Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“ፕሪምየር ሊጉን በሻምፒዮናነት የምናጠናቅቅበት እድላችን ሰፊ ነው”ያሬድ ከበደ /መቐሌ 70 እንደርታ/

በመሸሻ ወልዴ /G.BOYS/

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን ለሚመራው የመቐሌ 70 እንደርታ እግር ኳስ ክለብ በአጥቂው ስፍራ ላይ የሚጫወተው ያሬድ ከበደ በዘንድሮው የፕሪምየር ሊጉ የውድድር ተሳትፎአቸው ክለባቸው ዋንጫውን የሚያነሳበት እድሉ ሰፊ እንደሆነ አስተያየቱን ለሊግ ስፖርት ጋዜጣ ድረ-ገፅ ሰጥቶ ከአማኑኤል ገ/ሚካኤልም ጋር በመጣመር እየተጫወቱ ያለበትን ሁኔታም እንደወደደው ገልፃል፡፡
የመቐሌ 70 እንደርታው ያሬድ ከበደ በአጭር ጊዜ የእግር ኳሱ ህይወቱ ወደ መቐሌ 70 እንደርታ ክለብ ገብቶ የመጫወት እድልን አገኛለሁ ብሎም ፈፅሞ እንዳልጠበቀም ለሊግ ስፖርት ጋዜጣ ድህረ ገፅ ተጨማሪ አስተያየቱን የሰጠ ሲሆን በአሁን ሰአት ላይ ደግሞ በቋሚ ተሰላፊነት ለመቐሌ 70 እንደርታ ቡድን እየተጫወተ መሆኑም ከፍተኛ የደስታ ስሜት በውስጡ እንደፈጠረበትም ሀሳቡን አክሎ ገልጿል፡፡
የመቐሌ 70 እንደርታ እግር ኳስ ክለብ በሊጉ የውድድር ተሳትፎው የአሁን ሰአት ላይ አንድ ተስተካካይ ጨዋታ እየቀረው ተከታዩን ክለብ ሲዳማ ቡናን በሁለት ነጥብ ልዩነት በመብለጥ ሊጉን እየመራ ሲሆን የአንደኛው ዙርንም በመሪነት ማጠናቀቁን አረጋግጧል፤ የመቐሌ 70 እንደርታን የውድድር ዘመን ተሳትፏአቸውን አስመልከቶ በራሱ የተጨዋችነት ህይወት ዙሪያ እና ሌሎችንም ጥያቄዎች በማንሳት ከክለቡ ተጨዋቾች መካከል ከአጥቂው ያሬድ ከበደ ጋር ቆይታ አድርገናል፤ ተጨዋቹም ምላሹን እንደሚከተለው ሰጥቷል፡፡
ሊግ፡- ወደ እግር ኳስ ተጨዋችነቱ የመጣከው የት አካባቢ ተወልደህ በማደግ ነው?
ያሬድ፡- የእኔ ውልደቴም እድገቴም በአድዋ አካባቢ በሚገኘው ራማ በሚባለው ስፍራ ነው፤ ቦታው በሌላ አጠራሩም መረብለፈም ይባላል፤ በኤርትራ ቦርደር አካባቢም ነው ተወልጄ በማደግ ኳስን መጫወት የጀመርኩት፡፡
ሊግ፡- የእግር ኳስን የተጫወትክበት የመጀመሪያ ክለብህ መቐሌ 70 እንደርታ ነው?
ያሬድ፡- አይደለም፡፡ የእግር ኳሱ የመጀመሪያው ክለቤ አክሱም ከተማ ነው፤ እዛም ለአንድ ዓመት ተጫወትኩና ቡድኑን ክጓደኞቼ ጋር ወደ ከፍተኛ ሊግ እንዲገባ አደረግኩ፤ በኋላም ላይ የማሳየውን እንቅስቃሴ የተመለከተው የመቐሌ 70 እንደርታው አሰልጣኝ የነበረው ጌታቸው ዳዊት በጣም ስለፈለገኝ ከክለቡ ጋር ተስማምተን መቐሌን ተቀላቀልኩኝ፤ ከ2009 ዓ/ም ጀምሮም የቡድኑ ተጨዋች ሆንኩ፤ በመቀጠልም መቐሌን ወደ ፕሪምየር ሊጉ ስላስገባነው በጣም ነው የተደሰትኩት፡፡
ሊግ፡- በታዳጊነት ዕድሜህ ላይ እያለህ የእግር ኳስ ተጨዋች እሆናለሁ ብለህ አስበህ ነበር?
ያሬድ፡- አዎን፤ ያኔ የእግር ኳስን በጣም ነበር የምወደው፤ ኳስ ተጨዋች መሆንም የልጅነቴ ህልሜም ነበር፤ በጊዜው ታዲያ አካባቢያችን ቦርደር ከመሆኑ የተነሳ ብዙ ኳስ የሚጫወቱ ልጆች ባይኖሩም እዛ እኔን ያዩኝ ሰዎች አንተ ጥሩ ተጨዋች ነህ፤ በኳሱም የተሻለ ደረጃ ላይ ትደርሳለህ ሲሉኝ ጠንክሬ ሰራሁና በፈጣሪ እርዳታ ይሄን እልሜን አሳካሁት፡፡
ሊግ፡- ቤተሰባችሁስ በአንተ የእግር ኳስ መጫወት ላይ ፍላጎት ነበራቸው?
ያሬድ፡- ፈፅሞ አልነበራቸውም፤ እነሱ ኳስ እንዳልጫወት ከመፈለግ የተነሳ በቤተሰቤ በኩል ጫናው ነበረብኝ፤ በትምህርትህ ላይ ትኩረት ማድረግ አለብህ፤ ኳሱ ምንም አያደርግልህም፤ ምንም አይጠቅምክም ነበር የሚሉኝ፤ ተማሪ ሳለሁም በሃይስኩል ደረጃ ትግራይ ውስጥ የመላው የትምህርት ቤቶች ውድድር ይካሄድ ነበርና እዛም ተደብቄ ሄጄ ስጫወት ከወላጅ አባቴ ጋርም እየተጣላሁም ነበር ያደግኩት፡፡
ሊግ፡- ወደ መቐሌ 70 እንደርታ መግባትህ ለአንተ ታምር እንደሆነብህ ገልፀሃል፤ ያን ያልከው ከምን መነሻነት ነው?
ያሬድ፡- የእውነት ነው፤ ወደ ክለቡ መግባቴ ያልጠበቅኩት ስለነበር ነው ታምር የሆነብኝ፡፡ የእግር ኳስን ለአክሱም ከተማ ክለብ በምጫወትበት ጊዜ እኔ የምኖርበት አካባቢ ቦርደር በመሆኑና ብዙ ቦታዎችንም የማላውቅ ስለነበር ከአካባቢ መራቅ እፈራ እና ከዚህ ቡድን ወጥቼም ወደ ሌላ ቡድን አመራለው ብዬ አስቤም ስላልነበር እንደዚሁም ደግሞ ወደ መቐሌ 70 እንደርታ ክለብ ውስጥ በመግባት በፕሪምየር ሊግ ደረጃ እጫወታለው በሚልም ለአንድም ቀን ቢሆን አልሜም ሆነ አስቤም አላውቅም ነበር፤ የኳስ ህይወቴንም ለአክሱም ከተማ ክለብ በመጫወት አጠናቅቃለው ብዬም ነበር የጠበቅኩትና ወደ መቐሌ በመግባቴ የተገረምኩትና የተደሰትኩት ለእዛ ነው፡፡
ሊግ፡- ከመቐሌ 70 እንደርታው አማኑኤል ጋር ያላችሁን ጥምረት እንዴት ትገልፀዋለህ?
ያሬድ፡- በመቐሌ 70 እንደርታ ቆይታችን ከአማን ጋር ለሶስት ዓመት ያህል አብረን ብንጫወትም የሁለታችንን በጋራ ሆነን የምንጫወትበትን ጥምረት አሁን ላይ በተደጋጋሚ እውን ያደረገው ግን አሰልጣኝ ገብረ መድህን ሀይሌ ነው፤ ቀደም ሲል በነበረው የክለቡ ቆይታዬ ከአማን ጋር የተጫወትኩበት አጋጣሚዎች ቢኖሩም አምና በነበረው አሰልጣኝ ዩሃንስ ሳህሌ የኃላፊነት ዘመን ላይ ግን ብዙ የመሰለፍ እድል ስላላገኘው አብረን ብዙ ልንጫወት አልቻልንም፤ ይሄ ደግሞ የአሰልጣኝ ውሳኔ ስለሆነ ተቀብዬዋለው፤ የአሁኑ አሰልጣኝ ገብረመድህን ደግሞ ጥሩ አሰልጣኝ ስለሆነና በእኔ ላይም እምነት ስለጣለብኝ እያጫወተኝ ይገኛል፤ ከአማን ጋርም ጥሩ ተጣምረን ይገኛል፤ አማንንም በጣም የማደንቀው አጥቂም ሆኖልኛል፡፡
ሊግ፡- ለመቐሌ ከተማ እስካሁን ስንት ግቦችን አስቆጠርክ? የእግር ኳስ ህይወትህንስ በቀጣይ ጊዜ የት ለማድረስ አስበካል? ወደፊት ከአንተስ ምን ይጠበቅ….?
ያሬድ፡- ለመቐሌ ከተማ ክለቡን ከተቀላቀልኩበት ጊዜ አንስቶ እኔ ያስቆጠርኳቸው ግቦች ብዛት 15 ናቸው፤ ወደፊት ችሎዬን በማሻሻል ከዚህ በላይም በርካታ ግቦች እንዲኖሩኝ እፈልጋለው፤ በእግር ኳሱ ወደፊት ልደርስበት የምፈልገው ደረጃ ከፍተኛ ነው፤ በእግር ኳሱ ሀገሬን በጣም ማገልገል እና ትልቅ ደረጃ ላይም ደርሼ ታሪክን መስራት እፈልጋለሁ፡፡ በፕሪምየር ሊጉም ላይ በሚኖረኝ የቀጣይ የውድድር ዘመናቶች ቆይታዬም በርካታ ግቦችን እያስቆጠርኩ የሀገሪቱ ኮከብ ግብ አግቢ መባልም እፈልጋለው፡፡
ሊግ፡- የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን በምን ውጤት ታጠናቅቃላችሁ?
ያሬድ፡- የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመጀመሪያ ዙር ውድድርን ከሁሉም ክለቦች በተሻለ ጥሩ አቋምን ይዘን በመቅረባችን መሪ ሆነን አጠናቀናለን፤ የሁለተኛው ዙር ውድድራችንንም ቀደም ሲል የያዝነውን የአሸናፊነት መንፈስ በማስቀጠል ፕሪምየር ሊጉን በሻምፒዮናነት የምናጠናቅቅበት እድላችን ሰፊ ስለሆነ ይህን እልማችንን እናሳካለን፤ ለእዚህ የሚያደርስም ሙሉ አቅም አለን፡፡

ሊግ፡- የእግር ኳስን ስትጫወት የአንተ ተምሳሌት እና ሞዴልህ ማን ነው? ስንት ወንድም እና እህትስ አለ…የእረፍት ጊዜህንስ በምን ታሳልፋለህ?
ያሬድ፡- የእረፍት ጊዜዬን የማሳልፈው ከቤተሰቦቼ ጋር ነው፤ ሁለት እህት እና አንድ ወንድምም አለኝ፤ በእግር ኳሱ የእኔ ሞዴል የሆነው ተጨዋች ለብሔራዊ ቡድን በተደጋጋሚ ጊዜ ሲጫወትም ስላየሁት ሳህላዲን ሰይድን ነው፤ እሱን በጣም ነው የማደንቀው፡፡
ሊግ፡- የፕሪምየር ሊጉ ላይ የክለባችሁ ጠንካራ እና ደካማው ጎን ምንድን ነው?
ያሬድ፡- የውድድሩ ተሳትፎአችን ላይ እኛ ያለን ጠንካራው ጎን የማሸነፍ ሜንታሊቲያችን በጣም ከፍ ያለ መሆኑ ሲሆን፤ ከዛ ውጪም አንድነታችን እና ፍቅራችን የተለየ ነው፤ ልምምድ ስንሰራም በከፍተኛ ሞራል ነው፤ በዚህ በኩል ኮቺንግ ስታፉም በጣም እያገዘን ይገኛል፤ የደጋፊዎቻችንም ድጋፍና ብርታትም ከጎናችን አለና ይሄ አሁን እየተጓዝንበት ላለው መንገድ በጣም ጠቅሞናል፤ የክለባችንን ድክመት በተመለከተ አሁን ላይ ብዙ የለም፤ በውድድሩ መጀመሪያ ላይ ግን ወደ ክለባችን የመጡ አዳዲስ ልጆች ስለነበሩም ከእነሱ ጋር በፍጥነት መዋሀዱ ላይ ተቸግረን ነበርና ያ ተስተካክሏል፡፡
ሊግ፡- በመጨረሻ….
ያሬድ፡- የእግር ኳስ ተጨዋች የመሆን እልምና ፍላጎቴን በማሳካት ዛሬ ላይ ለደረስኩበት ደረጃ የረዱኝ ብዙ አካላቶች አሉ፤ በቅድሚያ ወደ ኳሱ እንድመጣ ያደረገኝ የመጀመሪያው ሰው ጓደኛዬ አድኃኖም ገብረ ኪዳን ነው፤ ለእሱ ታላቅ ምስጋናን አቀርበለታለው፤ ወደ እግር ኳሱ ጠልቄ ከገባው በኋላ ቤተሰቦቼ እና አሰልጣኝ ጌታቸው ዳዊትም ለእኔ ጥሩ ነገርን አድርገውልኛልና እነሱም ሊመሰገኑ ይገባል፡፡
የአሁን ሰዓት ላይ ደግሞ በሚሰጠኝ ምርጥ ስልጠና በችሎታዬ ከነበረኝ አቅም በላይ የበለጠ እንድለወጥ ያደረገኝ አሰልጣኝ ገብረ መድህን ኃይሌ ነውና እሱንም በጣም ማመስገን እፈልጋለው፤ ሌሎች የማልረሳቸው ደግሞ ምርጥ ድጋፍ የሚሰጡንን የክለባችንን የመቐሌ 70 እንደርታ ደጋፊዎችን ነው፤ እነሱንና የክለቤ አጋር ጓደኞቼን በጣም ማመስገን እፈልጋለው፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P