Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“ፕሪሚየር ሊጉ ከአቡበከር ናስር በኋላ አዲስ ክስተት ተጨዋች አላየሳየንም” “ተጨዋቾቹ ደንቡን መጣሳቸውን ካጋለጡ ከቅጣቱ ነጻ እንደሚሆኑ አሳውቀናል” “ሊጉ ከ1990 ጀምሮ ቢኖርም በክለብ ላይሰንሲንግ የተደራጀ አንድም ክለብ ግን  የለም” አቶ ክፍሌ ሰይፉ /የፕሪሚየር ሊጉ  ዋና ስራ አሴኪያጅ/

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ  የ2017 መረሃግብሩን ሊጀምር መሆኑን ምክንያት  በማድረግ የአክሲዮን ማህበሩ ዋና ስራ አስኪያጅ  አቶ ክፍሌ ሰይፉን እንግዳችን አድርገናቸዋል  የሊጉ ዮሴፍ ከፈለኝ ከፕሪሚየር ሊጉ ጅማሮ ዋዜማ  ከአቶ ክፍሌ ጋር ባደረገው ቆይታ ስለሊጉ ጥንካሬና ድክመት፣ ስለ አዲሱ የፋይናንስ ደንብ፣ የተቀጡት የሁለቱ ክለቦች ዕጣስ፣ አዲሱ ኮሚቴ ስለወሰደው ርምጃ፣ ከተጨዋቾች ስለሚጠበቀው ጥቆማ፣ ቃላቸውን ከሰጡ ተጨዋቾች 6ቱ ከቡና የወጡ ናቸው ለምን ተተኮረባቸው፣ ከዲ ኤስ ቲቪ ጋር ያለው ቀጣይ ጉዞስ ፣ ውድድሩን ወደ አዲስ አበባ ለመመለስ እያሰባችሁ ነው የሚሉና ሌሎች ጥያቄዎች ዙሪያ  አቶ ክፍሌ ምላሽ ሰጥተዋል።

ሊግ:- እንኳን ለ2017 አደረሰህ..?

ክፍሌ:- አመሰግናለሁ.. ለአንተም እንኳን አብሮ አደረሰን ለተጨዋቾች፣ ለአሰልጣኞች፣ ለደጋፊዎች፣ የኢትዮጵያ እግርኳስን  ለሚያፈቅሩ፣ ለሚዲያ አካላት፣ ለአክሲዮን ማህበሩ አመራሮችና ሰራተኞች በአጠቃላይ ለስፖርት ቤተሰቡ እንኳን አደረሳችሁ.. 2017 የብልጽግና የሰላም የደስታ እንዲሆን እመኛለሁ።

ሊግ:-አዲሱ አመት ውድድር ሊጀመር ነውና ለክለቦቹስ ምን ትላለህ..?

ክፍሌ:- አዲስ አመት ነው ሊጉ ገና አልተጀመረምና ሁሉም ክለብ እኩል ነጥብ ነው ያለው.. በአዲስ አመት  የተሻለ ውጤት እንዲገጥማቸው እመኛለሁ በተጨማሪም የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽንና የፕሪሚየር  ሊጉ አክሲዮን ማህበር  ያወጧቸውን ህጎች መመሪያዎችና ደንቦችን  የፊፋንም ህግ በአግባቡ እንዲፈጽሙ  አደራ እላለሁ ከዚህ በፊት የነበረው የተጨዋቾች ደመወዝ ተከፈለው አልተከፈለኝም ውዝግቦች እንዲቀሩ እግርኳሱ ሰላማዊ ኢንዱስትሪ እንዲሆን እመኛለሁ። በሰው ሁሉ የሚወደድ ስፖርት እንደመሆኑ ለቀጣዩ ትውልድ በሰላም የምናሸጋግረው  እንዲሆን እመኛለሁ።

ሊግ:- አስገዳጁን ህግ የተገበሩ ክለቦች ቁጥር 17 ደርሷል አሪፍ ስራ ነው የተሰራው …ቀሪ የሁለቱ  ክለቦች የአዳማ ከተማና  የወልቂጤ ከተማ ዕጣስ ..?

ክፍሌ:– ይሄ አመት ላይ ለመተግበር ካሰብናቸውና ካሳካናቸው አንዱ የክለብ ላይሰንሲንግ ትግበራ ነው … በክለብ ላይሰንሲንግ ትግበራ ውስጥ ደግሞ አዲሱ የክለቦች የፋይናንስ ስርዓት አስተዳደር መመሪያ ይጠቀሳል ትልቅና መሰረታዊ ነገሮች ናቸው  ሊጉ ከ1990 ጀምሮ ቢኖርም በክለብ ላይሰንሲንግ የተደራጀ አንድም ክለብ የለም  ይሄ ደግሞ ከሚመራው አካል ድክመት ነው ተገደው መስመር ውስጥ መግባት ነበረባቸው ያ አልሆነም ያ ችግር ተንጠልጥሎ መጥቶ አዳማና ወልቂጤ ላይ ተጽዕኖ አምጥቷል።

ሊግ:- በተቀመጠው መመሪያ ክለቦቹ ላይ ምን ሊፈጠር ይችላል ..?

ክፍሌ:- የስራው ሃላፊና አስፈጻሚ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ነው  ክለቦቹ በሊጉ መሳተፍ ቢችሉም በህጉ መሰረት 3 ነጥቦች ተቀንሶባቸዋል። ትልቅ ጉዳት ነው  ርምጃው ሲሪየስ መሆኑ ማሳያ ነው እንደዚያ ባይሆን ደስ ይለን ነበር የክለብ ላይሰንሲንግ መመዘኛውኮ የሚተገበር ነው ያን ያህል ከባድ አይደለም። የአመራሮች በጽናት የመስራትና የመጣር ድክመት ነው። አመራሮቹ ቁርጠኛ አለመሆናቸውና የሚሰሩት ሰራተኞቹ የሚጠበቅባቸውን ስራ ባለመስራታቸው የመጣ ቅጣት ነው  ክለቦቹኮ ትልቅ ናቸው ይሄ ያሳዝናል አሁንም  የሚመለከታቸው  አካላት  በቶሎ ምላሽ ሊሰጡ ይገባል።

ሊግ:- ከሁለቱ ክለቦች ውጪ  ቅጣት የተላለፈባቸው ክለቦች የሉም ..?

ክፍሌ:- በዚህ ዙሪያ ሙሉ መረጃ የለኝም ሃላፊነቱ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ነው ከፌዴሬሽኑ የክለብ ላይሰንሲንግ   ዲፓርትመንቱ ግን ሙሉ መረጃ ማግኘት ይቻላል እያንዳንዱ ጉዳይ ይመለከታቸዋል።

ሊግ:- ከዚህ ከተጨዋቾች  ዝውውር  አንጻር  የተዋቀረው ኮሚቴ የወሰደው  ተጨባጭ ርምጃ አለ..?

ክፍሌ:– የምርመራ ስራ ብዙ ጊዜ ይፈልጋል … ወደ ተጨባጭነት የሚወስዱ መረጃዎች እየመጡ ነው ትክክለኛ ርምጃ የሚያስወስድ  ግን አይደለም። ገና ከመሆኑ የተነሳ  መረጃዎች እየተሰበሰቡ ነው  ከጥር ወር ጀምሮ የሚተገበር ተጨማሪ የጥቆማ ስርዓት አውጥተናል በስልክ ፣በኢሜይልና በአካል መረጃ የማግኘት ስርዓት ተዘርግቷል ከዚህ ውጪ ተጨዋቾቹ ደንቡን የመጣስ ሁኔታ ውስጥ መግባታቸውን ካጋለጡ ከቅጣቱ ነጻ እንደሚሆኑ አሳውቀን ከእነሱም ጥቆማ እንጠብቃለን ይሄን ለሚመለከተው ሁሉ አድሬስ አድርገናል በስልክ እየተደወለ በአካል እየቀረቡ መረጃዎች እየሰጡን ያሉ ሃላፊነት የሚሰማቸውን ሰዎች እያየን ነው  በአጋጣሚው በጣም እናመሰግናለን ከዚህ በኋላ  ርምጃዎች ይጠበቃሉ።

ሊግ:- ግን  ግን ከተጨዋቾች መረጃዎችን እናገኛለን ብላችሁ ታምናላችሁ…?

ክፍሌ:- አዎ ህጉኮ እነሱን የሚከላከል ነው ተጨዋቾቹ በአግባቡ እንዲከፈላቸው የታለመ ነው ተጨዋቾቹ ገንዘባቸውን በውላቸው መሰረት እንዲያገኙ ሶስተኛ እጅ ከነሱ እንዲርቁ የሚያደርግ በመሆኑ ከተጨዋቾቹ ጥቆማ እንፈልጋለን ይሄም የሚሆነው በዋናነት ጥቅሙ ለነሱ ስለሆነ ነው ይሄን ማሰብ አለባቸው እግርኳስ ውስጥ ያሉ ተጨዋቾች ከወራት እስከ አመት ድረስ ደመወዝ አጥተው ሴለተጎዱና ያን ለመከላከል ሲባል የወጣ ደንብ ነው ራሳቸው ደንቡን መጠበቅ አለባቸው። ለራሳቸቸው ሲሉ ህጉን እንዲያስተገብሩ እጠብቃለሁ።

ሊግ:- ህጉ ለተጨዋቾች ነው ሲባል የጥያቄው መነሻ እነሱ ናቸው እያልከኝ  ነው ..?

ክፍሌ:- በፍጹም …መነሻዎቹ ክለቦቹ ናቸው እየተጎዳን ነው ተጎድተናል ይሄን የሚያስቆም ስርዓት የለምና አሰራሩ ክፍተት አለበት ይሄን ክፍተት የሚሞላ መመሪያ ይዘጋጅ ብለው ለተቋሙ ሃላፊነቱን  ሰጥተው የተሰራ ደንብ ነው የአክሲዮን ማህበሩም ግፊት የለበትም ይሄ መታወቅ አለበት  ችግሩ ሄዶ የሚያጠቃው ተጨዋቹን ነው  በውሉ መሰረት ደመወዝ የማይከፈለውኮ ተጨዋቹ ነው  አሰልጣኞቹ ብዙም አይደለም  ሌላው አካል የሚፈልገውን ነው የሚያገኘው ይሄን ክፍተት ለማስቆም ተጨዋቾቹ ሊተባበሩ ይገባል ብዬ አምናለሁ ችግሩ እንዲወገድ ኳሱ እንዲያድግ የነሱ አስተዋጽኦ ትልቅ ነው ብዬ አምናለሁ።

ሊግ:- ቃላቸውን ለመቀበል ከተጠሩት  ዘጠኙ 5ቱ የሲዳማ ቡና  2ቱ የድሬዳዋ ከተማ  ሁለቱ  የመቻል  ተጨዋቾች ናቸው … እነዚህ ብቻ ናቸው የተጠረጠሩት ….?

ክፍሌ:- ይሄ በጥቆማ የመጣና የመጀመሪያ ጥሪ የተደረገላቸው ናቸው  ሌላ ጥቆማ እየመጣ ስለሆነ የሚጠሩ ገና ሌሎች ይኖራሉ ማለት ነው።

ሊግ:- ብዙ ጥያቄ ከተነሳባቸው መሃልአንዱ ለመቻል የፈረመው ፍሪምፖንግ ነው ከፈረሰኞቹ ከፍተኛ ተከፋዮች  መሃል የሚገኝ ቢሆንም ለመቻል ፈረመ የተባለበት 150 ሺህ ብር  ብዙ ጥያቄ አስነስቶ እሱ አልተጠራም ሌሎችም አሉ ይሄንንስ እንዴት  አያችሀት ..?

ክፍሌ:- የተዋቀረው ኮሚቴ  የራሱ የሆነ የአጠራርና የአሰራር  ሂደት አለው  የአሁኑ እንደተቋቋመ ክለቦች ባነሱት ጥያቄና በሰጡት ጥቆማ የተደረገ ጠርቶ ቃል መቀበል እንጂ ገና ብዙ የሚጠሩ አሉ.. በቀጣይ ብዙ የሚጠረጠሩም አሉ … የአንዳንዶቹ ደግሞ  የተጋነነ ቅነሳ ያደረጉ ናቸው በቀጣይ አስፈላጊው ማጣራት እንደሚካሄድ አትጠራጠር።

ሊግ:- አጠያየቁ.. ቃል የተቀበላችሁበት  መንገድ ትንሽ ወረድ አለብኝ… ይሄንንስ እንዴት አየኧው ..?

ክፍሌ:- ይሄኮ እንደ ቃል አቀባበል ውሰደው…  በቀጣይ ግን ራሳችሁ ሃላፊነት ትወስዳላችሁ ብሐን አስጠንቅቀን ነግረን ነው  የሸኘነው ተጨማሪ የምርመራ ስራማ ይቀጥላል  በህግ ስርዓት አንጻር ካየነው  ቃል መቀበል ያለ ነገር ነው ይቀጥላል።

ሊግ:- ከ9ኙ ተጠርጣሪዎች   ስድስቱ ከኢትዮጵያ ቡና የለቀቁ  ተጨዋቾች ናቸውና  የአንድ ወገን ፍላጎት የማስፈጸም የመቶ አለቃ ጫና ያለበት ይሆን  ብለው ጥርጣሬያቸውን የሚያነሱ አሉ ..ምላሽህ ምንድነው ..?

ክፍሌ:- ይሄ ትክክለኛ ስጋት አይደለም ኮሚቴው በቀላሉ ይህን አድርግ የሚባልም አይደለም  አጋጣሚ ይሆናል እንጂ  ጥቆማ ከመጣኮ ሁሉም ከአንድ ክለብ ሊሆን እንደሚችል መታወቅ አለበት በዚያ ላይ መቶ አለቃ በዚህ ደረጃ አይታሙም  ትልቅ አቅም ያላቸው ህግና መመሪያውን በደንብ የሚያውቁ አውቀው የሚሰሩ ለሌሎች አካላት የሚያስተምሩ ለእኛ ደግሞ እንደ መጽሀፍ የሚነበቡ ሰው ናቸው ከርሳቸው ጋር በመስራቴ ሁሌም ደስተኛ ነኝ።

ሊግ:- እንደዚህ አይነት ሌባና ፖሊስ  ከመጫወት ለምን ደመወዝ ያልከፈለ ክለብን ነጥብን በመቀነስ አይጀመርም የሚሉ አሉ ..ምላሽህ ምንድነው ..?

ክፍሌ:- አንድ አካል ቅጣት የሚቀጣው መነሻ የሆነ ደንብና መመሪያ ሲኖረው ነው ከመሬት ተነስቶ መቅጣት አይቻልም ደንብና መመሪያም የለም ፌዴሬሽኑኮ ከክለብ ላይሰንሲንግ ጋር  ተያይዞ እየቀጣ ነው  ይሄ መመሪያ ግን ከውል ጋር ተያይዞ  ጥፋት የፈጸመ ዝውውር አያደርግም አሁን ደግሞ ወደ ነጥብ ቅነሳ ተዙሯል  የክለቦች የፋይናንስ አስተዳደር ስርዓትና የክለብ ላይሰንሱንግ  በጣም ተቀራራቢና ተመሳሳይነት አለው  በክለብ ላይሰንሲንግ ማሟላት ያለብህ ትክክለኛ የፋይናንስ ስርዓት ይኑርህ በውልህ መሰረት ክፈል ኦዲት አስደርግ የሚለው ከአምስቱ አንዱ ነው  ለዚህ ነው ሁለቱን ተደጋጋፊ ናቸው የምልህ… አዳማ ከተማና ወልቂጤ ከተማ የተቀጡት ቅጣት ከፋይናንሱ ጋር በተያያዘ በመሆኑ ጥሩ ማሳያ ይመስለኛል ከአምና ጀምሮ ያልከፈሉ እየተቀጡ ነው ወልቂጤኮ ከውጪ ዜጎች ጋር በተያያዘ ነው  የተቀጣው  ስለዚህ ህጉ እየተተገበረ ነው ማለት ይቻላል።

ሊግ:- እንደ ዋና ስራአስኪያጅ ደንቡ ይተገበራል የሚል እምነት አለህ….?

ክፍሌ:– አዎ…ያለጥርጥር…. አንድ መመሪያ ሲወጣ አይተገበር ይሆን ብለህ አትጀምርም ይሄ ልክ አይደለም መተግበሩ የግድ ነው አፈጻጸም ላይ ያለው ክፍተት በሂደት እየተስተካከለ ይቀጥላል … አሁን ባለው  ሂደት ከ19ኙ ክለቦች የተወሰየ ጥርጣሬ ያለው 3 ክለቦች ጋር ብቻ ነው ..ካሉት ክለቦች  ሶስቱ ብቻ  ወጣ ገባ ማለታቸው ለውጥ ነው። አንድ መመሪያ ላይ መንገጫገጭ መኖሩ ደግሞ አይቀርም ያም ቢሆን የግድ ይተገበራል ተቋሙም ኮሚቴው ጠንክረው እየሰሩ ናቸው…ውድድሩ ከተጀመረ በኋላ የክለቦቹን የፋይናንስ ባለሙያዎችን ጠርተን አፈጻጸሙን እንገመግማለን  ለህጉ መተግበር በፍጹም ወደኋላ አንልም።

ሊግ:- የዲ.ኤስ.ቲቪ ኮንትራት ዘንድሮ ይጠናቀቃል .. አይቀጥል ይሆን የሚል ስጋት የለም ..?

ክፍሌ:- የሁለታችን ጥምረት ጊዜው ለአምስት አመታት ነው ዘንድሮ አመቱን እንጨርሳለን ከፈለጉ ይመጣሉ ካልሆነ እንለያያለን ይሄ ይጠበቃል በእስካሁኑ ገንዘብ አግኝተንበታል። ሁለተኛ ውድድሩ በቲቪ መተላለፉ ስርዓት እንዲኖረው አድርጓል ..ከጊዜ ከዳታ አያያዝ የተጨዋችና የአሰልጣኝ  ፐርሰናሊቲ አንጻር ብዙ ተምረንበታል  ውድድራችን ዋጋ ማውጣቱ ለኛ እንደ መነሻ ነው ደስተኞች ነን … ሊጉ ከጀመረ በኋላ ስራችን የሚሆነው ይሄ ነው  ከእነሱ ጋር አምስቱን አመት ስለምንገመግም በዚያን ጊዜ እንደራደር ካሉ ጥሩ እንደራደራለን ካልሆነ ይፋዊ ጨረታ እናወጣለን ይሄ አመት ከቴሌቭዥን የማስተላለፍና የሊጉ ስያሜ አንጻር  ጠንካራ ስራ  ለመስራትና የተሻለ ገቢ ለማግኘት እንጥራለን።

ሊግ:- የሀገር ውስጥ ተቋማት በዚህ ላይ መሳተፍ ዕድሉ አላቸው ..?

ክፍሌ:- አፍሪካ ውስጥ በተለይ እነ አዛንኮ የሀገር ውስጥ ተቋም ናቸው አዛን ቲቪ ጠንካራ የሆነ ሃብት ያለው ትልቅ ተቋም ነው  ወደኛ ሀገር ስትመጣ የቴሌቭዥን ተቋማቶች የመንግስት ከፍተኛ ድጋፍ አላቸው  ቢሰሩ እንደሚያዋጣቸው ርግጠኞች ነን በዚህ ደረጃ ለመስራት ግን ሃሳቡ አላቸው ወይ የሚለው ነው ስጋቴ…. የማርኬቲንግ ስራም  በጣም መሰራት አለበት ተቋማቱ ከተዘጋጁ ማድረግ ይቻላል ስጋቴ ዝግጁነታቸው  አቅማቸውና ቁርጠኝነታቸው ላይ ነው ለምሳሌ የኦቢ ኤን  ማቴሪያሎች በጣም የሚገርሙና  ዘመናዊ የሆኑ አቅርቦቶች አሏቸው ጥያቄው ግን ይህን ለመስራት ያላቸው ፍላጎትና ቁርጠኝነት እንዲሁም የስፖርቱ ቢዝነስ ላይ ያላቸው መረዳትና እውቀት ምን ያህል ገብቷቸዋል የሚለው ነው ሌላው ሀገር ቢዝነስ ነው የኛ ሀገር የሚዲያ ተቋማትስ ምን ያስባሉ የሚለው ምላሽ ያስፈልልገዋል።

ሊግ:- እንደ ዋና ሃላፊነትህ እንደ ቅርበትህ ክለቦቹ አድገዋል ሊጉ ደረጃው ከፍ ብሏል ማለት ይቻላል ..?

ክፍሌ:- በሁለት መንገድ እንየው …. 240 ጨዋታዎች ዕቅድ ተይዞላቸው እየተገመገሙ ዝግጅታቸው ሲታይ 2016 የተሻለ ሆኖ አልፏል ጠንካራ አፈጻጸም ነበረው  የእግርኳሱ የአሰራርና የአፈጻጸም ስርዓት ጥሩ የሚባል ነው።  እኛ ብቻ ሳንሆን ሱፐር ስፖርት በግምገማው በጣም ጥሩ ችግር የሌለበት ከትንሽ መንገራገጭ ውጪ የተሻለ ነበር  ሜዳ ውስጥ ስንሄድ እግርኳሳችን መሰረታዊ ችግር አለበት ከሜዳ ውጪና በሜዳ ነበር ውድድሩ መካሄድ የነበረበት አልሆነም  ኮቪድ ገባና ከዚያ ጀምሮ አንድ ቦታ ሲካሄድ ነው አመታት የተቆጠረው …  ወደ ክለቦች ስንመጣ  አንድ ክለብ ትክክለኛ  ክለብ ነው የሚባለው አምስቱን የክለብ ላይሰንሲንግ መስፈርቶችን ሲያሟላ ነው። ከዚህ ስንነሳ ከፍተኛ ክፍተት አለው  እግርኳሱ አደገ ብል የኢትዮጵያ እግር ኳስ ያለበት ደረጃ የክለቦቹና የብሄራዊ ቡድኑ ውጤትና አቅም  የሚታይ ነው  እንደ አጠቃላይ ስርዓቱ ብቻ ተሻሽሏል ማለት ነው የሚቀለው… በአፍሪካና በዓለም ዋንጫ ማጣሪያዎች ውጤታማ አይደለንም ተፎካካሪ መሆን አቅቶናል … ብሄራዊ ቡድኑ ጠንካራ እንዲሆን ክለቦች መጠንከር አለባቸው ይሄ አልተሰራም  ተተኪ ታዳጊዎች አልመጡም  ክስተት የሆኑ ተጨዋቾች አልታዩም ከአቡበከር ናስር በኋላ ምንም አይነት አዲስ ኮከብ  ተጨዋች አላየንም ይሄ ሊጉ ላይ ያለውን ድክመት ያሳያል.. እዚህ ላይ ሳልረሳው የምናገረው አዲሱ የፋይናንስ ስርዓት ወጣቶችን እያሳየን ነው ውሎቹን ስናይ ካለፉት 4 አመታት በዘንድሮው ብዙ ወጣቶች  ወደ ሊጉ  እየመጡ ነው ይሄ ደስ ይላል ..  በፋይናንስ ስርዓቱ መሰረት  ውስን ሲሆን ክለቦቹ  ወጣቶቹን እያስፈረሙ እየመጡ ለነሱ ዕድል እየተፈጠረ ነው  ይሄ ደስ ይላል።

በመሰረተ ልማት ካየን የተሻለ የሆነውም ድሬዳዋ ነው የአመቱን የ2016 መዝጊያ ፕሮግራምን ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ድሬዳዋ የወሰድነው የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደርን ለማመስገንና በአካባቢው ያለውን እግርኳስ  ለማበረታታት ነው  ከጭቃ ወደ አርቴፊሻል  የተመለስነው ዘመናዊ መብራት ያየነው ድሬዳዋ ነው ከእግርኳስ ኢንቨስትመንት አንጻር ከእኛ ጋር የሄደው  የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ነው በጣም እናመሰግናለን ልሎች ጋር የተሰራ አዲስ ነገር ምንም የለም  የሀገራችን እግርኳስ ውስብስብ ነው

ሊግ:- ውድድሩን ወደ አዲስ አበባ ለማምጣት ምን አየሰራችሁ ነው ..?

ክፍሌ:- በየጊዜው እንጠይቃለን እንሞክራለን  ዘንድሮም እንጠይቃለን ለአሁኑ ግን  የመጀመሪያውን አዲስ አበባ ለማድረግ ባለማቀዳችን ጥያቄ አላቀረብንም .. ዘንድሮ ዘደ 342 ጨዋታ ስላለ ብዙ ሜዳ ስለሚያስፈልግ በቀጣይ እንጠይቃለን ..ዘንድሮ 19 ክለቦች ይወዲደራሉ 5 ክለቦች ደግሞ ይወርዳሉ በዚያፐላይ የቻን ውድድር መጥቷል የአለምና የአፍሪካ ዋንጫ የኢትዮጵያ ዋንጫ መርሃግብሮች ስላሉ የጊዜ ሰሌዳው ተጨናንቆብናል  ክለቦቹ ከሌሎቹ አመታት በተሻለ መዘጋጀት ይጠበቅባቸዋል እንደ አወዳዳሪ አካልም እኛም በደንብ እየተዘጋጀን ነው አምስተኛ አመት ላይ የተሻለ የመስራት ዕቅድ ቢኖረንም ጫናዎቹ በዝተዋል …ሜዳዎቹ ላይ ከፍተኛ ጫና እንደሚኖር እንገምታለን…ያም ሆኖ  ከእግዜር ጋር በስኬት እንደምንጨርሰው ተስፋ አደርጋለሁ።

ሊግ:- አርቢትሮች  የማሊያ ስፖንሰር በማግኘታቸው ትልቅ ደስታ ፈጥሯል …እንደ ሊግ ካምፓኒ እንዴት አየኧው..?

ክፍሌ:- በጣም ተደስቻለሁ ትልቅ ስራ  ነው ከዚህ በፊትም ሞክረን ነበር ግን ሃላፊነትና ስልጣኑ የኛ ባለመሆኑ አልገፋንበትም   ግን በጣም ትልቅ ስራ ነው  አንደኛ በትልቁ የሀገሪቱ ሊግ ላይ የሚያጫውቱ ዳኞች ከትጥቅ ጋር ተያይዞ መቸገር የለባቸውም… ስምምነቱ  ይሄን ስላስወገደ ደስ ብሎኛል ወደፊት የተሻለ ስራ መሰራት ይቻላል ብዬ አምናለሁ…

ሊግ:- ከእናኖተ ጋር የስምምነት መፋለስ አይፈጥርም ማለት ይቻላል ..?

ክፍሌ:– አዎ ምንም አያገናኘንም …ዳኞችን የሚመራው ብሄራዊ ፌዴሬሽኑ እንደመሆኑ  ከእኛ ጋር አያገናኘውም።

ሊግ:- የመጨረሻ ጥያቄዬ እንደ ሀላፊ  በ2017  ህልምህ  ምንድነው..?

ክፍሌ:- የኔ ትልቁ ህልም የውድድር  ፕሮግራም ላይ  መጣበብ አለ  አምስት ክለቦችም ይወርዳሉ  የስታዲየም ክፍተቶች አሉ ይሄ ትልቅ ፈተናን በብቃት ለመወጣት አልማለሁ .. 2016  በስኬት እንደጨረስን  2017ትንም ማጠናቀቅን አልማለሁ ሌላው ደግሞ  ሊጉ በ2018 የተሻለ የስያሜ መብትና የጨዋታ ማስተላለፍ የተሻለ  ገቢ እንዲያገኝ ከቦርዱ ጋር ጠንክረን የመስራት  እቅድ አለን  አዲሱን የክፍያ ስርዓት መመሪያ ክለቦቹ በታማኝነት ሲተገብሩ ማየትን እመኛለሁ። ብዙ የህብረተሰብ ክፍል እግርኳስ የሚጭበረበርበት ቦታ ነው ብሎ ያምናል ይሄን በጎ ያልሆነ ስም እንዲታደስ የማድረግና ስፖርቱ ሰላማዊ መሆኑን ማሳየት  እፈልጋለሁ  ኡንዱስትሪው አዝናኝ ሙያ መሆኑን  ተጨዋቾቹ እየተዝናኑ የሚከፈላቸው ተመልካቹም እየተዝናና የሚመለከተው መሆኑን  ለማሳየት አልማለሁ እንደተቋም  እንደ ቦርድ  እንደ ሰራተኛ በንጽህና እንደምንሰራ በተቻለ መጠን ተቋሙ ንጹህ ሆኖ እየሰራ መሆኑን  ማሳየት እንፈልጋለን እግዚአብሄር ንጹህ መሆንን ስለሚፈልግ እንደሚረዳን እናምናለን።

ሊግ:- አመሰግናለሁ መልካም የውድድር ዘመን ይሁንላችሁ…..

ክፍሌ:- አመሰግናለሁ …

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

ትኩስ ዜናዎች

P