Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“ከግል ሽልማት ይልቅ የኢትዮጵያ ቡና ክብር ይቀድምብኛል” “እኔ ገና ነኝ ጊዜ ያስፈልገኛል፤ ከአቡበከር ጋር አልነጻጸርም” አንተነህ ተፈራ /ኢትዮጵያ ቡና/

የተወለደው ኦሮሚያ ክልል በምትገኘው አዶላ  ወዩ ተብላ በምትጠራ ስፍራ ነው… በቦታዬ ከሀገር  ውስጥ አቡበከር ናስር፣ ጌታነህ ከበደና ሳላህዲን ሰይድን ከውጪ ክርስቲያኖ ሮናልዶን  እመርጣለሁ የሚለው የማን.ዩናይትድ ደጋፊ የሆነው እንግዳችን ከአራተኛ ሊግ ወደ ፕሪሚየር ሊግ በአጭር ጊዜ ውስጥ መዛወሬ እድለኛነቴን ያሳያል ሲልም ይናገራል። በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 8 ግብ አስቆጥሮ ለኮከብ ግብ አስቆጣሪነት እየተፎካከረ ያለው የኢትዮጵያ ቡናው አንተነህ ተፈራ ከሊጉ ዮሴፍ ከፈለኝ ጋር ያደረገው ቆይታ ይህን ይመስላል፡፡

ሊግ:-  አዶላ የወርቅ አካባቢ ናት ኳስ ተጨዋች ተገኘባት ሲባል ጥያቄ አያስነሳም..?

አንተነህ:- አዎ የወርቅ ምርት ያለባት አካባቢ ናት  ከዚያ ስፍራ ፕሪሚየር ሊግ ላይ ለመጫወት የቻልነው ፈቱዲን ጀማልና እኔ ነን በዚህም ደስተኛ ነኝ፡፡

ሊግ:- ራስህን ለአካባቢው እንደ አምባሳደር አድርገህ ነው የምትቆጥረው..?

አንተነህ:- አዎ ራሴን እንደ አምባሳደር  አድሬጌ ነው የምቆጥረው… በቢዝነሱ በኢኮኖሚ ካየን  ወርቅ ያለባት ናት በስፖርቱ ደግሞ እኔና ፈቱዲን ነን ..የቦታዋን ስም ስታስጠራ ደስ የሚል ነገር አለው.. ብዙ ሰው በኳሱ ሲያውቅህ ከየት እንደመጣህ ሲያውቅ ያው አምባሳደር ሆንክ ማለት ነው፡፡

ሊግ:- ፈቱዲን ቀድሞ እንደ መውጣቱ ተምሳሌት ነው ማለቴ ይቻላል…?

አንተነህ:- የፈቱዲን ቀድሞ መውጣት የተወሰነ ድርሻና ተጽእኖማ አለው፡፡ ግን እኔ ጠንክሬ ስለሰራው የወጣሁ ይመስለኛል፡፡ የሆነ ቦታ እንደምደርስ ስለማምን ጠንክሬ ሰርቼ እድሉን ሳገኝ የተጠቀምኩ ይመስለኛል፡፡ አራተኛ ሊግ እየተጫዘወትኩ አልመው የነበረውን ነው ያገኘሀት፡፡ በዚያ ላይ እኛ አካባቢ ወጥተው ሱፐር ሉግ ላይ የሚጫወቱ ነበሩ፡፡ እሱ ግን ፕሪሚየር ሊግ በመሆኑ እይታዬ ላይ ተጽዕኖ   ፈጥሯል። በግሉ ሊረዳኝም ሞክሯል 2008 ላይ ይጫወት የነበረው ለኢትዮጵያ ቡና ነበረና ከ17 አመት በታች ለመጫወት እድል ፈጥሮልኝ ሞክሬ ሳይሳካ መመለሴን አስታውሳለሁ፡፡ አሁንም እንገናኛለን ድጋፉ አልተለየኝም በዚህ አጋጣሚ አመሰግነዋለሁ።

ሊግ:- ህልም አለህ..?

አንተነህ:- እንደማንኛውም ተጨዋች ልጅ ላይ ሆኜ ህልም አለኝ …የመጀመሪያው ህልሜ ለብሄራዊ ቡድናችን መጫወትና ሀገሬን ማገልገል እፈልጋለሁ ሁለተኛው ደግሞ ከሀገር ውጪ ሄዶ መጫወት ህልም ነበረኝ፡፡ አሀንም መንገዱ ላይ እንዳለው ይሰማኛል አንድ ነገር ለማሳካት ታስብና ሲሳካ ደግሞ ሌላ ነገር ታልማለህ፡፡ በጊዜ ውስጥ ደግሞ ይህን የማሳካት እድል እስካገኝ ጠንክሬ የምሰራ ይሆናል ለዚህም ጥሩ የሚባል በራስ መተማመን አለኝ፡፡

ሊግ:- ኢትዮጵያ ቡና ጋር እንዴት ተገናኛችሁ..?

አንተነህ:- 2013 ላይ ከአዶላ  ወዩ ጋር በቢጫ ቲሴራ ከ17 አመት በታች ውድድር ተጫውተን ለክልል ሻምፒዮና ሳናልፍ ተመለስን እኔ ግን ኮከብ ግብ አግቢ ሆኜ ጨረስኩ 2014 የሊግ ውድድር ለመካፈል ወደ ሻኪሶ ሄድኩ። ከኦሮሚያ የክልል ሻምፒዮና ወደ አንደኛ ሊግ አለፍን በውድድሩም ሻምፒዮን ስንሆን ኮከብ ግብ አስቆጣሪ ሆኜ አጠናቀኩ አጋጣሚው ተመቻቸና በወቅቱ የኢትዮጵያ ቡና አሰልጣኝ  በነበረው ተመስገን ዳና ተመልምዬ ኢትዮጵያ ቡናን ተቀላቀልኩ፡፡ ከታችኛው ሊግ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ያደኩት በአጭር ጊዜ መሆኑ አስደስቶኛል።

ሊግ:- በአጭር ጊዜ መሳካቱ እድለኝነት አይመስልህም..?

አንተነህ:­- አዎ በጣም እድለኛ ነኝ በሊግ ደረጃ ብዙም አልተጫወትኩም ልምዱም አልነበረኝም ጠንክሬ ነው የምሰራው ኳስን በጣም ነው  የምወደው፡፡ ትምህርት ትቼ  የምኖርለት ስፖርት ነው. .እግር ኳስ ..የቤተሰቦቼ ድጋፍ በተለይ የአባቴን ሙሉ ድጋፍ ታክሎበት ሳይ የሚሳካ ነገር እንዳለው  የሚያስታውቅ ነገር  ነበረው… ተሳክቶልኝ ፈቱዲን በወጣበት ሂደት ለኔም ጊዜ ይመጣል ብዬ ሰርቼ ተሳክቶልኝ ለኢትዮጵያ ቡና  ለመፈረም  ችያለሁ፡፡ እኔ በመጣሁበት መንገድ እድለኛ ነኝ፡፡ ከአራተኛ ሊግ ወደ ፕሪሚየር ሊግ በፍጥነት አድጌ ለኢትዮጵያ ቡና መፈረሜ ትልቅ ደስታ ፈጥሮልኛል፡፡ እንዲህም ያደረገ የለም በዚህ ደስተኛ ነኝ አሰልጣኝ ተመስገን ዳና የሊግ ውድድር አድጎ  ብዙ ወጣቶችን መልምሎ ነበረና ተሳክቶልኛል፡፡ ከቡና ምልመላ በኋላ ዘንድሮ እነ ቅዱስ ጊዮርጊስ ኢትዮጵያ መድን ታች ወርደው ታዳጊ ላይ እየሰሩ ነው የቡና ምልመላ ለሌሎቹ እንደ በር ሆኗል .. ወጣት ላይ ማመን ወጣትን መያዝ ትልቅ ስኬት ያመጣል፡፡ አንድ ቡድን በሂደት ውጤት ያመጣል ብለህ ካሰብክ ወጣት ላይ ማመንህ የግድ ነው..ኢትዮጵያ ቡና ትልቅ ማሳያ ነው በሁለተኛ አመቱ ጥሩ ነገር እያሳየን ነው ብዙም ልምድ ያለው የለም እነ አስራት እነ አማኑኤልን ነው ሲኒየር ብለህ የምትጠራውና.. ሌሎቹ ሶስት አራት አመት ቢጫወቱም ወጣቶች ናቸው፡፡ ወጣት ላይ መስራት የአመታት እቅድ ውጤትን ያሰጣል ብዬ አስባለሁ፡፡

ሊግ:- ደጋፊው በደንብ ተቀበለህ..?

አንተነህ:- አዎ የኢትዮጵያ ቡናን ደጋፊ እንዲህ ነው ብለህ የምትናገረው አይደለም.. ለማንኜውም ሰው የሚገባውን ክብር የሚሰጡ ናቸውን አመሰግናለሁ፡፡ ደስ በሚል ሁኔታ ነው የተቀበሉኝ በዚህ አጋጣሚ ያለኝን ክብርና ፍቅር ልገልጽ እፈልጋለሁ እወዳቸዋለሁ፡፡

ሊግ:- በተጨዋችነት ዘመንህ አንድ ላይ መጫወት የምትፈልገው ከማን ጋር ነው..?

አንተነህ:- አብሬያቸው ልጫወት የፈለኳቸው ተጨዋቾች አሉ ግን በተለየ መልኩ ከሽመልስ በቀለ ጋር አብሬ ብጫወት እደሰታለሁ፡፡

ሊግ:- አራተኛ ሊጉም ይሁን ፕሪሚየር ሊጉ ላይ እያገባህ ነው…ተከላካዮቹ  ቀለሉህ..?

አንተነህ:-  ሊጉ ታች ቢሆንም ቀላል የሚባል አይደለም ጥሩ ጥሩ ተጨዋቾች አሉበት … ያም ሆኖ ግብ አስቆጥሬ ኮከብ ተብያለሁ እዚህ ግን ተደግፌ ታግዤ ነው፡፡ እያስቆጠርኩ ያለሁትና ለቡና በማስቆጠሬ ደስተኛ ነኝ የማገኘውን እድል እየተጠቀምኩ ነው፡፡ በተፈጥሮዬ ለጎል ቅርብ ሆኜ ነው የምጫወተው ያም ጠቅሞኛል፡፡

በፕሪሚየር ሊጉ አሰልጣኝ ነፃነት ይነግረኝ ነበር፡፡ ጥሩ እንደሆንኩ እንዲሰማኝ ይመክረኛል፡፡ ከታች ስለመጣሁ ብዙም እድል ባይሰጠኝም ጥሩ ድጋፍ አድርጎልኛል፡፡ እንድሰራ አደረገኝ ጠቅሞኛል በተለይ አሰልጣኞቼ የሚሉኝን በደንብ ስለምሰማ ውጤታማ ለመሆን ረድቶኛል ፡፡

ሊግ:- ኮከብ ግብ አግቢ ለመሆን አቅደሃል..?

አንተነህ:- መጀመሪያ  ከኔ ክብር ይልቅ ኢትዮጵያ ቡና አንድ ደረጃ ከፍ ሲል ማየትም እመርጣለሁ ለግሌ እደርሰበታለሁ…ለኔ ዋናው እኔ ልሁን መስፍን ወይም ብሩክ ዋናው ቡና ማሸነፉ ከፍ ማለቱ ነው ግላዊ ክብሬን አላስቀድምም እንደዚያ ነው የምናስበው ከግል ክብር ይልቅ ክለባችንን ወደ ዋንጫ ተፍካካሪነት መመለስ ነው የምንፈልገው ..ከግል ሽልማት የኢትዮጵያ ቡና ክብር ይቀድምብኛል ከዚያ በኋላ ግብ ማስቆጠሩ ለግል ክብር መጣሩ ይታሰብበታል። ቡድንህ በጥሩ መንፈስ ከተንቀሳቀሰ የማልጎላበት ምንም ምክንያት የለም በርግጥ የኔም ብቃት የክለቤም ስኬት የተያያዘ ነው ልቤ ግን ለክለቤ ያደላል፡፡

ሊግ:- ኢትዮጵያ ቡና ቀጣዩን አቡበከር አገኘ ማለት ይቻላል..?

አንተነህ:- በዚህ ሰአት ያን ማሰብና ከአቡበከር ጋር መነጻጸር አልፈልግም፡፡ እኔ ገና ጀማሪ ተማሪ ተጨዋች ነኝ አቡበከር ግን አጠር ባለ አመታት ውስጥ  ለቡና የሚገርም ግልጋሎት ሰጥቶ ለዋሊያዎቹ ወሳኝ አጥቂ ሆኖ ሀገር አገልግሎ ለደቡብ አፍሪካው ማማሎዲ ሰንዳውንስ እየተጫወተ ሀገር የወከለን ተጨዋች ጋር መስተያየት አልሻም፡፡ እኔ አንተነህ ተፈራ ገና ነኝ ጊዜ ያስፈልገኛል… ከአቡበከር ጋር አልነጻጸርም፡፡

ሊግ:- እያነጻጸርኩህ አይደለም.. የአቡኪ ደረጃ ላይ ገና ነህ ጥያቄዬ ተተኪው የቀጣይ አመታት የአቡበከር ቦታን የሚረከብ እንደሆንክ አይሰማህም ወይ እያልኩ ነው….?

አንተነህ:-  አመታቶቼ የሰኬት ጊዜዬ ወደፊት የሚመጣ ነው  አቡኪ የራሱን ነገር አድርጓል የሱን ስኬት እያየሁ የራሴን የሆነ ነገር ለክለቤና ለሀገሬ የማድረግ  ፍላጎት አለኝ፡፡ የተሻልኩ መሆኔ የራሴን ታሪክ መከሰቴ ወደፊት የሚመጣ ይሆናል ለዚህ ደግሞ  ርግጠኛ ነኝ፡፡

ሊግ:- ሁለት ጨዋታ በተከታታይ ተሸነፋችሁ ስሜት አይጎዳም ..?

አንተነህ:- በጣም ተበሳጭተናል  ማስተካከልና ወደ ድል መመለስ አለብን እኛ ውስጥ ትንሽ መቀዛቀዝ ተከስቷል፡፡ የትኛውንም ክለብ የሚገጥም ነገር ነው የገጠመን መቻል ኢትዮጵያ ንግድ ባንክም ገጥሟቸዋል። በርካታ ደጋፊ ስላለን ጫና ፈጥሮብን ሊሆን ይችላል ትንሽም ድካም ነበረብን አሁን የኛ ሀሳብ ወዳሸናፊነት መመለስ ጠንክረን መፋለም ነው የሚያስፈልገው፡፡ አንዴ ከጀመርን እንደምንሻሻል ርግጠኛ ነኝ  በቀጣይ ጨዋታ ላይ ከተደጋጋሚ ሽንፈት ወዳሸናፊነት የምንመለስ ይሆናል።

ሊግ:- በእስካሁኑ 18 ጨዋታዎች በማሸነፋችሁ የተደሰትክበት በተቃራኒው በመሸነፋችሁ የተበሳጨህበት ጨዋታ የትኛው ነው …?

አንተነህ:- ካሸነፍንባቸው የተደሰትኩት መቻልን ያሸፍንበት ጨዋታ ነው፡፡ 12 ተከታታይ ጨዋታ አሸንፎ ሊጉን እየመራ ስለነበር ስናሸንፈው ደስ ብሎኛል ሶስት ነጥብ መውሰድ ብቻ አይደለም በስነልቦና በጣም እንድንጠነክር አድርጎኛል፡፡ ከተሸነፍናቸው ደግሞ ያበሳጨኝ ድሬዳዋ ከተማ ያሸነፈን ጨዋታ ላይ ነው  ምክንያቱም ባለቀ ሰአት ነው ያገቡብን ..

ሊግ:- ሜዳውስ ተመቻችሁ..?

አንተነህ:- ካሉት ሜዳዎች አንጻር የተሻለ ነው የሚባለው፡፡ ብዙ አቅም የሚጠይቅ ሜዳ ቢሆንም ጸሃይ በሌለበት ቀን ለመጫወት አሪፍ ነው..

ሊግ:- የውጪ ጨዋታዎችን ታያለህ..?

አንተነህ:- አዎ ….በጣም ነው የምከታተለው ..

የማን.ዩናይትድ ደጋፊ ነኝ… በሰሞኑ ውጤቱ ደስተኛ አይደለሁም.. በአቋሙ ደስተኛ ባልሆንም  ለውጥ እንደሚመጣ ግን  ርግጠኛ ነኝ  ሻምፒየንስ ሊግ እንደሚገቡ አምናለሁ።

ሊግ:- በጥሎ ማለፍ ለኢትዮጵያ ዋንጫ ግማሽ ፍጻሜ ደርሳችኋል፡፡ ከሊጉና ከዚህ ዋንጫ የትኛው ላይ ልባችሁ አመዘነ..?

አንተነህ:- ሁለቱንም ላይ ነዋ….በሊጉም ከመሪው አልራቅንም 7 ነጥብ ልዩነት ነው፡፡ ከዋንጫ ፉክክሩ አለንበት ገና 12 ጨዋታዎች አሉ  ወደ አሸናፊነት  የግድ መመለስ አለብን ያኔ ተፎካካሪነታችንን እናሳያለን፡፡ በጥሎማለፉ ደግሞ ዋንጫውን አንስተን በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ካፕ ላይ መሳተፍ እንፈልጋለን፡፡ ለዚህም አቅሙ አለን  በአፍሪካ ደረጃ ኢትዮጵያን ከሚወክሉ መሃል እንደምንገኝ ተስፋ አድርጋለሁ፡፡ ለዚህም ተዘጋጅተናል የቡድናችን አዕምሮ  አቅም እንዳለን ስለሚነግረን ያለንን አውጥተን ያሰብነውን እንደምናሳካ ርግጠኞች ነን እኛ ጋር ተስፋ መቁረጥ ብሎ የገር የለም ለክለባችንም አንድ ታሪክ ማስቀመጥ እንፈልጋለን፡፡

ሊግ:- ለአንተ እዚህ መድረስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል ብለህ አንድ ሰው አመስግን ብትባል ማንን ትጠራለህ..?

አንተነህ:- ያለምንም ጥርጥር ቤተሰቦቼን…ከምንም ተነስተው እዚህ እንድደርስ ያበቁኝ እነሱ ናቸው፡፡ ለዚህሞ አመሰግናለሁ… ከነሱ በመቀጠል ደግሞ ሌሎችም መመስገን ያለባቸው አሉ… በዋናነት አሰልጣኝ ተመስገን ዳናን ከልብ አመሰግናለሁ የመለመለኝና ከዚያ ያበቃኝ እሱ ነው፡፡ ሌሎችም አስተዋጽኦ ያያደረጉትን በሙሉ ማመስገን እፈልጋለሁ እግዜር ይሰጥልኝ፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

ትኩስ ዜናዎች

P