Google search engine

“ፋሲልን በምርጥ ደጋፊዎቹ ፊት ልናሸንፍ ተዘጋጅተናል” ዳንኤል ደምሱ/ኢትዮጵያ ቡና/

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በኢንተርናሽናል ጨዋታዎችና በሌሎች ምክንያቶች መቆራረጥን ካበዛ በኋላ የአራተኛው
ሳምንት ግጥሚያዎች ዛሬ እና ነገ በሚደረጉት 6 ጨዋታዎች የሚቀጥል ይሆናል፤ ከሊጉ ፍልሚያዎ መካከልም
በነገው ዕለት በጎንደሩ ፋሲለደስ ስታዲየም የሚደረገው የፋሲል ከተማ እና የኢትዮጵያ ቡና ጨዋታ ከፍተኛ ትኩረትን
የሳበ ሲሆን ጨዋታውንም በርካታ የፋሲል ከተማ ደጋፊዎችና ከአዲስ አበባ የሚጓዙም የቡና ደጋፊዎች ግጥሚያውን
በስፍራው በመገኘት ያደምቁታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የአራተኛ ሳምንት ጨዋታቸውን ጎንደር ላይ የሚያደርጉት ፋሲል ከተማዎችና ቡናዎች ይህን
ጨዋታ በአሸናፊነት ለመወጣት ሙሉ ዝግጅታቸውን ያጠናቀቁ ሲሆን ከሜዳው ውጪ ከሚጫወተው የቡና ተጨዋቾች
መካከልም አንዱ የሆነው የአማካይ ስፍራው ተጨዋቹ ዳንኤል ደምሱም ግጥሚያውን አስመልክቶ በሰጠው አስተያየት
“ከፋሲል ከተማ ጋር የምናደርገው ጨዋታ ጠንካራ ፉክክር የሚደረግበት ነው፤ ክለቡም ከጠንካራነቱ ባሻገር በምርጥ
ደጋፊዎቹም ፊት ታጅቦ የሚጫወት ነውና ይህንን ግጥሚያ በሜዳቸውና በደጋፊዎቻቸው ፊት ልናሸንፋቸው ተዘጋጅተናል”
በማለት ምላሹን ሰጥቶናል፡፡
የኢትዮጵያ ቡናን እና የፋሲል ከተማን ጨዋታ በማስመልከት እንደዚሁም ደግሞ በቡና ወቅታዊ አቋም ዙሪያ ከቡና
ተጨዋቾች መካከል ዳንኤልን በማናገር የሰጠን ምላሽ የሚከተለውን ይመስላል፡፡
የኢትዮጵያ ቡናን ወቅታዊ አቋም አስመልክቶ
“ኢትዮጵያ ቡና የሊጉ ውድድር ተጀምሮ እስኪቋረጥ ድረስ በአቋሙጥሩ ነበር፤ ውድድሩ በኢንተርናሽናል ጨዋታዎችና
በሌሎች ምክንያቶች ወደ ሌላ ጊዜ ተላለፈ እንጂ ከዚህ የበለጠ ምርጥ ብቃታችንን ለማሳየትም እንችል ነበር፤ ከዛ
ውጪም ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ጋር የነበረንንም ጨዋታ በማሸነፍ እና ሶስት ነጥብን በመያዝ የነጥብ
ድምራችንን ወደ ዘጠኝም እንወስድ ነበርና የጨዋታው መቋረጥ ያን እንዳናሳካው አድርጎናል፤ ያም ሆኖ ግን አሁን ባለን
አቋምም ምንም እንኳን የነገው ግጥሚያችንን የምደርገው ጎንደር ላይ ተጉዘን ከሜዳችን በመውጣት ቢሆንም
ጨዋታው ላይከዚህ በፊት የነበረንን ብቃት አስቀጥለን ለመጓዝ በሁሉም መልኩ ዝግጁ ነን”፡፡
ከፋሲል ከተማ ጋር በነገው እለት ስላላቸው የሜዳቸው ውጪ ጨዋታና ስለሚያስመዘግቡት ውጤት
“ኢትዮጵያ ቡናና ፋሲል ከተማ በጎንደሩ ፋሲለደስ ስታዲየም ነገ የሚያደርጉት ተጠባቂው ፍልሚያ በሁለቱም ቡድኖች
በኩል ጥሩ ዝግጅት የተደረገበት ነው፤ ክለቦቹ ካላቸው ጥንካሬ እና የተፎካካሪነት መንፈስ አንፃርም ጥሩ ጨዋታን
ለደጋፊዎቻቸው እና ለስፖርት ታዳሚው እንደሚያሳዩም አምናለሁኝ፤ ክለባችን ይሄን ጨዋታ የሚያደርገው ከጥሩ
ቡድንና በጣም ምርጥ ደጋፊ ካላቸው ፋሲሎች ጋር ቢሆንም የእኛም ቡድን አሁን ላይ ባለው አቋም ጠንካራና
አስተማማኝም ስለሆነ የነገውን ጨዋታ ከፈጣሪ እርዳታ ጋር እናሸንፋለን”፡፡
የኢትዮጵያ ቡናን ጠንካራና ደካማ ጎን በሚመለከት
“የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ያለፉት ሁለት ጨዋታዎቻችን በድል ብንጀምርም ለውጤታችን ማማር ትልቁ ጥንካሬያችን
የነበረው ኳሱን በከፍተኛ ፍላጎት ለመጫወት በመቻላችን እና ከእዛ ውጪም ኳሱን ተቆጣጥረን መጫወታችን ነው፤
ይሄ አጨዋወት ረድቶናል፤ የሊጉ ጅማሬ ጨዋታ ላይ ያለብንን ድክመት በተመለከተ እስካሁን ለእኔ የታየኝ ነገር ብዙም
የለም”፡፡
የኢትዮጵያ ቡና በእዚህ ዓመት ከአንተ ምን ይጠብቅ?
“ብዙ ነገር ነዋ! ይህንንም ገና ከጅማሪዬ እያሳየውም እገኛለው፤ የኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ክለብን የዘንድሮ የውድድር
ዘመን ላይ ስቀላቀል ቡድኑ ካለው ስምና ዝና አንፃር እንደዚሁም ደግሞ በስሩ ከያዛቸው በርካታና ምርጥ
ደጋፊዎቹበመነሳት ምን ግልጋሎትን ለክለቡ ማበርከት እንዳለብኝ አስቀድሜ ነው የተረዳሁት፤ ለቡና የመጫወት
ፍላጎቴም የቤተሰቦቼ በተለይ ደግሞ የወላጅ አባቴና የራሴምየልጅነት ህልሜ ስለነበር ለዚሁ በብዙዎቹ ለሚደገፍ ቡድን
ውጤታማና ምርጥ ችሎታዬን አሳይቼም ለማለፍ በሁሉም መልኩ ዝግጁ ሆኛለሁ፤ ቡናን እየወደድኩትም ነው
ያደግኩትና ከጓደኞቼም ጋር በመሆንም ጭምር ነው ክለቡን የምጠቅመው”፡፡
የኢትዮጵያ ቡና በሊጉ ምን ውጤት ያመጣል?
“የኢትዮጵያ ቡና ሁሌም ሊጉ ላይ የሚጫወተው ለተሳትፎ አሊያም ደግሞ ጠንካራ ተፎካካሪ ሆኖ ለመጨረስ ሳይሆን
ዋንጫን ለማንሳት ነው፤ ያ ስለሆነም በእዚህ ዓመት ሻምፒዮና የመሆን እቅዳችንን እና ህልማችንን እናሳካለን”፡፡
የኢትዮጵያ ቡናን ደጋፊዎች በተመለከተ
“የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች እግር ኳስንና ክለባቸውን በጣም የሚወዱ እንደዚሁም ደግሞ የስታዲየምም አድማቂዎች
ስለሆኑ ሁልጊዜም ምርጥ እና የሚወደዱ ናቸው፤ በአደጋገፋቸው ስታይልም ለየት የሚሉም ሆኖ ነው ያገኘኋቸው፤
እናየእውነት ለእኔ ወደቡድኑ ከገባሁበት ጊዜ አንስቶ ለሚሰጡኝ ማበረታቻና አድናቆት ከፍተኛ ምስጋናን ነው
የማቀርብላቸው፤ በጣምም አከብራቸዋለው”፡፡
ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የተመረጥከው ቡናን ከተቀላቀልክ በኋላ ነው፤ የመመረጥ እድሉን ስታገኝ ምን አይነት ስሜት
ተሰማህ?
“የኢትዮጵያ ቡና ክለብን በክረምቱ የተጨዋቾች ዝውውር መስኮት ስቀላቀልና ፊርማዬን ሳኖር ዋንኛዬ ዓላማዬ
ካደረግኳቸው ጉዳዮች መካከል ለቡና ጥሩ ከመጫወት ባሻገር ክለቡንም ለውጤት ማብቃትና እንደዚሁም ደግሞ
ለብሔራዊ ቡድንም መመረጥ መቻል ነበርና ልክ ወደ ቡድኑ እንደገባው በክለቡ አሰልጣኝ ዲዲየር ጎሜዝ በመሰልጠን
እሱ በብዙ ነገር ሊለውጠኝ ችሏልና ትልቁን ምስጋና ይወስዳል፤ ከዛ ውጪም የቡድናችን ተጨዋቾችም ሜዳ ላይ ያለኝን
እንቅስቃሴም ሊያቀሉልኝ ስለቻሉም እነሱም ይመሰገናሉ፤ በአጠቃላይ ለብሔራዊ ቡድን በመመረጤ የተሰማኝ ስሜት
ከፍ ያለ ነው፤ በቀጣይ ጊዜው የብሔራዊ ቡድን ምርጫ ደግሞ በተደጋጋሚ ስኳዱ ውስጥ ኖሬ ለሀገሬ ብሔራዊ ቡድን
መጫወት እፈልጋለውና ለዛም ሁሌም ጠንክሬ ነው የምሰራው”፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

%d bloggers like this:
P