Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

ፋሲል ከነማ አራት ጨዋታዎች እየቀሩት የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ሻምፒዮና ሆነ“በዲ.ኤስ.ቲቪ የኢትዮጵያ እግር ኳስ መተላለፍ በጀመረበት ዓመት ላይ ጣፋጩን ድል ስለተጎናፀፍን እድለኞች ነን”“ፋሲል ከነማ ዘንድሮ ብቻ ሳይሆን ባለፉት ዓመታትም ዋንጫ የሚገባው ቡድን ነበር” አሰልጣኝ ስዩም ከበደ

ፋሲል ከነማ አራት ጨዋታዎች እየቀሩት የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ሻምፒዮና ሆነ

“በዲ.ኤስ.ቲቪ የኢትዮጵያ እግር ኳስ መተላለፍ በጀመረበት ዓመት ላይ ጣፋጩን ድል ስለተጎናፀፍን እድለኞች ነን”

“ፋሲል ከነማ ዘንድሮ ብቻ ሳይሆን ባለፉት ዓመታትም ዋንጫ የሚገባው ቡድን ነበር”

አሰልጣኝ ስዩም ከበደ

ፋሲል ከነማ ዛሬ 4 ሰዓት ላይ ከወልቂጤ ከተማ ጋር ጨዋታውን በሐዋሳ ዩንቨርስቲ ሜዳ ላይ ቢያደርግም የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ ማንሳቱን አረጋግጧል፤ ፋሲል ከነማ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ይህን ዋንጫ ያገኘውም ተከታዩን ኢትዮጵያ ቡናን በ14 ነጥቦች በልጦ በሚገኝበት ሁኔታ ላይ ሲሆን አራት ጨዋታዎች እየቀሩት ሻምፒዮናነቱንም ያገኘበት ውጤትም ሪከርድ ሆኖም ተመዝግቧል፡፡

የፋሲል ከነማ ሻምፒዮናነትን ተንተርሰን ከቡድኑ አሰልጣኝ ስዩም ከበደ ጋር አጠር ያለ ቆይታን አድርገናል፤ ተከታተሉት፡፡

የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ሻምፒዮና በመሆናቸው ስለተፈጠረበት ስሜት

“የውድድር ዘመኑ ሲጀመር አንስቶ ነው ይሄ ዋንጫ ለቡድናችን በጣም አስፈላጊ መሆኑን ስላወቅን ጠንክረንና ተግተን በመስራት የልፋታችንን ውጤት ለማግኘት የቻልነው፤ ለፋሲል ይሄ የሊግ ዋንጫ እንዳለው ጥንካሬ ባለፉት ተከታታይ ሁለት ዓመታቶች ይገባው ነበር፤ ከእነዛ መካከልም አንዱን ሊጉን እየመራን በነበርንበት ወቅት ላይ የኮቪድ ወረርሽኝ ወደ አገራችን በመግባቱና ውድድሩም ከጤና አንፃር በመቋረጡ ያን ስኬት ልናጣው ችለናል፤ ዘንድሮ ግን ባለን ቡድን ሁሉንም ክለቦችና የስፖርት አፍቃሪውን ባሳመነ መልኩ ጭምር ድሉ ይገባችዋል ተብለን የቤትኪንጉ ፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮና ለመሆን በቅተናልና ይሄን ስኬት በታሪክ ለአንድም ጊዜ የሊጉና ዋንጫ ባላነሳው ቡድን ውስጥ ልጎናፀፍ ስለቻልኩ በጣም ደስ ብሎኛል”፡፡

ኢትዮጵያ ቡና ከወላይታ ድቻ ባደረገው ጨዋታ ላይ ነበር አቻ መለያየታቸውን ተከትሎ ሻምፒዮናነታችሁን ያወጃችሁትና በዲ.ኤስ.ቲቪ እንደተመለከትናችሁ የአንተም ሆነ በተለይም ደግሞ የቡድን መሪያችሁ ሀብታሙ ዘዋለ ደስታ ለየት ያለ እንደነበር እና ስልክ ይዞ ማን እንደደወለለት

“ፋሲል ከነማ ሻምፒዮና መሆኑን ያረጋገጠበት ጨዋታ ምንም እንኳን ገና አራት ጨዋታዎች ከፊቱ እየቀሩትና ከእነዚህ ግጥሚያዎች ውስጥም አንድ ነጥብን ብቻ በሚፈልግበት ሁኔታ ላይ ቢሆንም ኢትዮጵያ ቡና ከወላይታ ድቻ ያደረገውን ጨዋታ አቻ በመለያየቱ እና ተከታዩን ቡናም በ14 ነጥብ በመብለጡ ከወዲሁ የውድድሩ የበላይነቱን አረጋግጧል፤ በጨዋታው ሻምፒዮና  መሆናችንን ካወቅን በኋላም እኔና ሀብታሙ ዘዋለ ደስታችንን ሳቅ በተሞላበት እና ስሜታዊነትንም ባሳየንበት ሁኔታ ልንደሰት የቻልነው ይሄ ቡድን ከዚህ ቀደም የሊግ ዋንጫን ካለማንሳቱ ጋር በተያያዘ የምትጓጓው ነገር ስለነበርና መጨነቅና መጠበቡም ስላለ ከዛ መነሻነትም ነው ደስታችን ሊታይ የቻለው፤ ሀብታሙን በተመለከተ ያሳየው የደስታ አገላለፅ እሱ ለዚህ ክለብ ትልቅ ሰው እና ቀላል የሚባል የቡድን መሪም ስላልሆነ ነው፤ ቡድኑን ለ13 ዓመታት ያህል መርቶታል፤ ለአሰልጣኞች ስራን የሚያቀል የቡድን መሪ ነው፤ ለተጨዋቾች ጥሩ ከበሬታ ኖሮት በጥሩ መንገድ እንዲጓዙም የሚያደርግ ነው፤ ከዛ ውጪም እንደ ድልድይ ሆኖ ክለቡን ከቦርዱ ጋር በብዙ ነገሮች እንዲገናኙ በማድረግ ትልቁን ስራ እያከናወነም የሚገኝ በመሆኑ ለክለቡ ካለው ጥልቅ ፍቅር በመነሳትም ነው ስሜታዊ ሆኖ ደስታውን አስገራሚ በሆነ የደስታ አገላለፅም ሊገልፅ የቻለው፡፡ ወደ እኔ ስመጣ አዎን ስልክ በመደዋወል ጭምርም ነበር ፈገግ እያልኩ ስደሰት የነበርኩት፤ ስልኩ የተደወለልኝም በሐዋሳ ዩንቨርስቲ ስታድየም የኢትዮጵያ ቡናንና የወላይታ ዲቻን ጨዋታ ከቡድናችን አባላቶች ውስጥ ሁለታችን ማለትም እኔና ሀብታሙ ብቻ እንከታተል ስለነበርን ተጨዋቾቻችን ናቸው ደውልው ደስታቸውን መግለፅ ጀምረው ነበርና እንኳን ደስ አላችሁ በማለት ጥሩ ምኞታቸውን የገለፁልን”፡፡

ወዳረፉበት ሆቴል ካመሩ በኋላ ስላጋጠማቸው ነገር

“ፋሲል ከነማ ይሄን የሊግ ዋንጫ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ያገኘ እንደመሆኑና ይህን ድል ለመጎናፀፍም ብዙ መስዋትነቶች ስለተከፈሉበትም ልክ ወደ ሆቴል ደርሰን እንደተመለከትነው የቡድናችን አጠቃላይ አባላቶች በከፍተኛ ፈንጠዝያ ላይ ሆነው ነው ያገኘናቸው፤ በደስታው ግማሹ እምባ እየተናነቀውና እያለቀሰ አንድአንዱም ድምፁ በተዘጋበት ሁኔታ ላይም ሆኖ እየጨፈረ አንዱን ከአንዱ መለየትም ያልተቻለበት ሁኔታም ነው የነበረው፤ ቀኑ ልዩ ከመሆኑ የተነሳ ረዘም ላሉ ደቂቃዎችም ሲጨፈር ነበርና እኛም እነሱን ተቀላቅለናቸው ደስታችንን በሚገርም ሁኔታ ልንገልፅ ችለናል”፡፡

በአንተ አሰልጣኝነት ዘመን ፋሲል ከነማ ይህን የሊግ ዋንጫ ለመጀመሪያ ጊዜ ስለማንሳቱ

“ከፋሲል ከነማ ጋር ይህን የሊግ ዋንጫ ለመጀመሪያ ጊዜ ማግኘት መቻሌ ለእኔም ሆነ ለቡድናችን በብዙ ነገሮች እድለኛ እንድንሆን ነው ያደረገን፤ ፋሲል ይህን ዋንጫ ያነሳው የሀገራችን እግር ኳስ በመላው ዓለም በዲ.ኤስ.ቲቪ መተላለፍ በጀመረበት ዘመን ላይና ሁሉም የስፖርት አፍቃሪዎችም በቤታቸው ሆነው በሚከታተሉበት ጊዜ ውስጥም ስለሆነ ለእኛ ቡድን ድልና ስኬት እንደዚሁም ደግሞ ምርጥ ቡድንነት ተስማምቶ ምስክርነቱን የሰጠበትም ስለሆነ በዛ ሻምፒዮና ለመሆን ችለናል”፡፡

ሻምፒዮና መሆናችሁ ተረጋግጧል፤ በቀጣይነት ስለምታደርጉት ጨዋታዎች

“የእኛ ቡድን የውድድር ዘመኑ ሻምፒዮና መሆኑን ያረጋግጥ እንጂ  በቀጣይ በሚኖሩት ጨዋታዎች ላይም ያለውን የቡድን ቅርፅ እና ክብሩን ጠብቆ በመጓዝ ነው ቀሪ ጨዋታዎቹንም በማሸነፍ አኩሪ ውጤትን ለማስመዝገብም የሚታገለው፤ በዚህ የጨዋታ ቆይታዎች ጊዜም የቡድናችን አጥቂ ሙጂብ ቃሲም ለኮከብ ግብ አግቢነት እየተፎካከረም ስለሆነ እሱ ያንን ክብር እንዲያገኝና የመጫወት እድልንም ብዙ ያላገኙ ልጆችንም በመጠቀም የውድድር ዘመኑን ማጠናቀቀቅ እንፈልጋለን”፡፡

በመጨረሻ…

“ፋሲል ከነማ ከትልቅ ቡድንነቱ አንፃር በሀገር ውስጥም ሆነ በባህርማዶ ባሉት ደጋፊዎቹ በመመራት ይህን የሊግ ዋንጫ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊያነሳ በመቻሉ ከፍተኛ ደስታ ሊሰማኝ ችሏል፤ ይሄ ቡድን ድሉን እንዲጎናፀፍም የብዙዎች አሻራም ይገኝበታል፤ ከእነሱ ውጪም ከዚህ በፊት ቡድኑን በመደገፍ እስከመቁሰልና እስከመሞት ደረጃ ላይም የደረሱ ስላሉ ለዚህ ቡድን ታሪክ ለለፉ የቀድሞም ሆነ የአሁን ደጋፊዎች እንደዚሁም ለቡድኔ ተጨዋቾች፣ ለኮቺንግ ስታፎቼ እና ለቦርድ አመራሮችም ከፍተኛ ምስጋናን ማቅረብ እፈልጋለው”፡፡

 

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P