል። ከእዛ ውጪም የአቡኪ እዚህ ደረጃ ላይ ደርሶ ለክለቡ ጎል ማስቆጠር መጀመሩም ሊያስደስተኝም ችሏልና ለእኔም ጊዜው ስላልረፈደ ጠንክሬ ሰርቼ እንደ እሱ ወጥቼ መጫወትን በጣም እፈልገዋለሁ።

ሊግ፦ በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ  ለሲዳማ ቡናና ለወልቂጤ  ከተማ ክለቦች በመጫወት ነው ብዙዎች የሚያውቁህ? ስለቆይታዎችህ ምን ትላለህ?

ጫላ፦ አንዳንዴ በእግር ኳስ ህይወትህ ጥሩ ሆንኩኝ ስትል ጉዳቶች አንተን ወደ ኋላ እንድትቀር እና እንድትሳብ ያደርጉሃል። ከጉዳትህ ድነህ ለማገገምም ብዙ ውጣ ውረዶችም ያጋጥሙሃል። እነዚህ ሁኔታዎች እኔም ላይ ደርሶ ስለነበር የኳስ ህይወቴን ትንሽ ወደ ኋላ ጎትቶብኛል፤ ያም ሆኖ  ግን ወደ ጤንነቱ ከመጣው በኋላ ለሲዳማ ቡና ጥሩ ልንቀሳቀስ ብችልም በአንድ አንድ ነገሮች ሳልስማማ ቀረውና ወልቂጤን በመቀላቀል ጥሩ የውድድር ጊዜያቶችን ለማሳለፍ በቅቻለሁ።

ሊግ፦ በሲዳማ ቡና በነበረህ ቆይታህ ዋንጫ ለማንሳት የተፎካከራችሁበት ጊዜም ነበር?

ጫላ፦ አዎ፤ ያ ቆይታችን መቼም ቢሆን አይረሳኝም፤ መቀለ 70 አንደርታ ዋንጫ ያነሳበት ዘመን ላይ ነበር እኛን ጨምሮ ቅ/ጊዮርጊስም ሌላው የዋንጫው ተፎካካሪ ነበር። እስከ መጨረሻው ጨዋታ ድረስ ጥሩ ልንፎካከርና  ለድሉም እኛ የተሻለው ዕድል ቢኖረንም በጥቃቅን ስህተቶች ነው ዋንጫውን አሳልፈን ለመስጠት የቻልነውና ያ ሁለተኛ ሆነን ሊጉን ያጠናቀቅንበት ጊዜም  የማይረሳኝ ነው።

ሊግ፦ ወደ ወልቂጤ ከተማ ካመራህ በኋላ በጣም ተመችቶህ ነበር ልበል?

ጫላ፦ አዎን፤  ወደ እዛ ተጉዤ ስጫወት ወደ ኋላ ተጎትቶ የነበረውን የኳስ ህይወቴን መልሼ ያገኘሁበትና ከፍ ያደረግኩበት ነው፣ ችሎታዬን  የመለስኩበት እና በቆይታዬም እንደ አዲስ ሆኜ  ጥሩ በመንቀሳቀስ ዳግም የተነሳሁበት ሆኖም ነው ያገኘሁት። ይሄ የማይካድም ነው። በእዚሁ አጋጣሚም በክለቡ ውስጥ ጥሩ ጊዜን ስላሳለፍኩም ለወልቂጤ ከተማ ቡድን ደጋፊዎች እና ለቡድኑ ትልቅ ፍቅር ስላለኝ ሁሉንም የክለቡን ማህበረሰብ ማመስገን እፈልጋለሁ።

ሊግ፦ በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ላይ ስለነበራችሁ የዘንድሮ ተሳትፎ ምን የምትለው ነገር አለ? በምትፈልጉት ሁኔታስ ነው ሊጉን ያጠናቀቃችሁት?

ጫላ፦ የእኛ የውድድሩ እልማችንና ግባችን የነበረው ሊጉን ከ1-5  ባለው ደረጃ ላይ ሆኖ እንዲያጠናቅቅ ነበር፤ ጥሩ ቡድንም ነበረን፤ ያም ሆኖ ግን የአሰልጣኞች መቀያየር ሲበዛ  ነገሮችን በምንፈልገው መልኩ ለማስኬድ ስላልቻልን ሊጉን በስምንተኛ ደረጃ ላይ ሆነን አጠናቀናል።

ሊግ፦ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ በአንተ አንደበት እንዴት ይገለፃል?

ጫላ፦ ይሄ ምንም የማይካድ ነው በሀገራችን እግር ኳስ ላይ ትልቅ መነቃቃትን ፈጥሯል። ዲ ኤስ ቲቪ መጥቶ ጨዋታዎቹ የቀጥታ ስርጭትን ማግኘታቸው ተጨዋቾች ራሳቸውን ለዓለም ለማሳየት ስለሚጥሩና ወደ ውጪ ሀገር ወጥተህ ስለመጫወትም ስለምታስብ ለኳሱ እድገታችን ትልቅ ነገር እየተፈጠረልን ነው ያለው። ይሄንም በአግባቡ ልንጠቀምበትም ይገባል።

ሊግ፦ በእግር ኳስ ጨዋታ ዘመንህ ምርጡ ጨዋታዬ እና ምርጡ ግቤ ብለህ የምታስበው የቱን ነው?

ጫላ፦ ምርጡ ግቤ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ዘንድሮ ስንጫወት በ12ኛው ሰከንድ ላይ ያስቆጠርኳትን ነው። ከእሷ ውጪም በጅማ አባጅፋር ላይ ያገባዋትም ሌላዋ የተለየች ግቤ ናት። ምርጡ ጨዋታዬ የምለው ደግሞ ብዙ ቢኖሩም ሁሌ ግን ከኢትዮጵያ ቡናና ከቅ/ጊዮርጊስ ጋር የምናደርጋቸው ጨዋታዎች የደጋፊዎቹ ድባብ ደስም ይላሉና  ለእኔ የተለዩ እና ምርጥም ጌሞች ናቸው ብዬ ነው የማስበው።

ሊግ፦ በሜዳ ላይ በጣም ፈጣን ተጨዋች ነህ፤ ጫላን ለኢትዮጵያ በመቶ ሜትር ብናስሮጠው የወርቅ ሜዳሊያን ሊያስገኝልን ይችላል የሚሉ አሉ?

ጫላ፦ /በጣም ከሳቀ በኋላ/ እሱን በቦታው ላይ ስሆን ነው መወሰን የምችለው። በጣም ፈጣን ነኝ። አንድ ቀን የመቶ ሜትሩን ሩጫ እሞክረውም ይሆናል።

ሊግ፦ ፍጥነቱ የመጣው በተፈጥሮ ወይንስ?

ጫላ፦ በተፈጥሮ ነው የመጣው። በኋላ ላይ ደግሞ በስራ አዳበርኩትና ፍጥነቴን ከራሴ ጋር ላቆየው ቻልኩኝ።

ሊግ፦ ከእግር ኳሱ ውጪ የእረፍት ጊዜህን በምን ታሳልፋለህ?

ጫላ፦ ብዙ ጊዜ ፊልም በማየት ነው የማሳልፈው። የውሃ ዋናም በጣም ነው የምወደው። በእነዚህ ነገሮችም ነው ጊዜያቶቼን የምጠቀመው።

ሊግ፦ በሻሸመኔ ከተማ ተወልደህ እንደ ማደግህ እዛ ለሚመጣ አንድ ወዳጅህ አንድ ነገርን አስጎብኝ ብትባል ምንን ታሳያለህ?

ጫላ፦ ሻሸመኔ የንግድ ሀገር ናት። የንግድ ሀሳብ ላለው ሰው ብዙ የማስመለክተው ነገር አለና ያን ነው እያወራሁለት የማሳየው።

ሊግ፦ ሙዚቃ ትወዳለህ?

ጫላ፦ ብዙም አይደለሁም።

ሊግ፦ የእግር ኳስን ልጅ ሆነህ ስትጫወት የትኞቹን ተጨዋቾች ተምሳሌት አደረግክ?

ጫላ፦ ያን ጊዜ ተምሳሌቶቼ ያደረግኳቸው ተጨዋቾች ከባህር ማዶ ታታሪ ሰራተኛ በመሆኑ  ክርስቲያኖ ሮናልዶንና ከሀገር  ውስጥ  ደግሞ ሳላህዲን ሰይድን ነው። ሁለቱን ተጨዋቾች በጣምም ነው የማደንቃቸው።

ሊግ፦ ከባህር ማዶ የምትደግፈው ቡድንስ ማንን ነው?

ጫላ፦ ሊቨርፑልን።

ሊግ፦ በእግር ኳስ ተጨዋችነትህ ማሻሻል የምትፈልገው ነገር ምንድን ነው?

ጫላ፦ አንዳንዴ ጎል አካባቢ ስደርስ  የምቸኩለው ነገር አለ፤ ያን ክፍተቶቼን በመጠየቅም ለወደፊቱ የማርማቸው ነገር አለ። ያለኝን ጥንካሬም  አስቀጥዬ በመጓዝ በ2015 የተሻለ የሚባለውን ጫላን ማስመልከትም ዋናው ምኞቴ ነው።

ሊግ፦ የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ዋንጫ አልናፈቀህም?

ጫላ፦ አግኝቼ ስለማላውቅ ይናፍቃል እንጂ። በ2015 ከፈጣሪ እርዳታ ጋር በቡና ይህን እልሜን ለማሳካት እጥራለሁ።

ሊግ፦ ከአመጋገብ ጋር በተያያዘ የተለየ የሚባል የምግብ ምርጫ አለህ?

ጫላ፦ ዶሮ ወጥ በጣም እወዳለሁ።

ሊግ፦ የአለባበስ ምርጫህስ?

ጫላ፦ ማች የሆኑ አለባበሰችን ነው የምመርጠው።

ሊግ፦ ወደ ማጠቃለሉ ስናመራ?

ጫላ፦ ለኢትዮጵያ ቡና ለመጫወት ወደ ክለቡ ማምራቴ የህይወቴ መጨረሻ ነው ብዬ አላስብም፤ በቡና ቡድን የወደፊት ቆይታዬ ከእነሱ ጋር  በኳሱ ለማሳካት የምፈልጋቸው ብዙ ሀሳቦች እና ፍላጎቶች አሉኝ።  ያ እንዳለ ሆኖ እስካሁን ደግሞ በኳሱ ለመጣሁበት መንገድ በህይወቴ ውስጥ ከጎኔ ሆነው ያገዙኝ ብዙ ሰዎች አሉ። ከእነዛም መካከል ሻሽመኔ በነበበርኩበት ሰዓት የፕሮጀክት አሰልጣኜን መስፍን፣ የሻሸመኔ አአሰልጣኝ የነበረውን ያሬድ አበጀን፣ ለታዳጊ ብሄራዊ ቡድን መርጦኝ ያጫወተኝን አሰልጣኝ አጥናፉ ዓለሙን እና በእኔ ህይወት ውስጥ አሻራ የነበራቸውን ሁሉ ማመስገን እፈልጋለሁ።

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P