በየሳምንቱ ቅዳሜ ለንባብ የምትበቃው ሊግ ጋዜጣ በነገው ዕለት ምርጥ ምርጥ ዘገባዎችን አካትታ እጅዎ ትገባለች….
በነገው ዕትም ከሀገር ውስጥ በሻምፒዮኖቹ በር ላይ ያንጸባረቀው የጸሀይ ባንክ ማርኬቲንግና ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አበባው ዘውዴ እንግዳችን ነው…. የሊግ ስፖርት ጋዜጣ ማኔጂንግ ኤዲተር ከሆነው አለምሰገድ ሰይፉ ጋር ቆይታ ያደረጉት አቶ አበባው “ሁሌም ከቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ጎን ነን” ሲሉ ተናግረዋል…ቃለምልልሱን ይዘነዋል…..
……በውጪ ዘገባ ደግሞ:…..
* የኢንተር ሚያሚው አጥቂ የዓለም ሻምፒዮኑ ሊዮኔል አንድሬስ ሜሲ በአሜሪካ ያለው ተጽዕኖ የጠነከረ መሆኑ ይነገራል…..ስለዚህ አፍቅሮተ ሜሲ የምንላችሁ አለ……
* ማን.ሲቲ ደክሞም ያስፈራል…መርተኸው እንኳን ዳኛው የጨዋታውን መጠናቀቅ የሚገልጽ ፊሽካ እስካልነፉ ድረስ መዘናጋት ዋጋ ያስከፍላል….በሲቲ ጥንካሬ ዙሪያ መረጃዎችን ይዘናል….
* የሊቨርፑልን የቡድን ጥንካሬ መነሻ አሊሰን ቤከር ለመሆኑ ጥርጥር የለውም….አሀን ግን ይሄ የሊቨርፑል ግብ ምሰሶ አሊሰን ቤከር ተጎድቷል…ሊቨርፑሎችም አጥተውታል….በግብ ጠባቂው ጉዳት ዙሪያ የሚያጠነጥን ዘገባ ይዘናል…
* ሃሪ ኬን በቡንደስሊጋው ይሁን በአውሮፓ ደረጃ ዋንጫ ማለም በሚችልበት ክለብ ውስጥ እየተጫወተ ነው ….የባቫርያኑ ባየርሙኒክ በሃሪ ኬን ግብ የተጋጣሚውን መረብም እየደፈረ ነው ….የኬን የባቫርያን ጅማሮን የዳሰስንበትን መረጃ አካተናል……
….. እናም ሌሎች ያልተሰሙ መረጃዎችን አካተናል …
ነገ ጠዋት ቡናዎን ሲፈልጉ ማኪያቶዎን ወይም ያሻዎት ሌላ ከሆነ ልብዎ የፈለገውን እየተጎነጩ ሊግን በእጅዎ ያስገቡ…
….ቅዳሜና እሁድዎ የሚደሰቱበት ቀኖችዎ ይሁኑ….