Google search engine

ፈረሰኞቹ እንግሊዛዊ አሰልጣኝ ቀጠሩ

ፈረሰኞቹ እንግሊዛዊ አሰልጣኝ ቀጠሩ::

ከፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ማኑኤል ቫዝ ፒንቶ ጋር የአንድ ዓመት ቀሪ ግዜ እያላቸው የተለያዩት ፈረሰኞቹ የ62 ዓመቱን ስቴዋርት ጆን ሀል ማስፈረማቸው የክለቡ የፋዊ ገፅ አስታውቋል ::

“አሰልጣኙ በቀደመው ጊዜ የበርሚንግሃም ሲቲ እግር ኳስ አካዳሚ ዳይሬክተር እና የተተኪ ቡድኑ እና ከ18 ዓመት በታች ቡድኑ አሰልጣኝ የነበሩ ሲሆን በርሚግንሐምን ለቀው የህንዱን ፑኔ ሲቲን ከ2007-09 እ.ኤ.አ አሰልጥነዋል፡፡ በ2009 መጨረሻ ሴንት ቪንሰንት እና ግሬናዲያንስ ዋናውን እና ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድንን በአሰልጣኝነት በመያዝ ከ20 ዓመት በታች ቡድኑን በኮንካካፍ ማጣሪያ ቡድኑን ከምድቡ አንደኛ በማድረግ ማሰለፍ ችለዋል፡፡”

አሰልጣኙ ከክለቡ ገፅ ጋር ቆይታ አድርገዋል

“በባንግላዴሽ ቆይታዬ ጥሩ ተከፋይ አሰልጣኝ ነበርኩ በሊጉም ዛሬ እዚህ አስክመጣ ድረስ በ18 ተከታታይ ጨዋታዎች ላይ ሽንፈትን አላስተናገድኩም፡፡ ነገር ግን ለ8 ዓመታት በምስራቅ አፍሪካ በተለያዩ ክለብና ብሔራዊ ቡድኖች ስቆይ ቅዱስ ጊዮርጊስን ማሰልጠን እፈልግ ነበር፡፡ በዚህ ወቅት ከክለቡ ጥያቄ ሲቀርብልኝ ባሳልፈው የምፀፀትበት ውሳኔ ይሆናል ብዬ የልቀቁን ጥያቄ ለክለቤ አቀረብኩኝ እነርሱም መልቀቅ ባይፈልጉም ጥያቄን ተቀብለውኛል፡፡

አዛም (ታንዛኒያ) እያለሁ ብዙ ድሎችን እና ውጤቶችም ማሳካት ብችልም ቡድኔ ደጋፊ አልነበረውም፡፡ አሁን ግን ወደ በርካታ ደጋፊዎች ባለቤት ወደሆነው ቅዱስ ጊዮርጊስ መጥቻለሁ በዚህም ደስተኛ ነኝ”፡፡

ከሴንት ቪንሰንት እና ግሬናዲያንስ ወደ ቀድሞ ቡድናቸው ተመልሰው የህንዱ ፑኔ ሲቲ በውድድር ዓመቱ ምንም ግብ ሳይቆጠርበት ቡድኑን ወደ ዋናው ፕሪሚየር ሊግ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ማሳደግ ችለዋል፡፡ በ2010 እ.ኤ.አ የዘንዚባር ብሄራዊ ቡድን አለቃ ሆነው ተሾሙ፡፡ ብሔራዊ ቡድኑ ታንዛኒያ ላይ ለተካሄደው ለምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ውድድር ይዞ በመቅረብ በግማሽ ፍፃሜ በኡጋንዳ በመለያ ምት ተሸንፈው ከውድድር ወጥተዋል፡፡ አሰልጣኙ ዛንዚባርን ለቀው የታንዛኒያውን አዛምን በመያዝ ቡድኑን በቮዳኮም ፕሪሚየር ሊግ 2ኛ ሆኖ እንዲያጠናቅቅና በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የማፓንዱዚ ዋንጫን እንዲያሸኝፍ አድረገዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በአዛም ቆይታቸው የፍንድሺፕ ዋንጫ ፍፃሜ ተፋላሚ እንዲሆንና በሴካፋ የክለቦች ውድድር ቡድኑ በመጀመሪያ ተሳትፎው ለፍፃሜ እንዲደርስ አድርገውታል፡፡

ከ2 ዓመት ቆይታ በኋላ ከቦርዱ ጋር ባለመስማማታቸው አዛምን ለቀው በ12 መስከረም 2012 እ.ኤ.አ የኬንያውን የተስካር ፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊ ክለብ ሶፋፓካን ተቀላቅለዋል፡፡ ነገር ግን የሶፋፓካ ቆይታቸው ከ7 ሳምንታት አልዘለለም ተመልሰው አዛምን መያዝ ችለዋል፡፡ አሰልጣኙ አዲስ ቡድን በመገንባት ቡድኑ በሊጉ ቀዳሚና እስከ ግማሽ የውድድር ዓመት ምንም ሽንፈት ያላጋጠመው ቡድን መስራት ችለው የነበረ ቢሆንም በ8/ጠቅምት/2013 እ.ኤ.አ ሌላኛውን የታንዛኒያ ክለብ ሲምቢዮን ፓውርን (ዳሬ ሰላም የሚገኘውን የሰንድርላንድ አካዳሚን መቀላቀል ችለዋል፡፡ ልክ እንደ አንድ የስራ ድርሻ የታንዛኒያን ከ17 እና ከ20 ዓመት በታች ቡድኖችን አሰልጥነዋል፡፡

በድጋሚ ወደ አዛም ተመልሰው የሴካፋን የክለቦች ዋንጫ (ካጋሚ ካፕ) ማሸነፍ ችለዋል፡፡ ከአዛም በ2016 ወደ ኬንያው ኤ.ሲ ሌዎፓርድ ለ2 ዓመት በሚቆ የውል ስምምነት ቢቀላቀሉም ከ1 ዓመት በላይ መቆት አልቻሉም፡፡ ከ2018 ጀምሮ የባንግላዴሹን ሳይፍ ስፖርቲንግ ክለብ በማሰልጠን ለ18 ተከታታይ ጨዋታዎች ያለሽንፈት መጓዝ ችለዋል፡፡
አሰልጣኙ የዩኤፋ የአሰልጣኛነትና የአሰልጣኞች አሰልጣኝነት ላይሰንስ ያላቸው ናቸው።

አሰልጣኙ በነገው ዕለት ስራ የሚጀምሩ ሲሆን በዛሬው ዕለት ከቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ስራ አመራር ቦርድ ዋና ፀሀፊ፣ የቡድን መሪ እና ኮቺንግ ስታፍ ጋር ትውውቅ የክለቡ የፋዊ ገፅ አስታውቋል ።”

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

%d bloggers like this:
P