በነገው ዕትም ከሀገር ውስጥ ዘገባችን ሀምበሪቾ ዱራሜና ወደ 9 የሚጠጉ ተጨዋቾች ተፋጠዋል…ክለቡ ከአራት ወር በላይ ደመወዝ አልተከፈለንም በማለት ቅሬታ ያቀረቡት 9 ተጨዋቾችን ሳይዝ ወደ ድሬዳዋ አቅንቷል። ክለቡ ካልወሰዳቸው ተጨዋቾች መሃል አንዱ ባለ ብዙ ልምዱ ብሩክ ቃልቦሬ ነው ….ከሊጉ ዮሴፍ ከፈለኝ ጋር ባደረገው ቃለምልልስ ” መብታቸውን የሚጠይቁ ተጨዋቾች በክለቦች አይወደዱም ” ብሏል። ብሩክ እንደሚናገረው ” የለፋንበትን ደመወዛችንን ስጡን ብለን ከመለመን ውጪ ምን ይመጣል..?” ሲልም ተናግሯል…ቃለ ምልልሱን ይዘናል….
….በውጪ ዘገባ ደግሞ….
*…..የፊታችን እሁድ ምሽት 12.3ዐ ላይ በአንፊልድ ሊቨርፑልና ማን.ሲቲ ለ196ኛ ጊዜ ክሎፕና ጋርዲዮላ ለ23ኛ ጊዜ ይፋጠጣሉ…በዋንጫ ፉክክሩ ላይ የጎላ ተጽዕኖ ስላለው ስለዚሁ ግጥሚያ መረጃዎችን ይዘናል…
*……መድፈኞቹ በተለይ ከዱባይ መልስ ስኬታማ ጊዜ እያሳለፉ ነው …. በ7 ጨዋታ 31 ግብ ያስቆጠሩበትን ጣፋጭ ጊዜ አሳልፈዋል…ለዛሬ ስለተነቃቁት መድፈኞች የምንላችሁ አለ…
*….. የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግን ለበርካታ ጊዜ በማንሳት ታሪክ የሰራው ሜን.ዩናይትድ በዘንድሮ የውድድር አመት ውጤታማ ጊዜ አላሳለፈም…ለዚህ ተጠያቂ ናቸው የተባሉትን አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሃግን ያሰናብታል ወይስ…? የሚለው ነብዙዎች ጥያቄ ሆኗል…በዚህ ላይ ያዘጋጀነው መረጃ አለ….
*……የሜሰን ግሪንውድ ዕጣ አልታወቀም የዩናትድ አለቆችም ራሳቸውን ከተጨዋቹ ማራቅ የፈለጉ ይመስላል..በዚህ ላይ የሚያጠነጥን መረጃ አካተናል….
*…..በሰማያዊያኑ ቤት የደበዘዘው ካይ ሃቨርትዝ የመድፈኞቹ ሀቨርትዝ ሆኖ ተነቃቅቷል… በተጨዋቹ ለውጥ ዙሪያ የምንላችሁ አለ…
*….የሊቨርፑሉ ዳርዊን ኑኔዝ .እግርኳሳዊ ዕድገት ቀዮቹን እየጠቀመ ነው …በዚህ ላይ የያዝነው መረጃ አለ….
….. እናም ሌሎች ያልተሰሙ መረጃዎችን አካተናል …
ነገ ጠዋት ቡናዎን ሲፈልጉ ማኪያቶዎን ወይም ያሻዎት ሌላ ከሆነ ልብዎ የፈለገውን እየተጎነጩ ሊግን በእጅዎ ያስገቡ…
….ቅዳሜና እሁድዎ የሚደሰቱበት ቀኖችዎ ይሁኑ…