Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“ለሴቶች መብት ስሟገት ይጣሉኛል አይወዱኝም አያከብሩኝም” አሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛው /ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች አሰልጣኝ/

/እኔ ማለት  ምንም ቅያሪ ልብሰሰ የሌለኝ ምንም የመኖር ዋስትና የሌለኝ በተጨማሪ ቁርስና ምሳ ለመብላት የማልችል ሰንበቴ አርባ እንዲሁም የተለያዩ ድግሶችን እየፈለኩ የምበላ የሆቴል ትራፊን የምፈልግ ሰው  ነበርኩ..ይሄ ነው የሚገልጸኝ …ፈጣሪ ብሎ ቀን አምጥቶ ለዚህ ደረጃ አብቅቶኛልና አመሰግነዋለሁ/

እንቁላል ንግድ  ክስረት  ወደ እግርኳስ አሰልጣኝነት   ስኬት የእንግዳችን የአሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛው የህይወት አካል ነው…..እንቁላል  የሸጠበት ብር በመዘረፉ አንድ ሳምንት የጎዳና ተዳዳሪ እንደነበረም ያወጋል..ወደ እግርኳሱ አሰልጣኝነት ሲመጣ ባለፉት 25 አመት 25 ዋንጫ በማሸነፍ የድል ታሪኩን የከሰተ አሰልጣኝ ነው ብርሃኑ ግዛው… ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በድል ተንበሽብሿል…. ባለፉት አራት አመታት የአመቱ ኮከብ ሽልማትን ደጋግሞ ወስዷል… አሁን ደግሞ በማንም የሀገሪቱ ክለብ ያልተደፈረ ታሪክ ሰርቷል። ኡጋንዳና ኬንያ ላይ ያልተሳኩ ግን ልምድ የሰጡ ታሪኮቹ ለአሁኑ ስኬቱ መንገድ ጠርጓል። የሴካፋ ዞንን በአፍሪካ የሴቶች ሻምፒየንስ ሊግ የመወከል ስኬትን አምጥቷል። ኢትዮጵያ ያዘጋጀችውን ውድድር በማሸነፍ በሻምፒየንስ ሊግ የመሳተፍ ዕድልን ያሳካው አንደበተ ርቱዕ የሆነው አሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛው ሙሉ ግልጽነት የታየበትን ቃለምልልስ ከሊጉ ዮሴፍ ከፈለኝ ጋር አድርጓል መልካም ንባብ…..

ሊግ:– እንኳን ደስ አለህ …ህልምህን እየኖርክ ነው  ማለት ይቻላል ..?

ብርሃኑ:– አዎ …በጣም ተደስቼ  ፍልቅልቅ ባለ ርካታ ውስጥ ነው የምገኘው …. ወደር የሌለው ደስታ ውስጥ ነኝኮ …. የአራት አመት ቁጭቴ ምላሽም ያገኘሁበት … ፕሪሚየር ሊጉ ከተጀመረ ባለፉት ሶስት አመታት  ለመጨረሻ ጊዜ ቀርበን  የተሳካው አሁን መሆኑ ደስታዬን የተለየ አድርጎታል…ህልሜንም እየኖርኩ ነው።

ሊግ:-  ጭፈራህ ..ደስታን የሚያሳብቀው ፊትህ…. ለጥ ብለህ ሜዳው ላይ የተኛህበት ስሜት እንዴት ይገለጻል..?

ብርሃኑ:- አንደኛ እልህ የተሞላበት ነው …. የማሸነፍ ብቃት አለን  ብዙውን ጨዋታ አሸንፈን አራቱ ውስጥ ስንገባ እንቸገራለን …የዋንጫ ዕለት ደግሞ እንዲህ አይነት ብቃት አላሳየንም ዘንድሮ ግን ልዩ ነበርን …በዚያ ላይ ግቡ ሳይቆጠር 79ኛ ደረጃ ደርሶ ነበረ… ዑጋንዳና እዚህ በተካሄደው ጨዋታ ላይ  ፈተና ሆኖብን አግብተን የማናሸንፈው ምንድነው ብለን እንቆጭ ነበረና ግቡ ትልቅ እፎይታ ፈጥራልናለች ያንን ይገልጻል ስሜቱ… ሌላው ወጣት አሰልጣኞች ወይም እንደኔ የቆዩት አሰልጣኞች ጠንካራ ጎኖች  እያሏቸው ዋንጫ የሚያጡበት ምክንያት  ሀገር ውስጥ ጥሩ ሆነው ውጪ አመርቂ ውጤት ሳይኖር ታሪክ ሳይኖራቸው የሚያልፉበት ሂደት ያበሳጨኝ ነበረና ያን ሁሉ አስታውሶኛል። በርግጥ ከተጨዋቾቼ ጋር ተነጋግሬ ድል ማስመዝገብ የነበረብኝ ያለፈው አመት ነበረና ያ ሁሉ ቁጭት እልህ ውስጥ ከቶኝ  የታየ የደስታ አገላለጽ ነው… የመጀመሪያው የሚወዱኝ ለኔ የሚያስቡ ሰዎችን አስቤ ደስታዬን ለመግለጽ ሲሆን  ሁለተኛው ላላመኑብኝና በየጊዜው ቁስሌን ለሚነካኩ ሰዎች  ምላሽ  የሰጠሁበት የደስታ አገላለጽ ነው /ሳቅ/

ሊግ:- ደስታቸውን የገለጹልህ ሰዎች በርካቶች ናቸው …ላንተ ከነዚህ ውስጥ የረካህበት የትኛው ነው ..?

ብርሃኑ:- በመጀመሪያ ስኬታችን ስኬታቸው ሆኖ ለተደሰቱ ደስታቸውን ለገለጹልኝ  ደውለው ቢዚ ሆኖ ላላገኙኝ ግን ለተደሰቱ ጊዜ ወስደው ሊያወሩኝ ለፈለጉ በሙሉ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።  ነገር ግን በጣም ያልጠበኩት የተደነኩበት ክቡር ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ  እንኳን ተሳካላችሁ ማለታቸውን ስሰማ ትልቅ ደስታ ተሰምቶኛል.. .መልዕክቱን የላኩት ለአለቆቼ ነው አስበው ስለደወሉ ደስታችንን ስለተጋሩ ተደስቻለሁ እኛ የምንሰራው ለሀገር ነው እያልን የሀገር መሪዎች አይከታተሉም ለሚለው ቅሬታ ቁርጥ ያለ ምላሽ የሰጠ ለካ  መሪዎቻችን ይከታተሉናል እንድንል ያደረገ ነውና በጣም ተደስቻለሁ። ከዚያ ውጪ ሎዛ አበራ ከአሜሪካ ደውላ ደስታዋን ገልጻለች  በፊትም በፕሪሚየር ሊጉም  ስናሸንፍና በሻምፒየንስ ሊጉ ጨዋታ ልናደርግ ስንል እየደወለች ታበረታታን አይዟችሁ ትለን ስለነበር አመሰግናለሁ አሁንም ውድድሩ ካለቀ በኋላ “እግዚአብሄር በፈቀደ ጊዜ ሆኗል ኮችዬ ይገባሃል ተጨዋቾቹም ለፍተዋል ይገባችኋል። ደስ ብሎኛል ለሰጣችሁን ነገር እናመሰግናለን ” ብላኝ ተደስቻለሁ እኔም “አንቺም የጀመርሽውን የአንቺ እህቶች ጨርሰውታል” ብዬ  አመስግኛታለሁ።  እሷ ያለቀሰችውን ሳስብ  ዲዲደር ድሮግባን አስታውኛለች

ሊግ:- ..ዲዲየር ድርግባ.. ..? በየት በኩል..?

ብርሃኑ:- /ሳቅ/  ስታለቅስ እውነቴን ነው  እሱ ነው የታወሰኝ … ድሮግባ በሀገሩ ኮትዲቯር ሰላም እንዲመለስ ጦርነት እንዲቆም አልቅሶ ብዙ ያደረገ ሰው ነው። ትልቅ ስራ ሰርቷል…በአፍሪካ ዋንጫም ለፍጻሜ አልፎ  ተሸንፎ ዋንጫ አጡ አለቀሰ …በቀጣይ የአፍሪካ ዋንጫ እሱና ያን የመሰለ የከዋክብት ትውልድ ሳይኖሩ አዲሶቹ የአፍሪካ ዋንጫ አሸንፈው ዋንጫውን ወደሀገራቸው ወሰዱ።  አምና ከነበሩ ደግሞ እኔም 8 ከዋክብቶች ሳይኖሩኝ  በታዳጊ ወጣቶቹ ታሪኩ ተሰራና ዋንጫ ወሰድን ምስስሉ ድቅን አለብኝ .. ሎዛም ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ይሁን ለገሯ ትልቅ ስራ የሰራች በጓደኞቿ ደስታ ስትደሰት ማየቴ አስደስቶኛል። ገና ውድድሩ ወደ ኢትዮጵያ  ስመጣ ኮችዬ አደራ ከተጨዋቾቹ ጋር ሆነህ ባለፈው ያጣነውን በህዝባችን ፊት አሳካ ብላ ያወራችኝ …በሷ ደስተኛ ነኝ።

ሌላዋ ደግሞ ረሂማ ዘርጋው ለንግድ ባንክ ስኬት ትልቅ ታሪክ የሰራች ናት  ሁለቱም  ንግድ ባንክን ከፍ ያደረጉ ኮከቦች ናቸው ደስታቸውን ገልጸውልኛል  አበረታተውኛል

በአጠቃላይ ለሁለቱም ትልቅ ክብር አለኝ …

ሊግ:- አሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛው  እንቁላል ሽጦ ያገኘው ገንዘብ ተዘርፎ ቤት እንዳይገረፍ  ለሳምንት ያህል ጎዳና ተዳዳሪ ከነበረበት ጅማሮው …. በአፍሪካ መድረክ ክለቡን ከፍታ ላይ አውጥቶ በሀገሪቱ ጠ/ሚ ምስጋና እስከቀረበለት ሰዓት  ድረስ ያለውን ታሪኩን እንዴት ይገልጸዋል…?

ብርሃኑ:- /ሳቅ/ ይሄ በምን ይገለጻል መሰለህ ….

እግዚአብሄር አንድን ትቢያ ማንሳት ማክበድ ማግነን ይችላል … አቅም አለው  ከታች አንስቶ ለሌላ ሰው አስተማሪነት መጠቀም ሁሉ ይችላል የኔ ታሪክ እንዲህ ነው .. በፍጹም በከፍታዬ አልታበይም …ከፍ ያደረገኝን አውቃለሁ …ለእግዚአብሄር የፈጠረኝ አንድ ፍጥረቱ ነኝ ግን በጉዞው ከጎዳና ከታች አንስቶ  በእግርኳስ ውጣ ውረድ ሲገጥመው ድብደባና ጫና ሲመጣበት  ከጎኑ ሆኖ አሳልፎት  ለዚህ ያበቃው ለማስተማሪያ ያስቀመጠው አንድ ሰው ነኝ አበቃ  ክብሩን እርሱ ይውሰድ የኔ አይደለም …በተቃራኒው ሞገሱን ስለሰጠኝ ለአምላኬ ክብር ምስጋና ይግባው …

ሊግ:- ከኢቴዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጋር ያላችሁ ግንኙነት የሚደረግላችሁ ድጋፍ ምን ይመስላል ..?

ብርሃኑ:- አሪፍ ጥያቄ ነው ያቀረብከው …. በኢትዮጵያ  እግርኳስ ፌዴሬሽንን ሊመሩ በመጡ አመራሮች የምታወቀው በተናጋሪነቴ ነው። ከ1988 ኢንጂነር ግዛው ተክለማሪያም እስከ አቶ ኢሳያስ ጅራ ዘመን ድረስ ባለፉት 28 አመታት  በሴቶች እግርኳስ ላይ እንደተናገርኩ እገኛለሁ። አሁን ግን ያለውን እግርኳስ ፌዴሬሽንን ማመስገን ግዴታዬ ነው። ውድድሩ ወደ አገራችን እንዲመጣ ከመጣ በኋላም በአሪፍ መስተንግዶ እንዲመለሱ አድርገዋል ሌላ ሀገር ላይ አንዳንድ ሆቴል አይሰጡም ሁለት ብሄራዊ ቡድን አንድ ሆቴል ሊያሳርፉ ይችላሉ…. ምግብ አንድ ወይም ሁለት አይነት ሊሆን ይችላል የሚቀርበው ….ጩኧት ያለበት ገበያ አካባቢ ቦታ ሊሰጡ ይችላል እዚህ ግን ጭራሽ በከፍተኛ አመራሮችና በሀገር ባህል ነው የተቀበሏቸው ጥሩ ግንኙነት ፈጥረው እኛንም አግዘውናል ሙሉ ፌዴሬሽኑን ከልብ አመሰግናለሁ ዋና ስራአስፈጻሚው አቶ ባህሩ ጥላሁን ሙሉ ውድድር ጊዜ ከእኛ ጋር ነበሩ ተደጋግፈን ይሄን ውጤት ያመጣነውና ማመስገን እፈልጋለሁ…. ውጤቱ የህዝቡ ፣ የባለሙያተኞች ፣  የተመልካች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አመራሮችና ሰራተኞች አጠቃላይ ማህበረሰቡን ማመስገን እፈልጋለሁ

ሊግ:- 25 አመትን በ25 ዋንጫ ማጀብህ …በሌሎች አሰልጣኞች ይደፈራል …?

ብርሃኑ:- የሚገርም ታሪክ ነው … ግን አገሪቱ ያሏት አሰልጣኞች ወይም ረጅም አመት የተጫወቱ ተጨዋቾች አይመዘግቡትም እንጂ  ስኬታማ የሆኑ ይኖራሉ…

ለምሳሌ እነ ብርቱካን ከእኔ በላይ ቁጥር ያለው ዋንጫ እንዳስመዘገቡ አምናለሁ የተጫወቱባቸው ክለቦችና ያሰለጠኗቸውን አሰልጣኞች ስመለከት ርግጠኛ ነኝ ከ3, በላይ ዋንጫ ሊኖራቸው ይችላል ብዬ አምናለሁ …እንደ አጠቃላይ ግን  የኔ ውጤት  ታሪኮቼ  ሊደፈሩ የሚችሉ ትምክህት የማላሳይባቸው ናቸው…ህልም ያለው የሴቶችን እግርኳስ ጥግ እስኸ ጥግ የማሳደግ አቅም ያላቸው አሰልጣኞች ጥለውት ይሄዳሉ / በነገራችን ላይ በግል ፔጅህ ላይ አሪፍ አዴርገህ የሰራኧው የ25 አመቱ 25 ዋንጫ  የሚለው ዘገባህን አይቼዋለሁ ከልብ አመሰግናለሁ/

ሊግ:–  አንድ መረጃ አግኝቼ  ነበር …13 አሰልጣኞች ሆናችሁ የትንሳኤ ዕለት  ምግብ እየበላችሁ 9ኙ አይነጋገሩም ነበር… አሁንም ተመሳሳይ ነው ..?

ብርሃኑ:- የኢትዮጵያ ሴት አሰልጣኞች  ማህበርን መመስረት ምክንያት የሆነው ይሄ ገጠመኝ በመሆኑና አሀን ለውጥ በመፈጠሩ ደስተኛ ነኝ ይሄ ውድድር ተጀምሮ እስኪያልቅ በማህበሩ ፔጅ  ላይ ያወሩኝ ነበር  ተጋጣሚያችን ያለውን ጠንካራና ደካማ ጎን ያወሩኝ ነበር.. በግል ስልኬ ደውለውም ያወሩኝ ይመክሩኝ ነበር የተጋጣሚያችንን አሰላለፍ እየነገሩኝ አግዘውኛል  በትንሳኤ ላይ ተነጋግረን ችግራችንን ፈትተን አሁን ለሀገር በጋራ እየሰራን መሆኑ ትልቅ ለውጥ ነው በፕሬዝዳንትነት የምመራው ማህበር ውጤታማ መሆኑ አኩርቶኛል  በዚህ አጋጣሚ ሁሉንም  ከልብ አመሰግናለሁ

ሊግ:- ኬንያ ላይ ዋንጫውን ያጣነው በኬንያ አሰልጣኞች ትብብር ነው ብለህ መንፈሳዊ ቅንዓትህን ተናግረሃል . አሁንስ ቅናትህ መልስ አገኘ..?

ብርሃኑ:- /ሳቅ/ የተወሰኑ ጉዳዮች ምላሽ አግኝተዋል የሚቀሩትም በቀጣይ ጊዜያት እንደሚሻሻሉ ተስፋ አደርጋለሁ አሁን ግን ቢያንስ ስንገናኝ ሰላምታ መባባላችን ለውጥ ነው …በዚያ ላይ ፌዴሬሽኑ የወከለው ባለሙያ የኛ ማህበር አባል ነውና መረጃ ያቀብለን ነበር ተከላካይ አጥቂው አማካዩ የቱ ጠንካራ ነው የቱን ብንይዝ ንግድ ባንክን እናሸንፋለን የሚሉትን የነሱን መረጃ ያቀብለን ነበር ይሄም አስደስቶኛል ትልቅ ለውጥ ማየቴ አስደስቶኛል በቀጣይም ባለሙያዎቹ ላይ  ያየሁት ለውጥ እንደሚጠናከር ተስፋ አደርጋለሁ።

ሊግ:– ወንዶች ሚስትና ልጆቻቸውን ይወዳሉ የህብረተሰቡ  ሲሆን ግን አያከብሩም አይወዱም ማለትህን ሰማሁ … ማሳያ አለህ..?

ብርሃኑ:- /ሳቅ/ ዋናው ያልኩት አብዛኞቹ እንደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መሪዎች ደፋር አይደሉም በተለያዩ ክለቦች ውስጥ የሴትና የወንድ መሪም የቦርድ አመራርም አሉ ለወንዶች ጉዳይ ሲሆን በደንብ የሚዘረጋው እጃቸው ለሴት ሲሆን ይሰበሰባል… ወንድ ገንዘብ  ሲያገኝ እኔንም ጨምሮ አብዛኛው አጥፊ ነን  ሴቶች ግን በተቃራኒው  ወደ ቤታቸው  ያደርጋሉ። የሚገርመኝ የሴት ቡድን መያዝ ላይ አይጥሩም ትንሽ ክለቦች ናቸው ለሴቶች እግርኳሰ የሚለፉት አብዛኞቹ በተቃራኒው ነው ወይም ከሌላ ባለሙያተኛ አንጻር የሚከፍሉት አናሳ ይሆናል.. የራሳቸውን ልጅ  ይወዳሉ የህብረተሰቡን ልጅ አይወዱም ያልኩት ለዚህ ነው  ኢትዮጵያ መድን  ግዙፍ  ተቋም ነው ሁሉም የሰው ዘር ይገለገልበታል የሴት ቡድን ግን የለውም ወላይታ ድቻን ተመልከት የሴት ቡድን የለውም የወላይታ ተጨዋች ግራ ገብቷት ምርጫዋን  ወደ አርባምንጭ ታደርጋለች ስደት በለው….  ወልቂጤ ከተማዎችም ተመሳሳይ ናቸው …   በጣም የገረመኝን ልጨምር።

ሊግ:- እዚሁ ላይ ልጨምርና  ሴት ላይ የሰሩ የሚመሰገኑ ክለቦችስ የሉም ..?

ብርሃኑ:– ወደሱ ልመጣ ነው … የገረመኝ ያልኩህ ወንድ ላይ ብቻ የተንጠለጠሉት ክለቦች የክለብ ላይሰንሲንግ መጥቶ የግድ ጆሯቸው ተይዞ  ሴት ቡድን መያዛቸው ጊዜው ያመጣው መሆኑ ይገርመኛል…. እዚህ ላይ ለመጨመር ድሬዳዋ ከተማ፣ አዳማ ከተማ፣ አርባምንጭ ከተማ ፕሪሚየር ሊግ ሳይገቡ ሴት ቡድን የነበራቸውና ለሴቶች ክብር ያላቸው  ክለቦች ናቸው .. .ይሄ እውነት ነው ምስክር ነኝ….  ከዚያ ውጪ ሁሌ ለሴቶች ስምሟገት ይጣሉኛል አይወዱኝም  አያከብሩኝም ነገር ግን ለሙያው የተሰጠሁ ሰው ስለሆንኩ አልበሳጭም … ከቅዱስ ጊዮርጊስና ኢትዮጵያ ቡና ውጪ አብዛኞቹ የመንግስት ተቋም በመሆናቸው ለአንዱ ብቻ አጭቀው ከመስጠት ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ለሴትም ለወንድም እግርኳስ በሚጠቅም መልኩ ቢያደርጉ መልካም ይመስለኛል።

ሊግ:- ዝናብ አጥቦት ጸሃይ የሚያደርቀው ሁሌ የማደርገው ሱሪ ነበረኝ አልክ …በማስታወሻነት አስቀመጥከው..?

ብርሃኑ:– /ሳቅ/ ለማስታወሻነት በፎቶ አስቀምጫለሁ…

እኔ ማለት  ምንም ቅያሪ ልብሰሰ የሌለኝ ምንም የመኖር ዋስትና የሌለኝ በተጨማሪ ቁርስና ምሳ ለመብላት የማልችል ሰንበቴ አርባ እንዲሁም የተለያዩ ድግሶችን እየፈለኩ የምበላ የሆቴል ትራፊን የምፈልግ ሰው  ነበርኩ..ይሄ ነው የሚገልጸኝ …ፈጣሪ ብሎ ቀን አምጥቶ ለዚህ ደረጃ አብቅቶኛልና አመሰግነዋለሁ ያቺ ሻማ ሱሪ የዚህ መገለጫ  ናት እንደ  አጠቃላይ ተስፋ መቁረጥ እንደማያስፈልግ ወጣቶች እንዲማሩበት  ተስፋ የቆረጠ ከሞተ ሰው እኩል መሆኑን  ለመግለጽ ነው።  የኔ ታሪክ ለሰው ሁሉ ማሳያ  ነው ማለት እችላለሁ…

ሊግ:- ተጨዋቾችህ አግብተውና ወልደው  ቤትና መኪና  ገዝተው ስታይ ምን ይሰማሃል ..?

ብርሃኑ:– ከሴንትራል ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስንመጣ የምንጠራው ብር አልነበረም …ምናልባት 1500 ወይም 2500 ብር ነበር የሚከፈለን …ነገር ግን ያቺን ብር ቢያገኙም በየወሩ እንዲቆጥቡ እነግራቸው ነበር ባንኩ ስለ  ቁጠባ በየሚዲያው  ይናገራል እኔ ግን ጃንሜዳ ውስጥ  ቀድሜ  አውቅ ስለነበር ለተጨዋቾቼ አስተምር ነበር ..የባንክ አካውንታቸውን እመለከትም ነበር በዚያ ላይ ዕቁብ እየገቡ የሚደርሳቸውን ምን ላይ ማዋል እንዳለባቸው እናወራ ነበረና ግማሹ ኮንዶሚኒየም ሌላው ላዳ ይገዛል።

አንዳንዱ ደግሞ ትዳር እየመሰረተ ሳይ ኩራት ተሰማኝ ተምሳሌት በመሆኔም ደስተኛ ነኝ ከስልጠና በዘለለ ለተጨዋቾቼ ተገቢውን የህይወት መንገድ በማስተማሬ ደስተኛ ነኝ ኩራት ይሰማኛል አሰልጥኖ ሜዳ ላይ ማሸነፍ አንድ ችሎታ ይሆናል  ተጨዋቾቼ ግን ከኳሱ በዘለለ የህይወትን ግጥሚያ እንዲያሸንፉ በማገዜ ደስታ ይሰማኛል …

ሊግ:- ፈተና  ገጠመኝ ባልክበት ዘመን ከጎንህ የነበሩትን መናገር ትችላለህ..?

ብርሃኑ:- አዎ ያውም ከምስጋና ጋር ነው የምናገረው …. መጀመሪያ  የማይከዳኝ ፈጣሪዬ ሁለተኛ ቤተሰቤ ሶስተኛ ደግሞ  ተጨዋቾቸቼ አጠገቤ ነበሩ ተጨዋቾቼ ማንንም ሳይሰሙ ከጎኔ ነበሩ ብርሃኑ አፋኝ ነው  ቡድንተኛ ነው ይላሉ  ተጨዋቾቼ አላዩብኝምና ከጎኔ ነበሩ  አንድ ነገር ልጨምር ሆቴል ስንይዝ ለሶስት ነገር ተጠቀሙ አላቸዋለሁ አንደኛ የሚተኙበት የሚያርፉበት መሆኑን ሁለተኛ እንደየዕምነታቸው እግዚአብሄርን የሚያመሰግኑበት እሱ ካለ አሸናፊነት እንዳለ አወራቸዋለሁ። ሶስተኛ  መጽሀፍ የሚያነቡበት እንዲሆን እመክራለሁ በዚህም እታወቃለሁ  ፈጣሪዬን ቤተሰቤንና ተጨዋቾቼን  እንደየ ደረጃቸው አመሰግናቸዋለሁ….

ሊግ:- በሴትች እግርኳስ ባህል አሪፍ  አርትና  ጨዋነት እንጂ ወንበር መስበር የለም ማለትህን የሰማ የስፖርት ቤተሰብ ደጋፊ በሌለበት ኳስ የምን መሰበር አመጣ የሚል አስተያየት  ሰጥቷል… ምን ምላሽ አለህ ..?

ብርሃኑ:- /ሳቅ በሳቅ/ አሁንማ ትልቅ ለውጥ አለው ደጋፊ አለ… በሻምፒየንስ ሊጉ በርካታ ተመልካች ስለነበር ከብዛቱ የተነሳ የቡናና የጊዮርጊስ ደጋፊ ናቸው እንዴ ብዬ ነበር ..በኋላ ሲቢኢ የሚል ሳይ ነው የኛ መሆናቸውን ያወቁት … ደጋፊው ቢዚ ነው ጥሩ ስለነበርን ከመደገፍ ውጪ ሌላ ነገር ለማሰብ ጊዜ አልነበረውም  በሊጉም ተመሳሳይ ባህሪ ነው የሚታየውና ወንበር መስበር በሴቶች  እግርኳስ ውስጥ የለም በሚለው ሀሳቤ አሁንም የጸናው ነኝ።  አርት ላይ ብቻ ስለምናተኩር  ለወንበር ሰበራ ጊዜ የለም ያልኩት ለዚህ ነው።

ሊግ:- የጎሰኝነት የዘረኝነት ችግር ሴት እግርኳስ ላይ አልገጠመህም…? የለም ማለት ይቻላል..?

ብርሃኑ:- ሀገር የምትጠራው በሴት ነው ሴት ደግሞ ሀገር እንጂ ዘር የላትም በቃ ሴት እንዲህ ናት አምራች ዜጋ ናት ሴት የሌለችበት ደግሞ አያምርም። ሴቶች ባሉበት ዘረኝነትን አታይም ..በሃይማኖትና  በጎሳ መቻቻል ካየህ ሴት አለች ማለት ነው.. በሁሉ ነገር መከባበር በሚታይበት የሴት እግርኳስ ውስጥ በመገኘቴ እኮራለሁ ሴትን ማሰልጠን የህሊናና የመንፈስ ርካታ አለ ምናልባት ጥቅም ሊቀርብህ ዬችላል … ከአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለና አሰልጣኝ ስዩም ከበደ ውጪ የወንዶቹ ሲኒየር ነኝ ተመልከት ልዩነታችንን..? የተንጣለለ ቤት ከፍ ያለ መኪና እንዳላቸው አምናለሁ እኔ ግን ያ ነገር ባይኖረኝም ሴቶች ላይ በዘራሁት መልካም ነገርና ለሀገሬ የከፈልኩት ዋጋ ክብር እንዲሰማኝ ያደርገኛል …

ሊግ:- ምነው ግን ሀብቴ የኢትዮጵያ ህዝብ ነው አልክ ..? አሁን ባለው ኑሮህ አልተደሰትክም እንዴ….?

ብርሃኑ:- አሁን ባለሁበት ደረጃ ራሴን የምችልበት አቅም ቢኖረኝም ሀብቴ የኢትዮጵያ ህዝብና ለሴቶች እግርኳስ ክብር  ያላቸው ሰዎች ናቸው…በርግጥ ከሴት እግርኳስ አሰልጣኞች በተወሰነ የተሻልኩ ብሆንም  ብዙ ባለሙያተኞች ጥሩ ሁኔታ ላይ አየደሉም ይሄ በራሱ አያስደስትም ክለቦች ለተጨዋቾች እንጂ ለአሰልጣኞች ጥሩ መክፈል አይፈልጉምና ያ የበለጠ ቁጭት ይፈጥርብኛል .. እንደ ሀገር ጥሩ እንድንሆን ሙያው መከበር  አለበት።

ሊግ:- ጨረስኩ …የመጨረሻ ቀረ የምትለው ..?

ብርሃኑ:- ስለ ሁሉም እግዚአብሄር ይመስገን ስለማይተካ ድጋፉ አመሰግነዋለሁ …. ለቤተሰቦቼ ለምወዳት ባለቤቴና ለልጆቼ፣ ለእናቴ ለእህት ወንድሞቼና አጠቃላይ ለደገፉን በሙሉ አመሰግናለሁ።  ከዚያ ውጪ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ድምጽ የማይሰማበት ሴት ልጅ የማትደፈርበት፣ የሴትና  የህጻናት መብት በጣም  የሚከበርበት የችግር ወሬ የማንሰማበት  በሰላም ወጥተን የምንገባበት የመኖር ዋስትናችን የሚጠበቅበት 2017  የእውነት አዲስ አመት እንዲሆንልን እመኛለሁ።  አንተ ደግሞ በሴቶች እግርኳስ ዙሪያ ያለህ ጥሩ ግንዛቤና  ድጋፍ ችግር ገጥሞን ህዝብ እንዲያውቅ ስንፈልግ ሁሌ ከጎናችን በመሆንህ  አመሰግናለሁ ለአንተም ትልቅ ክብር አለኝ አሁንም ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ድል ዕውቅና  ሰጥተህ   እኔን ለቃለምልልስ በመጋበዝህ  ከልብ እናመሰግናለን ለአንተም ለቤተሰቦችህም   መልካም  አዲስ አመት ብያለሁ።

ሊግ:– አመሰግናለሁ …ለእናንተም መልካም አዲስ አመት  ይሁንላችሁ …

ብርሃኑ:- አሜን አሜን …

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

ትኩስ ዜናዎች

P