Google search engine

የኢትዮጵያ ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዎች አጓጊ ሆነዋል

 

ወላይታ ድቻ ከኢትዮጵያ መድን……

ሀዋሳ ከተማ ከኢትዮጽያ ቡና

ኢትዮጵያን በኮንፌዴሬሽን ካፕ የሚወክል ክለብ የሚመረጥበት የኢትዮጵያ ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ዛሬና ነገ ይካሄዳል።

ከሁለቱ  ቸግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዎች ከፍተኛ ፉክክር የሚደረረግበት የተባለው  እሁድ 9 ሰአት የሚካሄደው የሀዋሳ ከተማና የኢትዮጵያ ቡና ጨዋታ ነው።  ሁለቱም ለማሸነፍ እንደሚገቡና ለዋንጫ  እንደሚያልፉ እየዛቱ

ነው ። በአሰልጣኝ ዘርአይ ሙሉና በአሰልጣኝ  ነጻነት  የሚሰለጥኑት ሁለቱ ክለቦች  በፕሪሚየር ሊጉ  ሁለቴ ተገናኝተው ኢትዮጵያ ቡና 2ለ1 እና 3ለ2 ማሸነፉ የሚታወስ ሲሆን እሁድ  ደግሞ በአመት ሶስተኛቸውን ጨዋታ ያካሂዳሉ ተብሎ ይጠበቃል። ለኮከብ ግብ አስቆጣሪነት እየተፎካከሩ ያሉት ባለ12 ግብ ባለቤቱ አሊ ሱሌይማንና ባለ 8 ግቡ አንተነህ ተፈራ መሃል ያለው ፍልሚያ አጓጊ ሆኗል።

ሌላኛው የግማሽ ፍጻሜ  ጨዋታ  ዛሬ  ከቀኑ 9 ሰአት ላይ የሚካሄደው የወላይታ ድቻና የኢትዮጵያ መድን ፍልሚያ ነው በቀድሞ አርቢትር የአሁኑ አሰልጣኝ ያሬድ ገመቹና   በአሰልጣኝ ገብረ መድህን ሃይሌ መሃል በሚኖረው የታክቲክ ፍጥጫ የሚደምቀው  ጨዋታ ጠንካራ ፉክክር ይካሄድበታል ተብሎ ይጠበቃል። ሁለቱ ቡድኖች በፕሪሚየር ሊጉ  ሁለቴ ተገናኝተው በአንደኛው ዙር  ወላይታ ድቻ 1 ለ 0  ረትቶ  በሁለተኛው ዙር 2ለ2 በመለያየታቸው  ለሶስተኛ ጊዜ የሚያደርጉት ጨዊታ ተጠባቂ ሆኗል።

አራቱም ክለቦች ከፕሪሚየር ሊጉ ዋንጫ ይልቅ  የቶሻለ  እድል ያላቸው ለግማሽ ፍጻሜ  በደረሱበት የኢትዮጵየያ ዋንጫ በመሆኑ ሁለቱ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዎች ታላቅቅ ፉክክር የሚደረግባቸው ግጥሚያዎች ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

ትኩስ ዜናዎች

%d bloggers like this:
P