Google search engine

‘‘የሊጉን ዋንጫ ለማንሳት ከሜዳችን ውጪ ያሉ ጨዋታዎችንም ልናሸንፍ ይገባል” አቡበከር ናስር /ኢትዮጵያ ቡና/

በመሸሻ ወልዴ

ሊግ፡- በመጨረሻው ሰዓት
በተቆጠረባችሁ ግብ ኢትዮጵያ ቡና 1 ወላይታ
ድቻ 1 የሚል ውጤት ተመዝግቧል፤
ጨዋታውን እንዴት አገኘኸው? ውጤቱስ
ምን ስሜት ፈጠረብህ?
አቡበከር፡- ከወላይታ ድቻ አቻ
የተለያየንበት የሊጉ ጨዋታ በእንቅስቃሴው
በኩል እኛም ሆንን እነሱ ጥሩ ያልነበርንበት
ቢሆንም ለእኛ ግን ግጥሚያውን በሜዳችን
እና በደጋፊዎቻችን ፊት እንደማድረጋችን
ማሸነፍ ነበረብን፤ በጨዋታው የጎል
ማስቆጠር እድል አግኝተን ሳንጠቀምበት
ቀርተናል፤ የመሪነት ጎል ካስቆጠርን በኋላም
ለማሸነፍ ተቃርበን ወደ ኋላ አፈግፍገን
መጫወታችን ሊጎዳንና በመጨረሻው
ሰዓት ላይም በተቆጠረብን ግብ የመረጥነው
አጨዋወት አቻ እንድንለያይ አድርጎናል፤
እሁድ ዕለት የተመዘገበው ውጤት
እኛንም ሆነ ምርጦቹን ደጋፊዎቻችንን
ያስከፋንና የተስፋ መቁረጥ ስሜት ውስጥም
የከተተን ነው፤ ስለዚህም በቀጣዩ ጨዋታ
ከዚህ ስሜት በፍጥነት ልንወጣና ልንላቀቅ
ይገባናል፡፡
ሊግ፡- ወላይታ ድቻን በእሁዱ ግጥሚያ
እንዴት አገኛችሁት?
አቡበከር፡- ወላይታ ድቻ ጠንካራ ቡድን
እንዳለው ያስታውቃል፤ ያን ዕለት ከሜዳው
ውጪ እንደመጫወቱ ብዙም መጥፎ የሚባል
አልነበረም፤ ጎል ከገባባቸው በኋላ በመጠኑም
ቢሆን ጥሩ ለመንቀሳቀስ ሞክረዋል፡፡
ሊግ፡- ወላይታ ድቻ በመጨረሻው ሰዓት
ላይ ጎል አስቆጥሮባችሁ አቻ ስትለያዩ የቱን
ግጥሚያ ነው ያስታወሰክ?
አቡበከር፡- የሐዋሳ ከነማ ጋር የነበረን
የዓምናው ጨዋታ ነው ትዝ ያለኝ፤ ያኔ
አሸንፈን ወጣን ስንል ነው አቻ የተለያየነው፡፡
ሊግ፡- ኢትዮጵያ ቡና የሊጉ ጅማሬው ላይ
ምርጥ ቡድኑን እያሳየ ነው?
አቡበከር፡- በፍፁም፤ በሊጉ የእስካሁን
ጨዋታዎቻችን አበረታች የሚባል ውጤትን
ከሌላው ጊዜ አንፃር አስመዘገብን እንጂ
ደጋፊውን የሚያስደስት እንቅስቃሴን እያሳየን
አይደለምና ውጤታማ ሊያደርገን የሚችልን
ጥሩ አቋም ለማሳየት ከአሰልጣኞቻችን ጋር
እየተነጋገርን ይገኛል፡፡
ሊግ፡- በዘንድሮው የውድድር ዘመን
ኢትዮጵያ ቡና ውጤታማ ሆኖ የሊጉን
ዋንጫ ለማንሳት ምን ማድረግ ይኖርበታል?
አቡበከር፡- ኢትዮጵያ ቡና በዓምናው
የሊጉ ተሳትፎው ዋንጫውን ለማንሳት
ባይችልም የሊጉን ዋንጫ ለማግኘት ተቃርቦ
የነበረው የሁለተኛው ዙር ላይ በነበረው
ጥንካሬ ነው፤ ያም ሆኖ ግን በእዚህ መልኩ
ብቻ ለውድድር መምጣት የሚያስገኘው
ጥቅም ብዙ ስላልሆነና ያን ስላወቀም
የዘንድሮ ውድድሩ ላይ ከመጀመሪያው ዙር
አንስቶ ውጤታማ ለመሆን ነው እየተዘጋጀ
የሚገኘው፤ የሊጉ ውድድር አሁን ጅማሬ
ላይ ነው ያለው፤ ጨዋታዎችን በሜዳችንም
ከሜዳችንም ውጪ ማሸነፍ ይኖርብናል፤
በተለይ ክልል ላይ ስንጫወት የአቻ
ውጤትን ብቻ ይዞ መምጣት ሻምፒዮና
እንደማያደርግም ስለተረዳን ከእዚህ በኋላ
የሚኖሩንን ጨዋታዎች ለማሸነፍም ጭምር
ነው ወደ ሜዳ የምንገባው ያኔም የውድድር
ዘመኑ ሻምፒዮና እንሆናለን፡፡
ሊግ፡- የባህር ዳር ከነማን በባህር ዳር
ስታዲየም ነገ ትፋለማላችሁ፤ ለጨዋታው
የሰጣችሁት ትኩረት ምን ይመስላል? ምንስ
ውጤት ከግጥሚያው ይመዘገባል?
አቡበከር፡- የባህር ዳር ከነማ ጋር ያለብን
የነገው ጨዋታ ተጋጣሚያችን ጥሩ ቡድን
ከመሆኑ የተነሳ ከፍተኛ ፉክክር የሚደረግበት
ነው፤ ከእነሱ ጋር በሲቲ ካፕ ላይ ተጫውተን
በሰፊ ግብ ልዩነት አሸንፈናችኋል፤ ያን ዕለት
እናሸንፋቸው እንጂ ቀላል ተጋጣሚያችን
አልነበሩም፤ በሊጉ የመክፈቻ ጨዋታ
ጠንካራውን ቅ/ጊዮርጊስ ማሸነፋቸው
ይታወሳልና ነገ በሚኖረን የሜዳችን ውጪ
ጨዋታ ለግጥሚያው ከፍተኛ ትኩረት
በመስጠት አሸንፈን ለመውጣት ተዘጋጅተናል፤
ቡና ለሻምፒዮናነት የሚጫወት ክለብ
ከመሆኑ አኳያም እንዲህ ያሉ የሜዳ ውጪ
ጨዋታዎችንም ማሸነፍ ይኖርበታል፡፡
ሊግ፡- የኢትዮጵያ ቡናን የሊጉ ጅማሬ
ላይ እንደተመለከትከው በዋናነት ምንን
ማሻሻል ይኖርበታል?
አቡበከር፡- በሊጉ የውድድር ጅማሬ
ሁሉም ክለቦች ላይ ክፍተቶች እንዳለ
ባምንም እኛ ክለብ ጋር በዋናነት የሚታየው
ችግር የጎል አጨራረስ ነው፤ ይህን ችግር
በፍጥነት ልንቀርፈው ይገባልም፡፡
ሊግ፡- እንደ ኢትዮጵያ ቡና
ተጨዋችነትህ ከአንተስ ዘንድሮ ምን
ይጠበቅ?
አቡበከር፡- የኢትዮጵያ ቡና ተጨዋች
ስትሆን ክለቡ ካለው ከፍተኛ ስምና ዝና
እንደዚሁም ደግሞ ከትልቅ ክለብነቱም
አንፃር ከዘርፈ ብዙ ደጋፊዎቹ የሚጠበቅብህ
ብዙ ነገር ስላለ ሁሌም ስኬታማ አቋምህን
ልታሳይ ይገባልና እኔም በምጫወትበት
የመስመር ስፍራ ላይ ለቡድኑ ውጤታማነት
ከእኔ የሚጠበቅብኝ ግልጋሎት አለና ዘንድሮ
ያንን ለማሳየት ዝግጁ ነኝ፤ በምጫወትበት
ቦታ ለቡና የተመቻቹ ኳሶችን ለአጥቂዎች
መስጠትና ራሴም የድል ጎሎችን ማስቆጠር
ስለሚኖርብኝ ጠንክሬ ሰርቼ ውጤታማ
እሆናለው፡፡
ሊግ፡- የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎችን
በምን መልኩ ትገልፃቸዋለህ?
አቡበከር፡- የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች
ለክለባቸው ያላቸው ፍቅርንና ምርጥ
አደጋገፋቸውን ማንም ያውቀዋል፤
በሜዳችንም ከሜዳችን ውጪም ስንጫወት
ሁሌም ከጎናችን አሉ፤ ቡድኑ ውጤት
ኖረውም አልኖረውም ከሜዳ በፍፁም
አይቀረውም፤ ያላቸው ፅናት የሚደንቅና
ከእውነተኛ ደጋፊም የሚጠበቅ ነውና
ይሄ ጉዞአቸው ሊያስደንቃቸው እና
ሊያስመሰግናቸውም የሚገባ ነው፤ የክለባችን
ደጋፊዎች ነገ እሁድ በባህር ዳር ከተማ
ላለብን የሊጉም ጨዋታ ወደ ስፍራው እኛን
ለመደገፍ እያመሩ ነው፤ የእነሱ ድጋፍ
ሁሌም ያበረታታናል፤ ያ ስለሆነም እነሱን
በውጤት ለማስደስት ጠንክረን እንሰራለን፡፡
ሊግ፡- በመጨረሻ….?
አቡበከር፡- የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ
የዘንድሮ የውድድር ዘመን ተሳትፎን እኛ
የቡድኑ ተጨዋቾች ለደጋፊው እንደ ዓምናው
ቃል-መግባት ሳይሆን ዋንጫውን ብቻ
ማንሳት ነውና ለዛ ዝግጁ ነን፤ እልማችንም
እንደሚሳካ አምናለው፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

%d bloggers like this:
P