ፋሲል ከነማ ጋናዊውን የመቀሌ 70 እንደርታ አጥቂ ኦሴይ ማዊሊን አስፈርሟል ።
ባለፈው ዓመት ከመቐለ 70 እንደርታ ጋር ጥሩ የውድድር ዓመት ያሳለፈው የሰላሳ ዓመቱ ጋናዊ አጥቂ ዛሬ በይፋ ለፋሲል ከነማ የአንድ ዓመት ኮንትራት ውል በመፈረም አፄዎቹን ተቀላቅሏል ።
ባለፈው የውድድር ዓመት በሁነኛ የአጥቂ ክፍል ተጫዋች እጥረት የተቸገሩት ዐፄዎቹም ቀደም ብለው የናይጀርያዊው አጥቂ ኢዙ አዙካ ውል ማራዘማቸው ሲታወስ ጋናዊውን አጥቂ መፈረም በቦታው አማራጭ ያሰፋላቸዋል ተብሎ ይገመታል።