Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“9 አመት በስልጠና ቆይቼ ልምድ የለህም ብባል አልቀበልም” አሰልጣኝ በረከት ደሙ /አርባምንጭ/

በተጨዋችነት  ዘመኑ ለአርባምንጭ ጨርቃጨርቅ ፣ አየር ሃይል፣ መተሃራ ስኳር፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ኒያላና  አርባምንጭ ከነማ ተጫውቷል። በተለይ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አራት አመት ለአርባምንጭ ከነማ ደግሞ 5 አመት  የተጫወተባቸው  ክለቦቹ ናቸው…  በአሰልጣኝነት ተጫውቶ ያሳለፈበትን አርባምንጭ ከተማን ይዞ በአንድ አመት ውስጥ  ከከፍተኛ ሊግ  ወደ ፕሪሚየር ሊጉ እንዲያልፉ  አድርጓቸዋል… ከደቡብ ክልል ርዕስ መስተዳድር ጀምሮ መላው ህብረተሰቡን በደስታ ያሰከረው አሰልጣኝ በረከት ደሙ ከሊጉ ዮሳፍ ከፈለኝ ለቀረቡለት ጥያቄዎች የሚከተለውን ምላሽ ሰጥቷል።

ሊግ:-  አርባምንጭ ከነማ  በወረደበት አመት ዳግም ወደ ፕሪሚየር ሊጉ በመመለሱ እንኳን ደስ አላችሁ..?

በረከት:- በጣም አመሰግናለሁ… እውነት ነው ደስ ብሎናል።

ሊግ:- አቀባበሉ ተመቻችሁ..? የሚገባንን አገኘን ማለት ትችላላችሁ..?

በረከት:- አዎ በጣም ተመችቶናል … ቡድኑ ሲወርድ  ደጋፊው ተጨዋቾቹ እኛም አጠቃላይ ተበሳጭተን ነበረና  ያንን ሀዘን ለማካካስና ለማስረሳት እንፈልግ ስለነበር  ራሳችንን ጫና ውስጥ ከተን ወደ ውድድር በመግባት ስለተሳካልን ህብረተሰቡን ደስተኛ ስላደረግን ደስ ብለኛል። በዋናነት ለሽልማት ሳይሆን  ሃላፊነታችንን ለመወጣት በመሆኑና ስላሳካነውም። ተደስተናል ለሰራነው ላመጣነው ውጤት  ደስተኛ ነን  በውጤቱም ሌሎች ነገሮች ተከትለውናል በሆነውም ነገር ደስ ብሎናል።

ሊግ:- የህዝቡስ ስሜት ምን ይመስል ነበር..?

በረከት:- ደጋፊው አምና  ቡድኑ ሲወድቅ በጣም አዝኗል  ቅርበት ስለነበረን የሀዘኑን ልክ አይተናል እኛም ብንሆን ስራችን አንድ ርምጃ ወደኋላ ስለመለሰብን ተከፍተናል  በአመቱ ሀዘኑ ወደ ደስታ ተቀይሮ ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ ነው። ደስታውን የገለጸው ይህም አስደስቶናል.. ተመጣጣኝ ምላሽ ነው የሰጠነው። የህዝቡ አቀባበል ቀጣዩ የቤት ስራችንን ከባድ ያደርገዋልና ይህን አደራ ለመቀበልና ጠንካራ ስራ ለመስራት አበረታቶናል ደስተኞች ነን አቀባበሉ ቀጣዩ ስራን ከባድ እንደሆነ አሳይቶናል።

ሊግ:- ከደረሷችሁ የደስታ መግለጫ ውስጥህን የነካህ የነማን ነው..?

በረከት:- ብዙ የደስታ መግለጫ ተልኮልናል ርዕሰ መስተዳደሩን ጨምሮ የሰፈር ሰው ጓደኞቼ በርካታዎቹ እንኳን ደስ አላችሁ የሚል መልዕክት ልከውልናል….  እግርኳስ ስልጠና ውስጥ ወደ 9 አመት ቆይቻለሁ…  ከታዳጊዎች ጋር ረጅም ጊዜ ሰርቻለሁ  ከ13 አመት ጀምሬ ይዣቸው የማሰራቸው ታዳጊዎች ነበሩ አሁን ወደ 17 እና 18 አመታቸው ጋር እየተጠጉ ነው ወደ ትልቅ ደረጃ ለመድረስ እየተንደረደሩ ነው።  እነሱን  ሳሰራ ከኳሱ ውጪ ዲሲፕሊንድ ሆነው እንዲያድጉ ትልቅ ስራ ሰርቻለሁ  ከሜዳ ውጪ ያሉ ነገሮች ለእግርኳስ ተጨዋቾች ምን ያህል እንቅፋት እንደሚሆኑ እየነገርኩ ነው ያሰራኋቸው … ማህበራዊ ነገራቸው በስነምግባር የተሞላ መሆን እንዳለበት  እግርኳስና ትምህርታቸውን እንዴት በስርዓት ማስኬድ እንዳለባቸው እየነገርን ነው ያሳደግናቸው….  እናም በጣም  የገረመኝ ትልቅ ሰው ሆነው  ኬክ  አንዳንድ ነገሮችም ይዘው መጥተው እንኳን  ደስ አለህ ሲሉኝ  ልቤን  ነክቶኛል  ተገርሜያለሁ ሰርፕራይዝም አድርገውኛል….

ሊግ:- ምን አይነት አሰልጣኝ ነህ …? ዲሞክራት ወይም አምባገነን…?

በረከት:- እግርኳስ የራሱ የሆነ መርህ አለው .. አሰልጣኙም ሆነ ተጨዋቹ የየራሳቸው ሃላፊነት አለባቸው። ያ መከበር አለበት። ለሃላፊነቱ ድንበር አበጅተው እንዲወጡ እፈልጋለሁ… እኔም የአሰልጣኝነት  ድንበር አለኝ ያንን ለማንም አልሰጥም..የሌሎቹንም መንካት አልሻም በመርህ ደረጃ ሁሉም በአግባቡ ዲሲፕሊኑን እንዲያከብርና እንዲሰራ እፈልጋለሁ ያ ካልሆነ መርሁ በሚፈቅደው መሰረት አምባገነን እሆናለሁ። በተቃራኒው ከሆነ ዳሞክራት ነኝ የአባትና ልጅ ግንኙነት እንዲኖርም እፈልጋለሁ። በአጠቃላይ የምሆነውን ነገር የሚወስነው የሚፈጠረው ነው።  ሁሉም አመጣጡን  ይወስናል።

ሊግ:- አሰልጣኝነት እንዴት ጀመርክ ፍላጎቱ  በውስጥህ ነበረ..?

በረከት:- አዎ ተጨዋች እያለሁ ጎን ለጎን የሚያሰለጥኑኝ አሰልጣኞቼን በሀሳብም  በአንዳንድ ነገሮች አማክር ነበር። ወደ መጨረሻዎቹ ጊዜዎቼ አምበልም  ስለነበርኩ በደንብ አግዝ ነበር እነሱም ያለኝን አይተው ያቀርቡኝ ነበር ያኔ አሰልጣኝነቱን እየጀመር ኩ መጣሁ.. በዋናነት ወደ አሰልጣኝነት ስገባ በትልቅ ደረጃ ነው የጀመርኩት … የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተወዳዳሪ የነበረው አርባምንጭ ከተማን  በጉዳት ሳቆም ወዲያውኑ ም/ል አሰልጣኝ ሆኜ አንድ አመት ተኩል ሰራሁ በጊዜያዊ አሰልጣኝነት ለ6 ወር  መራሁ። ከሁለት ትልልቅ አሰልጣኞች  ማለትም አሰልጣኝ ጸጋዬ ኪዳነማሪያምና አሰልጣኝ ጳውሎስ ጸጋዬ ጋር በምክትልነት ሰርቼ ወደ ታዳጊዎቹ ሄድኩ… ከ13 አመት ጀምሮ ከ15 እና  ከ20  አመት ቡድኖችን በደንብ አሰልጥኛለሁ ….ራሴን ችዬ የሰራሁት ከ15 እና 20 አመት ቡድኖቹ ላይ ነው ከዚያ ወደ ዋናው ቡድን ሃላፊነት አምና መጣሁ በአጠቃላይ በስልጠናው 9 አመት አሳልፌያለሀ…ተጨዋች ሆኜ የአሰልጣኝነት  ባህሪ ነበረኝ  ያ ለአሁኑ ጠቅሞኛል….

ሊግ:-  የተጫወተበትን ቡድን የማሰልጠን እድል ካገኙ እድለኛ አሰልጣኞች ጋር  ትመደባለህ ማለት ነው ..?

በረከት:- /ሳቅ/ አዎ  እድለኛ ነኝ .., ደስ  የሚል ስሜት አለው…ስጫወት በነበረበትጊዜ የደጋፊውንም ይሁን የአመራሮቹን ፍላጎት በደንብ ስለማውቅ ያን ለማሳካት በአሰልጣኝነት እንድመጣ እድል ማግኘት በጣም ያስደስታል። ለዚህ ክለብ ስኬት የማልከፍለው ዋጋ የለም ሲቪዬን ከፍ ከማድረግ በዘለለ የኔነት ስሜት ይፈጥራልና ደስተኛ ነኝ። በርግጥ ሙያውን ስለምወደው ያልተጫወትኩበት ክለብን ባሰለጥንሞ ልቤ ተመሳሳይ ነው።

ሊግ:-  ቡድኑን ስትረከብ ወደ ፕሪሚየር ሊግ እንደምትመልሰው ርግጠኛ ነበርክ..?

በረከት:- አዎ … ነበርኩ … ባለፈው አመት ጥቂት ጨዋታ ሲቀረኝ ነበር ቡድኑን የያዝኩትና በዚያቼ አጭር ጊዜ ምን አይነት ለውጥ እንደሚመጣ ማየት ችያለሁ  ከዚያ ውጪ ከግማሽ በላይ አምና የነበሩ ተጨዋቾች ናቸው ቡድኑን ሳልረከብም  ጨዋታዎችን በደንብ እመለከት ስለነበር ማን የተሻለ ጥሩ እንደሆነ አውቅ ነበር ከ20 አመት በታች ያሉትን ባሳድግ ውጤታማ እንደሚያደርጉኝ አምን ነበርና ሃላፊነቱ ሲሰጠኝ  ውል በነበራቸው ተጨዋቾች ላይ አዳዲስ ተጨዋቾችንም ጨምሬ ከታች በማሳደግ ውጤታማ ሆኛለሁ ይሄ ሃሳብ ስጀምር የነበረኝ ነው… አመራሮቹም  የስራ መድረክና ነጻነት ሰጥተው ሁኔታውን ስላመቻቹልኝ በጋራ ውጤታማ ሆነናል..

ሊግ:- የዘንድሮ  አመት ውድድር ቀላል ነው ጥሩ በጀት የነበረው ማለፍ ይችላል እናንተም ኢትዮ ኤሌክትሪክ የተሳካላችሁም ለዚህ ነው የሚሉ ወገኖች  አሉ..ምን ምላሽ አለህ..?

በረከት:-  ይሄ ውድድሩን ያላየ  ሰው መረጃ ነው ብዬ ነው የማምነው…. ውድድሩ ከዚህ ቀደም ከነበረው በበለጠ ትግል እንደነበረው ያየ ይመሰክራል ፋይናንስ በራሱ ብቻ ውጤት ያመጣል የሚል እምነቱ የለኝም። በውጪም ሆነ በሀገር ውስጥ ያየነው ይህንን ነው።  ጥራት ያለው ተጨዋችን መሰብሰብ ይሁን ፋይናንስ ብቻቸውን ውጤት አያመጡም። የነገሮች ድምር ውጤት ብቻ ይመስለኛል ምድባችን ምድብ ለ ውስጥ እነ ሸገር ከተማን ተመልከት አንደኛ ዙር ላይ የነበረው ብቃት የሚገርም ነበር አርሲ ነገሌና ሌሎቹም በጣም ተፎካካረመ ነበሩ… እኛ ማለፍን ብቻ አስበን ተዘጋጅተን አለፍን እንጂ ትግልማ ገጥሞናል ሸገር ከተማ የተሻሉ ተጨዋቾች የተሻለ የሚባል የፋይናንስ አቅም ነበረው ግን አላለፈም  የቤት ስራችንን ጠንክረን ስለሰራን ተሳካልን እንጂ የሊጉ ውድድር ከባድ ነበር…..አምናና ካቻምና የነበሩ ውድድሮችን የማየት እድሉ ነበረኝ የዘንድሮው ይለያል።

ሊግ:-  ከምድቡ እንደምታልፉ ርግጠኝነት የተሰማህ በየትኛው ጨዋታ ነው…?

በረከት:- አንደኛ ዙር ውድድርን የጨረሰነው  ተከታዩ አርሲ ነገሌን በ5 ነጥብ በልጠን ነው  ውድድሩ በሁለተኛ ዙር ሲጀመር የመጀመሪያ ጨዋታ የነበረን 3ኛ ከነበረው  ሸገር ሲቲ ጋር ነው። ይህን ጨዋታ ካሸነፍን የማለፍ እድላችን ሰፊ ነው ብለን ጠንክረን ገብተን  አሸነፍን …ያኔ ነው የፕሪሚየር ሊግ ተሳትፎ ለማግኘት አንድ እግራችን ቀድሞ እንደረገጠ ያመንኩት ..

ሊግ:- አጠቃላይ አመቱን ስናይ የተሸነፋችሁት አንድ ጨዋታ ብቻ ነው ….ሽንፈቱን በጸጋ ተቀበልከው..?

በረከት:-  እውነት ነው  26 የዙር አንድ የፍጻሜውን ሲጨመር  ከ27 ጨዋታ የተሸነፍነው አንዴ ነው  አንዷም ሽንፈት የገጠመን አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ነው 14 ተከታታይ ጨዋታ አሸንፈን። በ15ኛው ጨዋታ በ94ኛው ደቂቃ ላይ በተቆጠረ ግብ  ነበር የተሸነፍነው ….

ፕሪሚየር ሊግ ለመግባት እንጂ ለሪከርድ አልነበረምና  አልተበሳጨሁም በዚያ ላይ ከተከታያችን የ12 ነጥብ ልዩነት ስለነበረን ብዙም አላሰሰበንም ባይሆን ትንሽ የተበሳጨሁት በኢትዮጵያ  ዋንጫ በሀዋሳ ከተማ  ስንሸነፍ ነው በሩብ ፍጻሜ ተገናኝተን ወደ 40 ቀን አካባቢ ከውድድር ርቀን መጥተን ስንጫወት የተወሰኑት ተጨዋቾቼ ጉዳት ላይ ስለነበሩ በጥቃቅን ስህተትና በማች ፊትነስ ድካም በመሸነፋችን ተናድጃለሁ… በተረፈ በአመቱ ጉዞ የተከፋሁበት ጨዋታ የለም።

ሊግ:- ለአራት አመት የተጫወትክበት ኢትዮጵያ ንግድ ለፕሪሚየር ሊጉ ዋንጫ ከጫፍ ደርሷል …ምን ትላቸዋለህ..?

በረከት;-   እኛ ከተጫወትን ከትንሽ ጊዜ በኋላ ፈረሰ መባሉን ስሰማ  ዘጣም አዝኜ ነበር..የፋይናንስ ችግር የለበትምና ለምን ፈረሰ ብዬ ተከፋሁ.. ከአመታት በኋላ እንደገና ተመስርቶ  ወደ ፕሪሚየር ሊግ  ሲመለስ ደስ አለኝ። አሁን ደግሞ ለዋንጫ እየተፋለመ  መሆኑ ደስ የሚል ነው ለገለልተኛ ደጋፊም  የሚያስደስት ምርጥ እንቅስቃሴ ነው  የሚያደርገው.. አሰልጣኞቹ በጸሎትና ሲሳይም  ከአደረጃጀት ተጨዋች ከመመልመል ከታክቲክም አንጻር ጠንካራ ስራ እንደሰሩ ያስታውቃልና  እንደኔ እምነት ዋንጫው  ይገባቸዋል።

ሊግ:- አርባምንጭን አስተዋውቅ ብትባል በምን ትገልጻታለህ..?

በረከት:- አርባምንጭን የምገልጸው የእግርኳስ ከተማ ናት ብዬ ነው የምገልጸው….. ማንም ሰው ይህን ያውቃል ከበፊቶቹ እነ ተስፋዬ ፈጠነ ስንታየሁ ጌታቸው /ቆጬ/ በርካታ ተጨዋቾችን ለክለቦችም ይሁን ለብሄራዊ ቡድን ያፈራች ከተማ ናት  ህዝቡ ከማንኛውም ነገር ቅድሚያ ለእግርኳስ ይሰጣልና እንደኔ የእግርኳስ ከተማ ብለው ቢረዱ ደስ ይለኛል።

ሊግ:- የክለቡ አመራሮች በፕሪሚየር ሊጉ ዕድል ሊከለክሉኝ ይችላሉ ብለህ ትሰጋለህ…?

በረከት:- ኧረ በፍጹም …. ፕሪሚየር ሊጉን ተቀላቅለናል ለቀጣዩ ጉዞ ዝግጅት ወደማድረጉ ነው የምንገባው …

ቀሪ ኮንትራት አለኝ። ስለ ስንብትም አልሰጋም የሚፈለገው ልምድ አለኝ   ልምድ በእድሜ ብቻ አይደለም … 9 አመት በስልጠና ጥሩ ልምድ ነው።

9 አመት በስልጠና ቆይቼ ልምድ የለህም ብባል አልቀበልም ….በዚህ መልኩ እነ በጸሎትም የተወሰነ ተገፍተው ነበር  ነገር ግን ወደ ትራኩ ሲመጡ ምን መስራት እንደሚችሉ አሳይተዋል። በውጪውም እነ አርቴታ እነዣቪ አሎንሶ እነ ኔግልስማን ልምዳቸው ሳይሆን እውቀታቸው ውጤታማ አድርጓቸዋልና   የኔም አመራሩ ያለኝን አቅም አይቶ ነው ሃላፊነቱን የሰጠኝና የመሰናበት ስጋት የለኝም …. በራሴ እምነቱ አለኝ በቀጣይ አመትም ከክለቡ ጋር ቀጥዬ የተሻለ ነገር እሰራለሁ እንጂ የመሰናበት ስጋት ተፈጥሮብኝም አያውቅም።

ሊግ:- ደግሞ ላለመመለስ ዝውውር  ላይ መስራት ይጠበቃል …ለዚህ ዝግጁ ናችሁ.?

በረከት:- በዚህ አመት የዋንጫ አሸናፊ ብንሆንም የየተወሰኑ ጉድለቶች ይኖሩብናል ከቦርዱና ከቴክኒክ ዲፓርትመንቱ ጋር  ተወያይተን በክፍተቶቹ ላይ የተወሰኑ ተጨዋቾችን ጨምረን ጠንካራ ቡድን ይዘን እንደምንቀርብ  ርግጠኛ ነኝ።

ሊግ:- የውጪ ኳስ ታያለህ ….? በፍልስፍናው ማን ሳበህ..?

በረከት:- በደንብ ነው የማየው ሁሉንም ጨዋታ አይቻለሁ ማለት እችላለሁ እነሱ በትልቅ ደረጃ ነው የሚጫወቱት። ሁሉም ጠንካራ ነገሮች አሏቸው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አድናቂ  ነኝ  ያሉት አሰልጣኞች  ጥሩ ነገር አላቸው በይበልጥ የማን.ዩናይትድ አድናቂና ደጋፊ ነኝ። እንደ ባለሙያ ሳየው አሁን ያለው የቡድን ግንባታው ጥሩ ነው ብዬ አላምንም።  የሜዳ ላይ ውጤትና እንቅስቃሴውም  የሚያሳየው ይህንን ነው በሂደት እንጂ በአንድ ጀንበር ቡድን አይገነባምና በቀጣዩ ሁለት አመታት በችግር ውስጥ ሆኖ የሚያሳልፍ ይመስላል።  አሁን ዩናይትድን የያዘው ባለቤት እውቀቱ ጥሩ ስለሆነ ግን የሚስተካከልም ቡድን  ይመስላል በተቃራኒው በቅርብ አመታት ውስጥ አርሰናል እየገነባ ያለው የቡድን ግንባታ የወደፊቱ  ጥሩ ቡድን ይሆናል የሚል እምነቱ አለኝ ካላቸው የተጨዋቾች  እድሜና ጥራት አንጻር በሂደት ቡድኑን እየገነቡበት ያለው መንገድ ጥሩ ነው

ሊግ:-  ቅዱስ ጊዮርጊስና  ጅማ አባጅፋር ባደጉበት አመት የሊጉ ዋንጫ አሸናፊ ሆኑ  ኢትዮጵያ ንግድ ባንክም በተመሳሳይ  ባደገበት አመት የሊጉን ዋንጫ ሊያነሳ ከጫፍ ደርሷል…ይሄስ  ውጤት በአንድ ጀንበር አይመጣም ከሚለው ጋር አይጣረስም..?

በረከት:- ቆይ ቆይ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ውጤታማነትን ላብራራልህ …. ክለቡ የፋይናንስናና አስተዳደራዊ ችግር የለበትም  የቡድን  ግንባታቸውን ደግሞ እንይ… አምና በፕሪሚየር ሊጉ አንደኛ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሁለተኛ ባህርዳር ከተማ ሶስተኛ ኢትዮጵያ መድን ሆነው አጠናቀቁ ባንክ ቡድን ሲገነባ  ከቅዱስ ጊዮርጊስ  ሱሌይማንና አዲስን ወሰዱ ከባህርዳር ፈቱዲን፣ ፉአድና ተስፋዬን አስፈረሙ ከኢትዮጵያ መድን ዋና የሚባሉትን ባሴሩ ሀብታሙ ሲሞንና ኪቲካን  ወሰዱ….የማሸነፍ ስነልቦና ካላቸው ሶስቱ ክለቦች ዋና የሚባሉትን አስፈረሙ  ካሳደጓቸውና ከተለያዩ ቡድኖች አምጥተው ነው ቡድናቸውን የገነቡት.. ይሄ በአስተዳደራዊ ና ፋይናንሳዊ ችግር አለመኖር በጥሩ አሰልጣኞች ስር መሰራቱ ወደ ውጤት አምጥቷቸዋል እንደዚህ የሚሆንበት ጊዜ አለ…

ከነዚህ መሃል አንዱ ከጎደለ ግን የቡድን ግንባታው ይበላሻል  በዚያ ላይ ሊጉ እንደ አምና ጠንካራ ፉክክር የለውም በቅዱስ ጊዮርጊስና ፋሲል ከነማ ይደረጉ የነበሩት ፉክክሮች ቀንሰዋል የሊጉ ተፎካካሪ ክለቦች ድክመት አግዟቸው የባለሙያዎች ቡድን ግንባታ አቅምና ጥንካሬ እንደተጠበቀ ሆኖ ለአሁኑ የዋንጫ ጉዞ በቅተዋል።

ሊግ:-  ጨረስኩ…. የመጨረሻ ቃል ካለህ….?

በረከት:- በመጀመሪያ  ለዚህ ውጤት ያበቃኝ ፈጣሪ የተመሰገነ ይሁን … ያለኝን አአቅምና ብቃት ተገንዝበው  ሃላፊነት የሰጡኝን የቡድኑን አመራሮች ማመስገን እፈልጋለሁ። አብረውኝ በጸሃይና በአቧራ ሲሰቃዩ የውጤት ረሀብተኛ ሆነው ሲሰሩ የነበሩን ረዳቶቼን   እና ተጨዋቾቼን አመሰግናለሁ …ቤተሰቦቼንም  በጣም አመሰግናለሁ በታዳጊ እድሜያቸው ያሰለጠንኳቸው ሁሉም ተጨዋቾች ነገ ውጤታማ ሲሆኑ ማየት እፈልጋለሁና  በርቱ ማለት እፈልጋለሁ…. አመሰግናለሁ።

 

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

ትኩስ ዜናዎች

P