የአአ እግርኳስ ፌዴሬሽ በከተማ ዋንጫ ላይ ከሚሳተፉት የስምንት ክለብ አመራሮች ጋር በውድድር አጠቃላይ ሁኔታ ዙርያ ባደረገው ውይይት ውድድሩ የሚጀምርበትን ቀን አስመልክቶ ባቀረበው ሦስት አማራጭ ሀሳቦች መነሻነት ምክክር ከተደረገ በኃላ ውድድሩ በስኬት እንዲጠናቀቅ ከቀረቡት አማራጮች መካከል ቅዳሜ ጥቅምት 29 ቀን ቢጀምር የተሻለ ነው በማለት ሁሉም ክለቦች ከስምምነት ደርሰዋል።

በዚህም መሠረት 14ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ የሚጀምርበት ቀን ለውጥ በማድረግ ቅዳሜ ጥቅምት 29 ቀን የሚጀምር ይሆናል።
የመክፈቻ ጨዋታዎች
ቅዳሜ ጥቅምት 29 ቀን 2012
08:00 | ባህርዳር ከተማ ከ ወልቂጤ ከተማ
10:00 | ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ መከላከያ
እሁድ ጥቅምት 30 ቀን 2012
08:00 | ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከ ወልዋሎ
10:00 | ኢትዮጵያ ቡና ከ ሰበታ ከተማ