Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“ውጤታማ ሆኜ ሉሲዎችን የማሰልጠን እድል የተነፈኩ ብቸኛ አሰልጣኝ ስለሆንኩ እውነት ለመናገር ተስፋ ቆርጫለሁ” “ድሬዳዋ ከተማ ከፋይ ክለብ ነው ገንዘብ ያወጣል ይባላል ይሄ ግን ስህተት ነው” አሰልጣኝ አስራት አባተ /ድሬዳዋ ከተማ/

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አዲሰ አበባ ከተማን በዋና አሰልጣኝነት ከመያዙ በፊት ባሉት 13 አመታት በሴቶች እግር ኳስ ስኬታማ አሰልጣኝ ነበር ….በሴቶች ከ17 እና 20 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን ጥሩ የተባለ ውጤትን አስመዝግቧል ….. በወንዶች የዋሊያዎቹ ም/ል አሰልጣኝ ሆኖ ከአሰልጣኝ ውበቱ አባተ ጋር ሰርቶ ወደ ካሜሩን የአፍሪካ ዋንጫ አቅንቷል…. በአሁኑ ወቅት የድሬዳዋ ከተማ ዋና አሰልጣኝ ሆኖ እየሰራ የሚገኘው አሰልጣኝ አስራት አባተ “ስኬታማ ሆኜ ሉሲዎቹን ያልያዝኩ እኔ ብቻ በመሆኔ ተስፋ ቆርጫለሁ” የሚለው ወጣቱ አሰልጣኝ አስራት አባተ “በወንዶቹ አሰልጣኝነቴ መቀጠል ብቻ ነው የምፈልገው” ሲልም ይናገራል… ከሊጉ ዮሴፍ ከፈለኝ ጋር በነበረው ቆይታም ለተነሱለት የተለያዩ ጥያቄዎች የሚከተለውን ምላሽ ሰጥቷል….

ሊግ:– የድሬዳዋ ከተማ ቆይታህን እንዴት ትገልጸዋለህ..?

አስራት:- የተወለድኩት ድሬዳዋ እንደመሆኑ በተደጋጋሚ ጊዜ ላሰለጥነው የምፈልገውም ክለብ ነው፡፡ ይህ ህልሜ ተሳክቶልኝ ብዙ ክለቦች የመውረድ አደጋ ውስጥ በነበሩበት ከባድ ሰአት 13 ጨዋታ ሲቀር ሃላፊነቱን ተረከብኩና ከክለቡ ስታፎችና ተጨዋቾች በጋራ ከሊጉ እንዳይወርድ አደረግነው፡፡ በዚህም ደስተኛ ነኝ ውጤቱ ታሳቢ ተደርጎ የሁለት አመት ኮንትራት ፈረምኩ፡፡ ለዘንድሮ  ውድድር ጥሩ ተዘጋጅተን የሊጉን ፍልሚያ ጀምረናል በአጭሩ ቆይታዬ ይህን ይመስላል….

ሊግ:– የዘንድሮ አምስት ሳምንት ጨዋታዎች ውጤትስ..?

አስራት:– ክለቦች ከአምናው የውድድር አመት ተምረው ዘንድሮ በጣም ተጠናክረው ከባድ የውድድር ኣመትን እያሳለፍን ይመስለኛል። በዚህ ሂደት አብዛኞቹ ክለቦች ትላልቅ ዝውውር ነው ያደረጉት… ደግሞም በጣም የተጋነኑ የሚባሉ ዝውውር ያደረጉ ክለቦችም አሉ… እንደ ድሬዳዋ ከተማ ዋጋው ከመናሩ የተነሳ ባሰብነው መልኩ ባንሄድም በመለስተኛ ዋጋ ወጣቶች ላይ ትኩረት አድርገን ያሉትንም አስቀጥለን እየተፋለምን እንገናኛለን፡፡ በመጀመሪያው ጨዋታ አምበሪቾን አሸንፈን በሁለተኛው ጨዋታ በኢትዮጵያ ቡና ተሸንፈናል፡፡ በሶስተኛው ጨዋታ ከሀዋሳ ከተማ ጋር አቻ ተለያይተን በተከታታይ አራተኛና አምስተኛ ጨዋታዎች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክና በአዳማ ከተማ ተሸንፈን ሊጉ ተቆርጧል። በሶስቱ የተሸነፍናቸው ጨዋታዎች ተፎካካሪ ቡድን እንዳለን ያየንበት ነገር ግን በፈጸምነው ስህተት ተሸንፈን ማስተካከል ያለንብንን ክፍተት ያየንበት ነው፡፡ በአምስቱ ጨዋታ 4 ነጥብ ይዘን በ12ኛ ደረጃ ላይ እንገናኛለን። ያንን ጥንካሬ ለማስቀጠል ክፍተታችንን በማረም ደግሞ የተሻለ ጠንካራ ሆነን ለመቅረብ ተወያይተን ወደ ዝግጅት ገብተናል፡፡ ሊጉ ሲቀጥል ከምናገኘው ወላይታ ድቻ ጀምሮ ወደ ውጤት ለመመለስ የምንጥር ይሆናል፡፡ ዘንድሮ ጠንካራ ፉክክር እንዳለ ማሳያ ደግሞ የነጥብ መቀራረባችን ነው፡፡ ቶሎ ከነጥብ መጣሉ ወጥተን ወደ ድል መመለስ እንዳለብንም ተስማምተን ወደ ስራ ገብተናል።

ሊግ:- በአምስት ጨዋታ 15 ነጥብ ይገኛል እናንተ ደግሞ አራት ነጥብ ብቻ አግኝታችሁ ወደ 11 ነጥብ ጥላችኋል አጀማመራችሁ ደካማ መሆኑን እንጂ ጥንካሬ አለን ያስብላል…?

አስራት:- በውጤት ደረጃ ካየነው ደካማ አጀማመር የሚባል ነው፡፡ ነገር ግን ሌሎች ቡድኖችንም ማየት ያስፈልጋል ከእኛ በላይ ያሉ ጠንካራ ስብስብ ያላቸው ከፍተኛ ዝውውር ያደረጉትን ክለቦችንም ካየን ልዩነቱ በአሁኑ ሰአት ብዙ የሚባል አይደለም፡፡ አምና 3ኛ የወጣው ኢትዮጵያ መድን 5 ነጥብ፣ ሲዳማ ቡና 4 ወላይታድቻ 7 ኢትዮጵያ ቡናም ባህርዳር ከተማ 8 ነጥብም ነው ያላቸው፡፡ ውድድሩ ጠንካራ ፉክክር ያለውና ከእኛም ብዙ ያልራቁ መሆናቸውን ያሳያል ያም ሆኖ የኛ ጅማሮው ግን አያበረታታም ..

ሊግ:- ደካማ ውጤት አመጡ የተባሉት አሰልጣኝ ስዩም ከበደና አሰልጣኝ ጸጋዬ ወንድሙ በስምምነት ከየክለቦቻቸው ተለያይተዋል… አንተጋስ ስጋቱ የለም..?

አስራት:– ይሄ እግር ኳስ ላይ ያለ ነገር ነው… ጠንክረህ ካልሰራህ ውጤት ካላመጣህ የስንብት ስጋት አብሮህ ይኖራል… በእኛ ሀገር የእግር ኳስ ትልቁ ችግር በቡድን እድገት ላይ ወይም ነገ ባለው ተስፋ ላይ ሳይሆን የሚተኮረው ሁሌ ውጤት ላይ ብቻ ነው፡፡ ይሄ መስተካከል አለበት ባይ ነኝ።  አንዳንድ ክለቦች ከእኛ በተሻለ ጠንካራ ዝውውር ያደረጉና ከፍተኛ ውጤት የሚጠብቁም ሆኖ ይሆናል፡፡ እንደ አጠቃላይ ውጤት ከጠፋ የመሰናበት ስጋት መኖሩ አይቀርም፡፡ ግን ክለቦቹ የወሰዱት ርምጃ ትክክል ነው ብዬ አላስብም፡፡ አመራሮቹ ሁለቱ ክለቦች አንድ ጨዋታ ቢያሸንፉ የት እንደሚደርሱ ከሌሎቹ ክለቦች ጋር ብዙ የነጥብ መራራቅ አለመኖሩን ማሰብ ነበረባቸው ብዬ አምናለሁ.. በርግጥ ከውጤቱ ባሻገር ምን አይተው ርምጃውን እንደወሰዱ አላውቅም፡፡ ውጤት ብቻ ግን መመዘኛ ባይደረግ ደስ ይለኛል   ከውጤቱ በተጨማሪ ከእንቅስቃሴውና ነገ ካለው ተስፋ ጋር ተያይዞ ነው ክለቡም አሰልጣኙ መገምገም ያለባቸው ብዬ አስባለሁ።

ሊግ:– ሲዳማ ቡና በርካታ ዝውውር አድርጓል ውጤት ሊጠብቅ ይችላል …ድሬዳዋ ከተማስ..?

አስራት:– ቡድኑ ድጋፍ አድርጓል፡፡ ጉዳዩ ግን ከድጋፍ ጋር ብቻ የተያያዘ መሆን የለበትም… በውጪ እንደሚወራውም አይደለም፡፡ ድሬዳዋ ከተማ ከፋይ ክለብ ነው፡፡ ገንዘብ ያወጣል ይባላል ይሄ ግን ስህተት ነው፡፡ ድሬዳዋ ከተማ አሁን ባለው አሰራር ውጤት ሊያመጡ በሚችሉ ወጣቶችና ያልተጋነነ ክፍያ በመፈጸም ውጤት ለማምጣት እየሰራ ያለ ክለብ ነው ይሄ ነው እውነቱ…. ትላልቅ ዝውውር ያደረጉ ክለቦች ውጤት ሊጠብቁ ይችሉ ይሆናል፡፡ በአውሮፓ ከፍተኛ ዝውውር ያደረጉ ክለቦች የውጤት ማጣት ሲገጥማቸው ይታያል፡፡ ግን በትዕግስት ቡድኑን ሲያግዙ ይታያል፡፡ ይሄ ነው መሆን  ያለበት… ከፍተኛ ዝውውር ስላደረክ ብቻ ውጤታማ ልትሆን አትችልም፡፡ አምናኮ መቻልና ሲዳማ ቡናን ጨምሮ ወደ ስምንት ክለቦች ላለመውረድ ይጫወቱ ነበር… የተጋነነ ወጪ ባለማድረግ ክለቡን ለአደጋ ባለማጋለጥ በደረጃው በሚመጥነው ስብስብም ተፎካካሪ ማድረግ ይቻላል የሚል እምነት ስለነበረን በዚህ እምነት ቡድኑን አጠናክረን ውድድሩን ጀምረናል… በርግጠኝነት መናገር የምፈልገው ድሬዳዋ ከተማ ከፍተኛ ወጪ ካላወጡና ትላልቅ ዝውውር ካላደረጉ ጥቂት ክለቦችም መሃል አንዱ ነው ብዬ እናገራለሁ።

ሊግ:- በደመወዝ ክፍያ ከማይታሙ ክለቦች መሀል አንዱ ድሬዳዋ እንደመሆኑ የተረጋጋ አመራር ያለው ክለቡ ውጤት ቢጠብቅ ተገቢነት የለውም ….?

አስራት:- ቡድን ብለህ ለውድድር እስከቀረብክ ድረስ ውጤት መጠበቅ የግድ ነው… ይሄ አያከራክርም ነገር ግን  ድሬዳዋ ከተማ የተረጋጋና ለስፖርት ትኩረት የሚሰጥ አመራር ያለው የተረጋጋ ቡድን ያለበት መሆኑ ይታወቃል…ደመወዝና ጥቅማ ጥቅምን በወቅቱ መክፈል ለቡድናችን ተጨማሪ ድጋፍ ነው ብዬ እቀበላለሁ… ከፈልክም አልከፈልክም ግን አንድ ቡድን ውድድር ላይ እስከገባ ድረስ ውጤት መጠበቁ አይቀርም፡፡ በዚህ መንገድ ቢታይ ደስ ይለኛል።

ሊግ:-  አምና ልዩ ክስተት ቡድን ኢትዮጵያ መድን ነው ተብሏል… ዘንድሮስ የተለየ ቡድን ገጥሞሃል ..?

አስራት:- በዘንድሮ ውድድር ፉክክሩ ጠንካራ ሆኗል… ገና ስለሆነ ቶሎ ለማድነቅም እንዳንቸኩል እሰጋለሁ፡፡ ጥሩ አልነበሩም የተባሉ ቡድኖች ድንገት ተሻሽለው ሊቀርቡም ይችላሉ… ነገር ግን እስካሁን ባየሁት ወላይታ ድቻ ልቤን ሰርቆታል፡፡ ፋሲል ከነማ  ወደራሱ ሪትም ሲገባ አስቸጋሪ ቡድን እንደሚሆን አይተናል፡፡ ባህርዳርም … ኢትዮጵያ ቡናም በወጣቶቹ ጥሩ እንቅስቃሴ እያደረገ ነው።

ሊግ:- ውልህ ላይ አራት ተከታታይ ጨዋታ ከተሸንፍክ ስንብት እንዳለ ይገልጻል… በቀጣይ ደግሞ የምትገጥመው የሚገርም ቡድን የሆነብኝ ካልከው ወላይታ ድቻና ውጤት ጠምቶት አሰልጣኙን ካሰናበተው ሲዳማ ቡና ጋር ነውና የሆነ ስጋት አልተሰማህም..?

አስራት:- በጣም ትኩረት የሰጠህው በኔ ነጥብ መጣልና በእኔ ኮንትራት ዙሪያ ብቻ ሆነኮ..?

ሊግ:- ምክንያቴ ምን መሰለህ … ስጋት ውስጥ ያለውን ጫና ምን ያህል ለመቋቋም ዝግጁነቱ አቅሙ አለህ የሚለውን ማወቅ ፈልጌ ነው…?

አስራት:- የትኛውም አሰልጣኝ ውጤት ከሌለው ስጋቱ አይቀርም፡፡ ይሄ ግልጽ ነው፡፡ ከዚያ ውጪ በእኔና በክለቡ ውል ላይ የተቀመጠውን ማሳካት ካልቻልኩም መለያየቱ የግድ ነው፡፡ መላው አለም ላይም የሚሰራው እንዲህ ነው፡፡ በይበልጥ ስጋቱ ላይ ብቻ ስላተኮርክ ነው፡፡ በጎ ነገሮችም አሉኮ /ሳቅ/ በዚያ ላይ ሊጉ መቋረጡ ሁሉም ክለብ ራሱን እንዲያይ ክፍተቱ ላይ እንዲሰራ እድል ይሰጣል ….  አምና የዋንጫ ተፎካካሪ የነበሩና ከፍተኛ ነጥብ የነበራቸው  ክለቦችኮ አሁን ታች ናቸው.. ያ ማለት ግን እዚያው ይቀራሉ ማለት አይደለም፡፡ ለውጥና ተስፋ የሌለው ቡድን ከሆነ ግን ከውጤት ማጥፋት ጋር መያያዙ አይቀርም

ሊግ:– ቅዱስ ጊዮርጊስን ለተከታታይ  አመታት ሻምፒዮን ካደረጉ ተጨዋቾች መሃል ወደ 8 የሚጠጉ ቋሚ ተሰላፊዎቹን ለቆ በወጣት ተጠናክሮ ቀርቦ ሊጉን እየመራ ነው… ዋንጫውን በነዚህ ተጨዋቾች ቢወስድ የ15ቱን ክለቦች ሞራል አይነካም ..?

አስራት:- በፍጹም አይነካም ጥያቄው ራሱ አግባብ የለውም /ሳቅ/ ውድድሩ ራሱ አንድ አሸናፊ ይኖረዋል ሌሎቹ ተፎካካሪ ይሆናሉ… በቃ እውነቱ ይሄ ነው.. ከማፈር ሞራል ከመነካት ጋር አይገናኝም … ሌሎቹ  ክለቦች ውጤታማ ለመሆን ጠንክረው እንዲፋለሙ የሚያደርግ አመት ይሆናል ብዬ አስባለሁ፡፡ በውድድር ላይ የሀገራቸውን ሊግ ለረጅም ጊዜ አከታትለው የሚወስዱ ክለቦችኮ አሉ… በላሊጋው ሪያል ማድሪድና ባርሴሎናን ማንሳት ይቻላል፡፡

ሊግ:- ሁለት ወይም ከበዛ ሶስት ተጨዋቾችን እንጂ ከመጀመሪያ ቋሚ አስራ አንድ ተጨዋች ሰባቱን አሰናብተው አያውቁም የጊዮርጊስን ለየት ያደረገው ይሄ ነውኮ አሰልጣኝ አስራት…

አስራት:- ዝርዝር ውስጥ አልገባም፡፡ የቅዱስ ጊዮርጊስ አመራሮች በራሳቸው መንገድ ነው እያካሄዱ ያሉት… ስለ እውነት ለመናገር ቅዱስ ጊዮርጊስ ውጤት እያመጣ መቀጠሉ መደነቅ ነው ያለበት… ግን ገና 25 ጨዋታ ስለቀረ ይሄ ነገር ላይ ብዙ እንድናወራ ያደርጋል ብዬ  አላምንም፡፡ ጠንካራ ተፎካካሪዎች ያሉበት የውድድር አመት ይሆናል ብዬ ስላሰብኩ ስለዋንጫው ወደፊት ብናወራ ይሻላል፡፡

ሊግ:- የእውነት ግን የውድድር አመቱ  ጠንካራ ፉክክር የሚደረግበት ነው ማለት ይቻላል ..?

አስራት:– ይሄማ የሚያከራክር አይደለም.. አብዛኛው ክለቦች በደንብ የተዘጋጁበት ጠንክረው የመጡበት አመት ይመስለኛል… ከአሁን በኋላ ያለው ፉክክር እየከበደ የሚሄድ ይሆናል ብዬ አስባለሁ ….ታች ያሉ ክለቦችም ማንም በቀላሉ ያሸንፋቸዋል ብዬ አላምንም፡፡ በፊት በፊት ትላልቅ ክለቦች ባላቸው ነጥብ ላይ 3 ነጥብ ደምረው የሚመጡ ነበር፡፡ ዘንድሮ ግን ያንን አናይም …እነ አምበሪች ጥሩ ቡድን አላቸው ጥሩ ይፎካከራሉ፡፡ ነገር ግን በገጠማቸው የልምድ ማነስ ውጤት አጥተዋል … ያም ቢሆን 3 ነጥብን በቀላሉ ማግኘት የሚቻልበት አመት አይመስለኝም፡፡

ሊግ:- ከብሄራዊ ቡድንና ከክለብ የአሰልጣኝነት ሃላፊነት ከባዱ የትኛው ነው..?

አስራት:- ሁለቱም ይለያያሉ… ብሄራዊ ቡድን ሀገራዊ ብሄራዊ ስሜት ሃላፊነት ይዘህ ነው የምትሰራው፡፡ ሀገር የምትወክልበት ነው፡፡ እንደ ክለብ ቶሎ ቶሎ ውድድሩ አይካሄድም በውድድሩ ሲመለስ ግን ሁሉም ሀገሩ እንድትቀድም ይፈልጋልና ጫናው ከበድ ይላል..

ሊግ:- የሚደግፉት ክለብ ሲተች ዘራፍ የሚሉ ደጋፊዎች ዋሊያዎቹና አባላቶቻቸው ሲሰደቡ አላስፈላጊ ትችት ሲወርድባቸው ያን ያህል ሲቃወሙ አላየሁም.. ደሜ ነው ብለው የሚፋለሙት ለክለባቸው ነውና ጫናው የነሱ አይበልጥም ..?

አስራት:- ሃላፊነቱን ካየን ሀገራዊው ይበልጣል፡፡ ውድድሮቹ ውስን ናቸው፡፡ በውስን ጨዋታ ውጤት ማምጣት ይጠበቅብሃል … ለአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ ጥቂት ጨዋታዎች ላይ የምታመጣው ውጤት ይወስናል፡፡ የክለብ ግን ቶሎ ቶሎ ውድድር የሚኖርበት ውሳኔዎች ቶሎ ቶሎ የሚታዩበት  ውጤት የሚፈለግበት መሆኑ የተለየ ያደርገዋል፡፡ በክለብ ውድድር ብዙ አሰልጣኞች የማይረጋጉበት በመሆኑ ጫናው ከባድ ነው….

ስለጫናው ላልከኝ የክለብ ጫናው ይበዛል ውድድሮቹ ተደጋጋሚዎች፣ ተደጋጋሚ ውጤት የሚጠበቅበት ነው፡፡ /ውጤት ካመጣህ ግን ጫናው የሚቀንስ ይመስለኛል/ የብሄራዊ ቡድኑ ሃላፊነት ጫና የሌለበት ይመስላል፡፡ ግን በደንብ አለው ጫና ውስጥ ላለመግባት አሰልጣኙ የሚወስደው ርምጃ ይወስነዋል ባይ ነኝ፡፡

ሊግ:- በጣም የምትታወቀው በሴቶች እግር ኳስ ነው …አሁንስ አልናፈቁህም..?

አስራት:– /ሳቅ በሳቅ/ ወደ ብሄራዊ ቡድን ከመጣሁ በኋላ ቢዚ ሆኜ ስለነበር እንደልቤ ማየት አልቻልኩም፡፡ የብሄራዊ ቡድኖች ጨዋታን የማየት እድል ነው የገጠመኝ ጨዋታዎችን ለማየት እሞክራለሁ፡፡ እንደ ሀገር ውጤቱ እንዲመጣ እመኛለሁ የሊግ ውድድሮችን ማየት ግን ናፍቆኛል።

ሊግ:- ወደ ሴቶች እግርኳስ የመመለስ ፍላጎቱስ አለህ ..?

አስራት:- አይመስለኝም በሴቶች እግር ኳስ ላይ ሳላርፍ ለተከታታይ 13 አመታት ሰርቻለሁ፡፡ ከ17 እና 20 አመት በታችም ውጤታማ ነበርኩ፡፡ በሴቶች እግርኳስ ላይ ውጤታማ ሆኜ ሉሲዎችን የማሰልጠን እድል የተነፈኩ ብቸኛ አሰልጣኝ ስለሆንኩ  እውነት ለመናገር ተስፋ ቆርጫለሁ፡፡ አሁን ያለሁበትን ስራ ማጠንከር ነው የምፈልገው…

ሊግ:- ቦታውን እንደሚያውቅ አሰልጣኝ ለአዲሶቹ የዋሊያዎቹ አሰልጣኞች ምን ትላለህ..?

አስራት:- አሁን በዋሊያዎቹ ሃላፊነት ስር ያሉት ሶስቱ አሰልጣኞች በሀገሪቱ ከሚገኙ ታላላቅ አሰጣኞች መሃል የሚገኙ ናቸው ….ዋና አሰልጣኙ ገ/መድህን ሃይሌ የብሄራዊ ቡድኑ ተሞክሮ ያለው በሊጉ ከሚገኙ አሰልጣኞች መሃል ጠንካራው ከሚባሉ መሃል ይገኛል፡፡ ከረዳቶቹ ጋር በመሆን አንድ ነገር ያሳካሉ ብዬ አምናለሁ… የክለቦቹም ውድድር የመጨረሻ ግብ ለሀገራቸው አንድ ነገር ለማበርከት ከመሆኑም በተጨማሪ  የሀገሪቱ ውድድር ስኬታማ ሲሆን ክለቦች  አሰልጣኞች አመራሮች ፈታ የሚሉበት እንደመሆኑ መልካም እንዲገጥማቸው እመኛለሁ።

ሊግ:- የመጨረሻ ጥያቄ… ለድሬዳዋ ከተማ ደጋፊዎች የምትለው አለ..?

አስራት:-  እንደ አጋጣሚ ውድድሩ በዲ ኤስ ቲቪ አለመተላለፉ ውጤት መጥፋቱን እንጂ የቡድኑን  እያደገ ያለውን አቋም ማየት አልተቻለም…  በነጥቡ ምክንያት ስጋት እንደሚገባቸውም ይገባኛል… ጠንክረን ሰርተን ስጋቱን የማስወገድ ሃላፊነት አለብን፡፡ ያንን ለማድረግ እየሰራን ነው፡፡ ደጋፊዎች ሲቃወሙም ሲደግፉም ቤታቸው ሆነው ነውና እኛ ደግሞ ደጋፊያችንን ከቤት አስወጥተን ወደ ውድድር መድረክ የመመለስ ስራ እንሰራለን ብዬ አምናለሁ።

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

ትኩስ ዜናዎች

P