Google search engine

“በርግጠኝነት የምናገረው በግብጽ ፕሪሚየር ሊግ ላይ መጫወት የሚችሉ ተጨዋቾች አሉን” “የድሬዳዋ ስታዲየም ምቾት የጊዮርጊስ ተጨዋቾችን አቅማቸውን እንዲያሳዩ አድርጓቸዋል” አቤል ያለው /ዜድ ኤፍ.ሲ/ግብጽ/

በተለምዶ ሃያ ሁለት በሚገኘው 11 ሜዳ  ተወልዶ እድገቱ ግን በአቃቂ ነው…  አቃቂ በርካታ አቅም ያላቸው ወጣቶች ቢኖሩም እንደ እንግዳችን ገንነው ተሳክቶላቸው አልወጡም…በ2016  ለፈረሰኞቹ  ተጫውቶ በ8 ግብ የኮከብ ግብ አስቆጣሪነቱን እየመራ  ሳለ ከወደ ግብጽ የተጫወትልን ጥያቄ የቀረበለት  ..በአጭር ጊዜ ውስጥ የቀረበለትን ጥያቄ ተቀብሎ ተደራዶሮና ተስማምቶ በግብጽ ፕሪሚየር ሊግ  አምስተኛው ኢትዮጵያዊ ሆኖ ዜድ ኤፍ ሲ ለተባለ ክለብ ለሁለት አመት ከግማሽ የሚሆን ኮንትራት ፈርሞ  ወደ ካይሮ ካቀና ሳምንታቶች ቢሞላው ነው ….. እንግዳችን አቤል ያለው ዋሊያዎቹ ከሌሴቶ ጋር ላለባቸው ሁለት የወዳጅነት ጨዋታ ከካይሮ ወደ አዲስ አበባ በመጣበት ወቅት ከሊጉ ዮሴፍ ከፈለኝ ጋር ያደረገው ቃለምልልስ የሚከተለውን ይመስላል?

ሊግ:- አመሰግናለሁ አቤላ …  ሁለቱን የወዳጅነት ጨዋታ እንዴት አየሃቸው..?

አቤል:-  እየተሰራ ያለ ጥሩ ቡድን አለን ገና በደንብ ሲዋሃድ ደግሞ ምርጥ እንደሚሆን አልጠራጠርም ጊዜና እምነት ሊሰጠው ይገባል አሰልጣኙ ገብረመድህን ሃይሌ  አዲስ ቡድን መገንባት ላይ ስለሆነ ሁለቱ የወዳጅነት ጨዋታዎች ጥሩ ጥቅም ይሰጣሉ ብዬ አምናለሁ። ከተለያዩ ክለቦች እንደመምጣታችን የአቋም መፈተሻው አሪፍ ነው በመጀመሪያው ጨዋታ ለሜዳውም አዲስ ስለነበርን  ተቸግረን ነበር፡፡  ሁለተኛው ጨዋታ ግን ለውጥ ነበረው በአጠቃላይ ሁለቱ ጨዋታዎች ትልቅ  ጥቅም ነበራቸው፡፡

ሊግ:- በዚህ ቡድን ውስጥ አንተም ሲኒየር ልትሆን ነው  በትክክል ተተኪ  ተጨዋቾችን አይተሃል..?

አቤል:-  ገና እንደመመረጣቸው የልምድ  ችግር መኖሩ ተፈጥሯዊ ነው ጥሩ የተባሉ  ልጆች ተካተውበታል የዚያን ያህል ደግሞ ጊዜ ያስፈልጋቸዋል። ሁሉ  ነገር በአንድ ጀምበር አይመጣምኮ  በሂደት ጠንካራ የሚሆኑ የጥሩ ልጆች ስብስብ እንደሆነ ይሰማኛል፡፡ እነ ጀርመን ምርጥ ቡድን ቢሰሩ ረጅም አመት ቆይተው ለፍተው ታግሰው ነውና ጊዜ ይፈልጋል፡፡

ሊግ:- ስለሜዴው ስትናገር ሰማሁ…አልተመቻችሁም..?

አቤል:- ከውጪ ሲታይ አሪፍ ይመስላል ግን ያነጥራል ደርቋል ውሃም የጠጣም አይመስልም እኛም ተጋጣሚ ቡድንም ተቸግረንበታል እነሱም ተናግረው ነው የሄዱት መስተካከል አለበት፡፡

ሊግ:- ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊጉን እየመራ ነው …

አልናፈቀህም..?

አቤል:-/ሳቅ/  ምንም ጥያቄ የለውም ይናፍቃል ጥሩነቱ ግን እዛም ሆኜ እየተከታተልኩት ነው .. ትዝታውም ይመጣል… በዚያ ላይ ድሬዳዋ ስታዲየም ተመችቷቸዋል በደንብ እያሳዩበት ነው ሜዳ ምን ያህል ወሳኝ መሆኑን ያሳያል ግብጽ ሆኜ እያየኋቸው ነው ጥሩ ናቸው ከሌሎቹ ቡድኖች ሜዳው ለቅዱስ ጊዮርጊስ ጠቅሟል አቅማቸውን በሚገባ  እያሳዩም ናቸው፡፡

ሊግ:- ወደ ዜድ  ከተጓዝክ ወር ቢያልፍህ ነው እዚህ ያለው  ድባቡ ትዝ እያለህ አልተቸገስክም ..?

አቤል:- በጣም ትልቁ ፈተና ነው የመጀመሪያ  ጉዞዬ መሆኑ ከቤተሰብ ከጓደኞቼ ከለመድኩት ህይወት የተለየ ወደ ሆነው ቡድን ስገባ ተቸግሬ ነበር ያው ህይወት ነው የግድ እየለመድኩት ነው፡፡

ሊግ :- እንዴት ተቀበሉህ ..? ኢትዮጵያዊ መሆንህ አልከበደህም..?

አቤል:- /”ሳቅ/ አቀባበላቸው ደስ የሚል ነው በጥሩ ሁኔታ ነው የተቀበሉኝ ግን የተጋነነ ነገር የለም፡፡ ኢትዮጵያዊ መሆኔ ብዙ ቻሌንጅ የለውም ያው ኢትዮጵያ ብለው ነው የሚጠሩኝ /ሳቅ/

ሊግ:- የግብጽ ፕሪሚየር ሊግ ከእኛ ሀገር ጋር የተለየ ነው ማለት ይቻላል ..? ካየኧው ምንስ ገረመህ..?

አቤል:- አዎ ብዙ ነገራችን አይገናኝም ልዩነቱ ሰፊ ነው  የጨዋታ ስታይሉ የተለየ ነው፡፡ ወደዚያ ለመግባት ትንሽ ጊዜ ይጠይቃል .. የምንጫወትበት ሜዳው ፣  ቡድኑ የሚጠቅባቸውና ተሟልተው የሚታዩት ፋሲሊቲዎች አዚህ የሌለ ብዙ ነገር እዚያ አለ ራሳችንን የምናሻሽልበት  የተሟላ ጂምም ሁለ አለ… ራስህን ለማሻሻል የሚጠቅሙ ነገሮች ተሟልተው አይቻለሁ፡፡

ሊግ:- ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋርስ ያለው ልዩነት ሰፊ ነው?

አቤል:- ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ያለው ሂደትም አሪፍ ነው..ነገር ግን ከዚያኛው የክለቦች አደረጃጀት ጋር አይገናኝም… ከሀገራቱ እድገት ጋር የተያያዙ ልዩነቶች ታያለህ  የጨዋታ ዘይቤያችን ይለያያል..  ግብጽ ከልምምድ አንጻር  ረጅም ሰአት ነው የምንቆየው…የጂም ስራዎች አሉ በየጊዜው ውይይት እናደርጋለን በየቀኑ ቪዲዮዎችን እናያለን  ከዚያ ሜዳ ላይ ከ4-5 ሰአት እንቆያለን ሊሰለች ይችላል  ግን የግድ እንሰራለን… ዳኝነት ብታይ አይነጻጸርም በቀላሉ ፋወል ተብሎ አይነፋልህም ትግል ነው ቫርም  አለ፡፡

ሊግ:-በጣም ትልቅ የሚታይ ለውጥ ላይሆን ይችላል ..ግን ራስህ ላይ ያየኧው ለውጥ አለ..?

አቤል:– ገናኮ አንድ ወር ነው በጭንቅላት ማሰብ በስነ ልቦና መብሰል ላይ ለውጥ አለ ከኳስ ውጪ የምንሰራቸው ስራዎች ለውጥ ያመጣሉ ግን እኔ ገና ነኝ ብዙ ይቀረኛል  ገና አንድ ወሬ ነው ገብቼ በደንብ መጫወትም አልጀመርኩም፡፡

ሊግ:- አራት ኢትዮጵያዊያን ሳላህዲን ሰይድ ፣ ሽመልስ በቀለ፣ ኡመድ ኡኩሪና ጋቶች ፓኖም በግብጽ ፕሪሚየር ሊግ ተጫውተዋል…አምስተኛው አምባሳደር መሆንህ ይሰማሃል..?

አቤል:- አዎ እኔ የማሳየው ብቃት በኢትዮጵያዊያን ላይ እምነት እንዲጣል የማድረግ አቅም እንዳው አውቃለሁ የኔ ትጋት ለሌሎቹ በር የሚከፍት በመሆኑ  በተቻለ መጠን ጥሩ ለመሆን እጥራለሁ አደራ እንዳለብኝ ይሰማኛል፡፡

ሊግ:- ግብጽ ሊግ ላይ መጫወት የሚችሉ ተጨዋቾች አሉን ማለት ይቻላል..?

አቤል:– አዲስ ነገር መልመዱ ሊከብደን ይችላል እንጂ በሜዳ ላይ ላለው የሚጨመሩ የሚቀሩ ነገሮች ሲስተካከሉ ጥሩ ነው የምንሆነው አዚያም መጫወት እንችላለን  መጥተው የመጫወት  አቅም ያላቸው ተጨዋቾች  አሉን ምንምጨጥያቄ የለውም፡፡

ሊግ:- እረፍትህን እንዴት ነው የምታሳልፈው….?

አቤል:- ብዙም እረፍት የለም… ጠንክረን እየተዘጋጀን ነው ጥሩ ስትሆን ነው የምትሰለፈውና ተፍካካሪ ለመሆን የተቻለህን ትሰራለህ እረፍቱ በጠንካራ ስራ ይታጀባል ከሰራህ ከበረታህ ነው መሰለፍ ያለውና  ልምምዴን አጠንክሬ እየሰራሁ ኘው

ሊግ:- ገንዘቡ ጥቅማ ጥቅሙ ተመቸህ….? ኑሮስ በግብጽ ከባድ ነው…?

አቤል:-  ክፍያው ጥሩ ነው ኑሮውም ክፍያውም  አሪፍ ነው  ደስ ብሎህ እንድትሰራ ነው የሚያደርግህ …በተጨማሪም ኤጀንቴ  አዛሪያስ እዘያ ስለሆነ ብዙ ነገሮች  እያላመደኝ ነው አዚያ በመኖሩ እኔ እድለኛ ነኝ እሱ ባይኖር  ይከብደኝ ነበር አሁን ደግሞ ከርሱ ውጪ መንቀሳቀስ ጀምሬያለሁ፡፡ በዚህ ደስተኛ ነኝ በአጋጣሚውም አዛሪያስን ማመስገን እፈለልጋለሁ፡፡

ሊግ:- የሰፈር ጓደኞችህን ሄደህ አገኘሃቸው ..?

አቤል:-/ሳቅ/ ቤት ስለቀየርን ወደዚያ ስፍራው አልሄድኩም አላገኘኋቸውም ትዳር ከመሰረትኩ በኋላ  ሌላ አካባቢ ነው የምኖረውና አላገኘኋቸውም

ሊግ:- ከባለቤትህ ጋር አብራችሁ ናችሁ ..? ወይስ ምን ወሰናችሁ..?

አቤል:-  ለጊዜው አብረን አይደለም በቅርቡ ስለወለደች  ቤተሰብ ከጎኗ ነው፡፡ በቀጣይ አመት ግን የግድ ነው እኔ ጋር ትመጣለች ….

ሊግ:- የልጅህ ናፍቆትስ ..?

አቤል:- በጣም ነው የሚከብደው ህይወት ሲሆን ግን ምን ይደረግ እንዲህ ነው  በጣም ፈትኖኛል ትኩረቴንም ወስዷል ግን አማራጭ የለም

ሊግ:-  የውጪ ሃገር ኳስ ትከታተላለህ

አቤል:- /ሳቅ/ አዎ …በጣም ነው የምከታተለው፡፡ ኳስኮ በጣም ነው የምወደው…. የማን.ዩናይትድ ደጋፊም ነኝ

ሊግ:- በቦታህ ምርጡ ማነው..?

አቤል:- ቡድን እንጂ ተጨዋች ላይ አላተኩርም… የክርስቲያኖ ሮናልዶ አድናቂ መሆኔ ሳይረሳ…

ማን.ዩናይትድ  ማርከስ ራሽፎርድም ይስበኛል፡፡

ሊግ:- የመጨረሻ የምታመሰግነው ካለ..?

አቤል:- በቅድሚያ  ፈጣሪዬን ማመስገን እፈሌጋለሁ ከርሱ ቀጥሎ አሁን አብሮኝ ያለውንና ያገዘኝን አዛሪያን  አመሰግናለሁ ብዙ ደክሞልኛል ገና ብዙ ተጨዋቾችን አወጣለሁ ብሎ ያቅዳልና እንዲሳካለት እቅዱ እንዲፈጸም  እመኛለሁ  ባለቤቴን ቤተሰቦቼን ጓደኞቼን አሰልጣኞቼን በኔ ነገር ላይ አንድ ነነር ያበረከቱትን በሙሉ  አመሰግናለሁ…

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

ትኩስ ዜናዎች

%d bloggers like this:
P