Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“ፕሪምየር ሊጉን የተቀላቀልነው በልፋታችን፣ በላባችን እና በጠንካራ ስራችን እንጂ በሌላ ምንም ነገር አይደለም” አሰልጣኝ ክፍሌ ቦልተና /ሰበታ ከተማ/



ሊግ፡- የአሰልጣኝ ክፍሌ ቦልተናው ሰበታ ከተማ የምድቡ መሪ ሆኖ የፕሪምየር ሊጉን ተቀላቅሏል፤ ድሉ ይገባዋል?
አሰልጣኝ ክፍሌ፡- በጣም! ይህን ለማረጋገጥ ደግሞ ከእኔ ይልቅ የምድባችንን ሁሉንም ተወዳዳሪ ክለቦች መጠየቀም ይቻላል፤ በተለይም የቅርብ ተፎካካሪዎቻችን የሆኑት የለገጣፎ ለገዳዲ እና የኢትዮ ኤሌክትሪክ ክለቦችም ይህንን ምስክርነታቸውንም በጣሙን ሊሰጡህም ይችላሉና ሰበታ ከተማ የፕሪምየር ሊጉን የተቀላቀለው በሜዳውም ከሜዳውም ውጪ ጥሩ ተጫውቶ፤ የሁሉንም ደጋፊ አስጨብጭቦ እና ስለቡድናችንም የድል ተገቢነት በመሴጅ ጭምርም ነው ተልኮለት ይገባቸዋልም ሊባልለት የቻለው፡፡
ሊግ፡- የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን ለመቀላቀል የቻላችሁበት ዋንኛው ጥንካሬያችሁ ምን ነበር?
አሰልጣኝ ክፍሌ፡-በዋናነት በክረምቱ ወራት ለእኔ የተሰጠኝ የስራ ነፃነት ነው የጠቀመኝ፤ የስራ ነፃነቱ ተጨዋቾቼንም ሆነ በስራ የሚያግዙኝን የቴክኒክ ኮሚቴዎችን እንድመርጥ ስላስቻለኝ ከአዳማው የዝግጅት ጊዜ ጀምሮ ስራዬን በተቃና መንገድ እንዳስጉዝ ስላደረገኝ ነው ሰበታን ወደ ፕሪምየር ሊጉ እንዲያልፍ ያስቻልኩት፡፡
ሊግ፡- ሰበታ ከተማን ወደ ፕሪምየር ሊግ ለማሳለፍ የተሰጠኝ የስራ ነፃነት ጠቅሞኛል ብለሃል፤ በዛ ውስጥ አንተ የነበረህ የተጨዋቾች የአመላመል እና የአመራረጥ ሁኔታ እንዴት ነበር?
አሰልጣኝ ክፍሌ፡- የሰበታ ከተማ እግር ኳስ ክለብን ወደ ፕሪምየር ሊጉ እንዲቀላቀል ለማስቻል በክረምቱ ወራት የነበረው የእኔ የተጨዋቾች የአመላመል ሁኔታ ከዚህ ቀደም በተለያዩ ክለቦች ውስጥ የማውቃቸው እና ያሰለጠንኳቸው፤ እነዚህም ተጨዋቾች በነበሩበት ቡድን ውስጥ ክለቦቻቸውን ወደ ፕሪምየር ሊግ ያሳለፉ ተጨዋቾችን ነው የመረጥኩት፤ የዘንድሮው ቡድኔ ላይ ቀደም ሲል የጅማ ከተማ ቡድን አሰልጣኝ በነበርኩበት ወቅት ከቡድኑ ጋር እስከመጨረሻው ሰዓት ድረስ አብሬ ባልጓዝም እኔ አሰለጥነው የነበረው እና በኋላም ላይ ከክለቡ ጋር በመቆየት ጅማን ወደፕሪምየር ሊግ እንዲያልፍ ያደረገው እንደ እነ ናትናኤልና በፋሲል ከነማ ቡድን ውስጥም ደግሞ እንደ እነ ታደለ እና ከዚህ ቀደም ደግሞ ወደ ኢትዮጵያ ቡና ዋና ቡድን ያሳደግኩት እና በኋላ ላይ ደግሞ የፋሲል ከነማ ክለብን ወደፕሪምየር ሊግ እንዲያልፍ እና በፕሪምየር ሊግ ደረጃም የተጫወተው እንደ እነ ይስሃቅ መኩሪያ የመሳሰሉትን ተጨዋቾች በሁለተኛው ዙር ያስመጣንበትም ሁኔታ አለና እነዚህ ሊጠቅሙን ችለዋል፡፡
ሊግ፡- ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ለማለፍ በነበራችሁ የከፍተኛው ሊግ የውድድር ቆይታ ጠንካራ እና ክፍተት ጎናችሁ ምን ነበሩ?
አሰልጣኝ ክፍሌ፡- በቅድሚያ የሰበታ ከተማን ጠንካራ ጎን ለመፍጠር በማሰብ የውድድር አመቱ መጀመሪያ ላይ ለተጨዋቾቼ አንድአንድ ነገሮችን ነግሬያቸው ነበር፤ እነዚህም በከፍተኛው ሊግ የውድድር ተሳትፎ እያንዳንዱ ተጨዋች ስለሚያገኘው ደመወዝ ብቻ በማሰብ ህይወቱን መለወጥ እንደማይችል እና ከዛ ይልቅ ስራውን አክብሮ እና ጠንክሮ ሰርቶ ይሄን ቡድን ወደ ፕሪምየር ሊግ በማሳለፍ በጣም ተጠቃሚ እና ተፈላጊም የሚሆንበትን ነገር መፍጠር መቻል እንዳለበት ነው፤ ለዚህ ደግሞ ሁሉም ተጨዋች ዲሲፕሊን መሆንም እንዳለበት ነግሬያቸው ይሄን ነው እንደ ጠንካራ ጎን ያሳካነው፡፡ ከዛ ውጪም የእኔን አጨዋወትም እንዲለመዱ በማድረግ ውጤታማ መሆንም ችለናል፡፡
የሰበታ ከተማን ክፍተት ጎን ብዬ የምጠቅሰው ነገር ቢኖር ደግሞ የአየር ላይ ኳሶችን በጣም እንቸገር ነበር፤ ሌላው በተጨዋቾቼ ላይ ስሜታዊ የመሆንም ነገር ይታይና የቀይ ካርድ ሰለባ እስከ መሆን የደረስንበትም ጊዜ ነበርና እነዚህን ነው የምጠቅሳቸው፡፡
ሊግ፡- ሰበታ ከተማ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ያለፈው ተፈትኖ ነው ወይንስ በቀላሉ?
አሰልጣኝ ክፍሌ፡-ተፈትኖ ነው እንጂ! ለዛም በምክንያትነት የማነሳልህ ተደጋጋሚ ነገር አለ፤ ክለባችን ሊጉ ሲጀመር በርካታ ጎሎችን እያስቆጠረ ነበር ተጋጣሚዎቹን ሲያሸንፍ የነበረው፤ በኋላ ላይ ግን በአንድ አንድ ጨዋታዎቻችን ለምሳሌ መጥቀስ ይቻላል ከገላን ከተማ ጋር ስንጫወት ሁለት ተጨዋቾች በቀይ ካርድ ወጥተውብን ይህንን ግጥሚያ በአቻ ውጤት ለማጠናቀቅ የቻልንበት ሌላው ከወልድያ ከተማ ጋር ስንጫወት ጨዋታው በተጀመረ 20 ደቂቃ ውስጥ አንድ ተጨዋች በቀይ ካርድ ወጥቶብን ይህንን ግጥሚያ 2ለ1 ለማሸነፍ የቻልንባቸውጨዋታዎች እና ከዛ ውጪም ወደ ፕሪምየር ሊግ ለማለፍ ከጫፍ በደረስንበት የመጨረሻዎቹ የ3 እና የ4 ሳምንታት ጨዋታዎቻችን ላይ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ለማለፍ ከነበረን ጉጉት አንፃር በስነ-ልቦናው ደረጃ ጫና ነበረብንና በጠባብ 1ለ0 ያሸነፍንባቸው ጨዋታዎች በጣም አስቸጋሪ ነበሩና እነዛ አይረሱም፤ በተለይ ከደሴ ከተማ ጋር ስንጫወት ይሄን ግጥሚያ ማሸነፍ መቻል ወደ ፕሪምየር ሊግ የሚያስገባን ነበርና እነሱ በጣም ጠንክረውብን የነበሩ ቢሆንም አሸንፈናቸው ነው ሊጉን የተቀላቀልነው፤ ይሄን ግጥሚያ ባናሸንፍ ኖሮ ከለገጣፎ ለገዳዲ ጋር የሚኖረን ጨዋታ እነሱም ሊጉን ለመቀላቀል ካላቸው እድል አኳያ ለእኛ በጣም የጭንቀትም ይሆንብን ነበርና በአጠቃላይ ሊጉን የተቀላቀልነው ተፈትነን ጭምር ነው፡፡
ሊግ፡- አንድአንዶች ግን የቱም ቡድን ወደ ፕሪምየር ሊግ ሲያልፍ ክለቡ ያለፈበትን መንገድ ከሌላ ነገር ጋር ያያይዙታልና በዚህ ዙሪያ ስለ እናንተ ቡድን ምን የምትለው ነገር ይኖርሃል?
አሰልጣኝ ክፍሌ፡- የፕሪምየር ሊጉን እኛ የተቀላቀልነው በልፋታችን በላባችን እና በጠንካራ ስራችን እንጂ ሌላ በምንም ነገር አይደለም፤ በእዚህ አመት ተጨዋቾቻችን የቀይ ካርድ ሰለባ ሆነውብን በጎዶሎ ልጅ ተጫውተን አሸንፈናል፤ እኔም ሜዳ ገባሁ ተብዬ እና 3 ወር ተቀጥቼም ግጥሚያዎችን ማሸነፍ ችለናል፤ ሌሎች ብዙ ጫና ደርሶብንም የፕሪምየር ሊጉን መቀላቀል ችለናልና ለእዚህ ድል ያበቃን ጥረታችን እና ል ፋታችን ብቻ ነው፡፡

ሊግ፡- የሰበታ ከተማን ደጋፊዎች በምን መልኩ ነው የምትገልፃቸው?
አሰልጣኝ ክፍሌ፡-ሰበታ ከተማ ወደፕሪምየር ሊጉ የገባበት አንደኛው ጥንካሬው ደጋፊዎቻችን የሚሰጡን ድጋፍ ለእኛ ትልቅና ተጨማሪ የሞራል ብርታትና ኃይልም ስለሆነልን ነው፤ የሰበታ ከተማ ደጋፊ ውድድሩ በተጀመረበት አካባቢ በቡድኑ ወደ ፕሪምየር ሊግ ያለማለፍ ያለፈው ጊዜያት ተስፋ ቆርጦ ኳስን በብዛት ሆኖ አያይም ነበር፤ በኋላ ላይ ግን የክለቡ ስኬታማነት ከጨዋታ ወደ ጨዋታ ጥሩ ሲሆንና በውጤታማነትም ማማ ላይ ሲቀመጥ እና ወደ ፕሪምየር ሊጉ ስናልፍ ህፃኑ፣ ወጣቱ፣ ሴቱ፣ ሽማግሌዎች፣ እና አሮጊቶች ሳይቀሩ ነው በቡድኑ ድል በመደሰት እና ከቡድኑም ጎን ቆመው በያሉበት ቡድኑን ይደግፉና ያበረታቱም የነበረው፡፡
በዘንድሮው የውድድር ተሳትፎአችንም ለጨዋታ ወደ ቡራዬ ስንሄድ 30 እና 40 መኪና ነበር የተጓዘው፤ ይሄን ጨዋታም 1ለ0 ልናሸንፍ ችለናልና በአጠቃላይ የሰበታ ከተማ ደጋፊን እየተመለከትኩት እና እያመሳሰልኩት ያለሁት ልክ በኢትዮጵያ ቡና እያለሁ ከነበረው የቡና ደጋፊ እና በጅማ ከነማ በነበርኩበት ጊዜ ከነበረው የጅማ ከነማ ደጋፊ ጋር ነው፡፡
ሊግ፡- ሰበታ ከተማን ወደ ፕሪምየር ሊጉ አስገብተሃል፤ ከክለቡ ጋር ትቀጥላለህ ወይንስ……?
አሰልጣኝ ክፍሌ፡- የሰበታ ከተማ ጋር ያለኝ ኮንትራት የሚጠናቀቀው ነሐሴ 30 ነው፤ ስለዚህም ውሌን ከእነሱ ጋር ለመጨረስ ሶስት ወራቶች ይቀሩኛልና ከቡድኑ

Hatricksport, [22.06.19 20:11]
ጋር አሁን ላይ ኮንትራቴን ስለመጨረስ እንጂ ልቀጥል አልቀጥል የማውቀው ነገር የለም፡፡ ያም ቢሆን ግን የክለቡ ሰዎች ከወዲሁ እኔን ለማስቀጠል እያነጋገሩኝ ነው የሚገኘው፡፡
ሊግ፡- ሰበታ ከተማን በፕሪምየር ሊጉ ካሰለጠንክ ምን አይነት ቡድንን ስለመገንባት እና ምን አይነት ውጤት የሚያስመዝግብ ቡድንን ስለመስራት ታስባለህ?
አሰልጣኝ ክፍሌ፡- የሰበታ ከተማ ክለብ ግንባታን በተመለከተ እኔ ልሰራ የምፈልገው ቡድን እግር ኳስን በጥሩ እና በአማረ መልኩ የሚጫወት እና በአብዛኛው በወጣቶችም የተዋቀረ ቡድንን ነው፤ ለእዚህ ደግሞ በክለቡ ውስጥ አሁን ላይ ብቅ ብቅ ያሉ እና ወደፊትም ሃገሪቱን ሊጠቅሙ የሚችሉ ወጣት ተጨዋቾችም አሉን፤ ከዛ ውጪም ቡድናችንን ሊጠቅሙ የሚችሉ ጥቂት ልምድ ያላቸው ተጨዋቾችንም በማከተት ጠንካራውን የሰበታ ከተማ ቡድንን እንገነባለን፡፡
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ተሳትፎአችን ላይ የእኛ ቡድን እንዲያመጣ የምንፈልገው ውጤት ከፕሪምየር ሊጉ ለመውረድ እና ላለመውረድ በሚጫወትበት ደረጃ ሳይሆን የሊጉ ጠንካራ ተፎካካሪ የሚሆንን ቡድን ነውና ይሄ ነው የቡድናችን ዋናው ዓላማም ሊሆን የሚገባው፡፡

ሊግ፡- በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ከዚህ ቀደም አየር ሃይልን አሁን ላይ ደግሞ ሰበታ ከተማን አሰልጥነህ ወደ ፕሪምየር ሊጉ አስገብተሃል፤ አንድን ቡድን አሰልጥኖ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ስለማሳለፍ ምን ትላለህ?
አሰልጣኝ ክፍሌ፡- ይሄ የሚያመለከተው የከፍተኛው ሊግ ውድድር ምን ያህል ጠንካራ እና ፈታኝ ስለመሆኑ ነው፤ ለእዚህ ደግሞ አንድ ማሳያ ልንገርህ የፕሪምየር ሊግ ክለቦች የነበሩት ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና አርባምንጭ ከተማ እና ወልድያ ከተማ ወደ ከፍተኛው ሊግ ከወረዱ በኋላ አሁን ላይ በድጋሚ ለመምጣት አልቻሉምና ውድድሩ በጣም ጠንካራ ነው፤ ሰበታ ከተማ ሊጉን ዳግም የተቀላቀለው ከ8 አመት በኋላ ነው፤ ይሄን ቡድን ወደ ፕሪምየር ሊጉ ስለማሳለፍ ማሰብ የጀመርኩት ክረምት ላይ ነበርና በጣም ጠንክረን ስለሰራን ነው ሊጉን ልንቀላቀል የቻልነው፤ አየር ሃይልንም ወደፕሪምየር ሊጉ ሳሳለፍ ብዙ ለፍቼ ነው፤ የጅማ ከተማ ክለብንም እስከ መጨረሻው ሰዓት ድረስ ከክለቡ ጋር በመለያየቴ ልቀጥል ባልችልም አሰልጣኝ መኮንን የነበረውን ጅማሬ አስቀጥሎ ቡድኑን ወደ ፕሪምየር ሊጉ እንዲያልፍ በማስቻሉና ለቡድኑ ማለፍም መሰረቱን ጥዬ ስለሄድኩ፤ የእኔም አሻራ ስላለበት ያኔ ቡድኑን በያዝዙ ሰአት ከእነ ወልቂጤ ከተማ፣ ሻሸመኔ እና ሀድያ ሆሳህና ጋር ጠንካራ ተፎካካሪ ሆኜ ነው የአንደኛው ዙር መሪ ሆኜ ከቡድኑ ጋራ የተለያየሁት እና አንድን ቡድን ከታች ወደ ላይ ማሳለፍ ከፍተኛ ጥንካሬና ችሎታንም ነው የሚጠይቀው፡፡
ሊግ፡- የአሰልጣኝነት የሙያህ ዘርፍ ላይ የመጀመሪያ እልምህ ምንድን ነው?
አሰልጣኝ ክፍሌ፡- የአሰልጣኝነት ህይወቴ ላይ ብዙ ጊዜ ወጣት ተጨዋቾች ላይ በመስራት እታወቅ ነበር፤ ለእዚህም በፕሮጀክት ደረጃ፣ በኢትዮ ኤሌክትሪክ እና በአየር መንገድ እግር ኳስ ቡድኖች ውስጥ የሰራኋቸው ነገሮች ይታወቃሉ፤ በአሁኑ የሰበታ ከተማ ቡድን ውስጥም ጥሩ ብቃት ያላቸው እና እና ሀገርንም መጥቀም የሚችሉ ወጣት ተጨዋቾች አሉና በሙያ ቆይታዬ በጣም ከማልማቸው ነገሮች ውስጥ የቅድሚያውን ስፍራ የሚወስደው በኢትዮጵያ ብሄራዊ ወጣት ቡድን ውስጥ ተመርጦ መስራትን ነው፤ ሀገሬን በሙያዬ የማገልገልም ከፍተኛው ፍላጎት አለኝና ይሄን እድል ማግኘት እፈልጋለው፡፡
ሊግ፡- በመጨረሻ…?
አሰልጣኝ ክፍሌ፡- የሰበታ ከተማ እግር ኳስ ክለብን አሰልጥኜ ቡድኑን ለፕሪምየር ሊግ ማብቃት መቻሌ የፈጠረብኝ የደስታ ስሜት በጣም ከፍተኛ ነው፤ ይሄ ቡድን ለእዚህ ስኬት እንዲበቃ የሁሉም አስተዋፅኦ አለበት፤ ከቢሮ ስነሳ የከተማው ከንቲባ እና የፅህፈት ቤቱ ሰራተኞች የክለቡ ስራ አስፈፃሚ የቡድኑ ደጋፊዎች እና ተጨዋቾቼን ላመሰግናቸው እፈልጋለሁ፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P