በነገው ዕትም በሀገር ውስጥ ዘገባችን….. የኢትዮ ኤሌክትሪኩ ዋና አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ እንግዳችንነ ነው… ሁለት ተከታታይ አመታት ሻምፒዮን የነቀረው አሰልጣኝ ዘሪሁን አሁን ቅዱስ ጊዮርጊስን ለቅቆ ኢትዮ ኤሌክትሪክን ቢቀላቀልም ለፈረሰኞቹ ያለው ፍቅር አልበረደም …… “ቅዱስ ጊዮርጊስ ድሮም ዘንድሮም የማወራለት ክለቤ በመሆኑ እናትም አባቴም ነው ማለት ይቻላል” ያለው አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ “ኢትዮ ኤሌክትሪኮች አስቤውም አልሜውም የማላውቀውን ጥሩ አቀባበል አድርገውልኛል” ሲል አሞግሷቸዋል…..ቃለምልልሱን ይዘናል
*……ከውጪ ዘገባ ደግሞ ………
*…. ማን.ሲቲ የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ ለአምስት ተከታታይ አመታት ለማንሳት አቅዷል…ነገር ግን በፍርድ ቤት የተከሰሰበት ጉዳይ ተጽዕኖ እንዳይፈጥርበት ተሰግቷል…ስለዘንድሮ የሲቲ ወሳኝ አመት የምንላችሁ ነገር አለ….
*,….. የመድፈኞቹ ፊታውራሪ ስለሆነው ቡካዮ ሳካ መረጃዎችን ይዘናል …እንግሊዛዊው ወደ ታላቅ አጥቂነት ይለወጥ ይሆን ….? መረጃዎችን ይዘናል…
*…..ጇ ፊሊክስ በደስታ ወደ ስታምፎርድ ብሪጅ ሲመጣ ራሂም ስተርሊንግ ደግሞ አኩርፎ ስታምፎርድ ብሪጅ መውጪያ በር ላይ ይገኛል …. ..ስለሰሞነኛው የቸልሲ ጉዳይ የምንላችሁ አለ…
*… ኤልካይ ጉንዶጋን ወደ ኢትሃድ ተመልሷል…
ጀርመናዊው ተጨዋች በጋርዲዮላ ቡድን ውስጥ ያለው ሚናን በተመለከተ መረጃ ይዘናል….
*…ስለሪያል ማድሪዱ አዲሱ ስብስብና ስለጋላቲኮ ዕቅድ የምንላችሁ ነገር አለ…
*….በሊቨርፑል የመጋረጃ ጀርባ ምን እየተሰራ ነው..? አምበሉ ቨርጂል ቫንዳይክ ኮንትራትም ዙሪያ መረጃዎችን አካተናል…
… እናም ሌሎች ያልተሰሙ መረጃዎችን ይዘናል …
ነገ ጠዋት ቡናዎን ሲፈልጉ ማኪያቶዎን ወይም ያሻዎት ሌላ ከሆነ ልብዎ የፈለገውን እየተጎነጩ ሊግን በእጅዎ ያስገቡ…
….ቅዳሜና እሁድዎ የሚደሰቱበት ቀኖችዎ ይሁኑ…