Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“ቋሚ በጀት በሌለበትና ዕዳ ውስጥ ሆኖ በተረከብነው ፌዴሬሽን 134 ክለቦችን ማወዳደር አስማት ነው” አቶ ደረጄ አረጋ /የአዲስ አበባ ከተማ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት/

የአዲስ አበባ ከተማ እግር ኳስ ፌዴሬሽንን በፕሬዝዳንትነት መምራት ከጀመሩ አመት አልፏአዋል…. ፌዴሬሽኑ ከከተማው ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የበጀት ድጋፍ ባይደረግለትም 134 ክለቦችን ውድድር   የመሩበትን በሳቸው አገላለጽ ” አስማት” ያሉበትን አመት አሳልፈዋል። በተደጋጋሚ ጊዜ የሲ እና የዲ ላይሰንሶችን አስፈላጊ ወጪ ከራሳቸው በመሸፈን  ፌዴሬሽኑን መርተዋል… አቶ ደረጄ አረጋ….። ከሊግ ጋዜጣ ባልደረባው ዮሴፍ ከፈለኝ ጋር ቆይታ ያደረጉት ፕሬዝዳንቱ  ስለ ሲቲ ካፑ፣ ከወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ጋር ስላላቸው ግንኙነት፣ ስለ አመታዊ ውድድሩ፣ ስለ ሸገር ሰመር ካፕ፣ በግላቸው ስላሰሩት የሁለት አቅመ ደካሞች ቤት፣  እግር ኳሱ ላይ ማየት ስለማይፈልጉትና ሌሎች ጉዳዮቸ ምላሻቸውን ሰጥተዋል።

ሊግ:-  የሲቲ ካፑን ውድድር ፌዴሬሽኑ መርቶታል ማለት ይቻላል..? ጠንካራና ደካማስ ጎኑ ምን ነበር..?

ደረጄ:- ከአምናና ከካቻምና ለየት ባለ አካሄድ እየሄደ ነው ያለው… አምናና ካቻምና ፋይናንሱን ጨምሮ ሁሉንም የመራው ፌዴሬሽኑ ነው… ዘንድሮ ግን ከተለመደው በተለየ ባለድርሻ አካላት ጣልቃ ገብተው የገንዘብና የማቴሪያል ድጋፍ እያደረጉ እየተሰራ ያለ ውድድር ነው … ከዚህ አንጻር እንደ ጠንካራ ጎን ውድድሩ በደጋፊ ታጅቦ እንዲካሄድ መደረጉ የከተማው ወጣት የናፈቀውን እግር ኳስ በዚህ መልኩ መጥቶ ሲደግፍ ማየት ትልቅ ትርጉም አለው፡፡ ከክለቦች ጋር ተስማምቶ ሲወራ የነበረውን ወሬ ሰብረን ውድድሩ በደንብ መካሄዱ በምሳሌነት መጥቀስ ይቻላል። በቀጣይም ውድድሩን በአግባቡ መምራት ከተቻለ ለሌሎች ክልሎች ብቻ ሳይሆን ለአጎራባች ሀገራት የውስጥ ውድድር ተሞክሮ አርአያነት እንደሚኖረው ማሳያም ነው… ፌዴሬሽኑ ያስቀመጣቸውን ግቦች እያሳካ መሄዱ በራሱ ጠንካራ ጎናችን ነው እንደ ክፍተት ያየነው፡፡ ምክንያቱ ምንም ይሁን የከተማችን ክለብ የሆነው መቻል አለመሳተፉ ነው ያም ሆኖ በቀጣይ ይህን መሰልና ሌሎች ክፍተቶችን አርመን ውድድሩን ጠንካራ እንደምናደርገው ግን አልጠራጠርም።

ሊግ:-ከአዲስ አበባ ክለቦች ጋር ጥሩ መናበብ አለን ማለት ትችላላችሁ …?

ደረጄ:– ፌዴሬሽናችን  በስራ ከሆነ ከአቅሙ በላይ አብሮ ለመስራት እየታገለ ያለበት አመት ነው ..ክለቦች ምን ያህል ተረድተውታል የሚለው ጥያቄ ግን እንዳለ ሆኖ ማለት ነው፡፡ ዘንድሮ ፌዴሬሽኑ አንጋፋ ክለቦች ሳይቀሩ በፋይናንስ ደግፏል ከሁለት አመት በፊት የምትፈልጉን ሲቲ ካፑ ሲደርስ ብቻ ነው ብለው ቅሬታ የሚያነሱ አንዳንድ ክለቦች ነበሩ … ያን እንዳልሆነ ለማሳየት ክለቦቹን ይዞ እግር ኳሱ እንዲለወጥ ስትራቴጁ መቅረጽ እንዳለበት በመረዳት ከ17 አመት በታች ቡድኖቻቸውን  ከ13 አመት በታች እስከ ከፍተኛ ዲቪዚዮን  ድረስ ያሉ 134 ክለቦችን ከ48 ሺህ እስከ 68 ሺህ ብር  በሚደርስ ሂሳብ ደግፎ ያለፈበት አመት ነው…ከሲቲ ካፕ እስከ ታችኛው ድረስ ያሉ ክለቦቻችን ጥሩ የሚባል የስራ ሂደት ነበረን ማለት ይቻላል… በርግጥ በቂ ነው  ባይባልም የምንችለውን አሳክተናል፡፡ በአንድ አመት ውስጥ ሁሉን ማሳካት አይቻልም ከነበረው ግን የተሻለ ግንኙነት ፈጥረናል።

ሊግ:- ሲቲ ካፑ ላይ እየተሳተፉ ስላሉ የከተማው ክለቦች የሚሉት ነገር አለ..?

ደረጄ:- የዘንድሮው ሲቲ ካፕ ተካፋይ ክለቦች ለከተማው እግርኳስ ትኩረት በመስጠት አመራሩም ላይ ትልቅ እምነት በመጣል ዋጋ ከፍለው መወዳደራቸውን ማየት በቂ ነው… አንጋፋው ቅዱስ ጊዮርጊስ ተደራራቢ ውድድሮች እያሉበት የከተማው እግር ኳስ ቸል መባል የለበትም በማለት ባለኝ አቅም እሳተፋለሁ ብሎ ተሳትፏል፡፡ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክም አዲስ እንደመሆኑ ረዘም ያለ ዝግጅት እያስፈለገው ለውድድር መቅረቡ ኢትዮጵያ ቡናና ኢትዮጵያ መድን ያሳዩት ቀናነትም የሚያስመሰግናቸው ነው፡፡ በውይይታችንም ወቅት ፌዴሬሽኑ የናንተ ነው መደጋገፍ አለብን ተባብለን መተማመናችን የተሻለ ግንኙነት መፍጠራችንን ያሳያል።

ሊግ:- “ዕውቀታችን ለእግር ኳሳችን” የሚለው መርህ የተሳካ ነው ማለት ይቻላል..?

ደረጄ:- ስኬት እንደ እይታ ሊለያይ ይችላል…በኛ በኩል ግን የተሳካ ነው ማለት እንደፍራለን… የሩቁን እንደሚያስብ መሪ የረጅሙን ጊዜ አቅዶ እንደሚጓዝ ፌዴሬሽን “ዕውቀታችን ለእግር ኳሳችን” የሚለው የተሳካ ነው ብለን እናምናለን። እንደ ማሳያ ከተማው ውስጥ ያለው እግርኳሳዊ ቅቡልነት፣ ውድድር ላይ ያየናቸው ብልጭታዎች እንዲሁም ክፍተቶች ሲኖሩ ቡድኖችም ሆኑ ደጋፊዎች ያሳዩን ትዕግስትና መቻቻሎች ምን ያህል እውቀታቸውን ተጠቅመው ከጊዜው ይልቅ የሩቁን ማየት እንደቻሉ ያሳያል። ይሄም ትልቅ ደስታ ፈጥሮልናል… በእኛ ግምገማ “ዕውቀታችን ለእግርኳሳችን” በሚገባ እየሰራ ነው ለማለት አስደፍሮናል።

ሊግ:- ያለ ቋሚ የበጀት ድጋፍ ውድድሮችን መምራቱን እንዴት ቻላችሁት..?

ደረጄ:– …በመጠኑ ሰፋ ያለ ችግር ነው ያለፍነው.. ብዙ የማህበረሰብ ክፍል ባለበትና የከተማውን እግር ኳስ በመምራት ሂደት 134 ክለቦችን እያወዳደረ ያለ ትልቅ ተቋም ይቅርና ትንንሽ ስራዎችን ለሚሰሩም ያለ በጀት ከባድ ነው…. ችግሩ ግን ሳያቆመን በድል ተወጥተነዋል… ፈተናው እንደ ክረምት የወንዝ ውሃ አልፎ ሂያጅ ነው .. ትልቅ ስራ ሲሰራ ክፍተቶችና መንገራገጮች የሚጠበቁ ናቸው፡፡ ሆኖም ግን ስላለፍነውም ሆነ ስለ ነገው  በግልጽ መነጋገር አለብን። በገጠመን የፋይናንስ ችግር ክፍያ ያልተከፈላቸው ዳኞችና ኮሚሽነሮች አሉ፡፡ ውስን የኮሚቴ ክፍያዎች ይቀራሉ፡፡ ይሄ ድጋፍ ያስፈልገዋል… ያም ሆኖ ፕሬዝዳንቱ ወይም የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ብቻ እግር ኳሱ ላይ ለብቻቸው ለውጥ አያመጡም። ከፋይናንስ እጥረት ጋር ተያይዞ የሚከሰቱ የውድድር ጥራቶችን መጓደልን ለማስቀረት በቂ ስራ መሰራት አለበት፡፡ ለዚህም ሁሉም መተጋገዝ ይኖርበታል ቀላል ቢመስሉም የፋይናንስ ችግሩ የግድ መስተካከል አለበት… ከዚህ በተጨማሪ ከእኛ ጋር ለመስራት ውል የፈጸሙ አካላት አሉ፡፡ ነገር ግን ያ ውል መደናቀፉና ተግባራዊ አለመደረጉ ራሱን የቻለ ክፍተት ፈጥሯል። በቀጣይ በውይይት ችግሩ ይፈታል ብለን እናምናለን.. እግር ኳስ በባህሪው ያለፋይናንስ የማይሆን መሆኑ መታወቅ ግን አለበት።

ሊግ:- ስለ አመቱ የ134 ክለቦች ውድድር እናውራ…?

ደረጄ:- /ሳቅ/ መንግስት ደክሞበት ብዙ ሚሊዮኖች አውጥቶበት ከሚያንቀሳቅሰው አንዱ ኢንዱስትሪ እግር ኳስ ነው…. አመቱን በሙሉ 134 ክለቦችን ይዘን ውድድር ስናካሂድ ከባድ ትግል እንደሆነ እናውቃለን…ይህን ያህል ቁጥር ያወዳደርንበት ምንም ተሞክሮ አልነበረም …ብዙ አመት እንደመቆየቴ፣ ከተወዳዳሪነት ጀምሬ እንደማደጌና ፌዴሬሽኑን እንደማወቄ ታሪክ የመስራትና ተደራሽነቱን ማስፋት ፍላጎቴ ነበር…. 134 ክለቦችን በማወዳደር ከባዱን ስራ ጀምረናል፡፡ ያም ለተለያዩ መጠነ ሰፊ ጫናዎች ዳርጎናል፡፡ ያም ሆኖ ባለድርሻ አካላት እየደገፉን መጓዝ አለባቸው.. ሚዲያውም ማገዝ አለበት….ለዚህ ፌዴሬሽን ምን ተደረገ..? በምን ታገዘ..? የሚለው ትኩረት ሊቸረው ይገባል….

የእግር ኳስ ጨዋታን ውጤት ከመግለጽ በዘለለ ሚዲያው ከፋይናንስ፣ እግር ኳሱን ከማዘመን አንጻር ትልቅ ግብዓት  መስጠት ይችላልና የጀርባ አጥንትነቱን ሊተገብረው ይገባል.. ለሌሎች የሚመለከታቸው አካላትም ተደራሽነቱ ቢሰፋ ትልቅ ለውጥ የሚያመጣ እንደ መሪም የምኮራበት ነው.. አምና 67 ክለቦችን  ብቻ ያወዳደረ ፌዴሬሽን በጥቂት ወራት ውስጥ መጠነ ሰፊ ስራ ተሰርቶ ክለቦች ፈቃድ አውጥተው ቁጥራቸው መጨመሩ ራሱን የቻለ አስማት ነው…. እንደ መሪና እንደ ፌዴሬሽን ያገኘነው ቅቡልነት ሰርተው ይለውጣሉ ተብሎ መታመናችንን አሳይቶናል… በዚያ ላይ ብዙዎች ድፍረት የሚሉትን 134 ክለቦችን ውድድር አስጀምሮ ለማስጨረስ ከጫፍ መድረሳችን በራሱ ድፍረት ነው፡፡ ይህንንም ማሳካት በመቻላችን ተደስተናል…. ከዚህም በተጨማሪ 18 ክለቦች በነጻ የተመዘገቡበትና የተወዳደሩበት አመት ነው… ትልቅ የይቻላል መርህን ያሳየንበት በመሆኑ ለቀጣይም ብዙ ድጋፍና እገዛ እንደምንገናኝ አንጠራጠርም… ከዚህም በላይ ለመጀመሪያ ጊዜ የግዢ ባለሙያ፣ የማርኬቲንግ ባለሙያና የስቶር ባለሙያ የቀጠርንበትም አመት ሆኗል…በተጨማሪም ሙያውን ለማሳደግና ሳይንሳዊ ለማድረግ በርካታ የአሰልጣኞች ስልጠናና በሌሎችም ሙያዎች መጠነሰፊ ስልጠና የሰጠንበት አመት ነው…ቋሚ በጀት በሌለበትና ዕዳ ውስጥ ሆኖ በተረከብነው ፌዴሬሽን 134 ክለቦችን ማወዳደር  አስማት ነው።

ሊግ:-ከአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ጋር ያላችሁት ግንኙነት ምን ይመስላል…?

ደረጄ:- መንግስት ከፍተኛ በጀት ከሚበጅትበት ሴክተር አንዱ ስፖርት ነው፡፡ ያም ሆኖ ትልቁ የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ላይ በርካታ ሰራተኞች እንደመኖራቸው ሁላቸውም እግር ኳሱን ይረዱታል ማለት ይከብዳል… በዚህም ለእግር ኳሱ የማይጠቅሙ የግለሰቦች ፍላጎቶች ይኖራሉ… ይሄ የግለሰቦች ፍላጎት እግርኳሳችን ላይ ደስም የማይል ነገር የፈጠረበት ሂደት አለ… ያም ግን ለከፋ ነገር የሚጥል ነው ብለን አናምንም፡፡ የእይታና የመረጃ ክፍተት ሊኖር እንደሚችል ግን እንገምታለን… ፌዴሬሽናችን እየሰራ ያለውን ስራና ወደፊት ሊያመጣ የተዘጋጀውን ውጤት ካለመረዳትና ካለመገንዘብ የተነሳ በቢሮው ደረጃ ሳይሆን በግለሰብ ደረጃ ክፍተቶች እንዳሉ እንገምታለን፡፡ በቅርብ በተወሰኑ ቀናቶች ውስጥ የሚስተካከሉ ነገሮች እንደሚኖሩ ርግጠኞች ነን…

ሊግ:-  ከሸገር ሰመር ካፕ ጋር ተያይዞ የነበረው ልዩነት በዘላቂነት ተፈቷል ማለት ይቻላል..?

ደረጄ:- የተፈጠረውን ችግርና ልዩነት በዘላቂነት ተፈቷል ብለን እናምናለን… የፌዴሬሽኑ ተቋማዊ  አቅሙ የተረሳበት፣ ህጋዊ መብቶቹ ያልተከበረበት፣ በአዋጅና በስፖርት ፖሊሲው የተሰጠው ስልጣን ያልተከበረበት  ዘመናትን አሳልፏል። ያን በሚታይና በሚገባ መልኩ ቀልብሰናል ብለን እናምናለን…. ለማሳያነት በአቶ የኔነህ የሚመራው የሸገር ሰመር ካፕ አንዱ ነው.. በመንግስት ስልጣን የተሰጠው ፌዴሬሽን ባለበት በማን አለብኝነት ውድድር ለማዘጋጀት እግርኳሳዊ እንቅስቃሴ የማድረግ ስራ ሲሰራ ነበር፡፡ ዘንድሮ ግን በቁርጠኝነት ውድድሩ ከመጀመሩ አስቀድሞ መቆም አለበት፡፡ ወደ ህጋዊ መስመር ይመለስ ብለን ታግለን ሀሳባችንን አሳክተናል፡፡ እንደፈለግን መሆን እንችላለን የሚሉትን ወገኖች በህግና በደንብ እንጂ በሌላ አይቻልም ብለን ተማምነን  አዘጋጁ ኢትዮ ናሽናል አካዳሚ ወደ መስመር እንዲገባ ተደርጓል፡፡ በዚህ በቀጣዮቹ አመታት እንደተፈለገ  የመሆን ነገሮች ዳግም ይከሰታሉ ብለን አናምንም..

ሊግ:-የአምስት አመቱ ኦዲት የት ደረሰ…?

ደረጄ:- የ5 አመት ኦዲት እንዲደረግ ያወጣነውን ማስታወቂያ ተከትሎ ስራው ቀጥሏል… በተባራሪ መረጃ እንደምንሰማው ግን በዚህ የኦዲት ሀሳብ ቅር የተሰኙ ወገኖች እንዳሉ እየሰማን ነው .. መወሰድ ያለበት ግን ፌዴሬሽኑ ግልጽ አሰራርን እንዲከተል እንፈልጋለን፡፡ ያለንን ለመስጠት እስከመጣን ድረስ የኛ ፌዴሬሽን ክፍት መሆኑን አንዱ ማሳያችን ስለሆነ ጭምር ነው… እንደ ፌዴሬሽንም የምንደብቀወም ነገር የምንደበቅበት ጉዳይም እንዲኖር ባለመፍቀዳችን የተነሳ ፈዴሬሽኑ ኦዲት እንዲመረመር አድርገናል፡፡ ምንም እንኳን የተመደበ በጀት ባይኖርም እኔን ጨምሮ በተወሰን በበጎ ፈቃደኞች ድጋፍ እየተንቀሳቀሰ ቢሆንም በአካሄዱና በአሰራሩ ግልጸኝነት ለመፍጠር የተወሰነ ውሳኔ ነው.. ከዚያ በዘለለ አጀንዳ እንደሌለን መታወቅ አለበት.. በባለሙያዎች የሚሰራ ነው… ከሱ ይልቅ እንደ ኦዲቱ ሁሉ ነገ ላይ ምን አሰባችሁ ..? ምን አቀዳችሁ..? ተብለን ምክር ድጋፍ የምንቀበልበት ጊዜ መምጣት አለበት… ፊት ለፊት ቀርቦ መወያየት መነጋገር ይገባል፡፡ ከጀርባ ይልቅ ለፊት ለፊት ውይይትና ምክክር በራችን ክፍት ነው።

ሊግ:- እስቲ ወደ 1 ሚሊዮን ብር  አካባቢ ስለወጣበት ጉለሌ ክ/ከተማ ውስጥ ስለተሰራው በጎ አድራጎት ተግባር እናውራ….ለሁለቱ አቅመ ደካሞች ቤት ተሰርቶ ተመርቆ ሲረከቡ ምን ተሰማዎ..?

ደረጄ:- ዋው.. በጣም ያስደስታል… ክስተቱ ደስታን ከመፍጠር ያለፈ ነው… አቅመ ደካሞችን ማገዝ  ፊታቸው ላይ ፈገግታ ሳቅን ማየት ከሞት ወደ ህይመት ተመለስን ሲሉ መስማት ያለው ርካታ ይለያል.. ደስታው የአንድ ወይም የሁለት ቀን ጉዳይ ሳይሆን የእድሜ ልክ ትውስታ ነው.. ሰው መልካም ሰው ሆኖ ያለውን አካፍሎ መኖርን እንዲያስብ የሚያደርግ ትልቅ ክስተት ነው

ሊግ:- በግልጽ እናውራ…ወጣቶችና ስፖርት ፌዴሬሽኑ ሰራ ብሎ አመሰገነ…. የፌዴሬሽኑ የጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አለምነህ ስዩም ደግሞ እርስዎ መስራትዎን ይናገራሉ… ማነው ትክክል…?

ደረጄ:- /ሳቅ/ ከሰራው ይልቅ የተሰራው ነገር ክብር ሊሰጠው ይገባል…. የተሰራው ነገር ደስታ ፈጥሮ ሌሎች እንዲደግሙት ማበረታታት ያስፈልጋል…. ወደ ጥያቄው ስመጣ ሙሉ በሙሉ ወጪው የተሸፈነው በእኔ ነው፡፡  እግር ኳስ መልካም ስራ በጎ ተግባር የሚከወንበት ዘርፍ መሆኑን ዲ ኤስ ቲቪ ሲጀመር የሚለቀቀውን ማስታወቂያ ማየት በቂ ነው … የቅንነት የመልካምነት ማሳያ በመሆኑ የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈጻሚ ተወያየበትና በጀት የለም አቅም የለም በሚል መስራት አልቻለም። ያም ሆኖ ፌዴሬሽኑን ባለኝ አቅም በመደገፍ ጭምር እየመራው መሆኑን ከግምት በማስገባት ከባለቤቴ ጋር በመመካከር በእኔና ቤተሰቦቼ እንዲሁም በቅርብ በተባበሩኝ ወዳጆቼ ሙሉ ወጪ የተሰራ ነው በዚህም ደስተኞች ነን።

ሊግ:- ስለ ቤተሰብ ከተነሳ የግል ስራ አለ፡፡ ቤተሰብ አለ ፌዴሬሽኑም እንደዛው… ከጊዜ አንጻር እንዴት ተወጡት…?

ደረጄ:- እውነት ነው አንዳንዴ ይምታታል፡፡ ልጄ የሚናፍቀኝ ጊዜ አለ… ቤተሰብ ጊዜ ያጣና ይናፍቃል ያም ሆኖ  መሪነት ይሄ ነው ብለን እናምናለንና እንደ አመጣጡ ማስኬድ የግድ ይላል.. ነሀሴ 19/2014 ሃላፊነቱን ከጠቅላላ ጉባኤው ሲሰጠኝ ጊዜ ከመውሰዱ በዘለለ ከቤተሰብ ከማራራቁ ባለፈ ከበድ ፈተናዎች እንደሚኖሩ ይጠበቃል፡፡ እግር ኳስን በከተማ ደረጃ ለመምራት የሚፈልገው አቅም ቀላል አይደለምና ዝግጁነቱ የግድ ያስፈልግ ነበር፡፡ ም/ል የቢሮ ሃላፈው አቶ ዳዊት ትርፉ ጠቅላላ ጉባኤው ላይ ፌዴሬሽኑ ከነበረበት ቁመና አንጻር ይህን ሃላፊነት መቀበል ትልቅ ድፍረት ነው ማለታቸው የሚያሳየውም ይህን ነውና ብዙ ጫና እንዳለው ዋጋ እንደሚያስከፍል አምኜበት ስለገባሁ እንጂ ጫናው ትልቅ ነው ማለት ይቻላል። ከጊዜ ከእውቀትና ከገንዘብም ሰጥቼ ፌዴሬሽኑን ለማራመድ የጣርኩበት ፈታኝ አመትም ነበር፡፡ በዚህም ውስጥ ግን ላሰብኩት ግብ ተገቢ የሆነ መስዋትነት ነው ብዬ አምኜበታለሁ።

ሊግ:-  አቶ ደረጄ በእግር ኳሱ ባይኖር “ኖ ሞር ” የሚሉት ምን ይሆን…?

ደረጄ:- /ሳቅ በሳቅ/ ቀላል መልስ ተንኮል ነዋ…. ተንኮል፣ ቀና ያልሆነ አስተሳሰብ፣ በተንኮል የታጀበ ድርጊት፣ ከግለሰቦች ፍራቻ የተነሳ ይሁን ኳሱ እንዳያድግ በመፈለግ በከፍተኛ ሴራ የታጀቡ ተንኮሎች፣ የተሳሳተ መረጃ ፣ ውሸትና አሉባልታዎች የማይጠቅሙ ተቃርኖች ከከተማችን እግር ኳስ እንዲጠፋ እንጸልያለን፡፡ ጠንክረንም የምንሰራበት ይሆናል…. በተቃራኒው ግን ሊሰራ የመጣ  ወገን የሚደገፍበት እግር ኳሱን የሚያግዙ ሰዎች የሚበረታቱበት፣ አንተ ሁለት አሳብ ካመጣህ እኛ ደግሞ አንድ አንድ ጨምረን አራት አድርገን ወደፊት እናራምዳለን የሚል የስፖርት ቤተሰብ ባለሙያ የሚበዛበት የመጨመር ስሜት የተሞላበት በሀሳብ ላይ ተከራክሮ የተሻለ የሚጨመርበት እግር ኳስ እንዲሆን እመኛለሁ…።

ሊግ:-  ጨርሻለሁ ….የመጨረሻ መልዕክት ካለ..?

ደረጄ:- አዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ ከተለመደ መንገድ የወጣ ነው የሚሉ ወገኖች አሉ… እኛም አዎ ነው መልሳችን…የመጣነው የተለመደ ነገር ለመስራት ወይም ለማስቀጠል  አይደለም.. በርግጥም የነበረው ነገር መልካም ከሆነና ለእግርኳሱ ጠቅሞ ከነበረ አናስቀጥልም እያልን አይደለም… ለአመታት የነበረው ግን የከተማው እግርኳስ በሚፈለገው ደረጃ አሳድጎታል ብለን  አላመንም፡፡  ይህን ሚዲያውም ሆነ የስፖርት ቤተሰቡ ሲናገረው የነበረው ነው.. ሲመዘንም የከተማው እግርኳስን አላሰደገም…  በሜዳና ከሜዳ ውጪ ውድድሮችን በማድረግ  ከተለመደው ሁሉ ወጣ ያለ ስራ ሰርተናል ይህም ለእግር ኳሱ የሚጠቅም በመሆኑ ከተለመደው ወጥቷል ለሚሉን ጥቅም ያላመጣው ነገር እንዲቀጥል የሚፈልጉ ወገኖች አዲሱን አስተሳሰብና እግርኳሱን ወደፊት የሚያራምደውን እንዲደግፉ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል ከሚለው አስተሳሰባቸው እንዲወጡ ጥሪ አደርጋለሁ… በተጨማሪ እግር ኳስ የፕሬዝዳንቱ ወይም የፌዴሬሽኑ ብቻ ሳይሆን የሁሉም ድጋፍ የሚያስፈልገው በመሆኑ ሁሉም ከጎናችን ሆነው እንዲደግፉን እጠይቃለሁ፡፡ እንዲሁም ዳኞቻችን ክፍያቸው በከፊል በተከፈለበት ሁኔታ ኮሚሽነሮቻችን ደግሞ ክፍያ ባላገኙበት ክለቦቻችን ደግሞ በውስጣዊና ውጫዊ ተጽዕኖ ውድድሩን ባላጠናቀቅንበት ባሳዩን ትዕግስት ሰው አለን እንድንል አድርጎናልና በተጨማሪ ጉልበት ስለሆኑንም እናመሰግናለን። እንደዚሁም የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ተወዳዳሪ ክለቦች በ17ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ላይ በመሳተፍ ለሰጡን ድጋፍ እናመሰግናለን። እንደዚሁም እግርኳሳችን ወደተሻለ ደረጃ ከፍ እንደሚል ተማምነው ከጎናችን በመሆን ድጋፍ ላደረጉልን በሙሉ ልባዊ ምስጋናችንን በእኔና በፌዴሬሽኑ ስም እያቀረብኩ በቀጣይ አመታት ከዚህም በላይ የተሻሉ ስራዎችን እንደምንሰራ በማመን በህግና በመርህ ላይ የተመሰረተ ግንኙነት እንደምንፈጥር እምነቴ የጸና ነው።

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

ትኩስ ዜናዎች

P