Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“ፋሲል ከነማ ምርጥ ቡድን አለው፤ ወደፊትም ከእዚህ በላይ ይጓዛል” “የማንቸስተር ዩናይትድ ደጋፊ ብሆንም በእዚህ ዘመን የቫንዳይክ አድናቂ ነኝ” ያሬድ ባየህ ገብርየ /ፋሲል ከነማ/

 

በመሸሻ ወልዴ /G.BOYS/

የመቐለ 70 እንደርታ የሲዳማ ቡና እና የፋሲል ከነማ ክለቦች የሊጉን ዋንጫ ለማንሳት ዕድሉ ካላቸው ክለቦች መካከል ስማቸው የሚጠቀስ ሲሆን ይሄን ዋንጫ ወደ ቤቱ ለማስገባት መቐለ 70 እንደርታ ከሌሎች ቡድኖች አንፃር የተለየ ዕድልም አለው፤ የሊጉ ውድድር ወደ ወሳኝ ምሕራፍ ላይ እየተሸጋገረ ባለበት የአሁን ሰዓት ዋንጫውን ለማንሳት ዕድሉ ካላቸው ቡድኖች መካከል ለየክለቦቻቸው ጥሩ እየተጫወቱ ከሚገኙት ተጨዋቾች መካከል ከፋሲል ከነማ ያሬድ ባየህን እና ከመቐለ 70 እንደርታ አሌክስ ተሰማና አናግረናቸው ምላሻቸውን እንደሚከተለው ሰጥተውናል፤ ተከታተሏቸው፡፡

ሊግ፡- ለፋሲል ከነማ በመጫወት በየሜዳው በምታሳየው ጥሩ የመከላከል እንቅስቃሴ ከፍተኛ አድናቆትን እያተረፍክ ይገኛል፤ ኢትዮጵያ ቡናን በተፋለማችሁበትም የሰኞው ዕለት ጨዋታ በድጋሚ ለክለብህ ጥሩ ብቃትህን አሳይተሃል፤ በዚህ እና በሚሰጥህ አድናቆቶች ዙሪያ የምትለው ነገር ካለ?

ያሬድ፡- በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በተከላካይ ስፍራው ላይ መጫወት ከጀመርኩበት ጊዜ አንስቶ በሜዳ ላይ በማሳያቸው አበረታችና እና ጥሩ የሆኑ የጨዋታ እንቅስቃሴዎቼ በየጊዜው የሚሰጡኝ አድናቆት እና ሙገሳዎች ለእኔ ከፍተኛ ብርታትን ያስገኙልኝ ናቸው፤ የስፖርት አፍቃሪውም በሚሰጠኝ የሞራል እና የማበረታቻ ድጋፍም በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡
የፕሪምየር ሊጉ የውድድር ተሳትፎዬ ላይ እኔ እነዚህን አድናቆቶች ማግኘት የጀመርኩትም በፕሪምየር ሊጉ ደረጃ የእግር ኳሱን ለዳሽን ቢራ ክለብ ስጫወት ጀምሮም ነው፤ በየጊዜውም የሚሰጠኝ የማበረታቻ ድጋፍም ችሎታዬ ላይ እለት ከእለት ላመጣሁት ለውጥም ከፍተኛ አስተዋፅኦም አበርክቶልኛልና በዚህ አድናቆት ተበረታትቼ ከእዚህ በፊት የነበርኩበትን የብሄራዊ ቡድን ዳግም ለመቀላቀል እና ለአገሬም ብሄራዊ ቡድን ከእኔ የሚጠበቅብኝን ውጤታማ ግልጋሎትን ለመስጠት ራሴንም በጥሩ ብቃት አዘጋጃለው፡፡
ከእዚያ በተረፈ የፋሲል ከነማ ክለብ ውስጥ በአሁን ሰአት በሊጉ ሜዳ ላይ በማሳያቸው ጥሩ የጨዋታ እንቅስቃሴዎች በሰኞው ጨዋታ እኔን ላሞገሱኝ የቡና ደጋፊዎችም ሆነ የሁሉም ክለብ ደጋፊዎች ከፍተኛ ምስጋናዬን ለመግለፅም እፈልጋለሁ፡፡

ሊግ፡- የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ውስጥ በአሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ የኃላፊነት ዘመን ላይ በመመረጥ ተጫውተህ ነበር፤ ከዛ ጊዜ በኋላ ግን ለዋልያዎቹ አልተመረጥክም ለምን? ለብሄራዊ ቡድኑ አትመጥንም ማለት ነው?

ያሬድ፡- ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንማ በሜዳ ላይ ለክለቤ በማሳየው ወቅታዊ ብቃቴ በደንብ አድርጌ ነው የምመጥነው፤ ያም ሆኖ ግን ለዋልያዎቹ ለምን አልተመርጥክም ለሚለው ጥያቄ የእኔ ምላሽ የሚሆነው ለክለቤ ጥሩ መንቀሳቀስ ብችልም የብሄራዊ ቡድናችንን በሃላፊነት ለማሰልጠን የሚረከቡት አሰልጣኞች የየራሳቸው የጨዋታ ፍልስፍና ስላላቸው አንዱ ኳስን ይዞ መጫወትን ሌላኛው ደግሞ በተቃራኒው የረጅም ኳስ /ሀይ ቦልን/ የመጠቀም ነገርን የሚመርጡ ስለሆነ ከሁለት አንዱን በሚመርጡት የጨዋታ ፍልስፍና በአንዱ ላልመረጥ ችያለሁ፤ ከዛ ውጪ ደግሞ ምንአልባትም በአሰልጣኞቹ እይታ ከእኔ የተሻለ ተጨዋችንም ስለመረጡ የብሄራዊ ቡድኑ ውስጥ ሳልገኝ ቀርቻለሁ፤ ሌላው ለብሄራዊ ቡድን አልተመረጥኩም ብዬ የማስበው ጎን ደግሞ በአንድ ወቅት ጉዳትም አጋጥሞኝና ከሜዳም ርቄ ስለነበር ምንአልባት ለዛም ሊሆን ይችላል ብዬም አስባለሁ፡፡

ሊግ፡- ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ካለህ ጥሩ ብቃት አንፃር ሳትመረጥ ስትቀር አይከፋህም?

ያሬድ፡- በፍፁም አይከፋኝም፡፡ ምክንያቱም ከላይ እንደገለፅኩት ያልተመረጥኩት አሰልጣኙ ለሚፈልገው የጨዋታ ፍልስፍና ከእኔ ይልቅ ሌሎችን ተጨዋቾች መርጦ ሊሆን ስለሚችል እና እኔ ደግሞ ሁልጊዜም ቢሆን የአሰልጣኞችን የጨዋታ ፍልስፍና የማከብር አይነት ተጨዋች ስለሆንኩ እና የእኔን የአጨዋወት ፍልስፍና የሚወድ አሰልጣኝ ሲመጣ ደግሞ ለሀገሬ ብሄራዊ ቡድን እንደምመረጥ ስለማውቅ ጥሩ ብቃት ኖሮኝ አሰልጣኞች ባይመርጡኝም ምንም አይመስለኝም፤ የአሁን ሰአት ላይ ግን ካለኝ ወቅታዊ አቋም የተነሳ በየቱም የጨዋታ ፍልስፍና ለዋልያዎቹ መመረጤ አይቀሬ ነው፡፡

ሊግ፡- በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በሜዳ ላይ በምታሳያቸው የጨዋታ እንቅስቃሴዎች አንተ እንዴት የምትገለፅ ነህ? ምን አይነትስ ተጨዋች ነህ?

ያሬድ፡- በፋሲል ከነማ ክለብ ውስጥ ብቻ ሳይሆን ከእዚያ በፊትም በነበረኝ የጨዋታ ዘመኔ እኔ በሜዳ ላይ የምገለፅባቸው ነገሮች ብዙ ናቸው፡፡ ከእነዚያ ውስጥም የተወሰኑትን ልጥቀስ ይኸውም በመከላከሉ ላይ ኳስን ይዤ የምጫወት መሆኔ፣ ጊዜዬን /ታይሚንጌን/ ጠብቄ ከአጥቂዎች ላይ ኳስን ባለኝ ፈጣን የአህምሮ ፍጥነትና ንቁነት ከባላጋራ ቡድን ተጨዋቾች ላይ የምነጥቅ ተጨዋች መሆኔ፣ ከአጥቂዎች ጋርም ብዙ የማልታገል እና በብልሀትም የምጫወት መሆኔ እንደዚሁም ደግሞ የመከላከል አጨዋወታችን ላይ ኳስን ከኋላ በመመስረት እና ከጓደኞቼም ጋር የአንድ ሁለት ቅብብልን በማድረግ ኳሱን ወደፊት ይዤ በመሄድ የአማካይ ክፍሉን እና የአጥቂውን ክፍልም ለመርዳት የምተጋ ተጨዋች መሆኔ እና በመጨረሻም አልሸነፍ ባይነቴ እኔን ይገልፀኛል ብዬ ነው የማስበው እና ይሄንን ተሰጥቶዬን ወደፊትም አጠናክሬ እቀጥልበታለሁ፡፡

ሊግ፡- በእግር ኳስ ጨዋታ ዘመንህ በጣም የምታደንቀው ተጨዋች ማን ነው?

ያሬድ፡- የኢትዮጵያ እግር ኳስ ላይ ከሆነ ከተመለከትኳቸው ተጨዋቾች ውስጥ በሜዳ ላይ በሚያሳያቸው የጨዋታ እንቅስቃሴዎች በጣም የማደንቀው ተጨዋች ቢኖር ደጉ ደበበን ነው፤ ደጉ ጥሩ እና ምርጥ ተጨዋች ነው፤ እንዴት መከላከልም እንዳለበት በደንብ ያውቃል፡፡
የባህር ማዶ እግር ኳስ ላይ ደግሞ በጣም የማደንቃቸው ተጨዋቾች ምንም እንኳን የማንቸስተር ዩናይትድ ደጋፊ ብሆንም የአሁን ሰአት ላይ በሚያሳየው ብቃት የእኔ ምርጡ ተጨዋች ሆላንዳዊው የሊቨርፑሉ ተከላካይ ቫንዳይክ ነው፤ ቫንዳይክ አስገራሚ እና የሚስብ ችሎታም ያለው ተጨዋች ነውና እሱን ሞዴሌም አድርጌ እወስደዋለሁ፤ ከቫንዳይክ በመቀጠል ሌላ የማደንቀው ተጨዋች የፒ ኤስ ጂውን ተከላካይ ቲያጎ ሲልቫን ነው፡፡

ሊግ፡- የማንቸስተር ዩናይትድ ደጋፊ ነኝ ብለሃል፤ በአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የረቡዕ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ የምትደግፈው ቡድንህ ከባርሴሎና ጋር ያደረገውን ጨዋታ እንዴት ተመለከትከው?

ያሬድ፡- የማንቸስተር ዩናይትድ ቡድንን የደገፍኩት እና የወደድኩት የድሮውን እና በአሌክስ ፈርጉሰን ይመራ የነበረውን ቡድን ነው፤ አሁን ላይ ግን ኳስን ብዙም አላይም እና ረቡዕ እለት ስለነበረው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ግጥሚያውን ስላልተመለከትኩት ምንም የምልህ ነገር አይኖርም፡፡

ሊግ፡- የእግር ኳስ ተጨዋች መሆንህ ምን አይነት ስሜትን ሰጥቶህ አልፏል? ደስተኛስ ነበርክ?

ያሬድ፡- የእግር ኳስ ሙያው /ፕሮፌሽኑ/ እኛ አገር ላይ አለመከበሩ ምንም እንኳን ያበሳጨኝ እንጂ ኳስ ተጨዋች በመሆኔ ግን በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡ የእግር ኳሱ ተከብሮ ብንጫወትበት ደግሞ አስበው ደስታዬ ምን ሊሆን እንደሚችል፤ የእግር ኳሳችን ያልተከበረው እና የማያድገው በሁሉም አካላቶች ዘንድ ስራን ስላልሰራንበት ነው፤ ከዛ ውጪም ኳሱን ለማሻሻል ምንም አይነት ጥረቶችም አልተደረጉም፤ እንደ ውጪዎቹ እግር ኳሱን ሊያሳድግልን የሚችለውን ተጨማሪ ነገሮችንም አንሰራም፤ የስራ በዓላችንም ልክ አይደለምና ከዛ በመነሳት ለወደፊቱ የኳስ ለውጣችን ጥሩ ነገር ብንሰራ በጣም ደስ ይለኛል፡፡

ሊግ፡- የእግር ኳስን መጫወትህ ላይ ቤተሰብ አካባቢ ተፅህኖዎች ነበሩብህ?

ያሬድ፡- በፍፁም፤ በቤተሰቦቼ አቅራቢያ የእግር ኳስን እንዳልጫወት ብዙም የሚባል ተፅዕኖ አልነበረብኝም፤ በአንድ ወቅት ላይ ብቻ እህቴ መዓዛ ትምህርቴ ላይ እንዳተኩር በሚል መጫወቴን ትቃወም ነበር፤ በኋላ ላይ ግን የእኔን ጥሩ ደረጃ ላይ መድረስ ስታይና መለወጤንም ስታውቅ መቃወሙን ትታለች፤ ከእዛ ውጪ የእኔ ቤተሰቦች ኳስን እንድጫወት በጣም ነበር የሚያበረታቱኝ፤ ኳስ እየገዙልኝ እንድጫወት ያበረታቱኝና ይደግፉኝም ነበርና በእዚሁ አጋጣሚ እነሱ ሊመሰገኑ ይገባል፡፡

ሊግ፡- ከቤተሰቡ አባላት ውስጥ የእግር ኳስን የምትጫወተው አንተ ብቻ ነህ? ስንት ወንድምና እህትስ አለህ?

ያሬድ፡- በቤተሰባችን ውስጥ የእግር ኳስን የምጫወተውም ስፖርተኛውም እኔ ብቻ ነኝ፤ ሶስት እህቶች አሉኝ፤ ብቸኛው ወንድ ልጅም እኔ ነኝ፡፡

ሊግ፡- የእግር ኳስን የት የት ክለቦች ተጫውተህ አሳለፍክ? እነዚያን ጊዜያቶችስ በምን መልኩ ነው የምትገልፃቸው?

ያሬድ፡- የእግር ኳስን ከህፃንነት እድሜዬ አንስቶ ተወልጄ ባደግኩበት የባህር ዳር ከተማ ላይ መጫወት ብጀምርም በክለብ ደረጃ የተጫወትኩባቸው ቡድኖች የመጀመሪያው የባህር ዳሩ ሴንትራል ዩንቨርስቲ ክለብ ነው፤ በዛ ቡድን ያኔ እነ አሸናፊ ግርማም ነበሩ፤ ከክለቡም ጋር ለአንድ ዓመት ያህል ከቆየሁ በኋላ ወደ ባህርዳር ከተማ ክለብ ገባሁ፤ እዛም አንድ አመት ተጫወትኩና ቡድኑን ለቀቅኩ፤ በመቀጠልም ወደ አማራ ውሃ ስራዎች /አውስኮድ/ ቡድን በመግባት ለሁለት ዓመት ከተጫወትኩ በኋላ ሌላ የተጫወትኩባቸው ቡድኖች ከጥቂት አመታት በፊት ለፈረሰው የዳሽን ቢራ ክለብ እና አሁን እየተጫወትኩበት ላለው የፋሲል ከነማ ቡድን ነው፡፡
የእግር ኳስን ተጫውቼ ስላሳለፍኩባቸው ያለፉት ጊዜያቶች እኔ ማለት የምፈልገው በሁሉም ቡድን ውስጥ ጥሩ የሚባል ቆይታ እንደነበረኝ ነው፤ በተለይ ለዳሽን ቢራ ክለብ ስጫወት በሁለት ወራት የጨዋታ ጊዜያት ውስጥ በሜዳ ላይ የነበረኝን የጨዋታ ብቃት ተመልክቶ አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ እኔን ለብሄራዊ ቡድን የመረጠበት ጊዜ ነበርና ይሄን እድል በማግኘቴ በጣም ደስተኛ ነበርኩ፡፡

ሊግ፡- የእግር ኳስ ህይወትህ ፈጣን ነው ማለት ይቻላል?

ያሬድ፡- አዎን፤ በፕሪምየር ሊጉ ላይም ሆነ በታችኛው ሊግ ደረጃ ኳስን ለብዙ አመታት አልተጫወትኩም እና አሁን የደረስኩበትንና የምገኝበትን ስፍራ ስመለከት እድገቴ ለእኔም ሆነ ሌሎች ለሚያውቁኝ ፈጣን ነው፤ በየአመቱ በልምድም ሆነ በሜዳ ላይ በማሳየው አቋም ጥሩ መሻሻልንም በማሳየት እድገትን እያመጣሁም ነውና ይሄ በራሱ የተለየ የደስታ ስሜትም በውስጤ እንዲፈጠረብኝም አድርጓል፡፡

 

ሊግ፡- የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች በተደጋጋሚ “ገብርየ” ብለው ሲጠሩህ ሰማን፤ በስያሜውም እያሞገሱክ ይገኛልና ገብርየ ለምን አሉህ? የቡድናችሁ ሌላው ተጨዋች አይናለም ኃይሉም ሌላው ገብርየ ተብሎ የሚጠራ ተጨዋች ነውና ገብርየ ተብላችሁ ስትጠሩ ከሁለታችሁ ቀድሞ አቤት የሚለው ተጨዋች ማን ነው?

ያሬድ፡- የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች በሜዳ ላይ በማሳየው ጥሩ የሆነ የጨዋታ ብቃትም ሆነ በአይበገር አጨዋወቴ ሁሌም ከጎኔ በመሆን የሚያበረታቱኝ ናቸውና ገብርየ የሚለውን መጠሪያ ስም የሰጡኝ በእንግሊዝ እና ኢትዮጵያ አድርገውት በነበረው ጦርነት ጊዜ የአፄ ቴዎድሮስ ቀኝ እጅ እና የጦር መሪ የነበረው ገብርየ ነበርና እኔም እንደእሱ ቁርጠኛ ደፋርና አይበገሬም ስለሆንኩ ነው ስሙን ያወጡልኝ እና ሊያበረታቱኝ የቻሉት፤ በዚሁ ስም እንዳልከው አይናለም ኃይሉም ይጠራበታል፤ ለአይናለም ይሄ ስም የወጣለት ዳሽን ቢራ በነበረበት ጊዜ በዳሽን ቢራ ደጋፊዎች ነው፤ ስለዚህ አሁን ላይ ሁለታችንም ገብርዬዎች ነን ማለት ነው፡፡ ገብርየ ሲባል ማን ቀድሞ አቤት ይላል ላልከኝ ብዙ ጊዜ ስያሜው የሚጠራው በሜዳ ውስጥ ሆነን ነውና ይሄን ጥያቄ የምመለሰው አይደለም፡፡

ሊግ፡- የፋሲል ከነማ ክለብ ውስጥ ከአይናለም ጋር እስካሁን አብረህ ተጣምረህ ተጫውተህ ታውቃለህ? እሱን እንዴትስ ነው የምትገልፀው?

ያሬድ፡- በፋሲል ከነማ ክለብ ውስጥ ከአይናለም ጋር እሱ ጉዳት ላይ ስለነበርና አሁን ላይ ደግሞ ገና ወደሜዳ ስለተመለሰ እስካሁን አብሬው የመጫወት እድልን አላገኘውም፤ ከዚህ በፊትም እሱ ወደ እኛ ቡድን ሲመጣ እኔም ተጎድቼ ስለነበር ያኔም ከእሱ ጋር የመጫወት እድሉን አላገኘሁምና ይሄ አጋጣሚ የሚገርመኝ ነው፡፡
የቡድናችንን ተከላካይ አይናለምን በተመለከተ እኔ እሱን የምገልፀው በጣም ጥሩ ልጅ መሆኑን ነው፤ ይመክረኛል፣ ልምዱን ለሁሉም ተጨዋች ያካፍላል፤ ጥሩ መሪም ተጨዋች ስለሆነ እሱን የማከብረው ተጨዋች ነው፡፡

ሊግ፡- የፋሲል ከነማን የሊግ ጉዞ እንዴት ነው የምትመለከተው? ከቡና ጋር የነበራችሁንስ ጨዋታ በምን መልኩ ትገልፀዋለህ?

ያሬድ፡- የፋሲል ከነማ የሊግ ጉዞው በሜዳ ላይ ከምናሳየው ጥሩ የጨዋታ እንቅስቃሴ አንፃርና ተጋጣሚዎቻችንንም በኳስ ቁጥጥር እየበለጥን ከመውጣታችን አኳያ ስመለከተው ያመጣነው ውጤት እኛን ፈፅሞ የሚገልፀን አይደለም፡፡ ያም ቢሆን ግን ጠንካራና ጥሩ ቡድን አለን፤ አይቼ የማላውቀውም አይነት የቡድን መንፈስ ስላለን ቡድናችንን አሁን ላይ የምገልፀው በጥሩ መልኩ ነው፤ ከዛም ውጪም ጥሩ የተጨዋቾች ስብስብም ስላለን በቀሪ የሊጉ ጨዋታዎቻችን ላይ ያለንን አቅም አሟጠን በመጫወት ጥሩ ውጤት ለማምጣት ጥረትን እናደርጋለን፡፡
የኢትዮጵያ ቡና ጋር ስለነበረን ጨዋታ መናገር የምፈልገው ግጥሚያውን እኛ ማሸነፍ የነበረብን ቢሆንም በሜዳ ላይ የታየው የጨዋታ ፉክክር ጥሩ ነበር፤ ክለባችን ያገኛቸውን የግብ አጋጣሚዎች አለመጠቀሙ ብቻ ጨዋታውን እንዳያሸንፍ አድርጎታል፡፡

ሊግ፡- ፋሲል ከነማ በሊጉ መሪ መቐለ 70 እንደርታ በ9 ነጥብ በመበለጥ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ከመቀመጡ አኳያ ዋንጫውን የማንሳት እድሉ የቱን ያህል ነው?

ያሬድ፡- የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ተሳተፎአችን ላይ በደረጃው ሰንጠረዥ ምንም እንኳን በመሪው ክለብ በ9 ነጥብ ተበልጠን በ3ኛ ደረጃ ላይ እንገኝ እንጂ ሊጉ ገና ብዙ ግጥሚያዎች ያሉት ከመሆኑ አኳያ ዋንጫውን የማንሳት እድሉና ተስፋው አሁንም አለን ለዛም የቀሪ ግጥሚያዎቻችን ላይ ካሉን ብዙም ከባድ ያልሆኑ ጨዋታዎች አኳያ የነጥብ ልዩነቱን ማጥበብ እንችላለን፡፡ ከእዛ በተጨማሪም በሜዳችን ላይ ከእነሱ በተሻለ እኛ ያሉብን ግጥሚያዎች ብዙም የሚከብዱም ስላልሆኑና ከሜዳ ውጭ ደግሞ እነሱ ከበድ ያሉ ግጥሚያዎችም ስላሉባቸው በእዚያ ውጤታማ ሆነን እና አጋጣሚውንም ተጠቅመን የሊግ ዋንጫውን ለማንሳት እድላችንን እንሞክራለን፡፡

ሊግ፡- ፋሲል ከነማ በሊጉ ያለው ጠንካራ ጎን እንደዚሁም ደካማ ጎን ምንድነው?

ያሬድ፡- የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የዘንድሮው የውድደር ዘመን ተሳትፎአችን ላይ ሰሞኑን ከቡና ጋር ስንጫወት እንደተጠበቅነው ባንሆንም ቡድናችን ያለው ጠንካራ ጎን ኳስን ተቆጣጥሮና ፐሰስ አድርጎ መጫወቱ ነው፤ ከእዛ ውጪም ቡድናችን ኳስን ይዞ ከመጫወት ባሻገር ከፈለገም እንደተጋጣሚህ ቡድን እንቅስቃሴም ከኳስ ጋር የተያያዘም አግሬሲቭ አጨዋወትንም ሊጠቀም ይችላልና ይሄ ሊጠቅመን ችሏል፡፡
የፋሲል ከነማ ክለብ ውስጥ በደካማነት የማነሳው ጎን ቢኖር በግብ ማስቆጠሩ ላይ የአጨራረስ ችግር አለብን፤ ጨራሽ አጥቂ የለንም፤ አሁን በዛ ቦታ ላይ የሚጫወተው የተከላካይ ስፍራው ተጨዋች ሙጂብ ቃሲም ነው፤ እሱ ሁለገብ ተጨዋች በመሆኑ በዚህ ቦታ ተጫውቶ 5 ግቦችን አስቆጥሯል፤ አስበው በቦታው ላይ እውነተኛ አጥቂ ቢኖረን ደግሞ ከ5 ግቦች በላይም ልናስቆጥር የምንችልበት እድልም ነበረንና በአጨራረስ ላይ ያለብን ክፍተት እኛን ከጎዱን ነገሮች ውስጥ የሚጠቀስ ነው፡፡

ሊግ፡- የእግር ኳስን ስትጫወት የምትደሰተው እና የምትከፋው ምን ጊዜ ነው?

ያሬድ፡- ብዙ ጊዜ የምደሰተው ጨዋታዎችን ስናሸንፍ ነው፤ ያ ደስታዬ ደግሞ ልዩ የሚሆነው ጨዋታውን ዝም ብለን ስላሸነፍን ሳይሆን ተጋጣሚያችንን በኳስ ቁጥጥርም በልጠን እና አሳምነን ስንረታ እና የእግር ኳስ አፍቃሪውንም ሆነ ደጋፊዎቻችንን በጨዋታው ከሜዳ ተደስተው እንዲወጡም ስናደርግ ነውና በኳሱ ህይወቴ ይሄ ነው ለእኔ የተለየ የደስታ ስሜትን የሚፈጥርልኝ፡፡
በእግር ኳሱ ብዙ ጊዜ የምከፋው ደግሞ ውጤት ሳናመጣ ስንቀር ነው፤ በተለይ በዳኝነት ግልፅ የሆነ በደል እና ተፅዕኖ ተደርጎብን ስንሸነፍ ሳይ በጣም ያበሳጨኛልና ይሄ ነው የእኔ መከፋት፡፡

ሊግ፡- በእግር ኳሱ ላይ ምን አይነት አጨዋወት ያስደስትሃል?

ያሬድ፡- በኳስ ጨዋታው ላይ እኔን ሁሌም የሚያስደስተኝ የአገራችን የኳስ አፍቃሪ በሚደሰትበት መልኩ አንድ ቡድን በአንድ ግጥሚያ ላይ ጥሩ የጨዋታ ፉክክርን ከተጋጣሚው ቡድን ጋር አድርጎና ጨዋታውንም በኳስ ቁጥጥር ላይ ባመዘነ መልኩ ተጫውቶና ተመርኩዞ ከሜዳ ሲወጣ በጣም ደስ ይለኛል፤ የእኛም ቡድን እንዲህ አይነት ጨዋታን ስለሚጫወት ነው ደስ የሚለኝ፤ የእግር ኳስን ስትጫወት ብዙ ጊዜ ህዝቡን የሚያስደስት አጨዋወትን በሜዳ ላይ ልታሳይ ይገባል፡፡ ህዝቡን በኳስ ካላስደሰትከው ኳሱ ምንም ጥቅምም ትርፍም የለውም፡፡ ወደፊት ይህ ሲቀጥልም ክለቦችም ደጋፊዎችም ከሜዳ እየሸሹም ሊሄዱ ይችላሉና በዚህ ላይ ለእግር ኳሱ ልንጠነቀቅለት ይገባል፤ የእግር ኳስ ጨዋታ ደግሞ ያለ ደጋፊ ምንም አይደለም፤ በደከመው ኳስ ላይ ይሄን ህዝብ ከሜዳ ማራቅ ስለለሌብንም ሁላችንም በጋራ ኳሱ ላይ ልንሰራም ነው የሚገባን፡፡

ሊግ፡- የባህር ዳር ከተማ አንተን በኳሱ ያፈራች ክልል ናት፤ እስኪ ግለፃት?

ያሬድ፡- ባህር ዳር ምርጥና ደስ የምትል ሃገር ናት፤ ለመኖርም የምትመች ነች፤ የውሃ መዋኛ ስፍራም አላት፤ ከዛ ውጪ እንደ ሌሎች ከተሞች ተራራ ያልሆነችና ብዙም የእግር ኳስ መጫወቻ ሜዳ ያላት ስለሆነች እና ተጨዋቾችንም በማፍራት ላይ የምትገኝ የትውልድ ክልሌ ስፍራ ስለሆነች እሷን የምገልፃት በጥሩ መልኩ ነው፤ ባህርዳርን በጣም የምወዳት ከተማም ነችና በኳሱም ከእዚሁ ክልል በመውጣቴ በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡

ሊግ፡- የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች በአንተ አንደበት እንዴት ነው የሚገለፁት?

ያሬድ፡- የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች በሚሰጡን ድጋፍ ልዩ ናቸው፤ በአጨፋፈራቸውም ትገረማለህ፤ እነሱ 12ኛ ተጨዋቾቻችንም ናቸው፤ በእነሱ ታጅበህ ስትጫወትም ልዩ የደስታ ስሜት ይሰማሃልና ሁሌም ሞተውም ቢሆን ሊደግፉክ የተዘጋጁትን እነዚህን ደጋፊዎች በጣም ማመስገን እፈልጋለሁ፡፡

ሊግ፡- የእግር ኳስን በተከላካይ ስፍራው እየተጫወትክ ይገኛል፤ በሌላስ ቦታ ተጫውተህ ታውቃለህ?

ያሬድ፡- አዎን፤ የእግር ኳስን ተከላካይ ሆኜ ከመጫወቴ በፊት የመሀል ተጨዋች ነበርኩ፤ ያም ሆኖ ግን የባህር ዳር ከተማ ክለብ ውስጥ በነበርኩበት ሰአት የቡድናችን አሰልጣኝ የነበሩት መቶ አለቃ ጌታቸው ጨቡዴ ናቸው /የቀድሞ የኢትዮጵያ ቡና አሰልጣኝ ነበሩ/ በተከላካይ ስፍራው ላይ የሚጫወት ሰው ሲጠፋ ጊዜ እኔን በእዛ ቦታ ላይ አሸጋሽገው በማስገባት አጫወቱኝና ከዛም ጊዜ በኋላ ነው በሜዳ ላይ ጥሩ ስሆን ጊዜ ተመልክተው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች እንድሆን ያደረጉኝ፡፡

ሊግ፡- በእግር ኳሱ ቆይታህ ቀጣይ ላይ ያለህ እቅድ ምንድነው?

ያሬድ፡- የእግር ኳሱ ተሳትፎዬ ላይ ወደፊት ትልቅ ደረጃ መድረስ የምፈልግ ተጨዋች ነኝ፤ ከዚህ በመነሳትም በቀጣይነት ተፈላጊነቴን በጣም ጨምሬ በፕሮፌሽናል ተጨዋችነት ለመጫወት እና ከዛ ውጪም ለሌሎችም ታላላቅ ክለቦችም መጫወትን እፈልጋለው እና ያን ለማሳካት ከፍተኛ ጥረትን ነው የማደርገው፡፡

ሊግ፡- የፋሲል ከነማው አሰልጣኝ በስልጠናው የተለየ ነው?

ያሬድ፡- አዎን፤ እኛን በደንብ ተረድቶናል፤ በጥሩ መልኩ ስለተረዳንም ኳስን ፐሰስ አድርገን እንድንጫወት የሚሰጠን ስልጠና ጠቅሞናል፤ ቡድናችንም ውጤታማ እየሆነ የመጣውም እሱ በሚሰጠን ጥሩ ስልጠናም ነውና ቡድኑን እስከአሁን በኃላፊነት ከመሩት አሰልጣኞች መካከል ውበቱ አባተ ለእኔ በስልጠናው ለየት ብሎብኛል፡፡

ሊግ፡- በመጨረሻ…

ያሬድ፡- በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውስጥ ኳስ መጫወቱ ላይ በፍጥነት የአሁን ሰአት ላይ ለደረስኩበት ደረጃ የቅድሚያውን እና የጥርጊያውን በር የከፈተልኝ ሰው ቢኖር ኢንተርናሽናል አልቢትር ሀይለየሱስ ባዘዘው ነበር፤ እሱ ባህር ዳር ውስጥ ኳስ በምጫወትበት ሰአት ጥሩ አቅም እንዳለኝ ያውቅ ነበርና ከክልል ወጥቼ መጫወት የምፈራበት ሰዓት ላይ እሱ እያደፋፈረኝ ወጥቼ እንድጫወት ስላደረገኝ ዛሬ ለደረስኩበት ደረጃ አግዞኛልና ላመሰግነው እፈልጋለው፤ ከእሱ ውጪም የቤተሰቦቼ ድጋፍም የላቀ ነበር፡፡ በመቀጠል አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌም ለብሄራዊ ቡድን ለመጀመሪያ ጊዜ ሲመርጠኝ ያለኝን አቅም እንዳውቅ ያስቻለኝ ባለሙያ ስለሆነ እሱንና የፋሲል ከነማ ደጋፊዎችን በጣሙን ለማመስገን እፈልጋለሁ፡፡

PHOTO CREDIT-KEBRA Z GONDER

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P