በነገው ዕትም ከሀገር ውስጥ ዘገባችን ባለፉት 15 አመታት ለዋሊያዎቹ ወሳኝ ግልጋሎት የሰጠው… ለሀዋሳ ከተማና ቅዱስ ጊዮርጊስ አሁን ደግሞ ለመቻል እየተጫወተ ያለው …በግብጽ አራት ክለቦች ውስጥ ጉልህ ተሳትፎ ያደረገው ሽመልስ በቀለ እንግዳችን ነው …. “ጥሩ ሜዳ የለም ጥሩ ነው ብዬ የምጠራውም ክለብ የለም” ያለውና ከዋሊያዎቹ ራሱን ያገለለው ሽመልስ ከሊጉ ዮሴፍ ከፈለኝ ጋር በነበረው ቆይታ “መጫወት እንጂ የምንፈልገው ፕሮፌሽናሊዝምን
የማናውቅ ብዙ ነን” ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል…
ቃለምልልሱን ይዘናል…
*….የኢትዮጵያ ዳኞችና ታዛቢዎች ማህበር አመራሮች መሃል ንፋሴ ገብቷል…. ልዩነታቸው ፍርድ ቤትም ደርሷል…አመራሮቹ የሚጠቀሙበት ማህተምም በፍርድ ቤቱ ታግዷል…በጉዳዩ ላይ መረጃ ይዘናል…..
….በውጪ ዘገባ ደግሞ….
** በኮትዲቯር አስተናጋጅነት የሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ በጉጉት እየተጠበቀ ነው …. ነገ በሚጀመረው በዚህ የአፍሪካዊያን እግርኳሳዊ ድግስ ዙሪያ መረጃዎችን ይዘናል …ገና ከጅማሮው ዋንጫውን የሚያነሳውን ኦፕታ ይገምትልናል..በሻምፒዮናው የሚጠበቁ ኮከቦችን ዝርዝር አካተናል…. ምን እሱ ብቻ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በአዲስ መልክ ከተዋቀረ ጀምሮ በአፍሪካ ዋንጫው ላይ የነገሱትን የአፍሪካ ልጆችን እናስታውሶታለን …
** በሳውዲ አረቢያ እየተካሄደ ያለው የስፔን ሱፐር ካፕ ሊጠናቀቅ የኤልክላሲኮ ተፋላሚ የሆኑትን ሪያል ማድሪድና ባርስሎናን በፍጻሜው አፋጧል …እሁድ ምሽት አራት ሰአት ላይ ስለሚደረገው የዋንጫ ጨዋታ መረጃ ይዘናል…
** የአንቷን ግሪዝማን የአትሌቲኮ ማድሪድ ስኬት ያን ያህል እውቅና አልተሰጠውም …ለምን …? በዚህ የግሪዝማን እንቆቅልሽ ዙሪያ የምንላችሁ አለ…
….. እናም ሌሎች ያልተሰሙ መረጃዎችን አካተናል …
ነገ ጠዋት ቡናዎን ሲፈልጉ ማኪያቶዎን ወይም ያሻዎት ሌላ ከሆነ ልብዎ የፈለገውን እየተጎነጩ ሊግን በእጅዎ ያስገቡ…
….ቅዳሜና እሁድዎ የሚደሰቱበት ቀኖችዎ ይሁኑ…